የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
994 subscribers
1.5K photos
4 videos
1 file
51 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር አካሄደ

09/08/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን መጪውን የትንሣኤ በዓል አስመልክቶ ለማዕከሉ ሰራተኞችና ለሚያሳድጋቸው ህጻናት የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም አካሂዷል ።

በማዕድ ማጋራቱ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ አንድነታችንን በመደጋገፍና በመረዳዳት በተግባር በማሳየት በተለይ በዓላቶችን በሚከበሩበት ወቅት ማዕድ በማጋራት አብሮነታችን ማጠናከር አለብን በማለት ተናግረዋል፡

አክለውም አብሮነታችንን አንድነታችንን ለማጠናከር እንዲህ አይነት ኢትዮጵያዊ እሴቶችን አጠናክረን መቀጠል ይገባቸዋል በማለት በዓሉ የሰላም፣የደስታ እንዲሁም የአንድነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በማዕድ ማጋራት ተካፋይ የሆኑት የደንብ ማስከበር ኦፊሰር ወ/ሮ መሰረት ግርማ በህመም ምክንያት እረፍት ላይ መሆናቸው ጠቅሰው ተቋሙ በሚችለው አቅም ሁሉ ላደረገላቸው ድጋፍና በዛሬው ወቅት ለተደረገላቸው የበዓል ማዕድ ማጋራት ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

በተጨማሪም የባለስልጣኑ አመራሮች ለባለስልጣኑ ሰራተኞች የእንኳን አደረሳቹ መልእክታቸውን አስተላልፈው የሰው ተኮር ተግባራቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል ።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
ባለስልጣኑ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ፅ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች በማስተባበር የዝቅተኛ ደምወዝ ተከፋይ ሰራተኛ ቤት ሙሉ እድሳት አደረገ

ሚያዝያ 09/2017 ዓ. ም
** በአዲስ አበባ**

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የደንብ ማስከበር እና የሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት በማስተባበር ለአንድ ዝቅተኛ ደሞዝ ተከፋይ ሰራተኛና ሙሉ የቤት ዕድሳት በማድረግ ለፋሲካ በአል ቤቱን አስረክቧል።

በርክክቡ ስነስርዓት ላይ በመገኘት መልእክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘርሁን ተፈራ ባስተላለፉት መልዕክት ሁሉም ሰው ከሚያሰራው ሰራተኛ ጀምሮ ያለበትን የኑሮ ደረጃ በማየትና በመለየት መተጋገዝ፣ አብሮ መቆምና መመረዳዳት እንዳለበት አንስተው ወጣት እሸቱ የነበረበት የኑሮ ሁኔታ ከባድ እንደነበር በማየት እንደዚህ አይነት እገዛ እንዲደረግለት የተባበሩ አካላትን አመስግነዋል።

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አየለ በበኩላቸው የፓርቲያችን ብልጽግና ሀሳብ እና የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶክተር አብይ አህመድ መልካም ጅምር የሆነውን እንደዚህ አይነት ሰዉ ተኮር ተግባር በመስራት ዜጎችን ተጠቃሚ የማድረግ ስራ ላይ ለመሰማራት እድል በማግኘታቸው እንደተደሰቱ በማንሳት እንደዚህ አይነት ተግባር በሁሉም መለመድ እንዳለበት ተናግሯል።

በመጨረሻም ቤት የታደሰለት ወጣት እሸቱ መሐመድ የቤት እድሳቱን ላስተባበሩ ሁሉ እና ስጦታ ስለተበረከተላቸው ምስጋና አቅርቧል።
ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ-አስኪያጅ ለ2017 ዓ.ም ለትንሳኤ በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!
*******

ለመላው ኢትዮጵያውያንና ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለእየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!!!

የትንሳኤ በዓል የሰላም ፣የጤና ፣ የደስታ ፣ የፍቅር እና የመረዳዳት በዓል እንደሆንልን እመኛለሁ።

የትንሳኤ በዓል እየሱስ ክርስቶስ በሞቱ ለሰዉ ልጆች ሁሉ ምህረት ያስገኘበት ለሰው ልጆች መስዋትነት የተከፈለበት በዓል ነው።

በዓሉን ስናከብር የተቸገሩ ወገኖቻችንን በመርዳት፣ በመተዛዘን ካለን በማካፈል በዓሉን በአብሮነት ልናከብር ይገባል ።

ባለስልጣኑ በከተማዋ የሚስተዋለውን የደንብ መተላለፎችና ህገ-ወጥነትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚያደርገው ጥረት ህብረተሰቡ አጋዥ በመሆን የበኩሉን እንዲወጣ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።

መልካም የትንሳኤ በዓል!!!

ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ-አስኪያጅ
ባለስልጣኑ በተሰጠው ሀላፊነት መሠረት የከተማው ኮሪደር መሠረተ-ልማት ጥበቃው አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

12/08/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአዲስ አበባ ከተማ በሚሠራው የልማት ኮሪደር መሰረተ ልማቶችና በመሰራት ላይ ያለው ሥራ የጥበቃ ሥራው አጠናክሮ እንደሚሠራ አስታወቀ ።

ባለስልጣኑ በዛሬው በትንሳኤ በዓል እለት ከ11ዱም ክ/ከተማ የተውጣጡ 2400 የደንብ ማስከበር አመራሮችና ኦፍሠሮች በማሳተፍ በቂርቆስ፣በየካና በአራዳ ክፍለ ከተሞች የጽዳት ዘመቻ አከናውኗል።

በጽዳት ዘመቻው በካሳንቺስ የልማት ኮሪደር ካሳንቺስ፣ ሴቶች አደባባይ ፣መለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን፣ አዋሬ፣ ግቢ ገብርኤል አካባቢ ተካሂዷል።

ባለስልጣኑ በደንብ ቁጥር 167/2016 መሰረት በኮሪደር ልማት ጥበቃ ላይ ለህብረተሰቡ በተለያዩ አግባቦች ሰፊ የግንዛቤ ስራ መስራቱ የገለጸ ሲሆን ደንብ በሚተላለፉ ግለሰቦች ላይ አስተማሪ እርምጃዎች መውሰዱን አስታውቋል።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በበዓል ቤተሰባቸውን ጥለው በተሰጣቸው ሀላፊነት መሠረት በጽዳት ዘመቻው የተሳተፉ አመራሮችና ኦፍሠሮች ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።

አክለውም የከተማው የኮሪደር መሠረተ-ልማት ጥበቃው አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።