🍃بالقرآن نحي {በቁርአን እንኖራለን
914 subscribers
785 photos
299 videos
17 files
659 links
የተለያዩ ቁርኣናዊ አስተምህሮ’ዎች፣ ጣፋጭ ቲላዋዎች፣ ቁርኣንን የሚመለከቱና በቁርኣን ዙሪያ የሚሽከረከሩ መልዕክቶች የሚተላለፍበት ቻናል join ይበሉ !
ቁርኣን የወረደው ለሰው ልጅ መመሪያ፣ እንድናስተነትነውና እንድንገሰፅበት ነው።
አላህ እንዲህ ይላል፦ (ይህ) ወዳንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው፡፡ አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑና የአእምሮዎች ባለቤቶችም እንዲገሰጹ (አወረድነው)፡፡ {Q 38:29}
Download Telegram
መታወቅ የፈለገ.......
“ ዑመር ነህ ወይ?” አሏቸው።ሰወች ለምእምናን መሪ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ።
“አዎን ዑመር ነኝ።” አሏቸው።
“ኦ  ያ  ጀግናው!  ያ  ፋርሶችን ድል ያደረገው!  ያ ሩሞችን ያፈርስረሰው ዑመር?!”
አሏቸው።
“ላ ላ አይደለም። እኔ ዑመር ነኝ።  ያ የአላህ መልክተኛ ባልደረባ የነበረው ዑመር ነኝ። ከዚ የበለጠ ክብር ማእረግም የለኝም።”አሏቸው አሉ።

ያንቱ ኡመት ከመሆን የበለጠ ምን ክብር አለ  ያ ነቢየሏህ!!።


ከ ሶባሓል ኸይር! መጽሃፍ ከገጽ 160 ላይ የተወሰደ...
ውስብስብ ጉዳዮቹን ለአላህ አደራ የሰጠ ሰው አይከስርም፣ አይፀፀትም።

@fuadkheyr
አልሐምዱ ሊላህ አነጋን ዛሬም፡፡ ሌላ ቀን ተጨመረልን፡፡ ከሚለወጡት፣ ከሚስተካከሉት አላህ ያድርገን፡፡

ዛሬም  አምላካችንን አላህን ይዘን፣ እሱን አምነን ተነሳን፡፡ እሱን አስካለን ምን እንሆናለን፡፡

አልሐምዱ ሊላህ፡፡ አንተን እያለኝ ምን እሆናለሁ ያ ረብ፡፡ ሲጨንቀኝ መጠጊያዬ፣ ስፈራ መሸሻዬ፣ ሲከፋኝ ከለላዬ፣ ግራ ሲገባኝ እምነቴ፣ ሲደክመኝ ብርታቴ፣ ስሰበር ድጋፌ አንተ ነህ፡፡

የምወድህ ጌታዬ …
ሕይወት እንቆቅልሽ ስትሆንብኝ መልሴ፣
ስታረዝ ስራቆት ልብሴ፣
ነገር ሲጨልምብኝ ብርሃኔ፣
ባዶነት ሲሰማኝ ሙላቴ፣
የመኖር ትርጉሙ ሲጠፋኝ ምክንያቴ፣ …
አንተ ነህና ዛሬም፣ ሁሌም አመሰግንሃለሁ፡፡


https://t.me/MuhammedSeidAbx
"መጨረሻይቱም (ዓለም) ከመጀመሪያይቱ ይልቅ ላንተ በላጭ ናት፡፡" ይላቸዋል አላህ ሱረቱል ዱሓ ላይ 🧡

የኔ ውድ መልዕክተኛ ﷺ ምድር ላይ በነበራቸው ቆይታ ዱንያን አፍቅረው አልኖሩም። አብደላህ ኢብን መስዑድ እንዲህ በማለት ይናገራሉ: "አንድ ቀን መልዕክተኛው ﷺ ሰሌን ላይ ተኝተው ሲነሱ ጎናቸው ላይ ምልክት ሰርቶ ነበር። ከዛም ምልክት የሰራበትን ቦታ ማራገፍ ጀመሩ። ይሄኔ እንዲህ ብዬ ጠየቅኳቸው: "ያ ረሱለላህ ﷺ እዚህ ሰሌን ላይ ለስለስ ያለ ነገር ፈልገን እንድናነጥፍልዎ ቢፈቅዱልን'ስ?" ብዬ አልኳቸው። ...እሳቸውም እንዲህም አሉኝ:

"ما لي وللدنيا ؟ إنما مثلي ومثل الدنيا كراكب ظل تحت شجرة، ثم راح وتركها "

"ከዚህ አለም ጋር ጉዳዬ ምንድነው? የኔ ምሳሌ እና ይህ አለም ማለት እኮ ልክ ዛፍ ጥላ ስር እንዳረፈ መንገደኛ ማለት ነው። አልፎት ይሄዳል፤ ትቶትም ይሄዳል።" አሉ! ... ሸፊዒﷺ ይህንን ያሉት ብዙ ነገር ተጠይቀው ነበር እንዴ? አልነበረም! ግን አላህ የመጨረሻው ዓለም አሁን ካለው ይበልጣል ያላቸውን ሁሌም እንዳስታወሱ ነው። ለተከታዬቻቸውም በዚህ መልክ ነው አርኣያ የሆኑት ። ለዛም ነው ሐቢበላህﷺ እዚህ ምድር ላይ ጥለውት የሄዱት ንብረትም ሆነ ቁስ የሌለው! 🥹🧡! ...

ያ ረሱለላህﷺ! ናፍቆቴዋ ﷺ 🥲

اللهم صلي وسلم وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد وعلى آله وصحبه وسلم تسليما كثيرا 🧡🧡
اللهم صل على محمد وعلى آل محمد، كما صليت على إبراهيم، وعلى آل إبراهيم، إنك حميد مجيد، اللهم باعك على محمد، وعلى آل محمد كما باعكت على إبراهيم، وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد 
 Ř§Ů„لهم صل على محمد وعلى آل محمد، كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم باعك على محمد وعلى آل محمد كما باعكت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد❤️
በቻልነው አቅም እንፈራሃለን ጌታዬ።
አንተን ለማይፈሩት አሳልፈህ አትስጠን።

ሶባሐል ኸይር
አደራችሁ ወይ

https://t.me/MuhammedSeidAbx
…ታጋሽ ሁን!
ሰይዲና ኢብራሂም [ﷺ] በጌታቸው ተመኩ። ፍጡርን ከመሻት ቀልባቸውን ሰብስበው በአላህ ተብቃቁ። "ሐስቢየላህ ወኒዕመል‐ወኪል" አሉ።…
አላህስ ምን አደረገ?!

የማዳኑን ስራ ለሌላ አልተወውም። በኃያሉ ቁድራው ስር አደረገው። እሳትን በቀጥታ አዘዛት: ‐
(كوني بردا وسلاما على إبراهيم)
«እሳት ሆይ! በኢብራሂም ላይ ቀዝቃዛ፤ ሰላምም ሁኚ!»
ብርሃናማው ነቢይ. ....
    “ምንም የምናበራው ነገር ባልነበረን  በነዚያ የጨለማ ቀናት ውስጥ የሚበራልን የሙሃመድ ፊት ብቻ ነበር።” ትላለች ሞግዚታቸው የነበረችው ሐሊማ አስ-ሰዐዲያ።
እርሳቸው የፍጥረት አለሙ ብርሃን ናቸው። አካላቸው ብርሃን ነበር።  አስተምህሯቸው አለምን ከዳር እስከዳር አብርቷል። ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም።
صلو على النبي❤️


اللهم صل على محمد وعلى آل محمد، كما صليت على إبراهيم، وعلى آل إبراهيم، إنك حميد مجيد، اللهم باعك على محمد، وعلى آل محمد كما باعكت على إبراهيم، وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد 
 Ř§Ů„لهم صل على محمد وعلى آل محمد، كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم باعك على محمد وعلى آل محمد كما باعكت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد❤️
Forwarded from Tofik Bahiru
ታቢዒዩ ኢማም ሙጃሂድ [ረሒመሁላህ] እንዲህ ይላሉ: ‐ «ከዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር [ረዲየላሁ ዐንሁ] ጋር ነዋሪ አልባ ሆኖ በቀረ ኦና ቤት አለፍን።

«ሙጃሂድ ሆይ! አንተ ኦና ቤት ሆይ! ባለቤቶችህ ምን አደረጉ? ወዴት ሄዱ?!» ብለህ ተጣራ አሉኝ። እንዳሉት ተጣራሁ!…
ከዚያም ኢብኑ ዑመር [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንዲህ አሉ: ‐ «ሄዱ! ሥራቸው ብቻ ቀረ፤ እነርሱ ግን ሄዱ!»
:
ዛሬ የምንኖርበት ቤት የኛ አይደለም። የምንኖረበት በጊዜያዊነት ነው። ዘልዐለም የምንኖርበት ሀገር ዛሬ በምናሳልፈው ሥራችን የሚገነባው የአኺራ ቤታችን ነው። ሁሌም ወዲያ የሰደድነውን ሥራችንን እንመርምር። ነፍሳችንን ወደ ሰማይ ከፍ እናድርጋት። መሬት ለመሬት አንታሽ።

አኺራችንን አላህ ያሳምርልን!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
يارب لاتحسابنا يوم القيامه بدماء اطفال غزه يارب نعلم اننا خذلانهم فيارب خد بقلوبنا الي غزه😢
ቀናት ባለፉ ቁጥር በጣም እየተረዳሁ የመጣሁት ነገር ቢኖር፤
በዚህች ምድር ላይ የተረጋጋና የተሻለ ሕይወት እንደሚገባን ነው፡፡
ምቀኝነት የሌለበት፣ ክፋት የሌለበት፣ ሰዉን በክፉ መጠርጠር የሌለበት፣ ቅናትና የዐይን ቅላት የሌለበት፣ መጉዳትም ሆነ መጎዳት የሌለበት፤ አስረዳ፣ አብራራ፣ ምን ለማለት ፈልገህ ነው የሌለበት፣ መረበሽና ማስደንገጥ የሌለበት፣ ጥላቻና ስጋት የሌለበት፣ መጯጯህ የለሌበት፣
አዎ በቀሪው የሕይወት ዘመናችን ለኛ ጥሩ ሕይወት ይገባናል፡፡

ጁሙዓ ሙባረክ


Abx
#መሬት_ታዛቢ_ናት

አንድ ሰለፍ እንዲህ ይላሉ፦ « በአንድ ቦታ ላይ አላህ ላይ ካመጽክ (ወንጀል ከሰራህ) ከዚያ ቦታ ላይ አላህን ሳትታዘዝ እንዳትሄድ ምክንያቱም ቦታው አንተ ላይ እንደሚሰክረው ላንተም ይመሰክራል።»

ቁርኣን በአልዘልዘላ ምዕራፍ ላይ መሬት ስትርገፈገፍና የያዘችውን ጉድ ኹሉ ስትዘረግፍ
ሰዎች ምን ሆና ነው ብለው ይጠይቃሉ ይለናል።
{ إِذَا زُلۡزِلَتِ ٱلۡأَرۡضُ زِلۡزَالَهَا }
{ وَأَخۡرَجَتِ ٱلۡأَرۡضُ أَثۡقَالَهَا }
{ وَقَالَ ٱلۡإِنسَـٰنُ مَا لَهَا }.........
እርሷ መሬት ስለ ሰዎች የያዘችውን የታዘበችውን ኹሉ እንደምታወራ ይነግረናል። በምድር ላይ የሚከናወኑ ነገሮች ኹሉ መሬት በሚገባ ትመዘግባለች፣ ሰማይም ይመለከታል። ለዚህ ነው ምድርና ሰማያት ደጋግ ሰዎች ከዚህ ምድር ሲያልፉ የሚያለቅሱትም። በየትኛውም ቦታ በነፍስያችን ሰፊና የማያልቅ ፍላጎት በሰይጣንና በወስዋሰል ኸናስ ጉጎታ ወንጀል ላይ ብንወድቅ ሁሌም የገዛ ነፍሳችንን በብርቱ ይዘናት በሚገባት መልኩ ከርሷ ጋር ማውራት አለብን። ለርሷ ጥፋት የሚመጥን ማስተካከያም መስራት ይገባናል። ይህች ነፍስ ለሁሉም ዐይነት ሰው እጅግ በጣም ፈታኝ ነች። የበለጠ የምትፈትነው አውቄያለሁ፣ በቅቻለሁ፣ ጨርሼለሁ የምንለው ሰው ላይ ነው።

ስለዚህች [ነፍስ] አላህ ከፈቀደ ብዙ የምንባባለው ነገር ይኖራል፤ አላህ ከርሷ ወጥመድ ይጠብቀን፤ ይጠብቃችሁ!

መልካም ቅዳሜ ♥
* ከባድ ነው ብለን የምናስበው ነገር ለአላህ ቀላል ነው፤

* ትልቅ ነው ብለን የምሰጋው ለአላህ ትንሽ ነው፤

* እሩቅ ነው ብለን የምንፈራው ለአላህ ቅርብ ነው፤

* ዉስብስብ ነው ብለን የምንሸሸው ለአላህ ገር ነው፤

ኦ ይሔማ አይታሰብም ብለን የተውነው ለአላህ ምንም ነው፤
ወላሂ ምንም ነው፡፡
ብቻ ጉዳይህን ለርሱ ስጥ ..
ለአላህ የሠጡት ነገር ሁሉ መላ አለው፡፡

Abx
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከአሏህ በሆነ ብርታት እንድህ ይጸናል።
በአላህ ላይ ባለ እርግጠኝነት ጀነት ተስፋ ተደርጋ ዱኒያ መሸጋገሪያ ብቻ ትሆናለች።

ምን አጸናት........
ከሷ ከናታቸው በላይ ወደ የሚዝንላቸው ጌታ መልሳቸው ለምን አትጸና?!

https://t.me/bilQURANnehyaa
አላህዬ የተቆለፉ በሮችንን ከፋፍተህ ዩሱፍን ከጭንቅ ባወጣህበት ጥበብክ ተዘጉ ያልናቸውን መንገዶች ሁሉ ክፈትልን ያ ረብ!

https://t.me/bilQURANnehyaa