አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር በኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ አማካኝነት ለኅብረት ሥራ ማኅበሩ ሰራተኞች በአባላት አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ!!!
አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር በቅርብ ጊዜ ለተቀላቀሉ አዳዲስ ሰራተኞቹ እና በአባላት ቅበላ እና አገልግሎት ስራ ላይ ለተሰማሩ ከ25 በላይ ሰራተኞቹ በአባላት አያያዝ እና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ለተከታታይ ሁለት ቀናት በኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ አማካኝነት ስልጠና ሰጥቷል፡፡
ስልጠናው የኅብረት ሥራ ማኅበሩን የአባላት አያያዝ እና መስተንግዶን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንዲሁም የአባላትን የአገልግሎት እርካታ ለመጨመር ትልቅ አስተዋፅዖ እንዳለው የተገለጻ ሲሆን በቀጣይም ኅብረት ሥራ ማኅበሩ ለቅጥር ሰራተኞቹ የተለያዩ ስልጠናዎችን በማዘጋጀት የሰራተኞችን አቅም በመገንባት የኅብረት ሥራ ማህበሩን የእድገት ግስጋሴ ለማስቀጠል በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን የኅብረት ሥራ ማኅበሩ የሰው ሃብት አስተዳደር ስራ አስኪያጅ የሆኑት ወ/ሮ ገነት ጥላሁን ገልፀዋል።

በአዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበር መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘሪሁን ሸለመ የህይወት ታሪክ ዙሪያ የተፃፈው ‹‹የእናቱ ልጅ›› መፅሀፍ
የመፅሀፉ ይዘት 👉 መጽሐፉ በሶስት ምዕራፎች ተሰንዷል። በምዕራፍ አንድ የዘሪሁን ከውልደት እስከ ጉልምስና ያለው ታሪክ ተተርኮበታል። በምዕራፍ ሁለት የአዋጭ ምስረታ ታሪክና ዕድገት ከዘሪሁን አበርክቶ ጋር እየተዛነቀ ቀርቦበታል። በምዕራፍ ሶስት የመሪነት ጽንሰ ሃሳብ ከሕብረት ሥራ መሪው አቶ ዘሪሁን ሸለመ የተቋም አመራር እስከ ማህበራዊ ግንኙነት ተተንትኖበታል። በየምዕራፎቹ ህዳግ ስለዘርፉ ሁለንተና ተዳሶበታል። በጥቅሉ በአቶ ዘሪሁን ሕይወት ታሪክ ላይ ሰፊ ትኩረት ያለው ሆኖ ቢዘጋጅም አቶ ዘሪሁን ሲነሳ አብረው ስለሚነሱት ስለ አዋጭ ተቋማዊ ታሪክና አበርክቶ ብሎም ስለ ሕብረት ሥራ አጠቃላይ ሁኔታ ታሪክንና ምንነትን ማወቅ ለሚሹ በወፍ በረር የሚያስቃኝ እንዲሆን በማሰብ የእነዚህ የሶስቱ ጭምቅ የተካተተበት መፅሀፍ ነው።
ለኅብረት ሥራ ማህበሩ እና ለህብረት ሥራ ሴክተር ያለው ጠቀሜታ👉 መፅሀፉ የአዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበር ከምስረታ ሀሳብ ጀምሮ ከፍተኛ የእድገት ጉዞውን እያስቃኘ እስከ ወደፊት መዳረሻው ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል፡፡
መታሰቢያነቱ 👉 የእናቱ ልጅ የተሰኘው የአቶ ዘሪሁን ሸለመን የሕይወት ታሪክ የሚዳስሰው መፅሀፍ መታሰቢያነቱ ለእናቱ ወ/ሮ አየለች ወርቁ እና ባሎቻቸው ለሀገር ሲባል በውትድርና ሕይወታቸውን በመሰዋታቸው የተነሳ ልጆቻቸውን እንደ እናትና አባት ሆነው ላሳደጉ፣ በብዙ ውጣውረድ ላለፉ እና እያለፉ ላሉ የኢትዮጵያ እናቶች ሁሉ መታወሻ እንዲሆን ተደርጓል፡፡
የመፅሀፍ ምርቃት ዝግጅቱን በተመለከተ 👉 ባለታሪኩ፣ የባለታሪኩ ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶች፣ የተለያዩ ደራሲያን እና የጥበብ ሰዎች፣ የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች፣ የኅብረት ሥራ ሴክተር አመራሮች፣ ባለሙያዎች እና አባላት እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ቤተሰቦች በምርቃት ዝግጅቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡ በእለቱም የኢትዮጵያ እናቶች ተዘክረውበታል፤ ለሀገራችን ወጣቶች በብዙ ችግርና ፈተና ውጣ ውረድ አልፎ ለስኬት መብቃት እንደሚቻል ትምህርት አዘል መልእክት ተላልፎበታል፤ የሀገራችን የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበራት በሀገራችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን በመፍታት ረገድ እያደረጉት ያለው አስተዋፅዎ አድናቆትን አግኝቷል፡፡
የመፅሀፍ ዝግጅት 👉 መፅሀፉ በደራሲና ጋዜጠኛ ደመቀ ከበደ የተፃፈ ሲሆን የታሪክ ፍሰቱን በጠበቀ እና አጓጊ እና ማራኪ በሆነ የአፃፃፍ ስልት ቅልብጭ ተደርጎ ተዘጋጅቷል።
የመፅሀፉ መሸጫ ቦታዎች 👉 መፅሀፉ በመላው የህብረት ሥራ ማህበሩ ቅርንጫፍ ቢሮዎች እየተሸጠ ይገኛል፡፡ አቅራቢያዎ በሚገኘው የኅብረት ሥራ ማህበሩ ቅርንጫፍ ቢሮ ጎራ በማለት መፅሀፉን ገዝተው ያንብቡ፡፡