የክርስቶስ ፍቅር ❤️❤️ christ of love ..
114 subscribers
125 photos
20 videos
4 files
77 links
@በዚህ ቻናላችን እግዚአብሔርንና እግዚአብሔርን ብቻ የምናመልክበት እሱን የምናወድስበት ይሆናል ።
👍 በቻናላችን የእግዚአብሔርን ቃል የምናካፍልበት
👍አዳዲስ መዝሙሮችን የምንለቅበት
👍ወዘተ መንፈሳዊ መሠል ነገሮችን የምናደርስበት ነው

ይቀላቀሉን።
Download Telegram
አድስ ኪዳን የተጻፈበት የመጀመሪያ ቋንቋ ግርክ ነው፡፡ በግርኩ " apeitheo" የሚለው ቃል "የማያምን
ወይም የማይታዘዝ" በሚል በአማረኛ መጽሐፍ ቅዱስ እና "not believe ወይም not obey" በሚል በእንግሊዘኛ መጽሐፍ ቅዱስ ተተርጉሟል፡፡
የማያምን ማለት በአይምሮ ብቻ የማይቀበል ማለት ብቻ ሳይሆን የማይታዘዝ ማለትም ነው፡፡ሰለዚህ #የማያምን ማለት #የማይታዘዝ ማለት ነው፡፡ይሄን የእንግሊዘኛውንና የአማረኛው ቃላት ለማነጻጸር በሞባይላችሁ የአማረኛ መጽሐፍ ቅዱስ እዛው ከሥር በአማረኛ እና በእንግልዘኛ እየቀያየራችሁ ቃላቶቹን ተመልከቱ፡፡ የግርኩን ቃል ለማየት ከፈለጋችሁ ኮምፒውተር ያላችሁ "Iota" የሚል የመጽሐፍ ቅዱስ app በመጠቀም ጥቅሱ ያለበትን ቁጥር በመጫን በቃሉ ጎን ያለውን ቁጥር ደግማችሁ በመጫን የግርኩን ቃል ማነጻጸር ትችላላችሁ፡፡
*******************
**ጥቅሶቹ እነዚህ ናቸው*******
***************************
                  የዮሐንስ ወንጌል 3 : 36
..
-በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ #የማያምን(he that believeth not(KJV english)(apeitheo(በግርክ)) ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።
.......
      የሐዋርያት ሥራ 14 : 2
......
- #ያላመኑት(the unbelieving (KJV english)(apeitheo(በግርክ))አይሁድ ግን የአሕዛብን ልብ በወንድሞች ላይ አነሣሡ አስከፉም።
.....
                      ወደ ሮሜ ሰዎች 2 : 8
......
- ለዓመፃ በሚታዘዙ እንጂ ለእውነት #በማይታዘዙትና(do not obey(KJV english)(apeitheo(በግርክ))በአድመኞች ላይ ግን ቍጣና መቅሠፍት ይሆንባቸዋል።
........
                 ወደ ሮሜ ሰዎች 10 : 21
.....
- ስለ እስራኤል ግን። ቀኑን ሁሉ #ወደማይታዘዝና(a disobedient(KJV english)(apeitheo(በግርክ))ወደሚቃወም ሕዝብ እጆቼን ዘረጋሁ ይላል።
........
         ወደ ሮሜ ሰዎች 11 : 30
.......
- እናንተም ቀድሞ ለእግዚአብሔር #እንዳልታዘዛችሁ(have not believed (KJV english)(apeitheo(በግርክ))፥ አሁን ግን ከአለመታዘዛቸው የተነሣ ምሕረት እንዳገኛችሁ፥
.....
                    ወደ ሮሜ ሰዎች 11 : 31
......
- እንዲሁ በተማራችሁበት ምሕረት እነርሱ ደግሞ ምሕረትን ያገኙ ዘንድ እነዚህ ደግሞ አሁን #አልታዘዙም(not believed (KJV english)(apeitheo(በግርክ))።
......
              ወደ ሮሜ ሰዎች 15 : 31-32
......
- በእግዚአብሔር ፈቃድ በደስታ ወደ እናንተ መጥቼ ከእናንተ ጋር እንዳርፍ፥ በይሁዳ ካሉት #ከማይታዘዙ(them that do not believe(KJV english)(apeitheo(በግርክ)) እድን ዘንድ፥ ለኢየሩሳሌምም ያለኝ አገልግሎቴ ቅዱሳንን ደስ የሚያሰኝ ይሆን ዘንድ ጸልዩ።
.....
          ወደ ዕብራውያን 3 : 18
..........
- #ካልታዘዙትም(to them that believed not(KJV english)(apeitheo(በግርክ)) በቀር ወደ እረፍቱ እንዳይገቡ የማለባቸው እነማን ነበሩ?
.......
        ወደ ዕብራውያን 11 : 31
.......
- ጋለሞታይቱ ረዓብ ሰላዮችን በሰላም ስለ ተቀበለቻቸው #ከማይታዘዙ(them that believed not(KJV english)(apeitheo(በግርክ))ጋር በእምነት አልጠፋችም።
.......
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2 : 7
........
- እንግዲህ ክብሩ ለእናንተ ለምታምኑት ነው፤ #ለማያምኑ(unto them which be disobedient(KJV english)(apeitheo(በግርክ))ግን አናጢዎች የጣሉት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ የዕንቅፋትም ድንጋይ የማሰናከያም ዓለት ሆነ፤
........
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2 : 8
.........
- #የማያምኑ(being disobedient(KJV english)(apeitheo(በግርክ))ስለ ሆኑ በቃሉ ይሰናከሉበታልና፤ ለዚህ ደግሞ የተመደቡ ናቸው።
.......
           1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3 : 1-2
.......
- እንዲሁም፥ እናንተ ሚስቶች ሆይ፥ ከባሎቻችሁ አንዳንዱ ለትምህርት #የማይታዘዙ(obey not(KJV english)(apeitheo(በግርክ)) ቢኖሩ፥ በፍርሃት ያለውን ንጹሑን ኑሮአችሁን እየተመለከቱ ያለ ትምህርት በሚስቶቻቸው ኑሮ እንዲገኙ ተገዙላቸው።
......
        1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3 : 20
.........
- ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ፥ የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኅ ዘመን በቈየ ጊዜ ቀድሞ #አልታዘዙም(were disobedient (KJV english)(apeitheo(በግርክ))።
.......
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4 : 17
.......
-ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል #የማይታዘዙ(Of them that obey not  (KJV english)(apeitheo(በግርክ)) መጨረሻቸው ምን ይሆን?
*************************
**ሰለዚህ "ያለማመን" ማለት "ያለመታዘዝ " ከሆነ በሌላ አገላለጽ  "ማመን" ማለት ደግሞ በአይምሮ ብቻ የምደረግ እምነት ሳይሆን " በተግባር ለኢየሱስ ትምህርት መታዘዝ" ማለት ነው፡፡