የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.73K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ 31 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸዉ 13 የመንገድ ፕሮጀክቶችና 8 ድልድዮች ምረቃ ሥነ ሥርዓት ተካሄደ
ለህገ-ወጥ እርድ የተዘጋጁ 62 የቁም እንስሳት ተያዙ

01_10 2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የደንብ ማስከበር አባላት ከወረዳው የፖሊስ አባላት ጋር በመሆን በተደረገው ክትትል መሰረት እጅ ከፍንጭ በመያዝ የድርጊቱ ፈፃሚዎች በህግ ተጠያቂ በማድረግ በቦታው የተገኙት የቁም እንስሳቶች ለመንግስት ገቢ መደረጋቸው ተገለፀ።

የየካ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የቁጥጥርና ኢንስፔክሽን አስተባባሪ አቶ ሙሉሰው ድልነሳ እንደገለፁት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ልዩ ቦታው ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ጥናት ተካሂዶ በተደረገው ኦፕሬሽን የተገኙ የታረዱ በጎች ብዛት 12 ፤ የታረደ በሬ ብዛት 1 ፤ ያልታረዱ የቁም እንስሳት ብዛት 62 መያዛቸው ገልፀዋል።

በቦታው የተገኙ 62 የቁም እንስሳት ለጠፍ በረትና ገቢ የተደረገ ሲሆን የተያዘው ስጋ እንዲወገድ ለቄራዎች ድርጅት ማስረከቡ ለህገ-ወጥ እርድ ሲያከናውን የተያዘው ግለሰብ 15 ሺህ ብር በመቅጣት በህግ እንዲጠየቅ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉ ተገልጿል።

ባለስልጣኑ ህገወጥ ተግባራት በሚሰሩ አካላት ላይ የሚወስደው እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለፅ በዚህ ተግባር ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች ከቅጣት በዘለለ ለህግ እንዲቀርቡ እንደሚደረግ አስታውቋል።

ተቋሙ ህብረተሰቡ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች ጥቆማና መረጃ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
11👍6👏4