የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.73K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከሰላምና ፀጥታ ቢሮ ጋር በ2017 በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈጻፀም በነበረው ግምገማ ባለስልጣኑ የተሻለ አፈፃፀም ካስመዘገበባቸው መካከል፦

👉 የደንብ ጥሰትና ወንጀልን በተቀናጀ አሰራር እንዲቀንስ ማድረግ ተችሏል።

👉 ህግና ስርዓት እንዲከበር ግንዛቤ በመፍጠር ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል።

👉 የሚከናወኑ ተግባራት በእቅዱ መሠረት እየተገመገመ በመሄዱ ክፍቶችን በየ ጊዜ እየታረመ በመሄዱ ስኬት ተመዝግቧል።

👉 የህዝቡን ተሳትፎ በማሳደግ፣ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ምላሽ በመስጠት የህብረተሰቡ ቅሬታ እንዲቀንስ ተሰርቷል።

👉 አመራሩ፣ባለሙያውና ባለድርሻ አካላት በቅንጅት በመስራት የደንብ መተላለፎች በ64% እንዲቀንስ ተደርጓል።

👉 አመራሩና ባለሙያው በህብረትና በትብብር በመሰራቱ ለህገ-ወጦችና አጭበርባሪዎች መቆጣጠር ተችሏል::

👉 ህገ-ወጥ ንግድን በመቆጣጠር በፍትሐዊ የሀብት ክፍፍልና የገበያ ማረጋጋት ውጤት ተገኝቷል።

👉 የአደባባይ በዓላት በሰላም፣ በፍቅር፣ በአብሮነትና በመከበር ያለምንም የፀጥታ ችግር ማክበር ተችሏል።

መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
👍143
ባለስልጣኑ በቀሪ ወራት የሚከናወኑ ተግባራት እቅድና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አካሄደ

25/08/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት በዘጠኝ ወር እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መነሻ በማድረግ በቀሪ ወራት የሚሰሩ ስራዎችና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ከማዕከል አስከ ወረዳ ካሉ አመራሮች ጋር የግምገማዊ ውይይት መድረክ አካሂዷል ።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በአመራሩ እና ሰራተኛው ጥረት በዘጠኝ ወራት ውስጥ በተቋሙ ጥሩ አፈፃፀም መኖሩንና ይህንንም በቀሪ ጊዜያት ያሉንን ጠንካራ ጎኖች በማስቀጠል አንዳንድ ክፍተቶችን በመሙላት በትጋት በትኩረት ቀንና ሌሊት በመሠራት ውጤታማ በመሆን ከተማችን የደንብ ጥሰት የቀነሰባት ለነዋሪዎቿና ለእንግዶቿ ምቹ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል ።

በመድረኩ በቀሪ ወራት በክ/ከተሞች መሰራት ያለባቸው ዋና ዋና ተግባራትና ዝርዝር ተግባራት እቅድ በባለስልጣኑ እቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ አቅርበዋል።

በመድረኩ የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ ስራዎችን ስናከናወን ከመንግስትና ከህዝብ የተሰጠንን ኃለፊነት በመገንዘብ ከብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ መሆን እንደሚገባ ተናግረዋል ።

በዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ስራዎች በቅንጅት በመሰራታቸው በከተማ የነበሩ የደንብ መተላለፎችንና ህገ ወጥ ተግባራት እንዲቀነስ ማድረግ መቻሉን የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ገልጸዋል ።

በተጨማሪም በመድረኩ የስድስተኛ ዙር ፖራ ሚሊተሪ ምረቃትና ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተካሂዷል።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶበታል ።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍6
ባለስልጣኑ የ6ኛ ዙር ዕጩ ፖራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ደማቅ የምርቃት ፕሮግራም ለማዘጋጀት ውይይት አካሄደ

28/08/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከፌዴራል ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በጋራ የሚያሰለጠናቸውን የስድስተኛ ዙር የዕጩ ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የምርቃት ፕሮግራም አስመልክቶ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

በውይይት መድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች እና የሚመለከታቸው ዳይሬክተሮች ተገኝተዋል ።

በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ
በኢትዮጽያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ በመሰልጠን ላይ የሚገኙ የፖራ ሚሊተሪ ሰልጣኞች ስልጠናቸውን በብቃት አጠናቀው ወደ ስራ ሲገቡ ያማረና የደመቀ የምርቃት ፕሮግራም ለማዘጋጀት ከወዲሁ ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ስራ መሰራት መጀመሩ ጠቅሰው በቀጣይ ቀናቶች ፕሮግራሙ ባማረና በደማቀ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ከሁለቱ ተቋማት ጋር በቅንጅት መሰራት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል ።

ባለስልጣኑ ከፌዴራል ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በጋራ ያሰለጠናቸውን የዕጩ ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የምርቃት ፕሮግራም የተዘጋጀ እቅድ የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው አቅርበዋል ።

በእቅዱ የስድስተኛ ዙር ፖራ ሚሊተሪ ሰልጣኞች ስልጠናውን በብቃት አጠናቀው ለስራ ስምሪት ዝግጁ በማድረግ መነቃቃት በመፍጠር እንዲሁም የስራ መመሪያ ለመስጠት ደማቅ የምረቃት ፕሮግራም ለማከናወን የተለያዩ ኮምቴዎች በማዋቀር መታቀዱን ም/ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል ።

በመጨረሻም የቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ በቀረበው እቅድ መሠረት በየዘርፉ የተቋቋሙ ኮሚቴዎችን የተሰጣቸውን ሀላፊነት በአግባቡ በመወጣት የምርቃት ፕሮግራሙ ያማረና የደመቀ እንዲሆን የስራ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍41