🍃بالقرآن نحي {በቁርአን እንኖራለን
941 subscribers
779 photos
293 videos
17 files
644 links
የተለያዩ ቁርኣናዊ አስተምህሮ’ዎች፣ ጣፋጭ ቲላዋዎች፣ ቁርኣንን የሚመለከቱና በቁርኣን ዙሪያ የሚሽከረከሩ መልዕክቶች የሚተላለፍበት ቻናል join ይበሉ !
ቁርኣን የወረደው ለሰው ልጅ መመሪያ፣ እንድናስተነትነውና እንድንገሰፅበት ነው።
አላህ እንዲህ ይላል፦ (ይህ) ወዳንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው፡፡ አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑና የአእምሮዎች ባለቤቶችም እንዲገሰጹ (አወረድነው)፡፡ {Q 38:29}
Download Telegram
እሚን እንደወፍ ነው ይላሉ። ቀልቡ ንቁ ነው። ንፁሕና ዋህም ነው፡፡ ልቡ ደንዳና አይደለም ስስ ነው። ተዘናግቶ ብዙ አይቆይም ። ጠፍቶ አይቀርም ይባንናል። ከአላህ አንፃር ሁሌም ሁኔታዉን ይገመግማል ። አጥፍቼ፣ ተሳስቼ፣ መንገድ ስቼ ... ይሆን ይላል። ያጠፋዉን ቶሎ ያርማል። ያበላሸዉን ያስተካክላል። የበደለዉን ይክሳል።

ሙእሚን፤ አካሉ ዱንያ ላይ ቢሆንም ሀሳቡ ኣኺራ ነው። ሌቱን በሁለት ዐይኖቹ አይተኛም ። ምሽቱን ራሱን ጥሎ እንደግንድ ተጋድሞ አያድርም። ቀኑን፤ በግርግር መሀልም ቢሆን ንቁ ነው። የሆነ ቀን ላይ ዱንያን እንደሚሠናበት ያውቃል። ወዴት እየሄደ እንደሆነ አይጠፋዉም። ለዚያ ረጅም ጉዞው በቂ ስንቅ የያዘ ስለመሆኑ ይፈትሻል ።

ሶባሐል ኸይር

Abx
#ዙልሒጃ

ከተከበሩ የአላህ ወራት መካከል አንዱ የኾነው 12ኛው የሂጅሪያ ወር ሊገባ ቀናት ቀርተዋል። የፊታችን ጁምዓ አንድ ብሎ ይጀምራል። ዙልሒጃ 9 ቅዳሜ (ሰኔ 8 ) ታላቁ የዐረፋ ቀን ሲኾን እሁድ ዙልሒጃ 10 (ሰኔ 9) የዒድ አልአድሐ ክብረበዓል ነው።

ከቀናት ኹሉ ውድ የሚባሉ ቀናትን በጾም፣በዚክር፣ በቁርኣንና በሌሎች አምልኮዎች ለማሳለፍ ከወዲሁ እንነይት። በተለይም ዘጠነኛውን የዐረፋን ዕለት በተለየ መልኩ ከአላህ ጋር በአምልኮ ለመገናኘት ቀጠሮ እንያዝ።

አቤቱ አላህ ሆይ ... ደክሞናል፥ ሐዘን ሲያልፍ እንዳልነካው ያህል የገጠመንን ስብራትን ጠግንልና!!

ሁለመናችንን ታውቃለህ ብለን ተመልሰናል👌
በዚህች ምድር ላይ አላህ የፃፈላችሁን ነገር ከመውሰድ፣ ወይም ከማግኘት የሚከለክላችሁ አንድም ሰው የለም።


Abx
የዙልሒጃ ወር ነገ ጁመዓ እንደሚጀምር ታወቀ

በሂጅሪ አቆጣጠር 12ኛው የዙልሒጃ ወር የመጀመሪያ ቀን ነገ ጁመዓ እንደሚሆን የታወቀው በዛሬው እለት አዲስ ጨረቃ በመታየቱ ነው። በዚህም መሠረት ዛሬ ሐሙስ የዙልቀዕዳ ወር የመጨረሻ ቀን ይሆናል።

በሌላ በኩል የዘንድሮው ዓመት የዒድ አል አድሓ በዓል በወሩ አሥረኛው ቀን እሑድ ሰኔ 9/2016 ይከበራል።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
{ إِنَّ فِی خَلۡقِ ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تِ وَٱلۡأَرۡضِ وَٱخۡتِلَـٰفِ ٱلَّیۡلِ وَٱلنَّهَارِ لَـَٔایَـٰتࣲ لِّأُو۟لِی ٱلۡأَلۡبَـٰبِ (190) ٱلَّذِینَ یَذۡكُرُونَ ٱللَّهَ قِیَـٰمࣰا وَقُعُودࣰا وَعَلَىٰ جُنُوبِهِمۡ وَیَتَفَكَّرُونَ فِی خَلۡقِ ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تِ وَٱلۡأَرۡضِ رَبَّنَا مَا خَلَقۡتَ هَـٰذَا بَـٰطِلࣰا سُبۡحَـٰنَكَ فَقِنَا عَذَابَ ٱلنَّارِ (191) رَبَّنَاۤ إِنَّكَ مَن تُدۡخِلِ ٱلنَّارَ فَقَدۡ أَخۡزَیۡتَهُۥۖ وَمَا لِلظَّـٰلِمِینَ مِنۡ أَنصَارࣲ (192) رَّبَّنَاۤ إِنَّنَا سَمِعۡنَا مُنَادِیࣰا یُنَادِی لِلۡإِیمَـٰنِ أَنۡ ءَامِنُوا۟ بِرَبِّكُمۡ فَـَٔامَنَّاۚ رَبَّنَا فَٱغۡفِرۡ لَنَا ذُنُوبَنَا وَكَفِّرۡ عَنَّا سَیِّـَٔاتِنَا وَتَوَفَّنَا مَعَ ٱلۡأَبۡرَارِ (193) رَبَّنَا وَءَاتِنَا مَا وَعَدتَّنَا عَلَىٰ رُسُلِكَ وَلَا تُخۡزِنَا یَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِۖ إِنَّكَ لَا تُخۡلِفُ ٱلۡمِیعَادَ (194) }
[Surah Āli-ʿImrān: 190-194]
ይህ የሐጅ እና ዑምራን መማሪያዎች በቀላሉ ለመማር ይረዳ ዘንድ በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር የተዘጋጀ ነፃ፣ በመጠን አነስተኛ እና ብዙ ትምህርቶችን ያቀፈ መተግበሪያ አፕሊኬሽን ነው። ይጠቀሙበት ያስተዋውቁት፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=com.nesiha_org.Hajj
ነገር ሁሉ አላህ እጅ ነው። ከአላህ ይጀምራል ። አለህ ዘንድም ያበቃል። አላህ እጅ ባለ ነገር፤ ከአላህ በሚታዘዝ ነገር ፤ ሰው ልመና፣ ሰው ደጃፍ ስለምን ብዙ ትቆማላችሁ !!

ሶባሐል ኸይር !
Abx
ስለ አሥሩ የዘል ሒጃ ቀናት
****
- በኢስላማዊው አቆጣጠር 11ኛው  የዚል ሒጃ ወር ሲጀምር ይጀምራሉ፡፡ የዒድ አል-አድሓ ቀን ያበቃሉ፡፡

- እጅግ የተከበሩና የላቁ ከመሆናቸው ጋር ብዙዎች በነኚህ ቀናት ዉስጥ ሲዘናጉ ይታያሉ፡፡

- በነኚህ ቀናት ዉስጥ የሚሠሩ መልካም ሥራዎች በየትኛዉም ቀናት ዉስጥ ከሚሠሩት በላይ አላህ ዘንድ ተወዳጅ ናቸው፡፡

- የዐረፋ ቀን ፆም (ዘጠነኛው ቀን) የሁለት ዓመት ኃጢኣት ያስምራል፡፡ ያለፈን አንድ ዓመት እና የሚቀጥለዉን አንድ ዓመት፡፡

- ቀንም ሆነ ሌሊት በነኚህ ቀናት ዉስጥ በዒባዳና በማንኛውም መልካም ሥራ መበርታት ይገባል፡፡

- በነኚህ አሥር ቀናት ሌሊቶች አላህ ሱ.ወ. ምሎባቸዋል፡፡ ይህም ክብደታቸውን ያሳያል።

- ሱብሐነላህ፣ አልሐምዱ ሊላህ፣ ላ ኢላሀ ኢልለላሀ አላሁ አክበር ማለት ያበዙ፡፡

- ኢብኑ ዐመር እና አቢ ሁረይራ በነኚህ ቀናት ዉስጥ ተክቢራ እያደረጊ ወደ ገበያ ይወጡ ነበር፡፡ ሰዎችም አብረዋቸው ተክቢራ (አሏሁ አክበር) ይላሉ፡፡

- በነኚህ ቀናት ዉስጥ ዚክር ማብዛት፣ አላህን ማላቅ ይወደዳል፡፡

- የዐረፋ ቀን ትልቁ የሐጅ ቀን ነው። ዱዓና ዚክር ማብዛት ይመረጣል፡፡ በዚያ ቀን ውስጥ የሚባለው ትልቁ  ዚክር "ላ ኢሀ ኢልለሏህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ፤ ለሁልሙልኩ፣ ወለሁል ሐምዱ፣ ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲር … ነው፡፡

- በነኚህ ቀናት ዉስጥ የሚሠሩ ዒባዳዎች የተለያዩ ዓይነት መሆናቸው ቀናቶቹን ልዩ ያደርጋቸዋል፡፡ ሶላት፣ ፆም፣ ሶደቃ፣ ሐጅ … ሁሉም የተሰባሰቡባቸው ናቸው፡፡

- ደጋጎች የሚከተሉትን አሥርቶች ልዩ ትኩረት ይሠጧቸው ነበር፡፡ የረመዷን ወር የመጨረሻዎቹ አሥር ቀናት፣ የዚል ሒጃ ወር የመጀመርያዎቹ አሥር ቀናት፣ የሙሐረም ወር የመጀመርያዎቹ አሥር ቀናት፡፡

- አሥርቱ ዚል ሒጃ ቀናት፤ ከዱንያ ቀናት ሁሉ ምርጦቹ በመባል ይታወቃሉ፡፡

እንጠቀምባቸው።
ዛሬ አምስተኛው ቀን ላይ ነን፡፡


https://t.me/NejashiPP
Forwarded from Tofik Bahiru
ዛሬ የዙልሒጃ ወር ስምንተኛው ቀን ነው
ሐጀኞች በሙሉ ለነገው ዋናው የሐጅ ስራ— ለዐረፋው ዉቁፍ— እየተዘጋጁ ነው። ሁሉም ሚና ላይ ከትመዋል።
ዕለቱ የውሙት–ተርዊያ (ውሃን የማጠራቀም ቀን) ይባላል። ስያሜውን ያገኘው ሐጀኞች በዚህ ቀን የውሃ ማጠራቀሚያ "ቀርበታዎቻቸውን"— ለነገው የዐረፋ ቀን ጥም— ብለው የሚሞሉበት ቀን ስለሆነ ነው። ምክንያቱም ዐረፋ ሜዳ ላይ ውሃ አይገኝም።…

በዚህ አጋጣሚ ለኛ የሚሆን መልእክት ላንሳ…
ለአኺራ ስለመሰነቅ አስበባችኋል!?…
የኢማን፣ የተቅዋ እና የበጎ ስራ ጥም ነው ያን ቀን የሚኖረው። የዚክርና የአምልኮ ዝናብ ነው ከድርቁ የሚያተርፈው። ረዥም መንገድ አለ ውዶቼ። ስንቃችን ግን ምን ያህል ያስኬዳል!?… ቀልብህን ዛሬ በጎርፍ ሙላው። በተቅዋና በመልካም ስራ ጎርፍ።…

ነገ የዐረፋ ቀን ነው። ሐጀኞች ዐረፋ ላይ ይውላሉ። እኛ ደግሞ ከእነርሱ ጋር ለማበር እንፆማለን። የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁዐለይሂ ወሰለም) "የዐረፋ ቀን ጾም ያለፈውን አመት ኃጢያት ያስምራል" ብለዋል።
እና ምን ወሰናችሁ!?… እነሆ የሚምር ጌታ ኑ ልማራችሁ እያላችሁ ነው!…
ዱዐ የእለቱ ምርጥ ዒባዳ ነው። "ምርጡ ዱዐ የዐረፋ ቀን ዱዐ ነው" ብለዋል ነብያችን።
የዱዐን ጉድ በኋላ አወራችኋለሁ!
لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَحْدَهُ لاَ شَرِيكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ، وَلَهُ الْحَمْدُ، وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ