በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ደንብ የተላለፉ ተቋማት 1.5 ሚሊየን ብር ተቀጡ
04/09/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በለሚኩራ ክፋለ ከተማ ወረዳ 03 ኖህ ሪል እስቴት ከተቋሙ ግቢ የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ከወንዝ ጋር በቀጥታ በማገናኘታቸው በተደጋጋሚ በተፈጠረላቸው በግንዛቤ እና በተወሰደባቸው የገንዘብ መቀጮ ተምረው ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እና ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ባለመቻላቸው በዛሬው እለት ከአካባቢ ጥበቃ፣ ከሰላም ፀጥታ እና ከፖሊስ ጋር በመቀናጀት በሪከርድ የጥፋቱ እጥፍ 800,000 ብር መቀጣቱ አስታወቀ።
በተመሳሳይ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ሁለት ተቋማት ደንብ ቁጥር 180/2017 ተላልፈው በመገኘታቸው 700,000 በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል።
በአጠቃላይ በዛሬው እለት በክፍለ ከተማው ደንብ ቁጥር 180/2017 ተላልፈው በተገኙ ሶስት ተቋማት ላይ በተወሰደ እርምጃ 1,500,000 ብር መቀጣታቸው ገልጿል።
ባለስልጣኑ በከተማው ከአሁን በፊት ተቀጥተው ከድርጊታቸው የማይቆጠቡ ተቋምና ግለሰቦችን በሪከርድ የቅጣቱ እጥፍ በመቅጣት የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።
ተቋሙ ለከተማው ነዋሪዎች ማንኛውም የደንብ መተላለፎች ሲያጋጥሙ ለደንብ ማስከበር ባለስልጣን በነጻ የስልክ መስመር 9995 ጥቆማ እንዲያደርስ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
መረጃው፡- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሮክቶሬት ነው።

👍4
ባለስልጣኑ የደንብ ጥሰት የፈጸመውን የከተማ አብቶቢስ አሽከርካሪ መቅጣቱን አስታወቀ
07/09/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በለገሀር አከባቢ የከተማ አውቶቢስ ሹፌር ከመኪናው የጠረገውን ደረቅ ቆሻሻን አስፓልት ላይ በመጣሉ በደንብ ቁጥር 167/2016 መሰረት አምስት ሺህ ብር በመቅጣት ለመንግስት ገቢ ማድረጉን አስታወቀ ።
ድርጊቱን የፈጸመው ግለሰብ በጊዜው ተሸከርካሪዉን ይዞ ከቦታዉ ቢሰወርም በተደረገዉ ክትትል በዛሬዉ እለት የካ
ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ላይ ሹፈሩን ከነተሸከርካሪው በቁጥጥር ሰር በማዋል መንገድ በማቆሸሸ ለተላለፈዉ የደንብ ጥሰት የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት ህጋዊ እርምጃ ተወስዷል ።
ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ ለሰጠው ጥቆማ ከልብ እያመሠገነ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች መረጃ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።
መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው

👍17
ባለስልጣኑ ልምዱን እና ተሞክሮውን ለሐረሪ ከተማ አስተዳደር ልዑካን ቡድን አባላት አጋራ
12-09- 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከሐረሪ ከተማ አስተዳደር የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ለመጡ የልዑካን ቡድን አባላት በተቋም አደረጃጀት፣ በመመሪያ ዝግጅት ፤በገጽታ ግንባታ ፣ በሰው ሃይል አደረጃጀት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር በተመለከተ ባለስልጣኑ ያለውን ልምድና ተሞክሮ አጋርቷል፡፡
በልምድ ልውውጡ የባለስልጣኑ ዳይሬክተሮች እንደየስራ ክፍል አሰራሮችን እና የተቋሙ ተሞክሮዎች ን የገለጹ ሲሆን የሐረሪ ከተማ አስተዳደር ከተቋሙ ልምድ በመውሰድ እና ተግባራዊ በማድረግ ተጨባጭ ውጤት ማምጣት እንደሚችሉ ለልዑካን ቡድኑ አባላት አስረድተዋል፡፡
ባለስልጣኑ ሀረሪ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ተቋሙን ለማጠናከር በሚያደርገው እንቅስቃሴዎች በሚችለው ሁሉ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ለልዑካን ቡድኑ ገልፀዋል።
የልዑካን ቡድን አባላት ተቋሙ የተደራጀበት እና ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በመነጋገር እየሰራ ያለው ውጤታማ ስራዎች አድንቀው የወሰዱት ተሞክሮ ጠቃሚ እና ልምዱን በከተማቸው ተግባራዊ በማድረግ እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡
ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች ጥቆማ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ።
ዘገባው :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

👍1