🍃بالقرآن نحي {በቁርአን እንኖራለን
914 subscribers
785 photos
299 videos
17 files
659 links
የተለያዩ ቁርኣናዊ አስተምህሮ’ዎች፣ ጣፋጭ ቲላዋዎች፣ ቁርኣንን የሚመለከቱና በቁርኣን ዙሪያ የሚሽከረከሩ መልዕክቶች የሚተላለፍበት ቻናል join ይበሉ !
ቁርኣን የወረደው ለሰው ልጅ መመሪያ፣ እንድናስተነትነውና እንድንገሰፅበት ነው።
አላህ እንዲህ ይላል፦ (ይህ) ወዳንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው፡፡ አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑና የአእምሮዎች ባለቤቶችም እንዲገሰጹ (አወረድነው)፡፡ {Q 38:29}
Download Telegram
መከራ ሰውን ሊያስደነግጥ ይችላል፤  ወደ አላህ ግን ይመልሳል፡፡

ከሰው ሊያሸሽ ይችል ይሆናል ወደ አላህ ግን ያስጠጋል፡፡

ይሁን ለበጎ ነው። አላህን ያስታወሰን፣ ወደ አላህ የመለሰን ነገር ሁሉ መከራ ሳይሆን ድሎት ነው።

https://t.me/MuhammedSeidAbx
ሰበረኝ ትላለህ ምናልባት እኮ ጠግኖህ ይሆናል ።

ጣለኝ ትላለህ ምናልባት እኮ አንስቶህ ይሆናል ።

ከለከለኝ ትላለህ ምናልባት እኮ ሰጥቶህ ይሆናል ።

ከሰርኩ ትላለህ እውነታው ቢመረመር እኮ አትርፈሃል።

ያመለጠህ ይመስልሃል ግና ዕድልህ እኮ ወደፊት እየመጣ ይሆናል ።

እኛ ውጪውን እናያለን አላህ እውስጡን ያውቃል ።

መጥፎ በሚመስል ነገር የተሸፈኑ ብዙ መልካም ነገሮች አሉ።

እናንተ ከመረጣችሁት ይልቅ አላህ የመረጠላችሁን ምረጡ።

በአላህ ምርጫ ውስጥ ምንም መጥፎ ነገር የለም።


Abx
ኢላሂ!

የለገስከንን ሲሳይ በወንጀል አጥፍተን፣ በድጋሚ ሲሳይህን ለምነን አልነፈግከንም። በድጋሚ የሰጠኸንን ሲሳይ ተጠቅመን አንተን አመፅንህ። አንተ ግን ሸፈንክልን።

ሲሳይህን እንድትጨምርልን ለምነንህ አልከለከልከንም። ከጭማሪህ በኋላም ግን በገሀድ ማመፃችንን አልተውንም። አንተ ግን አላዋረድከንም።

ከዚያም በኋላ እኛም አመፅ አላቋረጥንም። አንተም ደጋግመህ በቻይነትህ እና በመልካምነትህ እኛን መመልከት አላቆምክም።

በእግራችን ተራምደን፣ እጃችንን ዘርግተን፣ በዓይናችን አተኩረን፣ በጆሯችን አድምጠን፣ በልሳናችንን ተናግረን የፈፀምነውን ወንጀላችንን ሁሉ ማረን።…
ጌትዬ መንገደን ባሮችህ ቢያውቁት ምን ሊሉ እንደሚችሉ ሳስብ አንተ ፊት የመቆም ክብደቱ ያስጨንቀኛል። እንደኔ ቢሆን የእስልምናን ወጋገን ባላሳየኸኝ ነበር እንደ እዝነትህ የኔ ጌታ!

የአንተን ብቻ አምላክነት'ና ንግስና  የ'ኔን የባርነት ውበት  ልቤ ላይ ባኖርክበት እዝነትህ ይሁንብህ ፊትህ ስታቆመኝ ወንጀሎቸን ሁሉ አፉ ብለህ ሳልሳቀቅ አንተን የማየትን ፀጋ አላብሰኝ ያ ረብ!


https://t.me/bilQURANnehyaa
ዐይኔ የሰው ነውር ማየት ታፍራለች።

ልቤ ደግሞ ካንተ በላይ ነውረኛ ማን አለ ትለኛለች ... የማትረባ።

ሱብሓነከ ረቢ

መሳአል ኸይር

MuhammedSeidAbx
{ أَوَلَمۡ يَرَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ أَنَّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ كَانَتَا رَتۡقٗا فَفَتَقۡنَٰهُمَاۖ وَجَعَلۡنَا مِنَ ٱلۡمَآءِ كُلَّ شَيۡءٍ حَيٍّۚ أَفَلَا يُؤۡمِنُونَ }
[Surah Al-Anbiyāʾ: 30]

እነዚያም የካዱት ሰማያትና ምድር የተጣበቁ የነበሩና የለያየናቸው መኾናችንን አያውቁምን ሕያው የኾነንም ነገር ሁሉ ከውሃ ፈጠርን፡፡ አያምኑምን
ስለ ቴክኖሎጂ መስኮችና አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ከምሁራን ጋር የምንወያይበት መድረክ በይፋ ተጀምሯል።

የቀጥታ ስርጭቱን ለመከታተል በዚህ ሊንክ ግቡ።

መጨረሻ ላይ ጥያቄዎች ካሏችሁ መጠየቅና ማብራሪያ ማግኘት ትችላላችሁ።

https://t.me/MuradTadesse?livestream
Forwarded from Tofik Bahiru
በርካታ በሮችን አንድ በአንድ ስታንኳኳ አይቶሃል። የሀብታም በር፤ የባለስልጣን በር፤ የባለ ዝና በር፤ የዘመድ በር፤… በየበሩ ስትወድቅ፣ በየመንገዱ ስትሰናከል አይቶሃል። አንዱ ሲያስከፋህ፣ ሌላው ሲያስደነግጥህ፣ ሦስተኛው ሲያሾፍብህ፣ ሌላኛው ሲያሴርብህ… ተመልክቷል።
ቀጥ ብለህ ስትቆም፣ ስትንዳለጥ፣ ስትወድቅ፣ ስትነሳ፣ ስትለፋ፣ ስታለቅስ… በመንገድህ ሁሉ የርሱን ደጃፍ እየዘለልክ ስትባትል አይቶሃል።  የርሱን ደጃፍ የምትረግጥበትን ቀን እየጠበቀ ነው። ከሁሉም ደጃፍ መፍትሄን አጥተህ በተሰበረ ልብ፣ በለቅሶ ተሞልተህ፣ በሀፍረት ተውጠህ፣ ተፀፅተህ በርሱ ግቢ የምትነጠፍበትን ቀን በናፍቆት ይጠብቃል።
:
«ሁሉም ቢገፉህ እኔ ደጋፊህ ነኝ!
ፍጥረት ቢጠሉህም እኔ ወዳጅህ ነኝ!
ቢያቆስሉህ እኔ ሀኪምህ ነኝ!
ከጎናቸው ቢያርቁህም እኔ ቅርብህ ነኝ!
ወደኔ ና!
ወደ እልፍኜ ጎራ በል!
ምንጊዜም ስትፈልገኝ አለሁ!
ከኔ ውጪ ሌላን አትጥራ! ምላሽ ከመስጠት አልታክትም! እኔ እበቃሀለሁ! ችግርህን እቀርፋለሁ! ጭንቀትህን እፈታለሁ! አግዝሃለሁ! እረዳሃለሁ! ስታስበኝ አስብሀለሁ! ስትለምነኝ እሰጥሀለሁ!»
እያለ!…
:
ስለ ''አል‐ወዱድ'' [ﷻ] ነው የማወራው!
Forwarded from أدهم شرقاوي
‏﴿فإنك بأعيننا﴾
‏﴿وحناناً من لدّنا﴾
‏﴿ولتصنع على عيني﴾
‏كيف تشعر وأنت تقرأها ؟
‏أمع الله جرح لا يبرأ ؟
‏أمع الله كسرٌ لا يُجبر ؟
‏ثق بالله تعالى وتوكل عليه وكفى بالله وكيلا.
رحل رجل من أشرف الرجال في زمن قل فيه الرجال رحل وبقي اسمه في قلب كل مسلم
ادعوا له بالرحمه
ሕይወትን በጠቅላላው ለአል-ቁድስ ነጻነት ሰጥቶ፣ ታጋይ ሆኖ መኖር፣

ከዚያም በዚሁ የነጻነት ጎዳና ላይ ጸንቶ የሰማዕትነትን ጽዋ ጨልጦ መሰዋት፣

ተፈልጎና ተመኝተውት የማይገኝ፣

ለጥቂቶች ብቻ የሚቸር ዕድል እና ታላቅ ስኬት ነው፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡

የእናንት የሰማዕታት ደም ብርሃን ፈንጥቆ፣ ለእኛ በድቅድቅ ጨለማዎች ውስጥ ለተዋጥነው ቀሪዎች ምሪት ይሆነናል፡፡
Forwarded from Tofik Bahiru
በሰሞኑን ክስተት ተከታታይና የተለያዩ ስሜቶች ሲፈራረቁብኝ ቆይተዋል። የመጨረሻው ትእይንት ግን የሚደንቅ ነው!
አንበሳው! በከባድ ሁኔታ ቆስሎ፣ በደም ተጨማልቆ ተቀምጧል። የቀረችውን እስትንፋስ እንኳን በቢላሽ ማሳለፍ አልፈለገምና በእጁ በቀረችው ዱላ ጠላቶቹን ለመምታት ሰነዘራት!…
«በአንዳችሁ እጅ ችግኝ እያለ ቂያማ ቢደርስና ቂያማው ከመቆሙ በፊት መትከል ከቻለ ይትከላት።» የአላህ መልክተኛ []

ይህ ትእይንት ከፊልም የተቀነጨበ ተውኔት አይደለም። በጠላቱ ሳይቀር የተመሰከረ የእውን ክንውን ነው!
:
የተመለከትነው ክስተት ጥልቅ ምክርና አስተምህሮን አዝሏል። ለበርካቶች የመንፈስ ምግብና የትጋት ምንጭ ይሆናል ተብሎም ይታሰባል። በአላህ መንገድ ለመሰዋት መናፈቅ በእውነተኞች ልብ ውስጥ የሚዘልቅ ጥልቅ ነገር እንጂ የምላስ ወግ እንዳልሆነ ያስረዳል!
:
በተረፈው ሰውየው የሕያ ነው። ስሙ ህያውነትን ያሳያል። የሸሂዱ ነቢይ የሕያም [ﷺ] ስም ነው። ሸሂድ ደግሞ ጌታው ዘንድ ህያው ነው!
አላህ ይቀበለው! መሬታቸውን ለተቀሙ፣ ለዲናቸውና ለክብራቸው ለሚፋለሙ ድኩማን ወንድሞቻችንም ድሉን ይስጥ!
አሚን!
Forwarded from ABX (Muhammed Seid)
የክህደት ዓይነቱ ብዙ ነው።

* ሰውየው ሳያውቅ እሱን መቅረጽ ክህደት ነው።

* ሰውየው ሳያውቅ ድምፁን ላውድ ላይ በማድረግ ሌላውን ማስደመጥ ክህደት ነው።

* ሰውየው ሳያውቅ የሱን ፎቶ አንስቶ መፖሰትም ክህደት ነው።

* እያዳመጡ ባለመምሰል የሰውን ሚስጢር ማዳመጥ ክህደት ነው።

* ምንም የማያውቁ ልጆችን ስለቤተሰባቸው ሁኔታ በማውራት ለማውጣጣት መጣርም ክህደት ነው።

*በሠራተኞች አማካይነት ጎረቤትን መሰለልም ክህደት ነው።

* የሰውን ነውር መከታተልም ክህደት ነው ።

* የሰው ሚስጢር መበተንም ክህደት ነው።

* የሠሩትን ለማጋለጥ በመዛት ሙስሊምን ማጨናነቅም ክህደት ነው።

* መርዳት በሚገባ ቦታ ላይ ሙስሊም ወንድም/እህትን አሳልፎ መስጠት ክህደት ነው።

ሙስሊም በሙስለም ወንድሙ ይተማመናል።
ይጠብቀኛል ብሎ ወንድሙ ላይ ራሱን ይጥላል ።

አንድ ሙስሊም ሚስጢር ሲያወራህ ይነግርብኝ ይሆን ብሎ ከተጠራጠረ ይከዳኛል ብሎ እየፈራ ነው ማለት ነው።

ወንድም እህቶቻችሁ አምነው የሚደገፉባችሁ አስተማማኝ ግድግዳ ሁኑ።


መሳአል ኸይር

https://t.me/MuhammedSeidAbx
Forwarded from Best kerim (Abdurezak N)
የሕይወት ሚዛን

የምንኖርባትን አጭር የዱንያ ዓለም በትዕግስትና በእርጋታ ካልተረዳናት ከዐለሙ በሰፋው ውስብስብ ጥልቀቷ ውስጥ እንድንዘፈቅ ታደርገናለች።

የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የዚህች ዐለም መከራ እንድንሻገር በርካታ መንገዶችን አድርገውልናል። የርሳቸውን ብርሃናማ ንግግሮች ለመረዳት ጥልቅ እምነት ቢያሻንም ንግግሮቻቸውን ደጋግሞ በማውራትና በማዳመጥ ልባችን ውስጥ ለመጻፍ ጥረት እናደርጋለን። ይህ በራሱ ዚክር ሲኾን በሌላኛው ዕይታ ደግሞ ሕክምና ነው።

የሚቀጥሉት አራት ሐዲሶች ለተረጋጋ ሕይወታችን መሠረቶች ናቸው።

አንደኛ፦ ምላስን ከክፉ ንግግር መቆጠብ

« በአላህና በመጨረሻው ዘመን ያመነ ሰው መልካም ንግግር ይናገር ወይም ዝም ይበል።» (ሐዲስ)

ክፉ ንግግሮች ከአንደበታችን ከሚወጡ ዝምታችን የተሻለ እንደኾነ የሚመክረን ሐዲስ ነው። ብዙ ጊዜ ሰዎች የሚያዙት በዝምታቸው ሳይኾን በንግግሮቻቸው ነውና!

ሁለተኛ፦ ከማያስፈልጉ ነገሮች መራቅ

የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦

« አንድ ሰው የማይመለከተውን ነገር መተዉ ከእስልምናው ማማር ነው።»

ያለንበት ጊዜ በማንፈልጋቸው በርካታ ጥፋቶች በግዴታ የምንነከርበት ነው። ይህ በመኾኑም በቀጥታ የማይመለከቱንን ነገሮች ከመስራት፣ ከማድመጥና፣ ከመናገር መቆጠብ እምነትን እንደሚያጠናክርና ንጽሕናን እንደሚያፋፋ መገንዘብ ተገቢ ነው።

ሦስተኛ፦ ራስን መቆጣጠር (ከቁጣ መጠበቅ)

አንድ ሰው የአላህ መልእክተኛን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲመክራቸው ጠይቋቸው ደጋግመው "አትቆጣ" አሉት።

ይህ የሚያሳየው ቁጣ የአዕምሮን ሚዛን የሚያዛባ ፍትሕን የሚያሳጣ ግለሰቦች ላይ ውስጣዊ ጉዳትን የሚያስከትል ከባድ ነገር መኾኑን ነው።

አራት፦ ንጹሕ ልቦና መያዝ

የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦

« ለራሳችሁ የወደዳችሁትን ለሌሎች እስካልወደዳችሁ ድረስ አላመናችሁም።»

ራሳችን ላይ ቢኾን የምንወደውን ነገር ሌሎች ላይ እንዲኾን መመኘት፣ ራሳችን ላይ እንዳይደረግ የምንጠላውን ሌሎች ላይ እንዳይደረግ ማሰብ የአማኝ ባሕርይ ነው። የእምነትም መለኪያ ነው። በዚህች ቅጽበታዊ ዐለም ተታለን ሰዎችን በልብም ኾነ በአካል ከመጉዳት መታቀብ ጥልቅ ከሆነ ከኢማን መንገድ መሸለም ነው።

አላህ ያስረዳን 🤲
Forwarded from Tofik Bahiru
መልካም ነገሮች የሚኖሩት ክስተቶች ላይ ሳይሆን በልባችን ውስጥ ነው። መልካም ዐይን ሲኖረን በሁሉም ነገር ላይ ያለውን ውበት እናያለን።
ሰይድ አቡበክርና አቡጀህል በእኩል አንድን ክስተት አይተዋል፤ ሰይዳችን ሙሐመድን [ﷺ]።
ዐይናቸውና ልባቸው ግን ተለያይቷል። አቡበክር በንፁህ ልብ ውበትን ለማየት በታደለ ዐይን አዩ። አቡጀህል በቆሻሻ ልብ ውበትን ማየት በማይችል ዐይን አየ።
ውሳኔያቸውም ተለያየ!
መልካሙን እይ። ክፉን ሸፍን።
ከፈለጉ ሞኝ ነው ይበሉህ፤ አንተ ግን በጎ አስብ!
:
t.me/fiqshafiyamh
Forwarded from ABX (Muhammed Seid)
ለሆነ ነገር ጉጉ መሆናችሁን ሰዎች ሁሉ እስኪያወቅባችሁ ድረስ ስለዚያ ነገር አብዝታችሁ አታንሱ፡፡ ገንዘብ፣ ትዳር፣ ዝና … ጥቂቶች ናቸው፡፡
ምኞታችሁን ለአላህ ብቻ ንገሩ፡፡ ሰው ፊት አንድን ነገር አብዝቶ ማውሳት ልመና ይመስላል፡፡

ሶባሐል ኸይር

https://t.me/MuhammedSeidAbx