የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.73K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ የደንብ ጥሰት የፈጸመውን የከተማ አብቶቢስ አሽከርካሪ መቅጣቱን አስታወቀ

07/09/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በለገሀር አከባቢ የከተማ አውቶቢስ ሹፌር ከመኪናው የጠረገውን ደረቅ ቆሻሻን አስፓልት ላይ በመጣሉ በደንብ ቁጥር 167/2016 መሰረት አምስት ሺህ ብር በመቅጣት ለመንግስት ገቢ ማድረጉን አስታወቀ ።

ድርጊቱን የፈጸመው ግለሰብ በጊዜው ተሸከርካሪዉን ይዞ ከቦታዉ ቢሰወርም በተደረገዉ ክትትል በዛሬዉ እለት የካ
ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ላይ ሹፈሩን ከነተሸከርካሪው በቁጥጥር ሰር በማዋል መንገድ በማቆሸሸ ለተላለፈዉ የደንብ ጥሰት የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት ህጋዊ እርምጃ ተወስዷል ።

ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ ለሰጠው ጥቆማ ከልብ እያመሠገነ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች መረጃ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው
👍17
ባለስልጣኑ ልምዱን እና ተሞክሮውን ለሐረሪ ከተማ አስተዳደር ልዑካን ቡድን አባላት አጋራ

            12-09- 2017 ዓ.ም
          አዲስ  አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከሐረሪ ከተማ አስተዳደር የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ለመጡ የልዑካን ቡድን አባላት በተቋም አደረጃጀት፣ በመመሪያ ዝግጅት ፤በገጽታ ግንባታ ፣ በሰው ሃይል አደረጃጀት እና ከባለድርሻ  አካላት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር በተመለከተ ባለስልጣኑ ያለውን ልምድና ተሞክሮ  አጋርቷል፡፡


በልምድ ልውውጡ የባለስልጣኑ ዳይሬክተሮች እንደየስራ ክፍል አሰራሮችን እና የተቋሙ ተሞክሮዎች ን የገለጹ ሲሆን የሐረሪ ከተማ አስተዳደር  ከተቋሙ ልምድ በመውሰድ እና ተግባራዊ በማድረግ ተጨባጭ ውጤት ማምጣት እንደሚችሉ ለልዑካን ቡድኑ አባላት አስረድተዋል፡፡

ባለስልጣኑ ሀረሪ  ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ተቋሙን ለማጠናከር በሚያደርገው  እንቅስቃሴዎች  በሚችለው ሁሉ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ለልዑካን ቡድኑ ገልፀዋል።

የልዑካን ቡድን አባላት ተቋሙ የተደራጀበት እና ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በመነጋገር እየሰራ ያለው ውጤታማ ስራዎች አድንቀው የወሰዱት ተሞክሮ ጠቃሚ እና ልምዱን በከተማቸው ተግባራዊ በማድረግ እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች ጥቆማ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ።

ዘገባው :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍1
የወንዞች ብክለት በአካባቢ እና በጤና ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ዙሪያ ግንዛቤ ተፈጠረ

18/09/2017 ዓ.ም
* አዲስ አበባ *

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ወንዝና የወንዞች ዳርቻ ልማት ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ለሲቪክ ማህበራት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

የባለስልጣኑ የቅድመ መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካለም ጌታሁን በደንቡ 180/2017 ዙሪያ በተለያዩ መድረኮች ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎችን በተደጋጋሚ መሰጠቱን እና ግንዛቤ እንደሚቀጥል በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው ገልጸዋል ።

"የወንዝ እና ወንዞች ዳርቻ ብክለት" በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን የስልጠና ሰነድ በባለስልጣኑ የህግ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ብርሃኑ ኮርሳ አቅርበዋል።

በሰነዱ በከተማዋ 76 ወንዞች መኖራቸውና የወንዞች ፅዳት ለህብረተሰቡ የጤና ስጋት በመፍጠራቸው ንጽህናቸው ለመጠበቅ ደንቡን መውጣቱ ገልጸዋል።

የወንዞች ደህንነት ለማስጠበቅ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በዚሁ ዙሪያ ጥናት ማጥናቱን ገልጸው ይህንን ደንብ በሚተላለፉ አካላት ላይ ከ2 ሺህ እስከ 1 ሚሊዮን ብር ድረስ የቅጣት መጠን መቀመጡንም አስታውቀዋል።

የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ስራዎች ለመስራት ከሲቪክ ማህበራቱ እገዛ እንደሚያስፈለግ እና ሲቪክ ማህበራቱ በደንብ ቁጥሩ ላይ የተሰጣቸው ስልጠና በሚኖሩበት አካባቢ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲያስገነዝቡ መልዕክት ተላልፏል።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋረ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበት መድረኩ ተጠናቋል።

ዘገባውን:- የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
1👍1