Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ
75K subscribers
7.88K photos
395 videos
18 files
17.4K links
አል-አይን የአማርኛ ዜና ድረ-ገፅ ሲሆን ፖለቲካዊ፡ኢኮኖሚያዊና ስፖርታዊ ዜና በዓለምአቀፍ ደረጃ በተአማኒነት የሚያቀርብ አንዱ የአል-አይን ሚዲያ ፕላት ፎርም ኔትወርክ ነው፡
Download Telegram
በመተከል ዞን “ከጸረ ሠላም ኃይሎች” ጋር ሲሳተፉና ሲያብሩ የነበሩ 15 ግለሰቦች እጃቸውን ሰጡ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ወረዳዎች የጸረ ሰላም ኃይሎችን ተልዕኮ በመፈጸም ሲሳተፉ እና ሲተባበሩ የነበሩ 15 ግለሰቦች በሠላማዊ መንገድ እጃቸውን መስጠታቸውን የክልሉ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
በዞኑ የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት እየተካሄደ ባለው ውይይትና በተደረሰው የጋራ መግባባት በወምበራ ወረዳ 14 እንዲሁም በማንዱራ ወረዳ ደግሞ 1 በድምሩ 15 ግለሰቦች በሠላማዊ መንገድ እጃቸውን መስጠታቸው ነው የተገለጸው፡፡ የክልሉ መንግስት ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመሆን በዞኑ በተደጋጋሚ የሚፈጠሩ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት እየሰራ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የፌዴራልና የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች አካባቢውን ወደ ሠላማዊ ሁኔታ ለመመለስ እየሰሩ ነው ተብሏል፡፡
52 ግብጻውያን የኮሮና ምርመራ ውጤት ሳይዙ አዲስ አበባ ገቡ

የኮሮና ምርመራ ውጤት ሳይዙ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ግብጻውያን በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲቆዩ መደረጉን በአዲስ አበባ የግብፅ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡ግብጻውያኑ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ለ14 ቀናት ያህል ቆይተው ወደ ኩዌት ለመሄድ ነበር ብሏል ኢምባሲው፡፡https://am.al-ain.com/article/52-egyptians-who-don-t-hold-covid-19-free-certificate-quarantined-at-bole-airport
በኤጂያን ባህር የተነሳ የመሬት መንቀጥቀጥ ቱርክና ግሪክን አንቀጠቀጠ

በኤጂያን ባህር የተከሰተ ጠንካራ የመሬት መንቀጥቀጥ ቱርክና ግሪክ ደርሶ ህንጻዎች እንዲደረመሱ ምክንያት ሆኗል፤በፈረንጆቹ 1999 በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ በእዝመር ከ17ሺ በላይ ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል፡፡https://am.al-ain.com/article/earth-quake-erupted-at-aegean-sea-cause-damage-in-greek-turkey
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 488 ሰዎች በኮሮና ሲያዙ 960 ሰዎች አገገሙ

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5866 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 488 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በዛሬው እለት 960 ሰዎች ሲያገግሙ 7 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
እስካሁን በአጠቃላይ 95,789 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህም 51713 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን የ 1,464 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።
ቴሌግራም https://web.telegram.org/#/im?p=@alainamharic
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
የታንዛኒያው ፕሬዘዳንት በድጋሚ ምርጫ ማሸነፋቸውን ምርጫ ኮሚሽን አስታወቀ
የታንዛኒያው ፕሬዘዳንት ጆን ማጉፉሊ አምስት አመት በስልጣን ለመቆየት የሚችሉበትን ሁለተኛ ዙር ምርጫ አሸንፈዋል፤ በውድድሩ ትልቅ ድል ቢያስመዘግቡም ተቃዋሚ ፓርቲው ምርጫው መጠነሰፊ ችግር ነበረበት እውነት የማይመስል ነው በማለት ተቃውመውታል፡፡
ማጉፉሊ12.5 ሚሊዮን ድምጽ ሲያገኙ ዋና ተቀናቃኛቸው የቻደማ ፓርቲ መሪ ቱንዱ ሊሱ 1.9 ሚሊዮን ድምጽ ማግኘታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ሁለተኛ ዙር ምርጫ ለማሸነፍ ማጉፉሊ ታላላቅ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን በመጨረስ ኢኮኖሚውን እንደሚያሳድጉ ቃል ገብተው ነበር፡፡
ሊሱ ቀደም ብለው የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበሉት ገልጸው ነበር፡፡
ቴሌግራም https://web.telegram.org/#/im?p=@alainamharic
መከላከያ ሚኒስቴር የትግራይ ክልል ስለሰራዊቱ ያወጣውን መግለጫ እንዲያርም ጠየቀ

ሚኒስቴሩ የትግራይ ክልል መንግስት “የሰራዊቱን ተልዕኮ ያላገናዘበ፣ ግዳጁንም ተንቀሳቅሶ እንዳይፈጽም የሚያስተጓጉል ሀገራዊና ክልላዊ ተግባሮቹንም በአግባቡ እንዳይወጣ የሚያደናቅፍ ሃላፊነት የጎደለው መግለጫ” ማውጣቱን ገልጿል፡፡

የትግራይ ክልል ከሰሞኑ “የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሃይሎች ተወያይተው ከሚያስቀምጧቸው ቀጣይ መፍትሄዎች ውጪ” የመከላከያ ሃይሎችን አደረጃጀትና ስምሪትን የተመለከቱ ወሳኔዎች“ተቀባይነትም ሆነ ተፈፃሚነት የላቸውም” ሲል መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ https://am.al-ain.com/article/ministry-of-defense-demands-tigray-region-to-correct-its-statement-issued-about-defense-force

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ማዕከላዊና ሰሜን ምዕራብ የተሰኙ ተጨማሪ ዕዞችን ማደራጀቱ ይታወቃል፡፡ዝርዝሩን ለማንበብ https://am.al-ain.com/article/ministry-of-defense-demands-tigray-region-to-correct-its-statement-issued-about-defense-force
የሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሥልጣን ለመልቀቅ ያነሱትን ሀሳብ ቀለበሱ

በተመድ እውቅና ያለው የሊቢያ መንግሰት ጠቅላይ ሚኒስትር ፋይዝ አልሳራጅ ከኃላፊነት ለመልቀቅ የወሰኑት ባለፈው መስከረም ወር ነበር፡፡https://am.al-ain.com/article/libya-s-un-recognized-government-pm-retracts-for-his-idea-of-resignation
በቅርቡ ግብፅን የጎበኙት የሱዳኑ አልቡርሃን ነገ አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሏል

አልቡርሃን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢትዮጵያ ግድብ ላይ ከሰጡትና ኢትዮጵያውያንን ካስቆጣው አስተያየታቸው በኋላ ወደ አዲስ አበባ የመጡ የመጀመሪያ መሪ ያደርጋቸዋል፡፡https://am.al-ain.com/article/sudanese-alburhan-to-visit-ethiopia-after-his-cairo-visit
ሁለቱ የታንዛኒያ መሪ ተቃዋሚዎች የምርጫውን ውጤት አንቀበልም አሉ

ሁለቱ የታንዛኒያ መሪ ተቃዋሚዎች በዛሬው እለት እንዳስታወቁት ለፕሬዘዳንት ጆን ማጉፉሊ ተጨማሪ የስልጣን ዘመን ያጎናጸፈውን የፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ውጤት እንደማይቀበሉት ተናግረዋል፡፡
የቻደማ ፓርቲ መሪ የሆኑት ፍሪማን ምብዌ በትዊተር ገጻቸው አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ እንደሚፈልጉ ጽፈዋል፡፡
ኢትዮጵያ የትራምፕ ንግግርን አስመልክቶ ዓለም አቀፍ የተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰብ ልትጀምር ነው

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የታላቁ ህዳሴ ግድብ በተመለከተ ባደረጉት ንግግር ላይ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰብ ልትጀምር መሆኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የድጋፍ አሰባሰብ ሥነ ስርዓቱ ዛሬ 10 ሰዓት ይጀምራል
ፕሬዚዳንት ትራምፕ እስራኤልና ሱዳን ዲፕሎማሲያዊ ግንኑነት መጀመራቸውን አስመልክቶ ከመሪዎቹ ጋር በስልክ ንግግር ባደረጉት ወቅት የሕዳሴ ግድብን ግብጽ ልታፈርሰው እንደምትችል ማውራታቸው ይታወሳል፡፡ ይህም ኢትጵያውያንን እና የኢትጵያን ወዳጆች ማስቆጣቱ ይታወሳል፡፡
የሕዳሴ ግድብ የሶስትዮች ድርድር ነገ ይቀጥላል

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ድርድር ነገ እንደሚቀጥል የሱዳን የመስኖ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በሦስቱ ሀገራት የውሃ ጉዳዮች ሚኒስትሮች ደረጃ ድርድር እንደገና እንደሚጀመር ገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ፣ሱዳንና ግብጽ መካከል ከሰሞኑ የተደረገው የሶስትዮሽ ድርድር ነገ ዳግም እንደሚጀመር ነው ካርቱም ያስታወቀችው፡፡

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ድርድር ከቀናት በፊት በወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር እና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲርል ራማፎዛ አነሳሽነት ከሰባት ሳምንታት በኋላ መጀመሩ ይታወሳል፡፡
በድርድሩ ሕብረቱ ድጋፍ እንደሚያደርግ ለተደራዳሪዎች ያረጋገጡት ራማፎዛ ቴክኒካዊ እና ህጋዊ ጉዳዮችን ጨምሮ ስምምነት ባልተደረሰባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ሀገራቱ እንደሚስማሙ ያላቸውን እምነት ገልጸው ነበር፡፡
በቱርክና በግሪክ ደሴት በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ 19 ሰዎች ሞቱ

በኤጊያን ባህር በተከሰተው 7.6 መጠን ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ 19 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ መንቀጥቀጡ ብዙ ህንጻዎች እንዲደረመሱና ንዝረቱ ወደ ወደብ ከተሞች መስፋፋቱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የመሬት መንቀጥቀጥ በተከሰተበት ወቅት በቱርኳ የወደብ ከተማ እዝመር ሰዎች በድንጋጤ ወደ መንገድ መውጣታቸውን ነዋሪዎች ገልጸው ነበር፤ አካባቢውም በፍርስራሽና በውሃ ተጥለቅልቆ ነበር በማለት የአይን እማኞች ለሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ህይወት የማዳን ስራው በተደረመሱ 17 ህንጻዎች ላይ መቀጠሉ ታውቋል፡፡