ባለስልጣኑ በዛሬው ያልተጣራ ፍሳሽ በመልቀቅ ወንዝን የበከለ ተቋም 1,000,000 ብር መቅጣቱ ገለፀ
25/07/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 10 የፋብሪካ ፍሳሽን ወደ ወንዝን በመልቀቅ ወንዝ የበከለው ተቋም 1,000,000 ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን ገለፀ።
ባለስልጣኑ ሞሃ የለስላሳ መጠጦች ማምረቻ ኢንዱስትሪ የሚለቁት ፍሳሽ በተደረገለት የናሙና ምርመራ ወንዝን የሚበክል መሆኑን የተረጋገጠ ሲሆን በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት በገንዘብ ቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዶበታል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፦
የሶሻል ሚዲያ ገፆቻችን ፎሎው፣ላይክ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
ዌብሳይት ገፃችን፦
https://www.aacea.gov.et/
የፌስ ቡክ ገፃችን፦
https://www.facebook.com/profile.php?id=100082525711518&mibextid
የቲክቶክ አካውንታችን
https://www.tiktok.com/@addisababacodeenforcemen
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/codeenforcement
የዩቱብ ቻናላችን
https://youtube.com/@A.A.C.ACODEENFORCEMENT

የባለሥልጣኑ 6ኛ ዙር ዕጩ ፓራ-ሚሊተሪምልምል ኦፊሰሮችን ወደ አፖስቶ የፌደራል ፖሊስ ማሰልጠኛ ሽኝት ተደረገ
27-07 -2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለ6ኛ ዙር የመለመላቸው ከ2000 በላይ ሰልጣኝ ዕጩ የፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በሲዳማ ክልል በሚገኘው አፖስቶ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ለማስገባት በዛሬው እለት የባለስልጣኑ እና የፌደራል ፖሊስ አመራሮች በተገኙበት ሽኝት ተደረገ።
በሽንት ፕሮግራሙ የተገኙት የባለ ስልጣኑ ዋና-ስራአስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣኑ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሠረት በከተማው የደንብ መተላለፎች ለመቀነስና የተጀመረው የልማት ስራዎች ደህንነት ጥበቃው ለማጠናከር ተጨማሪ የሰው ሀይል በማስፈለጉ እንደሆነ ገልፀዋል።
በስልጠናው ከ11 ክፍለ ከተሞች የተመለመሉ ዲግሪና ከዚያ በላይ የትምህርት ዝግጅት ያላቸው የአካልና የጤና ምርመራ በማድረግ በምልመላው ያለፉ መሆናቸው ተገልጿል
በስድስተኛ ዙር ዕጩ የፓራ ሚሊተሪ አዲስ ሰልጣኞችን የንድፈ ሀሳብ እና በወታደራዊ ሥልጠናው ከ2 ወር በላይ እንደሚቆዩ ተገልጿል ።
መረጃው፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።

የባለሥልጣኑ 6ኛ ዙር ዕጩ ፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ወደ አፖስቶ የፌደራል ፖሊስ ማሰልጠኛ ኮሌጅ በሰላም ደረሱ
27-07 -2017 ዓ.ም
**ይርጋለም**
ከጠዋቱ 12 ሰዓት ከአዲስ አበባ የተነሱት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን 6ኛ ዙር ምልምል እጩ ፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ወደ አፖስቶ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ማሰልጠኛ ኮሌጅ በሰላም ደረሱ።
ወደ ማሰልጠኛው እንደደረሱ በኮሌጁ ማህበረሰብና አስተባባሪዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
መረጃው፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
27-07 -2017 ዓ.ም
**ይርጋለም**
ከጠዋቱ 12 ሰዓት ከአዲስ አበባ የተነሱት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን 6ኛ ዙር ምልምል እጩ ፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ወደ አፖስቶ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ማሰልጠኛ ኮሌጅ በሰላም ደረሱ።
ወደ ማሰልጠኛው እንደደረሱ በኮሌጁ ማህበረሰብና አስተባባሪዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
መረጃው፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
ለመኪና ፓርኪንግ እየተሰራ ባለው ቦታ ላይ ህገወጥ ንግድ ሲያከናውኑ በነበሩ ግለሰቦች እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ
30/07/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
ባለስልጣኑ በአራዳ ክፍለከተማ ወረዳ 05 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የኦፕሬሽን እቅድ በማውጣት እና ሽፍት በማጠፍ ከጊዮርጊስ ቤተ-ክርስትያን ጀርባ የድሮው አወሊያ ት/ቤት አካባቢ በኮሪደር ልማት የፈረሰው እና ለመኪና ፓርኪንግ እየተሰራ ባለው ቦታ ላይ ህገወጥ ንግድ ሲያከናውኑ በነበሩ ግለሰቦች የወረዳው ደንብ ጽ/ት ሀላፊ ዋና ሳጅን መዝገቡ ዲማ ገለፁ።
ሀላፊው እንደገለፁት በተወሰደው እርምጃው ከፖሊስን አባላት ጋር በመቀናጀት በአይነት ከ35 እና ግምቱ 121,820 ብር በላይ አታክልት እና አልባሳት በመውረስ እርምጃ መወሰዱ ገልፀዋል።

የባለስልጣኑ 6ተኛ ዙር የፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና በይፋ ተጀመረ
02/08/2017 ዓ.ም
ይርጋለም /አፖስቶ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለ6ኛ ዙር የሚያሰለጥናቸውን ከ2000 በላይ ዕጩ የፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮችን ፌደራል ፖሊስ ዩኒቨርስቲ አፖስቶ ካምፓስ የወታደራዊ እና የንድፈ ሃሳብ ስልጠና የመክፈቻ ኘሮግራም አካሄደ።
በፕሮግራሙ የአዲስ አበባ የሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቤሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማና የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት እና የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ም/ኮሚሽነር መስፍን አበባ ፣ የሰላምና ጸጥታ እና የደንብ ማስከበር የክ/ከተማ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ የሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቤሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ከለውጡ ማግስት ጀምሮ የከተማውን ጸጥታ በማረጋገጥና የደንብ መተላለፎችን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራው በአግባቡ በመወጣት ለዜጎቿና ለእንግዶቿ ምቹ እንድትሆን በርካታ ስራዎች የተሰሩና ውጤት የተገኘ መሆኑ ገልጸዋል ።
ባለስልጣኑ የደንብ መተላለፍ ተግባራትን በዘላቂነት ለመከላከል ይቻል ዘንድ ቴክኖሎጂን ዘመናዊ መንገድ በመጠቀም የሚችል ደንብ ማስከበር ኦፊሰርን ለማብቃት መሉ ዝግጅት ተደርጎ በዛሬው ዕለት ስልጠናውን መጀመሩን በማብሰር መልካም የስልጠና ቆይታ ተመኝተዋል ።
ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በ2005 ተቋቁሞ በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችን ለመከላከል የተቋቋመ ሲሆን አሁን ላይ ራሱን በማዘመንና ሪፎርም በማድረግ 6ኛ ዙር የፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ለማስልጠንና በከተማችን የሚስተዋሉትን የደንብ መተላለፎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ስልጠናውን በዛሬው ዕለት በይፋ መጀመሩን የባለሥልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ገልጸዋል ።
አክለውም ባለስልጣኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የከተማውን ሰላምና ጸጥታ እያስጠበቀ ይገኛል አንዲሁም በተለያዩ ሰው ተኮር ስራዎችን በመስራት ፣ የአረንጓዴ አሻራ ላይ በመሳተፍ የተለያዩ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል ብለዋል ።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት እና የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ም/ኮሚሽነር መስፍን አበበ እንደገለፁት በከተማ ውስጥ ያሉ እንቅስቃሴዎች ሰላማዊ እንዲሆንና በከተማዋ ያሉ የደንብ መተላለፎችን ለመከላከል የኦፊሰሩ ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል ።
ፕሬዝዳንቱ ስልጠናው ህጎችንና ደንቡ ላይ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ፣ በአካል ብቃት እንዲዳብሩ፣ የህግ የበላይነት እንዲያከብሩና እንዲያስከብሩ የመስክና የክፍል ውስጥ ስልጠና በመሰጠት እጩ ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ውጤታማና ብቁ ሆኖ እንዲወጡ ዩኒቨርስቲው የበኩሉን እንደሚወጣ ገልጸዋል ።
ዘገባው ፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።