A+ Tutorial Class Official
16.8K subscribers
122 photos
4 videos
47 files
9 links
Download Telegram
ሰላም የተከበራችሁ የA+ ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ🤗

በA+ Tutorial Class ከዕለት ወደ ዕለት የሚቀላቀሉን ተማሪዎች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል። ስለዚህም አዳዲስ ተማሪዎች እንዲሁም እናንተ ውስጥ ያላችሁት መከታተል የምትፈልጉትን ኮርስ እንዲሁም ሌሎች ነገሮችን በቀላሉ Search በማድረግ ማግኘት የምትችሉበትን ቀለል ያለ መንገድ አመቻችተንላችኃል። ከታች ከሚገኘው መከታተል የፈለጋችሁትን hashtag (#) ያለበትን ቃል በመንካት ማግኘት ትችላላችሁ።

1. የA+ Tutorial Class የመጀመሪያው Well Come message እና መግቢያ ለማግኘት
📑 #intro

2. የA+ Tutorial Class መማሪያ Schedule ለማግኘት
📑 #Schedule

3. ለተከታታይ ቀናት "ትምህርታዊ ልዕቀት" በሚል ርዕስ የተሰጠውን ስልጠና ለማግኘት
📑 #AcademicExcellence

4. የCommunicative English Skill I Course Tutorialኦችን ለማግኘት
📑 #CommunicativeEng

5. የMathematics Course ለማግኘት
📑 #Math

6. የLogic and Critical Thinking Course ለማግኘት
📑 #Logic

7. የAnthropology Course ለማግኘት
📑 #Anthro

8. የGeneral Psychology Course ለማግኘት
📑 #Psycho

9. የGeneral Physics Course ለማግኘት
📑 #General_Physics

10. የዩኒቨርስቲ ሲነየር ተማሪዎችን የህይወት ተሞክሮ እና ምክር ለማግኘት
📑 #LifeSharing

መልካም ጊዜ🤗

ስኬትዎ ከA+ ጋር የተረጋገጠ ነው!
©A+ Tutorial Class
👍6327👏15🤔10🔥9🥰7😁7🤯1😱1😢1
📚 ምክር ለሚስኪን ወንድ ተማሪዎች
#LifeSharing

በተለይ ግቢ መግባት ስልጣኔ ለሚመስላቹህ

📚 ወንድሞቼ ግቢ ስትገቡ የተለያዩ አይነት ተማሪዎች ጋር ልትጃለሱ ትችላላቹህ ፤ ከነዛም ውስጥ የተወሰኑ ተማሪዎች ችግር ሊኖርባቸው ይችላል ።
ችግሮቹ ደግሞ እንደየ ሁኔታው ይለያያሉ
ለማንኛውም የግቢ ችግር በብዛት መንስዔው ጓደኛ ስለሆነ እባካቹህ ጓደኛ ስትጎዳኙ ጠንቀቅ በሉ።

★ጓደኛህ ባንተ ተፅዕኖ ስር ይሁን እንጂ አንተ በጓደኛህ ተፅዕኖ ስር እንዳትወድቅ ★

📚ብዙ ፍሬሽ ወንዶች ግቢ ሲገቡ ቺክ ማሯሯጥ፣መጠጥ ቤት መሄድ ፣ ጫት ምናምን መጀማመር እና ግሩፕ ፈጥሮ መኮፈስ የመሳሰሉት ችግሮች በይበልጥ ይስተዋሉባቸዋል ።

📚 በምንም ምክንያት እንደዚህ አይነት ድርጊቶች ላይ ዘው ብላቹህ አትግቡ በተለይ መጠጥ ቤት ፣ ጭፈራ ቤት ፣ parry ምናምን አትሂዱ ። most students ወደ እነዚህ ቆሻሻ ቦታዎች የሚሄዱት በራሳቸው አነሳሽነት ሳይሆን በጓደኛ ግፊት ነው ሼም ነገር ይዟቸው ማለት ነው፥ ስለሆነም ሼም ምናምን ብሎ ነገር ከቶ ዝር እንዳይልባቹህ በኋላ የሚደርስባችሁን ችግር ለሰከንድ እንኳ ላይጋሩላቹህ ይችላሉ የfake ጓደኞች ...

📚 አንዳንድ ተማሪዎች መጠጥ ቤት ወይም ጭፈራ ቤት አንሄድም ብለው ከገገሙ አዛኝ መሳይ ጓደኞች " አይዞህ እኛ ብቻ ነን ምንጠጣው አንት ከፈለክ ሚሪንዳ ትጠጣለህ " በማለት እንድትሄዱ ይጎተጉቷቹሃል አንዳንድ የዋሆች ከጓደኛዬ አልለይም በማለት ጭፈራ ቤት ድረስ ተከትለዋቸው ይሄዳሉ ።< ጭፈራ ቤት ሂዳቹህ መጠጥ አለመጠጣታችሁን አትዩ መጠጡን ባትጠጡ እንኳ ከመጠጡ ጋር ምን እንደሚቀርብላቹህ አታቁም ።

📚 ይሄን የምላቹህ ለማካበድ or ለማስፈራራት ሳይሆን ጉዳዩን በትኩረት እንድታዩት ነው በኋላ የሚመጣውን መዘዝ መቋቋም አትችሉም።

📚 አስቡት እስቲ ወንድ ልጅ ተደፈረ የሚል ዜና መስማት እንዴት እንደሚያስደነግጥ?(የሴት ልጅ መድፈር እንኳ በዚህ ዘመን አስደንጋጭ ነው)

📚 አዲስ አበባ አካባቢ የምትኖሩ ልጆች ለጆሯቹህ አዲስ ይሆንባቹሃል ብዬ አልስብም ምክንያቱም ከየትኛውም የሀገራችን ክፍል ግብረሰዶማውያን በቁጥር በብዛት ስለሚገኙ ማለቴ ነው፤
ስለዚህ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲና ሌሎች በጣም ከተሜነት የሚንፀባርቅባቸው ግቢዎች የምትገቡ ተማሪዎች ብዙ አትንቀልቀሉ ፤ አንድ ሴሚስተር እንኳ በቅጡ የማታውቁትን ጓደኛ ከልክ በላይ አትመኑ ( በማይረባ ጥቅም ይሸጧቹሃል )
🔳 የሚያሳዝነው ግን የአዲስ አበባ ልጆችም ግቢ ሲገቡ ይሸወዳሉ ፥መሸወዳቸው ብዙም አይገርመኝም ምክንያቱም አራዳ ናቹህ ሲባሉ እውነት ስለሚመስላቸው 😎😋

አዲስ አበባ እኮ
📌 ታክሲ ላይ ምናምን ሁለት ወንዶች ባልና ሚስት ነን ብለው ....
📌 ህፃናት ወንድ ተማሪዎች ትምህርት ቤት ውስጥ ተደፈሩ የሚባልበት ከተማ እኮ ነው
📌 ግብረ ሰዶማውያን በይፋ መብታችን ይከበር የሚሉበት ከተማ እኮ ናት
📌 Parry ደግሰው ብዙ ግፍ የሚሰሩበት
📌 ሌላም ብዙ ለመናገር የሚቀፉ ድርጊቶች የሚፈፀሙባት ሃገር ናት ።
So በጣም ተጠንቀቁ

እና መፍትሄው ምን ይመስልሃል ?

📚 እኔ እንደሚመስለኝ መፍትሄው ሀይማኖተኛ መሆን ነው ፤ ለሴሚስተርም ቢሆን ሀይማኖታቹህ ላይ ፅኑ ምክንያቱም የትኛውም እምነት ወደ መጥፎ ቦታ አያመላክትምና ።
በተረፈ ፈጣሪ ይጠብቃቹህ/ይጠብቀንም

📚 ይሄን ፅሁፍ እንድፅፍ ያነሳሳኝ አንዲት እህታቹህ ከሆነ ቻናል ላይ ያገኘችውን አሳዛኝ ታሪክ ለወንድሞቼ ምከርልኝ ብላኝ ነው ።
እስቲ ታሪኩንም አንብቡት👇
👍49👏1
"ስሜ ቴዲ ይባላል የምኖረው እዚሁ አ.አ ነው፡፡ የሳሪስ ሰፈር ልጅ ነኝ፡፡
#LifeSharing

📚 ከትምህርቴ ውጪ ለሌላ ነገር ጊዜ ኖሮኝ አያውቅም ነገር ግን በህይወቴ በሰራውት ትንሽዬ ስህተት ማንነቴን አጣሁት 😞

📚 የመጀመሪያ አመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ እያለው ነበር የክፍል ጓደኛችን የልደት party አዘጋጅቶ ስለጠራኝ ሽክ ሽብርቅ ብዬ የሄድኩት፡፡ ወደቤታቸው ስገባ ቤቱ ውስጥ ካሉት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ልጆች የተለያዩ ጪሳጪሶችን ያጨሳሉ፡፡ አብዛኞቹ የማውቃቸው የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሲሆኑ ትንንሽ የሃይስኩል ተማሪዎችም አሉበት፡፡ ሁኔታው ደስ ስላላለኝ ወደቤቴ መሄድ እንዳለብኝ ለባለልደቱ ነገርኩት፡፡ ቢያንስ ኬክ ብቻ በልቼ እንድሄድ አግባባኝና ትንሽ ቆየው፡፡ ኬኩ ተቆረሰ ለሁላችንም ተሰጠን፡፡ ኬኩን እየበላው ስስቅ ይታወቀኛል፡፡

📚 ከዛ በኀላ ግን የሆነውን ምንም ነገር አላስታውስም፡፡ ከገባውበት ሰመመን ስነቃ አጠገቤ ሁለት ጎረምሶች ተኝተዋል፡፡ በጣም ደንግጬ ለመነሳት ስሞክር የህመም ስሜት ተሰማኝ ፡ ተደፍሬ ነበር፡፡

ኬኩ ውስጥ ዕፅ ሊኖርበት እንደሚችል አሰቡክ ለረጅም ሰዐት መሳቄን ብቻ ነበር ማስታውሰው..

📚 ለረዥም ደቂቃዎች በስርዓት ማሰብ አልቻልኩም ነበር እየተረጋጋው ወደአዕምሮዬ ስመለስ አጠገቤ የነበሩት ልጆች በሩን ዘግተው እየወጡ ነበር፡፡ ውስጤ ጩህ ጩህ ይለኝ ነበር ብዙ ነገር ማውራት እየፈለኩ አንደበቴ ተሳሰረ፡፡ ህይወቴን ያመሰቃቀሉትን ሰዎች ምንም መናገር ሳልችል ከአይኔ በሚወርድ እንባ ብቻ ሸኘዋቸው፡፡ ህይወቴን ጠላዋት፡፡ መኖር አስጠላኝ፡፡ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራገባኝ፡፡ ተነስቼ እራሴን አስተካክዬ ከህመሜ ጋር እየታገልኩ ልብሴን ለባብሼ ካለውበት ክፍል ወጣው፡፡ አሁን ስሙን የማልነግራችሁ ትልቅ ሆቴል ውስጥ ነበርኩ፡፡ ቀስ እያልኩ ትልቁን መንገድ ተሻግሬ ታክሲ ይዤ ወደቤቴ ሄድሁ፡፡

📚 የደረሰብኝን የስነልቦናም ሆነ አካላዊ ጉዳት ለማንም ትንፍሽ ማለት አልቻልኩም፡፡ ካለሁበት ማህበረሰብና ተወልጄ ካደኩበት የክርስቲያን ቤተሰብ አንፃር ይህን ደፍሮ መናገር የማይታሰብ ነበር፡፡ ከአንድ ሳምንትና ከተወሰኑ ቀናት በኻላ ትምህርት ቤት ሄድኩ፡፡ ትምህርት አስጠልቶኛል፡፡ ሁሉም ነገር አስጠልቶኛል፡፡ በህይወቴ ላይ ያ ነገር ከተፈጠረ ቀን ጀምሮ ደግሞ በተደጋጋሚ የህመም ስሜት ይሰማኝ ነበር፡፡ የምግብ Appetite አልነበረኝም፡፡

ከቤተክርስቲያን መሪዎች ለአንዳቸው ላወጋ ፈለኩ ግን comfort አልተሰማኝም ይልቁንም ስጋት ሆነብኝ ...
ለማን
እንዴት
ወዴት ሄጄ ልተንፍስ

📚 እንደዚህ ባለ ሁኔታ ተጠላልፌ ራሴን ማግኘቴ ማይታመን ህልም ይመስለኝ ጀመር፡፡ ብቻ ክፍል በሚያስጠላ ሞራል ገብቼ ስወጣ ልደቱ ላይ ጋብዞኝ የነበረው ልጅ ከሁለቱ ጎረምሶች ጋር በመምጣት ይቅርታ ሊጠይቀኝ ሞከረ፡፡ አብረውት የነበሩትም ልጆች እያግባቡኝ ያለውበትን ሁኔታና ስሜት ነገሩኝ፡፡ ከእነሱ ጋር በድጋሚ ያንን ሰይጣናዊ ድርጊት ካልፈፀምኩ በውስጤ ትል እንደሚፈጠርና ያ ትል ካንሰር ሊያሲዘኝ እንደሚችል አወሩኝ፡፡ በሰዓቱ እየተሰማኝ ለነበረው ህመምም መድሃኒት ሊሆን የሚችለው ከእነሱ ጋር በድጋሚ ማደር ብቻ እንደሆነ ነግረውኝ አታስብ ቀስ በቀስ ትለምደዋለህ አታካብድ ብዙ የምታውቃቸው ስላሉ simple ነው ቀለሜ ብለው አላግጠውብኝ ሄዱ፡፡

📚 ዶርም ሄጄ ከህመሜ ጋር እየታገልኩ ስለነገሩኝ ነገር ማሰብ ጀመርኩ "የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም ነውና ተረቱ" ከህመሜ ከገላገሉኝ ብዬ ስልኬን አውጥቼ ደወልኩላቸው፡፡ በህይወቴ የሰራውት ሁለተኛው ትልቁ ስህተቴ ነበር፡፡

📚 ከዛን ቀን ጀምሮ ህመሜን ለማስታገስ እያልኩ የገባውበት ልምምድ ህይወቴን አመሰቃቀለው፡፡ ብዙ ተላመድኩት፡፡ ከዩኒቨርስቲ ጓደኞቼ አንስቶ ከውጪ ከሚመጡ የሌላ ሀገር አምባሳደሮች ጋር ጊዜ ማሳለፍ ጀመርኩ፡፡ ያለሁበት ሁኔታ እያስጠላኝ ተላመድኩት፡፡

እባካቹሁ ከዚህ እስራት መፈታት እፈልጋለሁ፡፡ በፀሎትም እርዱኝ❗️

እውነት እላችኋለሁ ይህን ስፅፍላችሁ የቀድሞው ማንነቴን በመናፈቅ ነው..."

፠የወንድማችን ታሪክ እንዳነበባችሁት ነው፡፡ ስሙና ሰፈሩ ብቻ ነው የተቀየረው ሌላው እንደወረደ ነው፡፡ ይህን ያደረግነው ለባለታሪካችን ምስጢር ጠባቂነት ስንል ነው፡፡

📚 ይህን አሳዛኝ ታሪክ ለአዲስ እና ነባር የግቢ ተማሪዎች ️መማሪያ ይሆን ዘንድ አንዲት እህታችን ናት ለወንድሞቼ አድርሱልኝ ብላ የላከችልን ።

© A+ Tutorial Class.
😢63👍28😱14🤯8🤮73
#Repost

ሰላም የተከበራችሁ የA+ ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ🤗

በA+ Tutorial Class ከዕለት ወደ ዕለት የሚቀላቀሉን ተማሪዎች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል። ስለዚህም አዳዲስ ተማሪዎች እንዲሁም እናንተ ውስጥ ያላችሁት መከታተል የምትፈልጉትን ኮርስ እንዲሁም ሌሎች ነገሮችን በቀላሉ Search በማድረግ ማግኘት የምትችሉበትን ቀለል ያለ መንገድ አመቻችተንላችኃል። ከታች ከሚገኘው መከታተል የፈለጋችሁትን hashtag (#) ያለበትን ቃል በመንካት ማግኘት ትችላላችሁ።

1. የA+ Tutorial Class የመጀመሪያው Well Come message እና መግቢያ ለማግኘት
📑 #intro

2. የA+ Tutorial Class መማሪያ Schedule ለማግኘት
📑 #Schedule

3. ለተከታታይ ቀናት "ትምህርታዊ ልዕቀት" በሚል ርዕስ የተሰጠውን ስልጠና ለማግኘት
📑 #AcademicExcellence

4. የCommunicative English Skill I Course Tutorialኦችን ለማግኘት
📑 #CommunicativeEng

5. የMathematics Course ለማግኘት
📑 #Math

6. የLogic and Critical Thinking Course ለማግኘት
📑 #Logic

7. የAnthropology Course ለማግኘት
📑 #Anthro

8. የGeneral Psychology Course ለማግኘት
📑 #Psycho

9. የGeneral Physics Course ለማግኘት
📑 #General_Physics

10. የዩኒቨርስቲ ሲነየር ተማሪዎችን የህይወት ተሞክሮ እና ምክር ለማግኘት
📑 #LifeSharing

መልካም ጊዜ🤗

ስኬትዎ ከA+ ጋር የተረጋገጠ ነው!
©A+ Tutorial Class
👍7221🥰13🤔10😁8👏5🤯5🔥3😢1🎉1

👍11320🔥12🥰11👏11😁11🤔11🎉7🤯1😢1💩1