የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.1K subscribers
1.79K photos
4 videos
1 file
53 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ በዛሬው እለት ደንብ ቁጥር 180/2017 የተላለፉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች 6,700,000/ስድስት ሚሊየን ሰባት መቶ ሺህ/ ብር መቅጣቱ ገለጸ

03/07/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቁ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት የገንዘብ ቅጣቶች በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱ ገለጸ፡፡

ባለስልጣኑ በዛሬው እለት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 1,800,000 ብር ፤በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 1,750,000 ብር፣ በአራዳ ክፍለ ከተማ 1,200,000 ብር፣በጉለሌ ክፍለ ከተማ 600,000 ብር ፣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ 400,000 ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል።

በተያያዘ ዜና በቦሌ ክ/ከተማ 450,000 ብር በኮልፌ ክ/ከተማ 400,000 ብር ፤በልደታ ክፍለ ከተማ 100,000 ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ በመውሰድ ለመንግስት ገቢ አድርጓል።

ባለስልጣኑ በአጠቃላይ በዛሬው እለት 24 ድርጅቶች እና 3 ግለሰቦች በድምሩ 6,700,000/ስድስት ሚሊየን ሰባት መቶ ሺህ/ ብር መቅጣቱ ገልጿል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍181
የወንዝ ብክለት ላይ ጠንከር ያለ የክትትልና የቁጥጥር ስራዎች እንደሚሰሩ ተገለፀ

04/07/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር "ንፁህ ወንዞች ፤ ለጤናማ ህይወት" በሚል መሪ ቃል የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት መከላከል ዙሪያ ከክፍለ ከተማው የደንብ ማስከበርና ከአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ጋር በመሆን ከ10ሩም ወረዳ ከተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት አካሄዷል።

የውይይቱ ዓላማ በየአካባቢው የሚገኙ ወንዞችን ከተለያዩ በካይ ቆሻሻዎችና ፈሳሾች ጥበቃ በማድረግ ተፈጥሮዓዊ ይዞታቸውን ይዘው እንዲፈሱ ለማስቻል እና የወንዝ ዳርቻ ልማት እና ብክለት መከላከል ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ የህብረተሰቡን ግንዛቤ መጨመር እንደሆነ ተገልጿል።

በመድረኩ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት በክፍለ ከተማችን ብሎም በከተማችን የከተማ አስተዳደሩ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቶች በማከናወን ላይ ይገኛል ይህም ወንዞች የቆሻሻ ማስወገጃ እንደሆኑ የነበሩ ዘልማዳዊ አስተሳሰቦች በመቀየር የህዝቦችን ተጠቃሚነት እና ኑሮን ያሻሻሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው አክለውም ከተማ አስተዳደሩ የወንዝ ዳርቻ ልማት እና ብክለት መከላከል ደንብ ቁጥር 180/2017 አውጥቶ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝና በደንቡ ዙሪያ በማስተማር ህጉን ተላልፈው በተገኙት ላይ አስተዳደሩ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል ብለዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳንኤል እዮብ በበኩላቸው የወንዝ ዳርቻ ልማት እና ብክለት መከላከል ደንብ ቁጥር 180/2017 አስመልክቶ የመወያያ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ ወንዞችንና የወንዝ ዳርቻዎችን በማልማት፤ ጠንካራ የብክለት ክትትልና ቁጥጥር ስራዎችን በመስራት አረንጓዴ ንፁህ ውብና ስፍራ እንዲፈጠርና የህግ ተከባሪነትን ለማረጋገጥ በሚሰሩ ስራዎች የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ተባባሪም መሆን እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በመልማቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው የወንዞችን ብክለትን ለመከላከል አካባቢያቸውን ንፁህ እና ማራኪ በማድረግ በሚሰሩ ተግባራት ላይ ተሳታፎዋቸውን እንደሚያጠናክሩ ተናግረዋል፡፡
👍1
የወንዝ ዳርቻ ልማትን ከማፋጠንና ብክለትን ከመከላከል ጋር ተያይዞ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ

መጋቢት 4/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወንዝ ዳርቻ ልማትን ከማፋጠንና ብክለትን ከመከላከል ጋር ተያይዞ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል።

በክፍለ ከተማው አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት እና በደንብ ማስከበር ጽ/ቤት አዘጋጅነት በተካሄደው መድረክ አመራሮች፣ የደንብና የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

በዕለቱም በደንብ ቁጥር 180/2017 አሰራርና አደረጃጀት ዙሪያ ማብራሪያ ሰነድ ቀርቦ ከተሳታፊዎች ሀሳብና አስተያየት ተሰጥቶበታል።

የክፍለ ከተማው ምክትል ስራ አስፈጻሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ድላየሁ ታምሬ የዲፕሎማሲና የቱሪዝም ከተማ የሆነችውን አዲስ አበባ ወንዞቿን ማልማትና ከብክለት መጠበቅ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል።

አቶ ድላየሁ አክለውም ወንዞችን ከኮሪደር ልማቱ ጋር በማቀናጀት ለልማትና ለመዝናኛነት ማዋል አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።

የክፍለ ከተማው አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስፋው ፋራህ በበኩላቸው የአካባቢ ብክለትን በመከላከል የከተማዋ ወንዞችን በጋራ በማልማት የድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል።

የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ መቶ አለቃ ቦጋለ አለሙ እንደገለፁት ህግና ስርዓትን በማስከበር፣ ግንዛቤ በመፍጠር እንዲሁም ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ ወንዞችን ከብክለት ለመጠበቅ በቅንጅት መስራት አለብን ብለዋል።
👍51