የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.73K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በቅንጅት የተሰሩ ስራዎችን ገመገመ

16/08/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከባለድርሻ አካላት ጋር በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ቅንጅታዊ ስራዎችን ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ የባለስልጣኑ ኃላፊዎች በተገኙበት ከባለድርሻ አካላት አመራሮች ጋር በጋራ የግምገማ መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በዘጠኝ ወራት ከባለድርሻ አካላት ጋር በተፈራረመው ስምምነት መሰረት የሰራቸውን ስራዎች በወቅቱ በመገምገም ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት በቀሪ ጊዜያት የአመቱን እቅድ ለማሳካት ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ስራዎችን በጋራ መገምገም አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል ።

ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የከተማችንና የአከባቢያችንን ውበት ማስጠበቅ ፣ የወንዝና የወንዝ ዳር ብክለትን በመከላከል ፣ የከተማችን ሰላምና ጸጥታ በማስጠበቅ ፣ ህገወጥነትንና ደንብ ጥሰትን ለመከላከል ከሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች ተቀናጅቶ በመስራት ውጤታማ መሆን መቻሉን ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል ።

የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከባለድርሻ አካላት ጋር በዘጠኝ ወራት በቅንጅት የተሰሩ ስራዎች በጥንካሬ እና በጉድለት በሰነድ ተለይተው በባለስልጣኑ የስታንዳርዳይዜሽን ዝግጅት፣ አገልግሎት አሰጣጥና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ቀጸላ ቀርቧል ።

የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎችን በማጠናከር ወደ ቅጣት ከመገባቱ በፊት ለህብረተሰቡ ስለ ደንብ ማስከበር በቂ እውቀት በማስገንዘብ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ቅንጅት በማጠናከር ከተማችን እንደ ስሟ አዲስና ውብ ለነዋሪዎች ምቹ ለቱሪስት መስብ እንድትሆን በትጋት መስራት እንደሚገባ የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ተናግረዋል ።

ባለስልጣኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በርካታ ስኬታማ ተግባራትን በማከናወንና የገጽታ ግንባታ ስራን አጠናክሮ በመስራቱ በህብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት አግኝቶ በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰቶች እንዲቀንሱ ማድረግ መቻሉን የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ ገልጸዋል ።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረክ መሪዎች ምላሽና አስተያየት በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል ።

መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
👍6
የደንብ ማስከበር ሰራተኞች ህዝብና መንግስት የሰጣቸውን ሀላፊነት በሙያዊ ስነ-ምግባር መፈፀም እንዳለባቸው ተገለፀ

ሚያዚያ 17-2017ዓም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤቱ ለክፍለ ከተማው ሁሉም ወረዳዎች ለሚገኙ ከ650 በላይ የደንብ ማስከበር ሰራተኞች በስነምግባር እና ፀረ-ሙስና ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በስልጠናው መልዕክት ያስተላለፉት የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ቅርንጯፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ደጀኔ ነገሮ በክፍለ ከተማው የሚገኙ የደንብ ማስከበር ሰራተኞች በጥሩ ስነ-ምግባር ታንፀው የደንብ መተላለፎችን ለማስቀረት አያደረጉት ያለው ጥረት ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ሰራተኞቹ የደንብ መተላለፎችን ከመከላከል ባለፈ በከተማዋ ሁለንተናዊ ልማት ላይ የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ በበኩላቸው የዘርፉ ሰራተኞች ጥሩ ስነ-ምግባርን ተላብሰው ከፀረሙስና የፀዳ አገልግሎት በመስጠት ህዝብና መንግስት የሰጣቸውን ሀላፊነት በሙያዊ ስነ-ምግባር መፈፀም እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡

ሰልጣኞች በበኩላቸው ከብልሹ አሰራር የፀዳና ደንብና መመሪያ መሰረት ያደረገ አገልግሎት ለመስጠት ስልጠናው ከፍተኛ አስተዎፅኦ እንዳለው ተናግረዋል::
👍4