የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
992 subscribers
1.5K photos
4 videos
1 file
51 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ በሩብ አመቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን የደንብ መተላለፎችን መቀነስ መቻሉ ተገለፀ

ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓም
* አዲስ አበባ *

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በ2017 በጀት አመት የመጀመሪያው ሩብ አመት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የተሰሩ ተግባራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ በዲ ሊኦፖል ሆቴል አካሂድዋል።

በመድረኩ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደገለፁት በበጀት ዓመቱ ሩብ ዓመት በሶስት ወራት ውስጥ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የደንብ መተላለፍን ለመቀነስ የተሰሩት ተግባራት ይበል የሚያሰኝ እና ለከተማው እድገት ጉልህ ሚና ያላቸው ተግባር መሆናቸው ገልፀዋል::

የአዲስ አበባ ምክር ቤት የሰላም፣ ፍትህና መልካም አስተዳደር ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ የተቋም ግንባታ ስራ፣ የስልጠናና ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ በስፋት የተሰራና የተሻለ ለውጥ የመጣበት መሆኑን ገልፀዋል።

አክለውም በቀጣይ የተገኙ መልካም ውጤቶችን በማጠናከር ክፍተት የታየባቸው ስራዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅ ተግባር ስለመሆኑ አሳስበዋል::

በመድረኩ የባለድርሻ ተቋማት አመራሮች፣የባለስልጣኑ የስራ ኃላፊዎችና ክፍለ ከተማ የሰላምና ፀጥታ፣የፖሊስ፣የደንብ ማስከበር እና ሌሎች አመራሮችና የዘርፉ ባለሙያዎች ተገኝተዋል::

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፦
የሶሻል ሚዲያ ገፆቻችን ፎሎው፣ላይክ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
የፌስ ቡክ ገፃችን፦
https://www.facebook.com/profile.php?id=100082525711518&mibextid
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/codeenforcement
የዩቱብ ቻናላችን
https://youtube.com/@A.A.C.ACODEENFORCEMENT
የቲክቶክ አካውንታችን
https://www.tiktok.com/@addisababacodeenforcemen
የትዊተር/X/ ሚዲያ ገፃችን
https://x.com/Addis_Denb?t=u8wW3qnxWk48GYzJ4RD96Q&s=09
ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ!
ባለስልጣኑ ደንብ መተላለፎችን በመቀነስ አዲስ አበባን የአፍሪካ ከተሞች ተምሳሌት ለማድረግ በተጠናከረ ሁኔታ እየሰራ መሆኑ ተገለፀ

ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም
*አዲስ አበባ*

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አዲስ አበባ ከተማን ውብና ጽዱ ለማድረግ የጀመረውን ስራ አስፈላጊውን ግባት በሟሟላት ንቁና የተሟላ ቁመና ያለው ደንብ አስከባሪ ለዘመነች አዲስ አበባ/SMART Code Eforcement Officers for SMART Cities!!/ ለከተማው ለእምርታዊ እድገት ተቋሙን በመገንባት ህግን ለማስከበር በተሟላ ቁመና ላይ መሆኑ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ገልፀዋል::

አክለውም የተቋም ግንባታ ለሃገራዊ ልዕልና ለማረጋገጥ ደንብና ህግ የማስከበርና ለከተማችን ለውጥ እጅግ ወሳኝና አስፈላጊ መሆኑ ገልፀዋል።

ባለስልጣኑ ከዚህ በፊት በኦፊሰሩ ሲያነሱት የነበሩትን የደንብ ልብስ ይሟላልን ጥያቄዎች በተለይ ጃኬት፣ የዝናብ ልብስ፣ ዱላ በማሟላት የነበረውን የግብአት ችግር በመቅረፍ በተሟላ ቁመና አዲስ አበባን ውብና ጽዱ ፤ለነዋሪዎቿ ምቹና ለአፍሪካ ከተሞችም ተምሳሌት ለማድረግ በትጋት እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል::

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፦
የሶሻል ሚዲያ ገፆቻችን ፎሎው፣ላይክ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
የፌስ ቡክ ገፃችን፦
https://www.facebook.com/profile.php?id=100082525711518&mibextid
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/codeenforcement
የዩቱብ ቻናላችን
https://youtube.com/@A.A.C.ACODEENFORCEMENT
የቲክቶክ አካውንታችን
https://www.tiktok.com/@addisababacodeenforcemen
የትዊተር/X/ ሚዲያ ገፃችን
https://x.com/Addis_Denb?t=u8wW3qnxWk48GYzJ4RD96Q&s=09
ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ!
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በቴክኖሎጂ የታገዘ የባለጉዳይ የቅሬታ ማቅረቢያ ፎርም ይፋ አደረገ።

*አዳስ አበባ*
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተቋሙ ላይ የሚፈጠሩ ቅሬታዎችን መቀበል የሚያስችል ባር ኮድ የያዘ ፎርም ይፋ አደረገ።

ተቋሙ የአሰራር ስርዓቱን በቴክኖሎጂ በማዘመንና ከመቼውም ጊዜ በላይ የህብረተሰብ አገልጋይነቱን ለማረጋገጥ የሚያስችለውን የቅሬታ ማቅረቢያ ፎርም ይፋ በማድረጉ ማንኛውም ባለጉዳይ በተቋሙ ላይ ያለውን ቅሬታ በቀላሉ በማቅረብ ቅሬታው መፈታቱን መከታተል እንደሚች ያሳወቁት የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ የምስራች ግርማ ናቸው።

አክለውም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ 9995 የተባለ ነፃ የስልክ መስመር እንዳለውና የተለያዩ ጥቆማዎችን እንደሚቀበልና ከህብረተሰቡ ጋር ተቀራርቦ እየሠራ እንደሚገኝ አስታውሰዋል።
በአካል ጉዳተኞች ፅንሰ ሀሳብ እና በወጡ የህግ ማዕቀፎች ላይ ስልጠና ተሰጠ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአካል ጉዳተኞች ፅንሰ ሀሳብ፣ በአካል ጉዳተኞች ዙርያ በወጡ የህግ ማዕቀፎች እና አካል ጉዳተኞችን አካቶ ሰለመስራት ከሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር በመተባበር ለሁሉም ክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች የቅድመ መከላከል ሽፍት መሪዎች ፣ አስተባባሪዎች እና የስልጠና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ፡፡

ለዜጎች የተሰጠውን መብት የአካል ጉዳተኞችም መብት በመሆኑ አካል ጉዳተኞችን በማንኛውም የማህበራዊ ጉዳዮች ታሳቢ በማደረግ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው የባለስልጣኑ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ላቀች ሀይሌ ተናግረዋል ፡፡

በስልጠናው ባለስልጣኑ በአካል ጉዳተኞችን ዙርያ የሚጠበቅበት ጉዳዮች በርካታ ቢሆኑም በዋናነት የግንባታ ተረፈ ምርቶችን በእግረኛ መንገድ ላይ እንዳይቀመጡ በመከታተልና እርምጃ በመውሰድ ፣ ህገወጥ የጎዳና ላይ ንግዶችን በመከላከል መንገዶች ለአካል ጉዳተኞች ምቹ እንድሆኑ በማድረግ እና በተለያዩ ጉዳዮች ለይ አካል ጉዳተኞችን በማገዝ ማህበራዊ ኃላፊነቱን መወጣት እንደለበት ተገልጿል ፡፡

በስልጠናው በአካል ጉዳተኞች ፅንሰ ሀሳብ ፣ በአካል ጉዳት ዙርይ የወጡ አለም አቀፍ ህጎች ፣ሀገር አቀፍ ህጎች እና ከአካል ጉዳት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ፓሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን አስመልክቶ ሰፊ ግንዛቤ ተሰጥቷል፡

ዘገባው ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው