የፈጠራ ባህል መፍጠር (creating a culture of creativity) እና ከማህበረሰብ ጋር ያለ ተግባቦት ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ
ህዳር 23/2018
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለማዕከል ዳይሬክተሮች ፣ ቡድን መሪዎች ፣ ለክፍለ ከተማ ቡድን አስተባባሪዎች እና የስልጠና ባለሙያዎች የፈጠራ ባህል መፍጠር (creating a culture of creativity) እና ከማህበረሰብ ጋር ያለ ተግባቦት ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ባለስልጣኑ የግንዛቤ ፈጠራ ላይ ትኩረት በመስጠት በርካታ ስራዎች እየሰራ መሆኑንና በዚህም የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሩን በተለያዩ ዙሮች ማሰልጠኛ በማስገባት ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ጠቁመዋል ።
የዛሬው ስልጠናም የፈጠራ ባህልን እንዴት ማሳደግ እንደሚቻልና ተቋማዊ ተግባቦት እንዴት መፍጠር እንደሚቻል የሚያሳይ ስለሆነ የሚሰጡትን ስልጠናዎች በትኩረት በመከታተል እንደሚገባ አሳስብዋል ።
የፈጠራ ባህል መፍጠር (creating a culture of creativity) እና በተግባቦት ክህሎት ስልጠና በአዲስ አበባ ከተማ አመራር አካዳሚ ከፍተኛ አሰልጣኝ አቶ ወልደመድህን መኮንን ተሰጥቷል።
ከማህበረሰብ ጋር ያለ ተግባቦት ዙርያ ስልጠና የሰጡት የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ የከተማ አመራር ልማት ዳይሬክተር እና ከፍተኛ አሰልጣኝ የሆኑት ወ/ሮ ነፃነት የምሩ ሲሆኑ ተግባቦት ለአንድ ተቋም ስኬትና ውጤት አንዱ መለኪያ እነደሆነ፣ የመሪና የተመሪ ተግባቦት ለስራ ቅልጥፍና እንደሚጠቅም ፣ ለአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት ጉልህ ሚና እንዳለው እና በተቋም ውስጥ ያሉ ሰራተኞች ጤናማ ተግባቦት እንደሚኖራቸው በስልጠናው ተመላክቷል ።

❤5
ባለስልጣኑ በትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታ እና ሙስናን መከላከል ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑ ተገለፀ
25/03/2018 ዓ.ም
ሰንዳፋ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለሁለተኛ ዙር የአካል ብቃትና የንድፈ ሀሳብ የአቅም ግንባታ ሰልጣኝ አመራርና ፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታ እና ሙስና በመከላከል ዙሪያ ሰንዳፋ በሚገኘው የፌደራል ፓሊስ ዩኒቨርሲቲ ግምገማዊ ስልጠና ሰጥቷል
በስልጠናው የባለስልጣኑ የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ እና የቁጥጥርና እርምጃ አወሳሰድ ዳይሬክተር አቶ ግሩም ወልደ መስቀል ተቋሙን ከስነ-ምግባር አኳያ በጥንካሬ እና በድክመት የሚታዩና ነባራዊ ሁኔታ ፣ የደንብ መተላለፍ መንስኤና ተፅዕኖ ፣ ተግዳሮትና የመፍትሄ ኃሳቦች እንዲሁም ሌሎች ነጥቦች በጥልቀት የያዘ ሰነድ ላይ መሰረት ያደረገ ግምገማዊ ስልጠና ተሰጥቷል
ከቀረበው ሰነድ በመነሳት ፈጻሚዎች ከቅርብ ኃላፊ ጋር ስላለው መልካም ግንኙነት፣ 24/7 ስምሪት አሰጣጥ ላይ በሚፈጠሩ የመናበብ ክፍተት፣ ደንብ በማስከበር ሂደቱ ላይ መወሰድ ስለሚገቡ ጥንቃቄዎች ስለሚገጥሙ ተግዳሮቶች፣ ብልሹ አሰራርን የሚጠየፍ እና በስነምግባር የታነፀ ኦፊሰር ከመፍጠር አንጻር መወሰድ ስለሚገባቸው የመፍትሄ ሀሳቦች ከሰልጣኞች በማንሳት ሰፊ ውይይት ተካሂድዋል
በመጨረሻም በተነሱ ጥያቄና ሀሳቦች ላይ በባለስልጣኑ ዳይሬክተሮች እና የስልጠና አስተባባሪዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት በቀጣይ ተቋሙ ለሚደረገው ትውልድን በስነ-ምግባር የመገንባትና ብልሹ አሰራርን የመከላከል ጉዞ ከስልጠናው በወሰዱት እውቀት በመታገዝ የተሻሉ ስራዎች ሊሰሩ እንደሚገባ የጋራ በማድረግ ግምገማዊ ስልጠናው ተጠናቋል
ዘገባው የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው

❤3👍1
የደንብና መመሪያዎች ተፈጻሚነት ለማረጋገጥ የበጎ ፈቃደኞች ሚና ጉልህ መሆኑ ተገለፀ
ህዳር 26/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ ልማት ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ከወረዳ እና ከክ/ከተማ ለተውጣጡ በጎ ፈቃደኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
በስልጠናው የቅድመ መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካለም ጌታሁን እንደገለፁት የስልጠናው ዋና ዓላማ የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ የወንዞች ዳርቻ ልማት ብክለት በመከላከል የህብረተሰቡ ጤና ለመጠበቅ የበጎ ፈቃደኞችን ሚና በማሳደግ የደንብና መመሪያዎች ተፈጻሚነት ለማረጋገጥ መሆኑን ገልፀዋል።
የወንዞች ዳርቻ ልማትና ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት በማድረግ የወንዝና ወንዝ ዳርቻ ስለማልማትና ከብክለት ስለመከላከል፣ ስለተከለከሉ ተግባራትና ቁጥጥር፣ ስለ ተቆጣጣሪው ተግባርና ኃላፊነት፣ ጥቆማና አቤቱታ አቀራረብ፣ ስለ አስተዳደራዊ እርምጃ አወሳሰድ እና ተደጋጋሚ ቅጣትና መሰል ጉዳዮች የዳሰሰ ሰነድ በባለስልጠኑ የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ የስልጠና ባለሙያ በሆኑት አቶ ናታናን ታዬ ቀርቧል።
በቀረበው ሰነድ በመቀጠል የበጎ ፈቃደኞችን ግንዛቤ ከማስጨበጥ አኳያ እየተሰሩ ያሉ ሰራዎች ምን ይመስላሉ ፣ በጎ ፈቃደኞች ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር በቅንጅት የመስራት ሂደቱና ኃላፊነት ከመወጣት አንጻር ያለበት ደረጃ እና እየገጠሙ ባሉ የግንዛቤ ክፍተቶች ላይ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በማንሳት ሰፊ ውይይት ማድረግ ተችሏል።
በመጨረሻም ተሳታፊዎች ባነሷቸው የግልጸኝነት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ ከመድረክ ምላሽ በመስጠት በቀጣይ እንደክፍተት በተጠቀሱ የግንዛቤና የደንብ መተላለፎች ዙሪያ ከተቋሙ ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ በመግለጽ ስልጠናው ተጠናቋል።
መረጃው፦ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

👍3