✞ ቤተ ያዕቆብ ✞
373 subscribers
838 photos
74 videos
76 files
392 links
እንኳን ደኅና መጣችሁ !
ዓላማ ፦
በ ✞ ቤተ እስራኤል ✞ ማኅበራችን የምንማማራቸውን ትምህርቶች ፣ የጥያቄ መልሶች ፣ ስነ ጽሑፎችና የመዝሙሮች ምስጋናዎች በዚህ የሚቀመጡበት ፤ ከተለያዩ ምንጮች የተገኙ መንፈሳዊ ጽሑፎችና የመጻሕፍት pdf የሚለቀቁበት Channel ነው ።

ለሐሳብ ወይም አስተያዬት @Wonde2010 ላይ ያስቀምጡልኝ !

ግሩፓችን 👉 https://t.me/betesrael
Download Telegram
ኒቆዲሞስ ክቡር
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
#ኒቆዲሞስ

ኒቆዲሞስ ኒቆዲሞስ ክቡር
ሌቱን በብርሃን የሚማር መምህር

በጨለማው ግርማ ኮከብ የደመቀ
በመከራው ፅናት ይህን ዓለም ናቀ
መምህር ሆኖ ሳለ ከመማር ያልራቀ
የትዕቢትን ጅረት በትህትና ተዋርዶ አደረቀ

ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ

#አዝ......

ፍርሃትን በሚጥል ፍፁም ፍቅር ያደረ
ከመስቀል አውርዶ ጌታውን ቀበረ
የመግነዙን በፍታ በሽቶ አከበረ
ከመቅደሱ አንቀፅ ላይረሳ አምድ ሆኖ ታጠረ

ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ

#አዝ......

ለሊትም ለሊት ዕውቀትን ነገረች
ህጉን ለሚያስበው ምክር አለኝ እያለች
ከጨለማ ሀጢያት ነግታ ብርሃን ከአየች
እንደ ኒቆዲሞስ ነፍስህም ተምራ ተመለሰች

ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ

@igziyabhern