ባለስልጣኑ የ6 ወራት ቅንጅታዊ ስራዎች አፈፃፀም የእውቅና ሰጠ
13/05/2017 ዓ.ም
**አዳማ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በ2017 በጀት ዓመት በመጀመሪያው 6 ወራት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የተከናወኑ ተግባራት አፈፃፀም በመገምገም የከተማውና የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ባለድርሻ አካላት በጣም ከከፍተኛ እና ከፍተኛ አፈፃፀም ለስመዘገቡ ለ27 ተቋማት እውቅና ሰጥቷል።

👍6
ለከተማው ፈጣን እድገት የሚመጥን ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥና እና ህገ-ወጥነትን መከላከል መቻሉ ተገለፀ
15/05/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የ 2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚገኙ አመራሮችና ዳይሬክተሮች በተገኙበት የጋራ የግምገማ መድረክ አካሄዱ ።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር እና ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ ባከናወናቸው ተግባራት የከተማችንን ፈጣን እድገት የሚመጥን በከተማችን ላይ ዘላቂ ሰላም ማምጣት፣ የህብረተሰቡን የጸጥታ ስጋት መቀነስ እና ህገወጥነትን መከላከል ተችሏል ሲሉ ገልጸዋል ።
አክለውም በቅርቡ በተከበሩት የአደባባይ በዓላት የሀይማኖታዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን የታየበት ሆኖ በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ለተወጡ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
የባለስልጣኑ ዋና ሰራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደተናገሩት በስድስት ወራት ውስጥ በቅንጅት በመሰራቱ የከተማችንን ሰላም ማስጠበቅ እና የደንብ መተላለፎችን መቀነስ መቻሉን ገልፀው።
በቀጣይ ህዝብን የሰላም ባለቤት በማድረግ አጋዥ ሀይል አንዲሆን ማብቃት ፣ ተቋማችንን በቴክኖሎጂ የማዘመን ሰራዎችን ማጠናከር እንዲሁም በመዲናዋ የተገነቡ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ደህንነታቸው እንዲጠበቅ እና ህብረተሰቡ በአግባቡ እንዲጠቀምባቸው እየተሰራ ያለው ሰፊ የጥበቃ ሰራ በቀጣይነት ሊሰራ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮን የ6 ወር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ማስረሻ ሀብቴ ቀርቧል።
ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅትና በትብብር በመስራት በከተማዋ ውስጥ ሠላምን የሚያደፈርሱ አዝማሚያዎችን ቀድሞ በመለየት እና አንዳንድ የተፈጸሙ የወንጀል ድርጊቶችን ሳይባባሱ በቅንጅት በመከላከል የከተማውን እና የህብረተሰቡን ደህንነት በማስጠበቅ ላይ እንደሚገኝ በሪፖርቱ ተጠቅሷል ።
የባለስልጣኑ የ2017 የግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በባለስልጣኑ እቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ ቀርቧል።
በሪፖርቱ ባለስልጣኑ የተቋም ግንባታ ሰራዎች ማከናወኑን ፣የሥልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን በስፋት መስራቱ ተጠቅሷል ።
ከደንብ ተላላፊዎች ቅጣት እና ከተወረሱ ንብረቶች ጨረታ ሽያጭ ከ135 ሚሊዮን ብር በላይ ወደ ፋይናንስ ገቢ ማድረግ መቻሉን ተገልጿል ።
በቀረቡት ሪፖርት ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን ለቀረቡት ሀሳብና አስተያየቶች የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እና የባስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ምላሽና ማብራሪያ ተሰቶባቸዋል።
ዘገበው :- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን ነው።

👍2
ባለስልጣኑ የመንገድ መሠረተ ልማት ያበላሸ ድርጅት 300,000 ብር በመቅጣት ተጠያቂ ማድረጉ ገለፀ
16/05/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ካሳንቺስ አካባቢ ጨለማን ተገን በማድረግ የሽንት ቤት ፍሳሽ ወደ ኮሊደር ልማት አስፓልት የለቀቀው ኢንተርናሽናል ሆቴል በደንብ ማስከበር ባለስልጣን፣ በሰላምና ጸጥታ እንዲሁም ከፖሊስ ጋር በጋራ በመሆን እጅ ከፍንጅ በመያዝ በጥፋታቸው መሰረት 300,000 ብር በመቅጣት ቦታውን እንዲያጸዱ ተደርጓል።
ባለስልጣኑ በከተማችን ውስጥ የተለያዩ ስራ ላይ የተሠማሩ የንግድ ድርጅቶችና ግንባታ ገንቢዎች ሁሉ ህግና አሰራርን በመከተል በተሠጣችሁ ፈቃድ መሰረት በመንግስትና በህዝብ ሀብት የተገነቡ መሠረተ ልማቶችን ደህንነት በመጠበቅ እንዲሰሩ መለዕክቱን አስተላልፏል፡፡
የአዲስ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በከተማው ደንብ በሚተላለፉ የግልና የመንግስት ድርጅቶች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቃል።
ዘገባው፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

👍10❤1
ባለስልጣናኑ አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ እና ከፋና ቴሌቪዥን በጋራ ለመስራት የስምምነት ፊርማ ተፈራረመ
16/05/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የደንብ መተላለፎችን በተመለከተ የሚሰጠውን ግንዛቤ ለህብረተሰቡ ተደራሽነቱን ለማሳደግ ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ በቴሌቪዥንና በሬዲዮፕሮግራም እና በፋና ቴሌቪዥን በኦሮምኛ ቋንቋ ፕሮግራም በጋራ ለመስራት የስምምነት ፊርማ ተፈራረመ ።
ባለስልጣኑ ህብረተሰቡን እያዝናና ግንዛቤ የሚፈጥሩ ፕሮግራም በማዘጋጀት የባለስልጣኑ ተልዕኮ ፣ የደንብ መተላለፍ አይነቶችና ጉዳታቸው ፣ ደንብ መተላለፎችና ቅጣታቸው የተመለከቱ ፕሮግራሞች በአዲስ ሚዲያ በአማርኛና በፋና ቴሌቪዥን በኦሮምኛ ቋንቋ በሰፉ ሴራ ፕሮግራም ለመስራት አቅዷል ።
በስምምነት ፊርማው የባለስልጣኑ አመራሮች ከተቋማቱ አመራሮችና ተወካዮች በተገኙበት ተፈራርመዋል።
ዘገበው :- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ነው፡፡

👍9👏5
ባለስልጣኑ የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር አከናወነ
19/05 /2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ሰኞ ማለዳ ከስራ ገበታ በፊት የሚያካሂደው የእውቀት ሽግግር ፕሮግራም የባለስልጣኑ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት አካሄደ፡፡
የመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ የእውቀት ሽግግር የተሞከሮ መድረክ በአመራሩና በሰራተኞች መካከል ያለውን ግንኙነት በማጠናከር ተቀራርቦ ለመስራትና ለስራዎች ውጤታማነት የሚያግዝ መሆኑ ገልፀዋል።
በዕለቱ የባለስልጣኑ የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዬብ ከበደ የራሳቸውን የህይወትና የትምህርት እና የስራ ተሞክሮና ልምዳቸውን ለሌሎች አስተማሪ በሆነ መልኩ አጋርተዋል።
በእውቀት ሽግግር መድረኩ ሰራተኞች ስራቸውን አክብረው በመስራት በእውቀትና በክህሎት ራሳቸውን መገንባት እንዳለባቸው እና ተገልጋዮችን በቅንነት ማገልገል እንደሚገባቸው አቶ እዬብ ከበደ ተናግረዋል፡፡
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡