የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.73K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች በ69.8% መቀነሳቸው ገለጸ

ሰኔ 19/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የ2017 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸሙም ግምገማ መድረክ አካሂዷል ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ደንብ ማስከበር በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ተልዕኮ ለመፈጸም ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ በእቅዱ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ ወደ ተግባር በመግባቱ የተሰጠውን ተልዕኮ በተሰካ መንገድ መወጣት መቻሉን ገልጸዋል ።

አክለውም የተቋም ግንባታ ስራን በማጠናከር ለሰራተኞች እንዲሁም ለተገልጋዮች ምቹ የስራ ቦታ በመፍጠር ፣ አዲስ 6ኛ ዙር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮችን አሰልጥኖ በማስመረቅ የስራ ሰዓቱንም እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት በማድረግ ከተማችን የደንብ ጥሰት የቀነሰባትና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ በርካታ ተግባራት እያከናወነ እንደሚኝ ተናግረዋል ።

በበጀት ዓመቱ በከተማችን የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች 69.8% እንዲቀንስ ማድረግ መቻሉንና በሰው ተኮር ተግባራት ላይ በመሳተፍ ከ የ14 የአቅመ ደካማ ቤት እድሳትና ገንብቶ በማጠናቀቅ ለባለቤቶቹ ማስረከቡን ዋና ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ ቀርቧል።

ባለስልጣኑ የተቋም ግንባታ ፣የሥልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን በስፋት መስራት እና በከተማዋ የሚታዪ ደንብ ተላላፊዎች ላይ ህጋማዊ እርምጃ በመውሰድ የተሰጠውን ተልዕኮ በቁርጠኝነት ከመወጣት ጎን ለጎን ወደ ህብረተሰቡ በመውረድ ሰው ተኮር ስራዎችን በመከናወን የአቅመ ደካማ ቤቶችን ገንብቶ በማጠናቀቅ ለባለቤቶቹ አስረክቦል፣ የአረንጓዴ አሻራ ተግባራት በማካሄድ ችግኞችን መትከልና መንከባከብ ስራ ተከናውኗል እንዲሁም ወላጅ አልባ ህጻናት በመንከባከብ እያሳደገ እንደሚገኝ ከቀረበው ሪፖርት መገንዘብ ተችሏል ።

ከደንብ ተላላፊዎች ቅጣት እና ከተወረሱ ንብረቶች ጨረታ ሽያጭ እስከአሁን ባለው ከ397 ሚሊዮን ብር በላይ መልሶ ለልማት የሚውል ለከተማው ገቢ ማስገባት መቻሉን በሪፖርቱ ተገልጿል ።

በመድረኩ ለተነሱ ሀሳቦች የባለስልጣኑ ኃላፊዎች ምላሽና አስተያየት ሰጥተው ቀጣይ የስራ አቅጣጫ በዋና ሰራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ተሰጥቶ መድረኩ ተጠናቋል ።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
5👍5
ባለስልጣኑ በስራ በመሰማራት ላይ የነበሩ ኦፊሰሮች ያለፈቃድ ፎቶ በማንሳት በቲክቶክ ያተሰራጨው ግለሰብ በፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዲውል ማድረጉ አስታወቀ

23/10/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በኮልፌ ክፋለ ከተማ ወረዳ 04 በስራ ስምርት የነበሩ የደንብ ማስከበር አባለት ያለፈቃዳቸው ፎቶ በማንሳትና ቪዲዮ በመቅረጽ በቲክቶክ ያሰራጨው ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።

ግለሰቡ በመደበኛ ስራቸው የነበሩ ኦፊሰሮች ተከታትሎ ፎቶ በማንሳትና ቪዲዮ በመቅረጽ ስም የማጥፋት እና የስራ እንቅስቃሴዎችን ከህግ አግባብ ውጪ ሲያሰራጭ የነበረ መሆኑ ተደርሶበት በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል በማድረግ ተጨማሪ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑ የክፍለ ከተማው የደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሙሉጌታ ጎንፋ ገልፀዋል።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍104
ለክፍለ ከተማና ለወረዳ የባለስልጣኑ ኮሙዩኒኬሽን ተወካዮች /focal person/ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ

23/10/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ለክፍለ ከተማ እና ለወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ለህዝብ ግንኙነት እና ኮሙዩኒኬሽን ፎካል ፐርሰኖች በሶሻል ሚዲያ ዜና አዘገጃጀት እና መሰረታዊ የህዝብ ግንኙነት ላይ የስልጠና መድረክ አካሂዷል ።

በመድረኩ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ሰራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ኮሙኒኬሽን ለተቋም ግንባታና ስራዎችን ተደራሽ ለማድረግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ በአዲስ ሚድያ ኔትወርክ ቴሌቪዥንና ሬድዮ ፣ በፕሬስ ድርጅት በጋዜጣ አምድ ፣ እንድሁም በተቋሙ ማህበራዊ ሚድያዎች የባለስልጣኑን መረጃ በማሰራጨትና ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ ላይ መሆኑን ገልፀዋል ።

በቀጣይም ያለንን የመረጃ ቅብብሉን በማጠናከር የተቋሙን ገጽታ ለመገንባት ከተለያዩ ሚዲያዎች ጋር በመቀናጀት አንዲሁም የተቋሙን የሚዲያ አማራጮች በመጠቀም ጠንካራ የኮሙኒኬሽን ስራ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ እንደተናገሩት ባለስልጣኑ የሚሰጠውን አገልግሎት ለህብረተሰቡ የፈጠነ ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ የሚዲያ አግባቦችን በመጠቀም ላይ ይገኛል በተጨማሪም የስቱዲዬ ግንባታ ስራውን በማጠናቀቅ የተቋሙን ገጽታ ግንባት አጠናክሮ በመስራት ላይ ይገኛል ።

ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ የመረጃ ቅብብሎሽ በማጠናከር የተቋሙን ገጽታ በመገንባት ህብረተሰቡ አዎንታዊ አመለካከት እንዲኖረውና ህገ-ወጥነትን የሚጸየፍ ዜጋን ለማፍራት የፎካል ፐርሰኖች ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት አማካኝነት የሚዘጋጁ ሲሆን ስልጠናዎችን ተግባራዊ በማድረግ ሁሉም የመረጃ ባለሙያ ለተሻለ ስራ ብቁ መሆን እንደሚገባው ተናግረዋል ።

የስልጠናው ተሳታፊዎች የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት የስራ ክፍሎችን ፣ የተቋሙን ስቲዲዮ እንዲሁም በዳይሬክቶሬቱ የተዘጋጀውን የባለስልጣኑ ዓመታዊ ስራዎች በከፊል የሚያሳይ የፎቶ አውደ ርዕይ ጉብኝት አካሂደዋል ።

ለክፍለ ከተማ እና ወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የኮሙዩኒኬሽን ፎካል ፐርሰኖች የተዘጋጀው መሰረታዊ የህዝብ ግንኙነት ስልጠና የሬ/ቴ/ህ/ፕ ዝግጅት ቡድን መሪ አቶ ሄኖክ ታደሰ ቀርቧል።

በተጨማሪም የተግባቦት ክህሎት /communication skill/ የተዘጋጀው ሰነድ በባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ የምሰራች ግርማ ቀርቧል።

ከዚህ ስልጠና በኃላ ሰልጣኞች በተግባብት ክህሎት ላይ በቂ ግንዛቤ ፈጥረው ለሚዲያ ግብዓት የሚሆኑ አጫጭር መረጃዎች እንዲያዘጋጁ የሚያግዝ ይሆናል ሲሉ አቶ ምስራች ተናግረዋል ።

ተሳተፊዎቹ የተቋሙ ኮሙዩኒኬሽን በጉብኝቱ ወቅት ያሳየን ተግባራትና ያመጠው ለውጥ በቀጣይ ለምናከናውነው የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ስራዎች የሚያነቃቃና በዕውቀት የተደገፈ ስራ እንድናከናውን የሚያግዝ ነው ሱሉ ተናግረዋል ።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች በባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃለፊ ተስፋሁን አሉላ እና በባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ የምሰራች ግርማ ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶበት ስልጠናው ተጠናቋል ።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍6👏2