የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.02K subscribers
1.53K photos
4 videos
1 file
51 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ አስከ ምሽቱ 4 ሰዓት አገልግሎት ለመስጠት ውይይት አካሄደ

06/10/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የከተማው የምሽት የስራ እንቅስቃሴ መሠረት በማድረግ የስራ ሰዓቱን እሰከ ምሽቱ 4 ሰዓት በ3 ሺፍት ለመስራት የሚያስችል አሰራር ለማስጀመር ከክፍለ ከተማና ከወረዳ ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት አመራርሮች ጋር ውይይት አደረገ ።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ-አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ተቋማችን በከተማ አስተዳደሩ በተሰጡት ሀላፊነት መሠረት ኃለፊነቶችን በአግባቡ ለመወጣት አዲስ የተመረቁ ኦፊሰሮች መሠረት ያደረገ የአሰራር ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑ ገልፀዋል።

አክለውም ከተማውና ወቅቱን ያገናዘበ የደንብ መተላለፎች መከላከልና መቆጣጠር እንዲቻል በምሽትና በሦስት ሽፍት እንዲሰራ መወሰኑ ገልፀዋል።

የባለሥልጣኑ በ3 ሽፍት መስራት የሚያስችል የአመራርና የኦፊሰር ስምሪት ማስፈጸሚያ አጭር እቅድ በባለስልጣኑ የደንብ መተላለፍ ክትትል ቁጥጥርና እርምጃ አወሳሰድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ግሩም ወ/መስቀል ቀርቧል።

በእቅዱ በከተማ አስተዳደሩ በየጊዜው መልካቸው እየቀየሩ የመጡት ለደንብ መተላለፎች ለመቆጣጠር ምሽትንም ጭምር በመስራት በቦታና በጊዜ ስምሪት በመስጠት ለሚፈጠረው ክፍተት ተጠያቂነት ማስፈን ለማስቻል መሆኑን አቶ ግሩም ወ/መስቀል ገልጸዋል ።

በተዘጋጀው እቅድ ላይ ሰፊ ውይይቱ የተደረገ ሲሆን በእቅዱ ተፈፃሚነት ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶችና መደረግ ያለባቸው ቅድመ ዝግጅቶች በተመለከተ አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል ።

መረጃው፡-የባለሥልጣኑ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
ባለስልጣኑ የቀጣይ 90 ቀናት ማስፈጸሚያ እቅድ ላይ ከክ/ከተማ እና የወረዳ የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሄደ

06-10 -2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የቀጣይ 90 ቀናት እቅድ በተመለከተ የባለስልጣኑ አመራሮች በተገኙት ከክ/ከተማ እና የወረዳ የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር የውይይት መድረክ በባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በ90 ቀናት በምናከናውናቸው ተግባራት የከተማችን ህብረተሰብ የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በመመለስ የሰው ተኮር ስራዎቻችንን በማጠናከር እንዲሁም የደንብ ጥሰቶችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲያስችል በየደረጃው ያሉ መዋቅሮችንና ህብረተሰቡን አስተባብረን የምናከናውነውን ተግባራት በተቀናጀ ሁኔታ መፈጸምና እቅዳችንን በስኬት በማጠናቀቅ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የ90 ቀናት እቅድ በባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው በዝርዝር አቅርበዋል ።

በዕቅዱ የሰላም ግንባታ ስራ በተቀናጀ የህብረተሰብ ተሳትፎ ማጠናከር ፣ የደንብ ጥሰት የቅድመ መከላከልና ቁጥጥር ስራዎችን ማጎልበት፣ የክረምት የበጎ ፍቃድ ስራዎችን በላቀ ሁኔታ መምራት ፣ የኑሮ ውድነትን ማረጋጋትና ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴን መከላከል መቆጣጠር ፣ የአረንጓዴ አሻራና የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ እንዲሁም የኮሪደር ልማት እና የመሰረት ልማት ጥበቃ ስራዎችን በተሳካ ሁኔታ ሊከናወኑ እንደሚገባ በ90 ቀናት እቅድ ተገልጿል ።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በዘጠና ቀናት አቅድ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት ለስራዎች መሳካት ከወዲሁ ዝግጅታቸውን በመጀመር ውጤታማ ተግባር ለማከናወን ቁርጠኛ መሆናቸው ገልጸዋል ።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶበት ቀጣይ የስራ አቅጣጫ የባለስልጣኑ ዋና ሰራ አስኪያጅ አስቀምጠው መድረኩ ተጠናቋል ።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
ለስድስተኛ ዙር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የምስጋና፣የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራም ተካሄደ

07-10 -2017 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ለስድስተኛ ዙር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰር ከስልጠና ጀምሮ እስከ ምርቀት ፕሮግራም መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት በሳሬም ሆቴል የምስጋና እና እውቅና ፕሮግራም ተካሄደ ።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የስድስተኛ ዙር ስልጠና እንዲከናወን ሌት ተቀን በመስራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የባለስልጣኑ እና አጋር ተቋማት ሰራተኞች በተቋሙ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

አክለውም በስራውም ላይ በመተባበር ከተማዋን ከደንብ መተላለፍ የጸዳች ለነዋሪዎቿ እና ለእንግዶች ምቹ ማድረግ ይገባናል ሲሉ ተናግረዋል ።

የእለቱ የክብር እንግዳ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ ስልጠናው በታሰበለት ግብ ውውጤታማ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከታችሁ አካላት በሰላምና ጸጥታ ስም ምስጋናቸውን አቅርበው የተሰጣችሁ እውቅናና ምስጋና ለቀጣይ ተጨማሪ ኃላፊነትም ጭምር እንዲሆን ለማስታወስ እወዳለሁ ብለዋል።

ከተማችን ከመዘመኗ ጋር አብሮ የዘመነ የጸጥታ ሀይልና ደንብ አስከባሪ ሰራዊት ያስፈልጋታልበዚህ አግባብ የደንብ ስራንም በማጠናከር ፈረቃውን ወደ ሶስት በማድረግ በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች ላይ በቁርጠኝነት መከላከል እንደሚገባ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ አሳስበዋል ።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
ባለሥልጣኑ የቀጣይ 90 ቀናት እቅድ በተመለከተ ከማዕከል ሰራተኞች ጋር ውይይት አደረገ

ሰኔ 9/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የቀጣይ 90 ቀናት እቅድ በተመለከተ አና በኢትዮ ኮደር የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙት ከማዕከል ሰራተኞች ጋር በባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ የውይይት አካሂዷል ።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በቀጣይ 90 ቀናት በይበልጥ ሰው ተኮር ስራዎች የሚሰሩበት እንደመሆኑ ሁሉም የበኩሉን መወጣት እንደሚገባ እና የኢትዮ ኮደር ስልጠናንም ሁሉም ሰራተኛ ሊተገብር እንደሚገባ ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

የባለስልጣኑ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቡድን መሪ በሆኑት በአቶ ሚሊዮን ካሳሁን አማካኝነት ስለ ኢትዮ ኮደር ምንነት፣5ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ምንድን ነው፣የፕሮግራሙ አለማ፣ ያሉ ፕሮግራም እና አጠቃቀም አስመለክቶ በዝርዝር አቀርቧል ።

የባለስልጣኑ የ90 ቀናት እቅድ በተመለከተ ባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ በአቶ ንጋቱ ዳኛቸው አማካኝነት አቀርቧል ።

በዕቅዱ ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴን መከላከል መቆጣጠር ፣ የአረንጓዴ አሻራና የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ በችግኝ ተከላ ፣ቤት እድሳት ፣ማዕድ ማጋራት እንዲሁም የኮሪደር ልማት እና የመሰረት ልማት ጥበቃ ስራዎችን በተሳካ ሁኔታ ሊከናወኑ እንደሚገባ ዕቅዱ በዝርዝር አቀርቧል ።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡