ባለስልጣኑ ያስገነባውን የሬዲዮና የቴሌቪዥን ቀረፃ ስቱዲዮዎች በሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የማኔጅመንት አባላት ተጎበኘ
28/08/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በከተማ አሰተዳደሩ የሚፈጠሩ የደንብ መተላለፎች ቀድሞ ለመከለከል የተሰጠውን ተልዕኮ ለማስፈፀም መመርያዎችን ደንቦችን አዋጆችን ለህብረተሰቡ በሚዲያ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ዘመናዊ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ቀረፃ ስቱዲዮ በመገንባት በሬዲዮ፣በቴሌቪዥን እና በሶሻል ሚዲያዎች የሚተላለፉ ፕሮግራሞች ማዘጋጀት መጀመሩ አስታወቀ።
በጉብኝቱ የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ ባለስልጣን መስርያ ቤቱ ያስገነባውን ስቱዲዮ ባለስልጣን መስርያ ቤቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ የመፈፀም እና የማስፈፀም አቅሙን እያሻሻለ በመምጣቱ በተለይ በከተማችን ላይ የተሰጠውን ተልዕኮ በመፈፀም እምርታዊ ውጤቶች ማስመዝገቡ ጠቁመውው ስራዎቹ በህዝብ ግንኙነት ሲደገፉ የበለጠ እንደሚያጎላው ገልፀዋል።
አክለውም አንድ ተቋም የተሻለ አፈፃፀም የሚኖረው የተቋም ግንባታ ስራ ሲሰራ በመሆኑ ይህንንም የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በሰው ሀይል፣ በቴክኖሎጂ እና በዘመናዊ የሰራ መገልገያዎች የተደገፉ ስራዎችን በመስራት ላይ መሆኑ የስቱዲዮ ግንባታው ስራው አንዱ ማሳያ መሆኑ ተናግረዋል።
በባለስልጣኑ የሚሰሩ ስራዎችን በህዝብ ግንኙነት በማጀብ እና ለማህበሰሰቡ ተደራሽ የማድረግ ስራው አሁን ያለንበት ጊዜ የሚጠይቅ በመሆኑ በመግለፅ የሰላምና ፀጥታ ቢሮም እንደተሞክሮ ቀምሮ ወደ ቢሮው እንደሚወስድ ባደረጉት ጉብኝት ተናግረዋል ።
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስገነባውን ዘመናዊ ስቱደዮ በቀጣይ አስፈላጊ ግባቶች በሟሟላት ለማህበረሰቡ በሬዲዮ፣በቴሌቪዥን እና በሶሻል ሚዲያዎች ሰፊና ተከታታይነት ያላቸው የተደራጀ የግንዛቤ ስራዎች ተደራሽ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
በመጨረሻም ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ቀረፃ ስቱዲዮ ስራው ለደገፉና እና ላስተባበሩ የባለስልጣኑ አመራሮች እና ተልዕኮ በመቀበል ስረውን ለዚህ ያደረሱ ስራተኞችን አመስግነዋል።
ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

❤4👍1
የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች የባለስልጣኑ 6ኛ ዙር ዕጩ ፖራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና ሂደት ጎበኙ
29/08/2017 ዓ.ም
**ይርጋለም/አፖስቶ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በጋራ አየተሰጠ የሚገኘው የ6ኛ ዙር የዕጩ ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የአንድ ወር የወታደራዊና የንድፈ ሀሳብ የስልጠና ሂደትን የደረሰበትን ደረጃ የሚመለከት ጉብኝት አደረጉ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ ለማሀበረሰብ ዘብ የቆመ የደንብ ጥሰትን የሚከላከል የሚቆጣጠር እና ተፈጽሞም ሲገኝ ተገቢውን እርምጃ የሚወስድ ብቁ የሰው ሀይል መፍጠር የስልጠናው ተቀዳሚ ዓላማ እንደሆነ አንስተው ይህንንም በጉብኝቱ ወቅት መመልከት እንደተቻለ በመጥቀስ ይህ እንዲሆን ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበው በቀጣይ በታየው ልክ ወጥ የስልጠና ሂደትን የማስቀጠል ስራው በቅንጅት ሊቀጥል እንደሚገባ አያይዘው ገልጸዋል።
ጉብኝቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ምክትል ኮ/ር ጌቱ ተክለዮሀንስ እንዲሁም የተቋማቱ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
አጠቃላይ የአንድ ወር የስልጠና ጊዜ አጭር ሪፖርት በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ አፖስቶ ካምፓስ ኃላፊ ኮ/ር ቦጋለ መሀመድ በወታደራዊ ስልጠና እና የንድፈ ሃሳብ ት/ት አሰጣጥ ዙሪያ እንዲሁም የባለስልጣኑ የስልጠና አስተባባሪ ሻምበል ኑርልኝ ገ/ኪዳን በስልጠና ወቅት ባጋጠሙ ተግዳሮቶች ላይ አጭር ሪፖርት በማቅረብ ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱም ላይ የባለስልጠኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በተሰጣቸው ኃላፊነት ሰልጣኙን ለማብቃት ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ለሚገኙ የባለስልጣኑ እና የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የስልጠና አስተባባሪዎች ምስጋና በማቅረብ በጉብኝቱ የታየው አጠቃላይ የሰልጣኙ አቀባበል እና በቅንጅት የተሰራው ስራ ሊቀጥል እንደሚገባ በማንሳት በቀጣይም ኃላፊነቱን የሚወጣ በስነምግባር የታነጸ ሰልጣኝ ማፍራት እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።
በመጨረሻም ቀጣይ በተጠቀሱት ተግዳሮቶች ላይ በማዕከል እና በዩኒቨርሲቲው መፍትሄ የማስቀመጥ ሂደቱ እንደሚቀጥል በመግለጽ ለምርቃት መርሀ ግብር ከስልጠናው ጎን ለጎን ሊታሰብ እና ስራዎች ሊጀመሩ እንደሚገባ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል።
በሳምራዊት ዘሪሁን:-
ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ አፖስቶ ካምፓስ

👍2
የባለስልጣኑ የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ የ9 ወራት የእቅድ አፈፃፀም ውይይት አደረገ
ሚያዚያ 30/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ የ9 ወራት የእቅድ አፈፃፀም እና የቀሪ ወራት ስራዎች በተመለከተ ከ11 ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የስራ ሂደት አስተባባሪዎች እና ቡድን መሪዎች ጋር ውይይት አደረገ።
በውይይቱ የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና በሚያዚያ ወር ድጋፍና ክትትል የታዩ ስራዎች በድክመትና ጥንካሬ የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ዳይሬክቶሪት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሠርካለም ጌታሁን ያቀረቡ ሲሆን በሪፖርቱ በአጠቃላይ በዘጠኝ ወራት ውስጥ የተደረጉ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችና ስልጠናዎች ለባለድርሻ አካለት ፣ ለሲቪክ ማህበራት ፣ለበጎ ፈቃደኞች፣ ለፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች፣ ለፖለቲካ አመራሮች እና ለሀይማኖት አባቶች በተለያዮ ርዕሰ ጉዳዮች የተሰጡ ስልጠናዎች ና የግንዛቤ ሰራዎችን በዝርዝር አቅርበዋል።
በተለይ በደንብ ቁጥር 150/2015 ዓ.ም ለማሰፈፀም ተሻሽሎ በወጣው ደንብ ቁጥር 167/2016 ዓ.ም እና በወንዞች ዳርቻ ልማት አስመልክቶ በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ከፍተኛ የህዝብ ንቅናቄ መድረኮች በመፍጠር የግንዛቤ ስራው ተደራሽ ማድረግ እንደተቻለ እና ውጤቶች መገኘቱ በሪፖርቱ ተመላክቷል።
በመድረኩ በክፍለ ከተማ እና በወረዳ በተደረገ የክትትልና ድጋፍ ግብር መልስ ለማሳያነት የሚሆኑ የለሚ ኩራ ፣ የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 የአዲስ ከተማ እና የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች በጥንካሬ እና በክፍተት የነበራቸው ግብረ መልስ በመድረኩ ለማቅረብ ተችሎል።
በመጨረሻም በውይይቱ በቀረበው ሪፖርት እና ግብረ መልስ ላይ ከተሳታፊዎች አስተያየት እና ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን ከመድረክ ምላሽ ተሰጥቶባቸው የቀጣይ ወራት የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል።
ዘገባው፦ የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

👍1