የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
993 subscribers
1.5K photos
4 videos
1 file
51 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
በከተማዋ በ64% የደንብ መተላለፎች እንዲቀንስ ማድረግ መቻሉ ተገለፀ

ሚያዚያ 08/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከክፍለ ከተማ እና ከወረዳ አመራሮች ጋር በሳሬም ሆቴል የግምገማ መድረክ አካሂዷል ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣኑ በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ እየተወጣ ከተማችን እንደ ስሟ አዲስ ውብ ለነዋሪዎቿ ምቹ የቱሪስት መስህብ እንድትሆን እየሰራ መሆኑ ገልፀዋል።

አያይዘውም በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችን በመከላከል ደንብ በማስከበርና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የከተማዋን ሰላምና ጸጥታ በማስጠበቅ የበኩሉን እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ባለስልጣኑ በዘጠኝ ወራት ውስጥ በከተማችን የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች በ64% እንዲቀንስ ማድረግ መቻሉንና በሰው ተኮር ተግባራት ላይ በመሳተፍ ከ የ14 የአቅመ ደካማ ቤት እድሳትና ገንብቶ በማጠናቀቅ ለባለቤቶቹ ማስረከቡን ዋና ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በባለስልጣኑ እቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በኮለኔል አድማሱ ተክሌ ቀርቧል።

በሪፖርቱ ታቅደው የተፈጸሙ ክንውኖች ፣ በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ተግዳሮቶችን ለመፍታት የተወሰዱ መፍትሔዎች ተገልፃል።

በ9 ወሩ ከደንብ ተላላፊዎች ቅጣት እና ከተወረሱ ንብረቶች ጨረታ ሽያጭ ከ290 ሚሊዮን ብር በላይ ለከተማው ገቢ ማስገባት መቻሉን በሪፖርቱ ተገልጿል ።

በመጨረሻም በቀረበው ሪፖርት ዙሪያ ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጁ አቶ ንጋቱ ደኛቸው እና ም/ስራ አስኪያጁ ከፍያለው ታደሰ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም የማጠቃለያ ንግግርና የቀጣይ የስራ አቅጣጫ በዋና ሰራ-አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተቀምጦ መድረኩ ተጠናቋል ።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
ባለስልጣኑ የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር አካሄደ

09/08/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን መጪውን የትንሣኤ በዓል አስመልክቶ ለማዕከሉ ሰራተኞችና ለሚያሳድጋቸው ህጻናት የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም አካሂዷል ።

በማዕድ ማጋራቱ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ አንድነታችንን በመደጋገፍና በመረዳዳት በተግባር በማሳየት በተለይ በዓላቶችን በሚከበሩበት ወቅት ማዕድ በማጋራት አብሮነታችን ማጠናከር አለብን በማለት ተናግረዋል፡

አክለውም አብሮነታችንን አንድነታችንን ለማጠናከር እንዲህ አይነት ኢትዮጵያዊ እሴቶችን አጠናክረን መቀጠል ይገባቸዋል በማለት በዓሉ የሰላም፣የደስታ እንዲሁም የአንድነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በማዕድ ማጋራት ተካፋይ የሆኑት የደንብ ማስከበር ኦፊሰር ወ/ሮ መሰረት ግርማ በህመም ምክንያት እረፍት ላይ መሆናቸው ጠቅሰው ተቋሙ በሚችለው አቅም ሁሉ ላደረገላቸው ድጋፍና በዛሬው ወቅት ለተደረገላቸው የበዓል ማዕድ ማጋራት ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

በተጨማሪም የባለስልጣኑ አመራሮች ለባለስልጣኑ ሰራተኞች የእንኳን አደረሳቹ መልእክታቸውን አስተላልፈው የሰው ተኮር ተግባራቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል ።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
ባለስልጣኑ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ፅ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች በማስተባበር የዝቅተኛ ደምወዝ ተከፋይ ሰራተኛ ቤት ሙሉ እድሳት አደረገ

ሚያዝያ 09/2017 ዓ. ም
** በአዲስ አበባ**

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የደንብ ማስከበር እና የሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት በማስተባበር ለአንድ ዝቅተኛ ደሞዝ ተከፋይ ሰራተኛና ሙሉ የቤት ዕድሳት በማድረግ ለፋሲካ በአል ቤቱን አስረክቧል።

በርክክቡ ስነስርዓት ላይ በመገኘት መልእክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘርሁን ተፈራ ባስተላለፉት መልዕክት ሁሉም ሰው ከሚያሰራው ሰራተኛ ጀምሮ ያለበትን የኑሮ ደረጃ በማየትና በመለየት መተጋገዝ፣ አብሮ መቆምና መመረዳዳት እንዳለበት አንስተው ወጣት እሸቱ የነበረበት የኑሮ ሁኔታ ከባድ እንደነበር በማየት እንደዚህ አይነት እገዛ እንዲደረግለት የተባበሩ አካላትን አመስግነዋል።

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አየለ በበኩላቸው የፓርቲያችን ብልጽግና ሀሳብ እና የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶክተር አብይ አህመድ መልካም ጅምር የሆነውን እንደዚህ አይነት ሰዉ ተኮር ተግባር በመስራት ዜጎችን ተጠቃሚ የማድረግ ስራ ላይ ለመሰማራት እድል በማግኘታቸው እንደተደሰቱ በማንሳት እንደዚህ አይነት ተግባር በሁሉም መለመድ እንዳለበት ተናግሯል።

በመጨረሻም ቤት የታደሰለት ወጣት እሸቱ መሐመድ የቤት እድሳቱን ላስተባበሩ ሁሉ እና ስጦታ ስለተበረከተላቸው ምስጋና አቅርቧል።