የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.22K subscribers
2.3K photos
5 videos
1 file
56 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
የከተማው ምክር ቤት የፍትህና መልካም አስተዳደር የቋሚ ኮሚቴዋች የባለስልጣኑ የ1ኛ ሩብ አመት አፈፃፀም ገመገሙ

ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበበ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም የፍትህ መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴዎች የከተማ አስተዳደሩ ደንብ ፣ማስከበር ባለስልጣን የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት የተሰሩ የዕቅድ አፈፃፀም ስራዎችን ገመገሙ፡፡

በግምገማው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የሰላም ፍትህና መልካም አስተዳደር የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር መሀመድ ገልማ ባለስልጣኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እራሱን በማሳደግ በለውጥ መንገድ እየሄደ መሆኑንና የከተማ አስተዳደሩን የደንብ ጥሰቶች በመከላከል በመቆጣጠር ሰፊ ስራዎችን እየሰራ መሆን ገልፀዋል ።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣኑ በቋሚ ኮሚቴዎች ክትትልልና ድጋፍ እርምቶችንና ማስተካካያዎችን በማድረግ በ2017 በጀት አመት ተሸለሚ መሆኑን በመግለፅ በዚህም አፈፃፀሙን በመገምገም እና ዕውቅና በመስጠት ወደ 2018 በጀት መሻገሩን ተናግረዋል ።

አያይዘውም በሩብ አመቱ በርካታ ስራዎችን በመሰራታቸው በከተማዋ ከለፈው አመት ተመሳሳይ ጊዜ አንፃር የደንብ ጥሰቶችን በ83.8% መቀነሱን ጠቅሰው ለሀገሪቱ ክልል ከተሞችም ተሞክሮ እና ልምድ በማካፈል አስተዎፆ እያበረከተ መሆኑን አስገንዝበዋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የ2018 በጀት አመት የ1ኛ ሩብ አመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ በአቶ ተስፋሁን አሉላ ቀርቧል ።

በሪፖርቱ በሩብ ዓመቱ የአገልግሎት አሰጣጥን ከማዘመን ፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመፍታት ፣ አገልግሎትን በአንድ ማዕከል በመስጠት፣ የተገልጋይ መማክርት ካውንስል ስለመቋቋሙ ፣በርካታ የሥልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ስለመሰራታቸው ፣ በበጎ ፍቃድና ሰው ተኮር ሰራዎችን በስፋት መስራቱ በሪፖርቱ ተካቷል።

በከተማዋ ከሚታዪ የተለያዩ የደንብ መተላለፎችን የመከላከል የመቆጣጠር ስራዎች በመስራት እርምት የሚያስፈልጋቸውን አስተዳደራዊ እርምጃ በመውሰድ ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ለከተማው ገቢ ማስገባቱ በሪፖርቱ ቀርቧል ፡

ከቋሚ ኮሚቴው አባላት ባለስልጣኑ ከዕለት ወደ እለት እራሱን በማሻሻል አዳዲስ ስራዎችን የሚያመጣ በስኬት የተከበበ መሆኑን በመጠቆም በተለይ የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰር ስምሪት መስተካከል መቻሉ፣ቅንጅታዊ አሰራር መፈጠሩ አና መሬት ባንክ የገቡ መሬቶች መጠበቅ መቻለቸው ባለስልጣኑ ኃላፊነቱን በትኩረት በመስራት እየተወጣ መሆኑን የቋሚ ኮሚቴው ተወካዮች ገልፀዋል።

በመጨረሻም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ከቋሚ ኮሚቴ አባለት የተነሱላቸውን ሀሳብ አስተያየት ጥያቄዎች ማብራርያ እና ገለፃ በማድረግ ምዘናው ተጠናቋል ።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
2
ባለስልጣኑ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን 820,000(ስምንት መቶ ሀያ ሺህ) ብር መቅጣቱ አስታወቀ

6/02/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በዛሬው ዕለት በወንዞችና የወንዞች ዳርቻ በካይ ቆሻሻ የለቀቁ ድርጅቶችና ግለሰቦችን መቅጣቱ አስታውቋል።

ባለስልጣኑ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የሽንት ቤት ፍሳሽ ቆሻሻ ከድሬኔጅ ጋር አገናኝቶ የለቀቀ ቱሉዲምቱ ማህበር ቤት 300,000 ብር ተቀጥቷል።

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ደንብ ማስከበር ፅህፈት ቤት አሳማ እርባታ ድርጅት በካይ ፍሳሽ ቆሻሻን ከጎርፍ መውረጃ ቦይ ወደ ወንዝ በማገናኛት 400,000 (አራት መቶ ሺህ ብር) በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዶበታል።

በእለቱ በደንብ ቆሻሻን በአግባብ አለመያዝና በአይነት ባለመለየትና ወደ ወንዝ በመጣል ደንብ የተላለፉ ግለሰቦች 120,000 ( አንድ መቶ ሃያ ሺህ) ብር አስተዳደራዊ ቅጣት በመቅጣት እርምጃ እርምጃ ተወስዷል።

ተቋሙ መረጃውን ለባለስልጣኑ በመስጠት የአካባቢ ብክለት መከላከል እንዲቻል የጠቆሙትን የህብረተሰብ ክፍሎችን እያመሰገነ በቀጣይ ህብረተሰቡና ተቋማት ከዚህ ዓይነት ድርጊት እንዲቆጠቡም አሳስቧል:

በተጨማሪም ህብረተሰቡ ለማንኛውም አይነት የደንብ መተላለፍ በነፃ ስልክ 9995 መረጃና ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍71👏1
ባለስልጣኑ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከለ ድርጅት 400,000(አራትት መቶ ሺህ) ብር መቅጣቱ አስታወቀ

07/02/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በዛሬው ዕለት ወንዝና የወንዝ ዳርቻ በካይ ቆሻሻ ከከፍሳሽ ማስወገጃ ያገናኘው ድርጅት ሳውዝ ጌት ፕላዛ ድርጅት 400,000 ብር የቅጣት እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

ድርጊቱ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ኤድናሞል አካባቢ ሳውዝ ጌት ፕላዛ/South Gate plaza/ ፍሳሽ ቆሻሻን ከሽንት ቤት ፍሳሽ ጋር ከ drainage ጋር በማገናኘት ወደ ወንዝ እየለቀቀ መሆኑ ተደርሶበት ተቀጥተዋል ።

ህብረተሰቡ ለማንኛውም አይነት የደንብ መተላለፍ በነፃ ስልክ 9995 መረጃና ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍21
ባለስልጣኑ የደንብ መተላለፎች ግንዛቤ ለማሳደግ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ደጋፊዎች ማህበር እና ከበጎ ተጽዕኖ ፈጣሪ ቲክቶከር ወጣቶች ጋር ተወያየ

07/02/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የደንብ መተላለፎች ግንዛቤ ለማሳደግ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ደጋፊዎች ማህበር እና ከበጎ ተጽዕኖ ፈጣሪ ቲክቶከር ወጣቶች ጋር በተቋሙ ተግባርና ኃላፊነት ዙሪያ ለግንዛቤ የሚሆን እና አብሮ መስራት የሚያስችል የውይይ መድረክ በባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣኑ ከተማዋን ከደንብ መተላለፍ የጸዳች ለማድረግ በርካታ ስራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑ ገልፀዋል።

የሶሻል ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ እንደመሆናቹ፤ የተቋሙን ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም የተለያዩ የሚያከናውናቸውን ሰው ተኮር በጎ ተግባራትን ለህብረተሰቡ በማሳወቅ የበኩላችሁን ሀላፊነት እንዲወጡ ጠይቀዋል።

በተጨማሪም ከተቋሙ ጎን ሆናችሁ አንዳንድ የሚስተዋሉ ክፍተቶች እንዲታረሙ መልካም ተግባሮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ሀሳብና አስተያየቶችን እየሰጣችሁ ከተማችን የደንብ ጥሰት የቀነሰባት ውብ ጽዱና፣ ለነዋሪዎቿና ለእንግዶች ምቹ የማድረግ ተግባርን በጋራ እንድንወጣ እናንተም የዜግነት ግዴታችሁን የበኩላችሁን በማድረግ ልታግዙ ይገባል ሲሉ ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከየት ወዴት ? በሚል የተዘጋጀው ሰነድ በባለስልጣኑ የደንብ መተላለፍ መከላከልና የግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክተር ወ/ሮ ስርካለም ጌታሁን ቀርቧል ።

በሰነዱ ባለስልጣኑ ከተመሰረተበት ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ አስከ አሁን ድረስ ያለው ነባራዊ ሁኔታና ያከናወናቸው ተግባራት ፣ መዋቅራዊ አደረጃጀቶቹ በዝርዝር ተገልጿል ።

ከተማችንን ከደንብ መተላለፍ የጸዳች የጸጥታ ችግር የሌለበት ለማድረግ ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራው ያለው ጠቀሜታ ሰፊ በመሆኑ ወጣት የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ስራዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ከተቋሙ ጋር ተቀናጅተው መሰራት እንደሚገባ የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ ገልጸዋል ።

አክለውም የዛሬው መድረክ በጋራ ስራዎችን ለመስራትና የመጀመሪያ የምክክር ፕሮግራም መሆኑንና በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል ።

በመድረኩ የተገኙት ተሳታፊዎቹ ስለ ተቋሙ ተግባርና ኃላፊነት የተደረገላቸው ገለጻ ከዚህ በፊት ስለ ደንብ ማስከበር የነበራቸው አላስፈላጊ ግንዛቤ የቀየረና መቅጣት ብቻ ሳይሆን በርካታ ሰው ተኮር ስራዎችንን የሚሰራ እና የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎችን በሰፊው በመስራት የደንብ መተላለፍን የሚከላከል መሆኑን በመገንዘብ በቀጣይም የተቋሙ አምባሳደር በመሆን በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸው ገልጸዋል ።

በመጨረሻም ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ደጋፊዎች ማህበር ሰብሳቢ ጋር በቀጣይ አብሮ ለመስራት የስምምነት ፊርማ ተፈራርመዎል።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
1👏1😎1