የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
992 subscribers
1.5K photos
4 videos
1 file
51 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
የከተማው ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች የባለስልጣኑ የ2017 ዓ.ም ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ገመገመ

ህዳር 05/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአዋጅ በተሰጠው ስልጣንና ተግባር ተቋሙ እያከናወነ ያለ ተግባራት እና ያለበት ሁኔታ በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የፍትህና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴዎች የመስክ ምልከታ በማድረግ የተሰራውን ስራ በተመለከተ የባለስልጣኑ ሀላፊዎችና የሚመለከታቸው የስራ ክፍል ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች በተገኙበት ገመገመ።

በግምገማው በሩብ ዓመቱ በቅንጅት ለመስራት በእቅዶች ላይ በመወያየት ከባለድርሻ አካላት ጋር ስምምነት ሰነድ መፈራረም መቻሉ እና ወደ ስራ መገባቱ፣ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዬች ዙሪያ ለፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች እና ለሲቪል ሰራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች መሰጠታቸውን፣በቁጥጥርና እርምጃ አወሳሰድ ዘርፍም በሩብ ዓመቱ በአብዛኛው የደንብ መተላለፎችን በመቀነስ ሂደት ላይ እንዳለ፣ በበጎ ተግባራት በተመለከተ የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ እንዲሁም ወላጅ ያጡ ህፃናትን እርዳታ ማድረግ መቻሉን በጥንካሬ ተነስቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት የፍትህ እና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክቡር አቶ መሉነህ ደሳለኝ ተቋሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ገልፀው አሁንም በርካታ ስራዎች እንደሚቀሩ እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የማዘመን ስራዎች ላይ ትኩረት ተሰቶ ሊሰራ እንደሚገባ ገልፀዋል።

በባለስልጣኑ የሚሰጡ አስተያየቶችን መነሻ በማድረግ ክፍተቶችን ለመሙላት ያለው ተነሳሽነት እና ፈጣን ምላሽ ይበል የሚያሰኝ መሆኑን ገልፀው ሊቀጥል እንደሚገባ ተናግረዋል።

በተጨማሪም የቋሚ ኮሚቴ አባል ዶ/ር ወርቅነሸ ምትኩ ባለስልጣኑ የኮሪደር ልማት ላይ የተሰጠውን ድርሻና የተወጣበት መንገድ በጠቅላይ ሚኒስተሩም ዘንድ እውቅና የተሰጠበት መሆኑ የሚበረታታና በቀጣይ ተጠናክሮ መቀጠል የሚገባው እንደሆነ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የተለያዩ የደንብ መተላላፎችን በከተማው ላይ ወቅቱን ጊዜውንና ባህሪውን እየቀያየሩ የሚሰሩ ስራዎች መኖራቸውንና ተቋሙ በቁርጠኝነት አሁንም የደንብ መተላለፎችን ለመቀነስ አጠናክሮ እየሰራ እንደሆነና በጋራ ከሚሰራቸው አካላት ጋር እንዲሁም ከከተማው ነዋሪ ጋር ያለውን ቅንጅታዊ ስራን በቀጣይም በማጠናከር የሚታዩ ክፍተቶች ላይ አጠንክረን እንሰራለን ብለዋል።

ዘገባው:-የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ደረቅ ቆሻሻ በመኪና ጭነው ያስገቡ ግለሰቦች 300,000 ብር ተቀጡ

ህዳር 11/2017 ዓ.ም
**ከአዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ደረቅ ቆሻሻን ወደ ከተማዋ በመኪና ጭነው በማስገባት ባልተፈቀደ ቦታ የጣሉ ግለሰቦች በገንዘብ መቅጣቱ አስታወቀ።

ግለሰቦቹ ከነ ተሽከርካሪአቸው በቁጥጥር ስር በማዋል በባለስልጣኑ በተሻሻለዉ የቅጣት ሰንጠረዥ 2 ደንብ ቁጥር 167/2016 ተራ ቁጥር 31.2 መሰረት እያንዳንዳቸው 100,000 /መቶ ሺህ/ ብር በድምሩ 300,000/ሦስት መቶ ሺህ/ ብር መቀጣታቸው የወረዳው ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ሃላፊ ሻለቃ ዋጋዬ አቶምሳ ገልፀዋል።

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተማዋ ውብ፣ጽዱ እና ማራኪ ለማድረግ ቀን ከሊሊት እየሰራ ባለበት ሰዓት የአካባቢ ውበቱ ሆን ብለዉ የሚያበላሹ ግድ የለሽ ግለሠቦችን አስተማሪ ቅጣት እየቀጣ መሆኑ ባለስልጣኑ አስታውቋል።

ባለስልጣኑ የደንብ መተላለፉን የፈፀሙ ግለሰቦች ተጠያቂ እንዲሆኑ መረጃውን ለሰጡትና እገዛ ላደረጉ የከተማዉን ነዋሪዎች እያመሰገነ በቀጣይም ሁሉም የከተማው ነዋሪዎች ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጡ ጥሪውን ያቀርባል።

መረጃው፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው ።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በባለስልጣኑ በ15 ቀናት የተከናወኑ አበይት ሁነቶች በዜና
ባለስልጣኑ በመንገድ መሠረተ ልማት ጉዳት ጉዳት ባደረሱና ባበላሹ ግለሰቦችን ተጠያቂ አደረገ

ህዳር 14/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ራስ መኮነን ድልድይ አካባቢ በኦቪድ ኮነስትራክሽን ግንባታ የሚሰሩ ግለሰቦችን በመንገድና በአረንጓዴ መሠረተ ልማት ላይ ጉዳት ባደረሱና ያበላሹ ግለሰቦችን በህግ ተጠያቂ አደረገ።

ባለስልጣኑ በአካባቢው በመንገድ መሠረተ ልማት ጉዳት ባደረሱና፣አረንጓዴ ቦታዎች በማበላሸትና በመርገጥ የተሠጣቸውን ቅጣት ባለመቀበል በአራዳ ክ/ከ ራስ ደስታ ፖሊስ ጣቢያ በፈፀሙት ጥፋት መሰረት በተሻሻለው የደንብ ቁጥር 167/16 መሠረት ክስ በመመስት ክትትል እያደረገ ይገኛል።

ባለስልጣኑ ክስ የመሠረተባቸው የድርጅቱ ሰራተኞ
1ኛ-አቶ ናሆም ብርሃነ ስላሴ አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት
2ኛ -አቶ ፍቅሩ ፅጌ ሰርቪስ አገልግሎት
3ኛ- አረጋይ በርሄ ፕሮጀክት ማናጀር ናቸው።

ባለስልጣኑ በከተማችን ውስጥ የሚገኙ በግንባታ ስራ ላይ የተሠማሩ ድርጅቶችና ሰራተኞች የከተማ አስተዳደሩ ያወጣቸውን ህግና ደንቦችና አሰራሮችን በመከተል በመንግስትና በህዝብ ሀብት የተገነቡ መሠረተ ልማቶችን በመጠበቅና እንዲሠሩ መልዕክቱን ያስተላልፋል።

ባለስልጣኑ በደንብ ተላላፊዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ አሳውቋል።
የባለስልጣኑ የአገልግሎት አሰጣጥ ቅሬታ ማቅረቢያ ፎርም