የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.73K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ የመንገድ መሠረተ ልማት ያበላሸ ድርጅት 300,000 ብር መቅጣቱ አስታወቀ

03-06 -2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ምሽትን ተገን በማድረግ የቆሸሸ ውሃ አዲስ ወደ ተሠራው አስፓልት የለቀቀው የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ ) ብር በመቀሰጣት ያቆሸሸውን አካባቢ እንዲያጸዳ አድርጓል ፡፡

ባለስልጣኑ የህብረተሰቡ የጋራ ሀብት የሆኑ የኮርደር ልማትና በሌሎች አካባቢ የማገኙ መሠረተ ልማቶችን፣ለህዝብ የተሰሩ አረንጓዴ ስፍራዎች እና የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶችን ደህንነት በመጠበቅ እንዲገለገል መልዕክቱን አስተላልፏል ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በከተማዋ ደንብ የሚተላለፉ የግልና የመንግስት ድርጅቶች እና ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል ።

ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች መረጃ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
👍20👏2
ባለስልጣኑ በክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ሲያካሄድ የቆየውን የህዝብ ንቅናቄ መድረክ ማጠቃለያ ፕሮግራም አካሄደ

04/06/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በወረዳዎችና በክፍለ በከተሞች ሲካሄድ የቆየው የደንብ መተላለፍ እና ተያያዥ ህገ-ወጥ ተግባራት ለመከላከል ያለመ የህዝብ ንቅናቄ መድረክ ማጠቃለያ ፕሮግራም ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ ከተወጣጡ የከተማው ነዋሪዎች ጋር የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በጉለሌ ክ/ከተማ መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ከእቅድ አንፃር የተከናወኑ በርካታ የደንብ መተላለፎችን የመከላከል እና የመቆጣጠር ተግባራት እንዳሉ ጠቅሰው እነዚህ ተግባራት በህብረተሰቡ ተሳትፎ እና በባለድርሻ አካላት ትብብር የታገዙ እንደነበርና በቀጣይ ቀሪ ወራቶችንም ህብረተሰቡ ከጎናችን በመቆም በጋራ ሆነን ደንብ መተላለፎችን የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባር አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል ብለዋል ።

አክለውም በተሰጠን ተልዕኮ ዘጠኙ የደንብ መተላለፎችን በመከታተል እና በመቆጣጠር በህጋዊ መንገድ የሚሰራውን ማህበረሰባችን በአግባቡ በማገልገል እየተከናወነ ያለውን የሪፎርም ስራዎቻችንን በማጠናከርና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስራዎችን በማከናወን ከመቼውም ጊዜ በላይ ህብረተሰቡን ለማገልገል ዝግጁ መሆንናቸውን ገልፀዋል።

በመድረኩ የባለሥልጣኑ የ2017 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የተቋሙ እቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ አቅርበዋል ።

በሪፖርቱ ባለስልጣኑ የተሰጠውን ተልዕኮ በቁርጠኝነት ከመወጣት ጎን ለጎን ወደ ህብረተሰቡ በመውረድ ሰው ተኮር ስራዎችን በመከናወን በግማሽ ዓመቱ 11 የአቅመ ደካማ ቤቶችን ገንብቶ በማጠናቀቅ ለባለቤቶቹ አስረክቦል፣ የአረንጓዴ አሻራ ተግባራት በማካሄድ ችግኞችን መትከልና መንከባከብ ስራ ተከናውኗል እንዲሁም ወላጅ አልባ ህጻናት በመንከባከብ እያሳደገ እንደሚገኝ ተገልጿል ።

በተጨማሪም በመድረኩ የባለስልጣኑ የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የመልካም አስተዳደር ብልሹ አሰራር አፈጻጸም ሪፖርት እና በተሻሻለው ደንብ ቁጥር 167/2016 ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቧል።

በመጨረሻም በቀረቡት ሪፖርት እና ሰነዶች ዙሪያ ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች በባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል ።

ዘገባው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
👍9👏1
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት 38ኛው የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ በሰላም እንዲጠናቀቅ ለሰራተኞቹ የስራ ስምሪት መስጠቱ ገለፀ

5/06/2017
**አዲስ አበባ**

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በዛሬው ዕለት 38ኛው የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ በተሳካ ሁኔታና በሰላም እንዲጠናቀቅ ለክፍለ ከተማው ፓራሚሊተሪ ሰራተኞች የስራ ስምሪት (ኦረንቴሽን) ሰጥቷል ፡፡

በመድረኩ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳኜ ሂርጳሳ እንደገለፁት እንግዶች በምቹ ሁኔታ ጉባኤያቸውን አጠናቀው ወደ ሀገራቸው በሰላም እንዲመለሱ ሽፍት በማጠፍ አዳርን ጨምሮ የበኩሉን የፀጥታ ስራ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት 24 ሰዓት እንዲሰሩ ጥብቅ ስምሪት መሰጠቱና ክትትለሰ መጀመሩ ገልጿል ፡፡

በተያያዘ ዜና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በኮሊደር ልማት መንገድ አህዮች ሲያዘዋውር የተገኘው ግለሰብ ወድያው በቀጠና ኦፊሠሮች በቁጥጥር ሰር ውለው 5000/አምስት ሺህ/ ብር በመቅጣት ወደ ፋይናስ ገቢ ሆኗል።
👍5👏2
ባለስልጣኑ በሁለተኛው የብልጽግና መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ ከሰራተኞቹ ጋር ውይይት አካሄደ

06/06 /2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን "ከቃል እስከ ባህል" በሚል መሪ ቃል በ2ኛ የብልፀግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ ከማዕከሉ ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሄደ።

በውይይት መድረኩ የሁለተኛው የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ዙሪያ የተዘጋጀው ሰነድ በባለስልጣኑ የስነ-ምግባርና የጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዬብ ከበደ ቀርቧል።

በመድረኩም የፓርቲው የጉባዔ ውሳኔዎችና የቀጣይ አቅጣጫዎች በዝርዝር ቀርበዉ ሰፊ ዉይይት ተደርጓል የብልፅግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ላይ ቀጣይ ትኩተረት ሊሰጣቸው እንደሚገቡ አቅጣጫ በተቀመጠባቸው ነጥቦች በዝርዝር ቀርበዋል፡፡

በውይይቱ የባለስልጣኑ አመራር እና ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን ጠንካራ ተቋም መገንባት፣ ብሄራዊ ገዥ ትርክትን ማጠናከር ፣ የኢኮኖሚ እና ልማትን ከማፋጠን፣ ማህበራዊ ብልጽግና ከማረጋገጥ ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራዎችን መሠራቱ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ፓርቲው በአጭር ጊዜ በኢኮኖሚ ፣ በማህበራዊ እና በዲፕሎማሲው ረገድ አመርቂ ለውጦች ማምጣት ተችሏል ቀጣይነት እንዲኖረው ሁሉም የመንግስት ሰራተኛ የሚጠበቅበትን ሃላፊነት መወጣት ይኖርበታል ብለዋል።
👍6👏2🥰1