🫂ሰው ሁን ከሰውም ሰው🫂
12.5K subscribers
246 photos
30 videos
2 files
112 links
Schedule

ሰኞ፡ mental Health
ማክሰኞ፡ sucess
ረብዕ፡ psychology
ሐሙስ፡ relationship
አርብ፡ bed time stories
ቅዳሜ፡ general
እሁድ፡ general

ያለ አእምሮ ጤና ምንም ጤና የለም
For Any Comment Inbox Me @umbeya
Download Telegram
#ነገ_የሚባል_ጊዜ_የለም!

🔹 በምድር ላይ ትልቁ ስቃይ ተስፋ ይባላል። ነገ ከዛሬ የተሻለ ይሆናል የሚሉት አመለካከት።

🔹 ነገ የሚታሰብበት ቅጽበት ከዛሬ የተሻለ አጋጣሚ ነው። በተጭበረበረ ስሜት ከሆነ ለዘላለም መኖር ይቻል ይሆናል።

ትምህርትህን ከጨረስክ በኋላ ታላቅ ነገር መስራት ትችላለህ።

ስራ ካገኘህ በኋላ ታላቅ ትሆናለህ።

🔹 ለነገ ማቀድ ትክክል አይደለም ለማለት ሳይሆን፣ እቅድ የህይወት አካል ስለሆነ ነገር ግን በዚህ ህይወት ተስፋ አስፈላጊ ነገር አይደለም። በዚህ ህይወት የሚያስፈልገው  ሁሌም፣ በምንም ሁኔታ ውስጥ የተነቃቃ መንፈስ ነው - ብርታት!!

🔹 አሁንን  በመኖር የሚያስፈልገው ህይወትን ማስተጋባት ነው።  ሁሉንም ነገር ማድረግ የሚቻለው #አሁን በሚባል ጊዜ ውስጥ ነው። ነገ ማድረግ አይቻልም። ነገን መኖር አይቻልም! ሁሌም መኖር የሚቻለው አሁንን ብቻ ነው!

☑️ ስለዚህ በተስፋ ነገ እጀምረዋለሁ። ነገ እሰራዋለሁ፣ ነገ እጠይቃለሁ፣ ነገ እመልሰዋለሁ አትበል። የተነቃቃ መንፈስ ይኑርህ። ነገ የሚባል ጊዜ እንደሌለ እመን። ሁሌም አሁንህን ኑረው።

ምናልባት ቀጠሮ ኖሮህ (ነገ የለም ማለት ትርጉሙ አልገባህ ይሆናል) ቀጠሮህ ላይ ስትደርስ ያለህ ጊዜ አሁን ብቻ መሆኑን ትረዳዋለህ።

#የሕይወት_ኬሚስትሪ መጽሐፍ

✍ታዚ