ባለስልጣኑ በኮሪደር መሠረተ-ልማት ላይ በእግረኞች መንገድ በተሽከርካሪ በመሄድ ደንብ ተላልፈው የተሰወሩ አሽከርካሪዎች 300 ሺህ ብር መቅጣቱ አስታወቀ
10/10/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በትላንትናው እለት በቂርቆስ ክፋለ ከተማ ወረዳ 03 ወሎ ሰፈር አካባቢ በተሠራው የኮሪደር ልማት መሰረተ ልማት የእግረኞች መንገድ ላይ በተሽከርካሪ በመሄድ ደንብ ተላልፈው የተሰወሩ አሽከርካሪዎች ከአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ፖሊሶች ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር በማዋል መቅጣቱን አስታወቀ ።
ግለሰቦቹ በህብረተሰቡ ጥቆማ መሠረት ክትትል በማድረግ 3 አሽከርካሪዎች ከነ ተሽከርካሪአቸው በቁጥጥር ስር በማዋል እያንዳንዳቸው 100.000 (አንድ መቶ ሺህ ብር )በድምሩ 300,000/ሦስት መቶ ሺህ/ ብር መቀጣቱን ገልጸዋል ።
ባለስልጣኑ የህብረተሰቡ የጋራ ሀብት የሆኑ የኮርደር ልማትና በሌሎች አካባቢ የማገኙ መሠረተ ልማቶችን፣ለህዝብ የተሰሩ አረንጓዴ ስፍራዎች እና የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶችን ደህንነት በመጠበቅ በሀላፊነት እንዲገለገል መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በከተማዋ ደንብ የሚተላለፉ የግልና የመንግስት ድርጅቶች እና ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል ።
ህብረተሰቡ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች መረጃ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።
መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

👍20❤4
ለስድስተኛ ዙር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና መሳካት የማዕከሉ ሰራተኞች ላደረጉት አስተዋጽኦ የምስጋና ፕሮግራም ተካሄደ ።
12-10 -2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ለስድስተኛ ዙር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰር ከስልጠና ጀምሮ እስከ ምርቀት ፕሮግራም መሳካት የማዕከሉ ሰራተኞች ላበረከቱት አስተዋጽኦ የምስጋና ፕሮግራም ተካሄደ ።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የስድስተኛ ዙር ስልጠና እንዲከናወን ሌት ተቀን በመስራት ስልጠናው በታሰበለት ግብ ውጤታማ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከታችሁ አካላት የባለስልጣኑ ዳይሬክተሮችና ሰራተኞች በተቋሙ ስም ምስጋና አቅርበዋል።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡

👍18😁4
ባለስልጣኑ በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች በ69.8% መቀነሳቸው ገለጸ
ሰኔ 19/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የ2017 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸሙም ግምገማ መድረክ አካሂዷል ።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ደንብ ማስከበር በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ተልዕኮ ለመፈጸም ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ በእቅዱ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ ወደ ተግባር በመግባቱ የተሰጠውን ተልዕኮ በተሰካ መንገድ መወጣት መቻሉን ገልጸዋል ።
አክለውም የተቋም ግንባታ ስራን በማጠናከር ለሰራተኞች እንዲሁም ለተገልጋዮች ምቹ የስራ ቦታ በመፍጠር ፣ አዲስ 6ኛ ዙር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮችን አሰልጥኖ በማስመረቅ የስራ ሰዓቱንም እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት በማድረግ ከተማችን የደንብ ጥሰት የቀነሰባትና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ በርካታ ተግባራት እያከናወነ እንደሚኝ ተናግረዋል ።
በበጀት ዓመቱ በከተማችን የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች 69.8% እንዲቀንስ ማድረግ መቻሉንና በሰው ተኮር ተግባራት ላይ በመሳተፍ ከ የ14 የአቅመ ደካማ ቤት እድሳትና ገንብቶ በማጠናቀቅ ለባለቤቶቹ ማስረከቡን ዋና ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ ቀርቧል።
ባለስልጣኑ የተቋም ግንባታ ፣የሥልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን በስፋት መስራት እና በከተማዋ የሚታዪ ደንብ ተላላፊዎች ላይ ህጋማዊ እርምጃ በመውሰድ የተሰጠውን ተልዕኮ በቁርጠኝነት ከመወጣት ጎን ለጎን ወደ ህብረተሰቡ በመውረድ ሰው ተኮር ስራዎችን በመከናወን የአቅመ ደካማ ቤቶችን ገንብቶ በማጠናቀቅ ለባለቤቶቹ አስረክቦል፣ የአረንጓዴ አሻራ ተግባራት በማካሄድ ችግኞችን መትከልና መንከባከብ ስራ ተከናውኗል እንዲሁም ወላጅ አልባ ህጻናት በመንከባከብ እያሳደገ እንደሚገኝ ከቀረበው ሪፖርት መገንዘብ ተችሏል ።
ከደንብ ተላላፊዎች ቅጣት እና ከተወረሱ ንብረቶች ጨረታ ሽያጭ እስከአሁን ባለው ከ397 ሚሊዮን ብር በላይ መልሶ ለልማት የሚውል ለከተማው ገቢ ማስገባት መቻሉን በሪፖርቱ ተገልጿል ።
በመድረኩ ለተነሱ ሀሳቦች የባለስልጣኑ ኃላፊዎች ምላሽና አስተያየት ሰጥተው ቀጣይ የስራ አቅጣጫ በዋና ሰራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ተሰጥቶ መድረኩ ተጠናቋል ።

❤5👍5