🍃بالقرآن نحي {በቁርአን እንኖራለን
914 subscribers
785 photos
299 videos
17 files
659 links
የተለያዩ ቁርኣናዊ አስተምህሮ’ዎች፣ ጣፋጭ ቲላዋዎች፣ ቁርኣንን የሚመለከቱና በቁርኣን ዙሪያ የሚሽከረከሩ መልዕክቶች የሚተላለፍበት ቻናል join ይበሉ !
ቁርኣን የወረደው ለሰው ልጅ መመሪያ፣ እንድናስተነትነውና እንድንገሰፅበት ነው።
አላህ እንዲህ ይላል፦ (ይህ) ወዳንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው፡፡ አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑና የአእምሮዎች ባለቤቶችም እንዲገሰጹ (አወረድነው)፡፡ {Q 38:29}
Download Telegram
#መሬት_ታዛቢ_ናት

አንድ ሰለፍ እንዲህ ይላሉ፦ « በአንድ ቦታ ላይ አላህ ላይ ካመጽክ (ወንጀል ከሰራህ) ከዚያ ቦታ ላይ አላህን ሳትታዘዝ እንዳትሄድ ምክንያቱም ቦታው አንተ ላይ እንደሚሰክረው ላንተም ይመሰክራል።»

ቁርኣን በአልዘልዘላ ምዕራፍ ላይ መሬት ስትርገፈገፍና የያዘችውን ጉድ ኹሉ ስትዘረግፍ
ሰዎች ምን ሆና ነው ብለው ይጠይቃሉ ይለናል።
{ إِذَا زُلۡزِلَتِ ٱلۡأَرۡضُ زِلۡزَالَهَا }
{ وَأَخۡرَجَتِ ٱلۡأَرۡضُ أَثۡقَالَهَا }
{ وَقَالَ ٱلۡإِنسَـٰنُ مَا لَهَا }.........
እርሷ መሬት ስለ ሰዎች የያዘችውን የታዘበችውን ኹሉ እንደምታወራ ይነግረናል። በምድር ላይ የሚከናወኑ ነገሮች ኹሉ መሬት በሚገባ ትመዘግባለች፣ ሰማይም ይመለከታል። ለዚህ ነው ምድርና ሰማያት ደጋግ ሰዎች ከዚህ ምድር ሲያልፉ የሚያለቅሱትም። በየትኛውም ቦታ በነፍስያችን ሰፊና የማያልቅ ፍላጎት በሰይጣንና በወስዋሰል ኸናስ ጉጎታ ወንጀል ላይ ብንወድቅ ሁሌም የገዛ ነፍሳችንን በብርቱ ይዘናት በሚገባት መልኩ ከርሷ ጋር ማውራት አለብን። ለርሷ ጥፋት የሚመጥን ማስተካከያም መስራት ይገባናል። ይህች ነፍስ ለሁሉም ዐይነት ሰው እጅግ በጣም ፈታኝ ነች። የበለጠ የምትፈትነው አውቄያለሁ፣ በቅቻለሁ፣ ጨርሼለሁ የምንለው ሰው ላይ ነው።

ስለዚህች [ነፍስ] አላህ ከፈቀደ ብዙ የምንባባለው ነገር ይኖራል፤ አላህ ከርሷ ወጥመድ ይጠብቀን፤ ይጠብቃችሁ!

መልካም ቅዳሜ ♥