🎤ቦርፎሪኮን🎸
1.97K subscribers
478 photos
103 videos
56 files
667 links
♦️ #የዚህ_የቴሌግራም_ቻናል_አላማ ♦️
ለራሱ ለቤተሰቡ እና ለሀገሩ የሚጠቅም ፤ በመልካም ስነ ምግባር የታነፀ ፤ ራሱን በፅድቅ እቃ ጦር ያስታጠቀ ፤ በቅድስና የተያዘ ፤ ራሱን የሚገዛ እንዲሁም ፍቅርን የሚኖር ትውልድን ማፍራት ነው።
ቦርፎሪኮን ቻናል , ኢትዮጵያ
ለአስተያየት, @john11 ይጠቀሙ።
We have weekly #maranata program in Sunday at 3:00 pm
Download Telegram
✍የድንጋይ ላይ ፊደል
*************
የድንጋይ ፊደል፣ ጽላተ ሙሴ
በመላዕክቱ እጅ፣ ሲወርድ ጊዜ
በኩነኔ ስር፣ ረግጦ ገዝቶ
የሰውን ጆሮ፣ በወስፌ በስቶ
አድርግ አታድርግ፣ ከፍርድ አጀብ ጋ
ሁሉን ከኃጢአት፣ በታች የዘጋ
ሰርቶም ላይጸድቅ፣ ልፋት ስር ጥሎት
ሕይወት የማይሰጥ፣ የሞት ግልጋሎት
የማያነጻ ፣ ያዳምን በደል
ክቡሩ ገዳይ፣ የድንጋይ ፊደል
ሞቱ በስራ፣ የማይመከት
ኮናኙ ፊደል፣ የሲናው ስብከት
የሚፈጽመው፣ ጀግና ቢታጣ
የተስፋው ጸጋ፣ ሰው ሆኖ መጣ
------------------------------------------
የምድር በጎች፣ ማንጻት ባይችሉ
የሰውን ኃጢአት፣ መንቀል ከስሩ
ታርዶ የሚያወርድ፣ ታላቅ ምህረት
እግዚአብሔር ሰጠን፣ ከራሱ በረት
እንደ ናሱ እባብ፣ ተንጠለጠለ
ሁሉን ፈጽሞ፣ ተፈጸመ አለ
ለአለም ሁሉ፣ ታረደ በጉ
ፈጻሚ አግኝቶ፣ ተሸኘ ሕጉ
ፊደሉ ትዕዛዝ፣ ሆኖ ሲገ'ለን
ቃል ስጋ ሆኖ፣ በሞት አዳነን
ከሲኦል ወ'ተን፣ ጽዮን ገብተናል
በፊደል ሞተን፣ በቃል ድነናል♥


✍ጸጋ ትምህርት ሳይሆን ኢየሱስ የሚባል ሰው ነው!!


#ሄኖክ_አሸብር
#share_with_pride
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@borforiconn
@abenezer_merjan