የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.73K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ ከሰላምና ጸጥታ ጋር በመሆን ከበጎፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ጋር የእግር ኳስ ውድድር አካሄደ

11/06 /2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ከሰላምና ፀጥታ ቢሮ ጋራ በመሆን ከበጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ሰረተኞች ጋር በተደረገው የእግር ኳስ ጨዋታ አምስት ለሶስት በሆነ ውጤት በማሸነፍ ተጠናቋል።

ውድድሩ ስፖርት ለሰላም በሚል መሪ-ቃል የተደረገ ሲሆን የደንብ ማስከበርና የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሰራተኞች ቡድን 5 ለ3 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

ጨዋታው ባለስልጣኑ በቀጣይ ለሚያቋቁመው ተስፋ የሚጣልባቸው ተጫዋቾች የታየበት ሲሆን በፍጹም የስፖርታዊ ጨዋነት
ተጠናቋል።
👏2
ባለስልጣኑ የስድስተኛ ዙር የኦፊሰር የምልመላ ሂደት በተመለከተ ውይይት አካሄደ

11-06 -2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስድስተኛ ዙር የኦፊሰር ምልመላ ሂደት እና የነባር ኦፊሰሮች ምደባ ዙሪያ የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር ውይይት ተካሄደ ።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ለተቋሙ ህገ-ወጥነትና ብልሹ አሰራርን የሚጸየፍ ፤የከተማውን ደህንነት የሚያስጠብቅና ለስራዎች መሳካት ዝግጁ የሆነ አባል ስለሚያስፈልገው የምልመላ መስፈርቱን መሠረት በማድረግ የሚያሞሉ ወጣቶችን ብቻ መመዝገብ እንዳለበት ገልጸዋል ።

የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ በበኩላቸው እንደተናገሩት የሚመዘገቡት ምልምል ኦፊሰሮች የወጣውን የዕድሜ ፣ የትምህርት ማስረጃ ፣ የአቋም፣ የስነምግባርና የመሳሰሉት መስፈርቶችን የሚያሟሉትን ጥርት ባለ መልኩ ምልመላ ማካሄድ ይገባናል ሲሉ ገልጸዋል ።

በውይይቱ መድረኩ የስድስተኛ ዙር የኦፊሰር ምልመላ ምዝገባ ሂደት አሁናዊ ሪፖርት የተመረጡ ክፍለ ከተሞች አቅርበው
የሰልጣኞች ምልመላም የተሳለጠ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስቸል በመሆኑ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት ምዝገባው መጀመራቸውና መስፈርቱን የሚያሟሉ ሰልጣኞች በወረዳዎች እየተመዘገቡ እንደሚገኙ የክ/ከተማ ኃላፊዎች ገልጸዋል ፡፡

የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ስነ-ምግባር የተላበሰና የሰላም ሀይል ለከተማው ሆኖ የሚያገለግል የኦፊሰር ምልመላ ለማድረግ ወደ ህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል ።

አክለውም ከአደረጃጀት አመራርና ከፖለቲካ አመራር ጋር የምልመላ ሁኔታውን የጋራ ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

በመድረኩ የኦፊሰሩን ሁኔታ ያገናዘበ የስራ መደብ ሁኔታ በማዘጋጀት ጥናት ተጠናቆ ወደ ተግባር መገባቱ ገልጸው ምደባው በጥንቃቄና በመመሪያው መሠረት መከናወን እንዳለበት የባለስልጣኑ የሰው ሀብት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ይልማ ተናግረዋል ።

በመጨረሻም በውይይቱ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች በባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች ምላሽ ተሰጥቶበታል ።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
👍2👏2
ባለስልጣኑ የቢሮ ሰራተኞች የደንብ ልብስን ይፋ አደረገ

የካቲት 13/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለቢሮ ሰራተኞች ያዘገጀውን የደንብ ልብስ ምርቃት ፕሮግራም በአድዋ ሙዚየም መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል ።

በፕሮግራሙ የአዲስ አበባ ምክር ቤት የፍትህና የመልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ ፣ የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች ፣የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥና አውት ሶርሲንግ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተመስገን በቀለ ፣ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ኮ/ር አህመድ መሀመድ ፣የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊዎች ፣የክፍለ ከተማ እና የወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፣ የማዕከሉ ዳይሬክተሮችና ሰራተኞች ፣ኦፊሰሮች አንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ አንደተናገሩት ቢሮው የተሰጠውን ተልዕኮ ከማከናወን ጎን ለጎን የሪፎርምና የለውጥ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱንና በዛሬው ዕለትም የዚሁ ሁለንተናዊ ሪፎርም አካል የሆነው ለቢሮ ሰራተኞች የተዘጋጀውንየ ደንብ ልብስ የማስተዋወቅ ስራ እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል ።

አክለውም የተቋም ግንባታ ስራዎችን በማጠናከር የስራ ቦታን ለሰራተኛው እና ለተገልጋዮች ምቹና ማራኪ አድርጓል፤ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር ስማርት ቢሮ ለመገንባት በሂደት ላይ መሆኑን ተናግረዋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥና አውት ሶርሲንግ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተመስገን በቀለ ከተማችን አዲስ አበባ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሪፎርም ስራ በማስፋት የተለያዩ የልማት ስራዎችን በማከናወን ከተማችን እንደ ስሞ አዲስና ውብ እንድትሆን 24/7 ጠንክሮ በመስረት የተለያዩ ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸውና በመመረቃቸው ከተማችንን ውብና ድንቅ ከተማ ማድረግ እንደተቻለው የአገልግሎት አሰጣጡንም በዚያ ደረጃ ማሻሻል እና አገልግሎትን በስታንዳርድ ልክ መስጠት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ምክር ቤት የፍትህና የመልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ ተቋሙ የተሰጠዉን ተልዕኮ ለመወጣትና ለስራዎች መሳካት የአመራሩና የሰራተኛው ቅንጅትና ግንኙነት በቀጣይም አጠናክሮ በማስቀጠል የስራ አፈጻጸሙን ከዚህ የተሻለ በማድረግ ውጤታማነቱን ማረጋገጥ ይችላል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከየት ወዴት ? በሚል የተዘጋጀው ሰነድ እና የ2017 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የተቋማት፣ዳይሬክተሮች፣ቡድኖች ፈጻሚዎች ምዘና ሪፖርት በባለስልጣኑ የስታንዳርዳይዜሽን ዝግጅት፣ አገልግሎት አሰጣጥ ድጋፍና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ቀጸላ ቀርቧል ።

በሰነዱ ባለስልጣኑ ከተመሰረተበት ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ አስከ አሁን ድረስ ያለው ነባራዊ ሁኔታና ያከናወናቸው ተግባራት ፣መዋቅራዊ አደረጃጀቶቹ በዝርዝር ተገልጿል ።

በመድረኩ በባለስልጣኑ የተለዩ የትጉህ ሰራተኞች የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡