በደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ለተቋሙ በጎ ፈቃደኞች ግንዛቤ ተፈጠረ
17/08/2017 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ወንዝና የወንዝ ዳርቻዎች ልማት ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ከ11ዱም ክፍለ ከተማ ተወጣጡ በጎ ፈቃደኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ በንግግራቸውም ባለስልጣኑ የከተማ አስተዳደሩ የኮሪደር ልማትን የመጠበቅ ፣ህጋዊ ንግድ የመፋጠር፣ ቆሻሻዎች በአግባቡ እንዲወገዱ የማድረግ ፣ የከተማን ፕላን የጠበቀ ግንባታ እንዲፈፀም የማድረግ ፣የመንግስትን መሬት የመጠበቅ እና ህጋዊ እርድ እንዲፈፀም የማድረግ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልፀው ደንቡን በሚተላለፉት ላይ አስተማሪ እርምጃ እንደሚወስድ ተናግረዋል።
አክለውም የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ስራዎች ለመስራት ከበጎ ፈቃደኞች እገዛ አይነተኛውን ሚና እንደሚጫዎት እና በጎ ፈቃደኞች በደንቡ ላይ ግንዛቤ አግኝተው በሚኖሩበት አካባቢ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ደንቡን እንዲያስገነዝቡ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
በባለስልጣኑ የቅድመ መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት የግንዛቤ ማስጨበጥ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ደመረ በለጠ አማካኝነት በቀረበ ሰነድ የአዲስ አበባ ከተማ ወንዞች ብክለት፣ በአካባቢ እና በጤና ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ፣ መፍትሔዎች እንዲሁም የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል የወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 እና የቅጣት ሰንጠረዥ በዝርዝር ቀርቦ ግንዛቤ ተፈጥሯል።
በመድረኩ የባለስልጣኑ የቁጥጥር እና እርምጃ አወሳሰድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግሩም ወ/መስቀል ደንቡን በተላለፉ ድርጅት እና ግለሰብ ለይ ዝቅተኛው የገንዘብ ቅጣት ሁለት ሺህ ብር እስከ ከፍተኛው አንድ ሚሊዮን ብር ድረስ አስተዳደራዊ ቅጣት እንደሚያስቀጣ ገልፀዋል።
የባለስልጣኑ የቅድመ መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካለም ጌታሁን በደንቡ ዙሪያ በተለያዩ አግባቦች ለህብረተሰቡ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎችን በተደጋጋሚ መሰጠቱን እና ግንዛቤ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል።
በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋረ ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበት መድረኩ ተጠናቋል።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከሰላምና ፀጥታ ቢሮ ጋር በ2017 በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈጻፀም በነበረው ግምገማ ባለስልጣኑ የተሻለ አፈፃፀም ካስመዘገበባቸው መካከል፦
👉 የደንብ ጥሰትና ወንጀልን በተቀናጀ አሰራር እንዲቀንስ ማድረግ ተችሏል።
👉 ህግና ስርዓት እንዲከበር ግንዛቤ በመፍጠር ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል።
👉 የሚከናወኑ ተግባራት በእቅዱ መሠረት እየተገመገመ በመሄዱ ክፍቶችን በየ ጊዜ እየታረመ በመሄዱ ስኬት ተመዝግቧል።
👉 የህዝቡን ተሳትፎ በማሳደግ፣ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ምላሽ በመስጠት የህብረተሰቡ ቅሬታ እንዲቀንስ ተሰርቷል።
👉 አመራሩ፣ባለሙያውና ባለድርሻ አካላት በቅንጅት በመስራት የደንብ መተላለፎች በ64% እንዲቀንስ ተደርጓል።
👉 አመራሩና ባለሙያው በህብረትና በትብብር በመሰራቱ ለህገ-ወጦችና አጭበርባሪዎች መቆጣጠር ተችሏል::
👉 ህገ-ወጥ ንግድን በመቆጣጠር በፍትሐዊ የሀብት ክፍፍልና የገበያ ማረጋጋት ውጤት ተገኝቷል።
👉 የአደባባይ በዓላት በሰላም፣ በፍቅር፣ በአብሮነትና በመከበር ያለምንም የፀጥታ ችግር ማክበር ተችሏል።
መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡

ባለስልጣኑ በቀሪ ወራት የሚከናወኑ ተግባራት እቅድና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አካሄደ
25/08/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት በዘጠኝ ወር እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መነሻ በማድረግ በቀሪ ወራት የሚሰሩ ስራዎችና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ከማዕከል አስከ ወረዳ ካሉ አመራሮች ጋር የግምገማዊ ውይይት መድረክ አካሂዷል ።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በአመራሩ እና ሰራተኛው ጥረት በዘጠኝ ወራት ውስጥ በተቋሙ ጥሩ አፈፃፀም መኖሩንና ይህንንም በቀሪ ጊዜያት ያሉንን ጠንካራ ጎኖች በማስቀጠል አንዳንድ ክፍተቶችን በመሙላት በትጋት በትኩረት ቀንና ሌሊት በመሠራት ውጤታማ በመሆን ከተማችን የደንብ ጥሰት የቀነሰባት ለነዋሪዎቿና ለእንግዶቿ ምቹ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል ።
በመድረኩ በቀሪ ወራት በክ/ከተሞች መሰራት ያለባቸው ዋና ዋና ተግባራትና ዝርዝር ተግባራት እቅድ በባለስልጣኑ እቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ አቅርበዋል።
በመድረኩ የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ ስራዎችን ስናከናወን ከመንግስትና ከህዝብ የተሰጠንን ኃለፊነት በመገንዘብ ከብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ መሆን እንደሚገባ ተናግረዋል ።
በዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ስራዎች በቅንጅት በመሰራታቸው በከተማ የነበሩ የደንብ መተላለፎችንና ህገ ወጥ ተግባራት እንዲቀነስ ማድረግ መቻሉን የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ገልጸዋል ።
በተጨማሪም በመድረኩ የስድስተኛ ዙር ፖራ ሚሊተሪ ምረቃትና ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተካሂዷል።
በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶበታል ።
መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።