የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
993 subscribers
1.5K photos
4 videos
1 file
51 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
የባለሥልጣኑ 6ኛ ዙር ዕጩ ፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ወደ አፖስቶ የፌደራል ፖሊስ ማሰልጠኛ ኮሌጅ በሰላም ደረሱ

27-07 -2017 ዓ.ም
**ይርጋለም**

ከጠዋቱ 12 ሰዓት ከአዲስ አበባ የተነሱት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን 6ኛ ዙር ምልምል እጩ ፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ወደ አፖስቶ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ማሰልጠኛ ኮሌጅ በሰላም ደረሱ።

ወደ ማሰልጠኛው እንደደረሱ በኮሌጁ ማህበረሰብና አስተባባሪዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

መረጃው፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
ለመኪና ፓርኪንግ እየተሰራ ባለው ቦታ ላይ ህገወጥ ንግድ ሲያከናውኑ በነበሩ ግለሰቦች እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ

         30/07/2017 ዓ.ም
           **አዲስ አበባ**

ባለስልጣኑ በአራዳ ክፍለከተማ ወረዳ 05 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የኦፕሬሽን እቅድ በማውጣት እና ሽፍት በማጠፍ  ከጊዮርጊስ ቤተ-ክርስትያን ጀርባ የድሮው አወሊያ ት/ቤት አካባቢ በኮሪደር ልማት የፈረሰው እና ለመኪና ፓርኪንግ እየተሰራ ባለው ቦታ ላይ ህገወጥ ንግድ ሲያከናውኑ በነበሩ ግለሰቦች የወረዳው ደንብ ጽ/ት ሀላፊ ዋና ሳጅን መዝገቡ ዲማ ገለፁ።

ሀላፊው እንደገለፁት በተወሰደው እርምጃው ከፖሊስን አባላት ጋር በመቀናጀት በአይነት ከ35 እና ግምቱ 121,820 ብር በላይ አታክልት እና አልባሳት በመውረስ እርምጃ መወሰዱ ገልፀዋል።
የባለስልጣኑ 6ተኛ ዙር የፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና በይፋ ተጀመረ

02/08/2017 ዓ.ም
ይርጋለም /አፖስቶ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለ6ኛ ዙር የሚያሰለጥናቸውን ከ2000 በላይ ዕጩ የፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮችን ፌደራል ፖሊስ ዩኒቨርስቲ አፖስቶ ካምፓስ የወታደራዊ እና የንድፈ ሃሳብ ስልጠና የመክፈቻ ኘሮግራም አካሄደ።

በፕሮግራሙ የአዲስ አበባ የሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቤሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማና የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት እና የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ም/ኮሚሽነር መስፍን አበባ ፣ የሰላምና ጸጥታ እና የደንብ ማስከበር የክ/ከተማ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ የሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቤሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ከለውጡ ማግስት ጀምሮ የከተማውን ጸጥታ በማረጋገጥና የደንብ መተላለፎችን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራው በአግባቡ በመወጣት ለዜጎቿና ለእንግዶቿ ምቹ እንድትሆን በርካታ ስራዎች የተሰሩና ውጤት የተገኘ መሆኑ ገልጸዋል ።

ባለስልጣኑ የደንብ መተላለፍ ተግባራትን በዘላቂነት ለመከላከል ይቻል ዘንድ ቴክኖሎጂን ዘመናዊ መንገድ በመጠቀም የሚችል ደንብ ማስከበር ኦፊሰርን ለማብቃት መሉ ዝግጅት ተደርጎ በዛሬው ዕለት ስልጠናውን መጀመሩን በማብሰር መልካም የስልጠና ቆይታ ተመኝተዋል ።

ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በ2005 ተቋቁሞ በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችን ለመከላከል የተቋቋመ ሲሆን አሁን ላይ ራሱን በማዘመንና ሪፎርም በማድረግ 6ኛ ዙር የፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ለማስልጠንና በከተማችን የሚስተዋሉትን የደንብ መተላለፎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ስልጠናውን በዛሬው ዕለት በይፋ መጀመሩን የባለሥልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ገልጸዋል ።

አክለውም ባለስልጣኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የከተማውን ሰላምና ጸጥታ እያስጠበቀ ይገኛል አንዲሁም በተለያዩ ሰው ተኮር ስራዎችን በመስራት ፣ የአረንጓዴ አሻራ ላይ በመሳተፍ የተለያዩ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል ብለዋል ።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት እና የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ም/ኮሚሽነር መስፍን አበበ እንደገለፁት በከተማ ውስጥ ያሉ እንቅስቃሴዎች ሰላማዊ እንዲሆንና በከተማዋ ያሉ የደንብ መተላለፎችን ለመከላከል የኦፊሰሩ ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል ።

ፕሬዝዳንቱ ስልጠናው ህጎችንና ደንቡ ላይ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ፣ በአካል ብቃት እንዲዳብሩ፣ የህግ የበላይነት እንዲያከብሩና እንዲያስከብሩ የመስክና የክፍል ውስጥ ስልጠና በመሰጠት እጩ ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ውጤታማና ብቁ ሆኖ እንዲወጡ ዩኒቨርስቲው የበኩሉን እንደሚወጣ ገልጸዋል ።

ዘገባው ፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
በባለፈው አንድ ወር በወንዞችና የወንዝ ዳርቻ ብክለት መከላከል ላይ የተሰሩ ስራዎች ተገመገሙ።

03/08/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እና የውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ በጋራ በመሆን በወንዝ እና የወንዞች ዳርቻ ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ከየካቲት 24 እስከ ሚያዝያ 02/2017 ዓ.ም ድረስ የተሰሩ ስራዎች የተቋማቱ ከፍተኛ አመራሮች እና የክ/ከተማ ጽ/ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት ሪፓርት ሪፓርቱ ቀርቦ ተገምግሟል።

በግምገማው ላይ ንግግር ያደረጉት የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በቅንጅት የመስራት ሂደቱ ያመጣው ውጤት መልካም መሆኑን ጠቅሰው፤ በተለይም 2,858 የሚሆኑ የብክለት ድርጊቶች ከሚፅሙት ወንጀል መታቀብ በመቻላቸው ይበል የሚያሰኝ ከፍተኛ ለውጥ መሆኑን እና የሚለቀቁ ፍሳሾች የጉዳት መጠን በላቭራቶሪ በመመርመር እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በወንዝ ዳርቻ ልማትና ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ የተሰሩ ተግባራትን አፈፃፀም ሪፖርት በአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የግንዛቤ ቡድን መሪ አቶ አንበሳው ፈንታ ቀርቧል።

በሪፖርቱም በደንብ ቁጥር 180/2017 ዙርያ 2,354,443 የህብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ መፈጠረ መቻሉን፣2,858 ከሚፈፅሙት ወንጀል ማስተካከያ መደረጉ እና ህግን ተላልፈው በተገኙ ድርጅቶች እና ግለሰቦችን 68,896,000 (ስልሳ ስምንት ሚሊዮን ስምንት መቶ ዘጠና ስድስት ሺህ ብር ) የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱ ተገልጿል።

በቀረበው አፈፃፀም ሪፖርት ላይ በአሰራር ላይ ያጋጠሙ አጠቃላይ ሂደቶች በክፍተት በታዩ እና በቀጣይም መስተካከል የሚገባቸው አሰራሮች ላይ ከቤቱ ሀሳቦች ተንሸራሸረዋል። በዚህም የተለያዩ አስተያየት እና ጥያቄዎችን በማንሳት ሰፊ ምክክር ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዲዳ ድሪባ በበኩላቸው የስራ አፈፃፀሙ በጣም ጥሩ መሆኑን ገልፀው፤ ይህም ሊመጣ የቻለው በቅንጅት በመግባባት ስራዎች በመሰራታቸው በመሆኑ ከቀሩ ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት ይበልጥ ለውጥ እንደሚያመጣ ጠቁመዋል።

የአዲስ አበባ ወንዞች ሲፀዱ እኔም ተሳታፊ ነበርኩ የሚል ታሪክ ነጋሪ ለመሆን ወንዞች በዋናነት የሚበክሉት በማን ነው የሚለውን በማየት በቁርጠኝነት ስራዎች በጋራ እንስራ ያሉት ደግሞ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግርማ ሰይፉ ናቸው።

በመጨረሻም በተቋማቱ የበላይ አመራሮች የቀጣይ የአሰራር አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

ዘገባው፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።