Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ
94.5K subscribers
8.39K photos
402 videos
18 files
19.4K links
አል-አይን የአማርኛ ዜና ድረ-ገፅ ሲሆን ፖለቲካዊ፡ኢኮኖሚያዊና ስፖርታዊ ዜና በዓለምአቀፍ ደረጃ በተአማኒነት የሚያቀርብ አንዱ የአል-አይን ሚዲያ ፕላት ፎርም ኔትወርክ ነው፡
Download Telegram
1495ኛው የነብዩ መሀመድ የልደት በዓል እየተከበረ ይገኛል

የ1495ኛው የነብዩ መሀመድ የልደት በዓል ወይንም መውሊድ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በኢትዮጵያ እየተከበረ ይገኛል፡፡

በዓሉ በተለይ በአዲስ አበባ በአኑዋር መስጅድ ሲከበር የሃማኖቱ ተከታዮችና እንግዶች በተገኙበት እየተከበረ ሲሆን በበዓሉ ላይ ሃይማኖታዊ መልእክቶች እየተላለፉ ነው፡፡ ሙሰሊሙ ህብረተሰብ ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ በየመስጅዱ በመሄድ በዓሉን እያከበረ ነው፡፡
የዘንድሮው የመውሊድ በዓል የኮሮና ወረርሽኝ ከተከሰተው ወዲህ ሲሆን የእምነቱ ተከታዮች ጥንቃቄ በማድረግ እንዲያከብሩ መልእክት ተላልፏል፡፡

አል ዐይን አማርኛ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ ይላል፤ መልካም በዓል፡፡
በሶማሌና አፋር ክልል አዋሳኝ ቦታ በተፈጠረ ግጭት የ27 ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል

ክልሉ እንደገለጸው በጠቅላላ የሞቱት 27 ሰዎች ሲሆኑ ከእነዚህ መካከል 10ሩ በትናንትናው እለት በሲቲ ዞን የሞቱ መሆናቸው ገልጿል፡፡https://am.al-ain.com/article/a-clash-that-erupted-at-somali-afar-border-claimed-life-27-people
1495ኛው የነብዩ መሃመድ የልደት በዓል ተከበረ

በአንዋር መጂጊድ በዓሉ ሲከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ “የሰው ልጅ የደስታ ቀኑን በተለያዩ መልኩ ያከብራል፤ እኛም ዛሬ ነብዩ መሃመድ የተወለዱበትን የደስታ ቀን ነው የምናከብረው”ብለዋል።https://am.al-ain.com/article/1495th-birthday-of-prophet-mohammed-marked-in-ethiopia
የሴኔጋል ፕሬዘዳንት መንግስታቸውን አፈረሱ

የሴኔጋሉ ፕሬዘዳንት ማኪይ ሳል ከ18 ወራት በኋላ 32 አባለት ያሉትን ጠንካራ የመንግስት ቡድን አፍርሰዋል፡፡
የፕሬዘዳንቱ ቃል አቀባይ አብዶ ላቲፍ ኩሊባሊ እንደተናገሩት ፕሬዘዳንቱ ለማፍረስ የሚያስችል ውሳኔ ቢያሳልፉም ለምን እንደሚያፈርሱና መቼ አዲሱን ካቢኔ እንደሚመሰርቱ አላሳወቁም፡፡
አዲስ መንግስት እስከሚዋቀር ድረስ ተሰናባች ሚኒስትሮችና የየግዛቶቹ ኃፊቀዎች ስራቸውን ማከናወናቸውን እንደሚቀጥሉ የፕሬዘዳንታዊው መግለጫ ጠቅሶ ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡ ሳል በተለመደ መልኩ የካቢኔ ስብሰባ የመሩ ሲሆን በሚያዚያ ወር የተዋቀረውን ካቢኔ ለማፍረስ ያላቸውን ፍላጎት አላሳዩም ነበር፡፡
በፈረንሳይ ኒስ ከተማ ሶስት ሰዎች በጩቤ ተወግተው ተገደሉ

በፈረንሳይ ኒስ ከተማ ሶስት ሰዎች ቤተክርስቲያን ውስጥ በጩቤ ተወግተው መገደላቸውን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
የከተማዋ ከንቲባ ክርስቲያን ኤስትሮሲ በመሀል ከተማው በሚገኘው ኖትሬ ዳም ቤተክርስቲያን ውስጥ የተፈጸመው ጥቃቱ የሽብር ድርጊት ስለመሆኑ ማስረጃዎች ያመለክታሉ ብለዋል፡፡
ተጠርጣሪው ጥቃቱን ከፈጸመ በኋላ ብዙም ሳይቆይ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ የፈረንሳይ ብሄራዊ የፀረ-ሽብር አቃቤ ህጎች የግድያ ምርመራ ከፍተዋል፡፡ ተጨማሪ ሰባት ሰዎችም መጎዳታቸውን ፍራንስ 24 ዘግቧል፡፡
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
“የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደራጅ ኮሚቴ” አመራሮች እና የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ዕርቅ ፈጸሙ

ሊቀ አእላፍ በላይ መኰንንን ጨምሮ “የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደራጅ ኮሚቴ” አመራሮች ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ ያስተላለፈውን እግድ አንስቷል፡፡
https://am.al-ain.com/article/leaders-of-the-oromia-church-organizing-committee-and-the-eo-church-reconcile
በሁለት ቀናት 6 ኪ.ግ ያህል ኮኬይን በቦሌ ኤርፖርት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት ጋር በመተባበር በዛሬው እለት ጥቅምት 19 ቀን 2013 ዓ.ም ወደ ዱባይ ሊጓዝ የነበረ 3.35 ኪሎ ግራም የሚመዝን ኮኬይን የተሰኘ አደገኛ ዕፅ በአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ተገለፀ፡፡
የፌደራል ፖለስ በፌስቡክ ገጹ እንደገለጸው ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ላይ ፣ የታይላንድ ዜግነት ያላት ተጠርጣሪ ከአዲስ አበባ ወደ ዱባይ ለመጓዝ ሻንጣዋን ስታስፈትሽ ነው አደገኛ ዕፁ እና ግለሰቧ በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡
ከትናንት በስቲያ ከምሽቱ አራት ሰዓት ደግሞ ከአዲስ አበባ ወደ ታይላንድ ባንኮክ ሊጓዝ የነበረ 2.6 ኪ.ግ የሚመዝን ኮኬይን የታይላንድ ዜግነት ካላት ተጠርጣሪ ጋር እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ተገልጿል፡፡ በድምሩ በሁለቱ ቀናት 5.95 ኪ.ግ. ኮኬይን ተይዟል፡፡
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሶማሌ ክልልን እና ድሬዳዋ ከተማን ጎብኝተዋል


በዛሬው ዕለት በሶማሌ ክልል የተለያዩ አካባቢዎችን የጎበኙት ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው በሶስት ፕሮጄክቶች ተከፋፍሎ የሚገነባውን የጎዴ ቀላፎ - ፈርፈር የመንገድ ፕሮጀክት ጨምሮ ከ300 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው እና ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት የተያዘላቸውን የመንገድ ፕሮጄክቶች ግንባታ አስጀምረዋል፡፡ ከጅግጅጋ - ገለልሽ የተገነባው 56 ኪ.ሜ መንገድም ተመርቆ ለአገልግሎት ተከፍቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ 2,000 ሄክታር የቆላ ስንዴ ሰብል የለማበትን የጎዴ የመስኖ ግድብን እና በሶማሌ ክልል አውባሬ ወረዳ የበርሃ አንበጣ ያደረሰውን ጉዳት እንዲሁም በወረዳው በ100,000 ሄ. መሬት ላይ የሚለማውን የስንዴ ማሳ ጎብኝተዋል፡፡
ከሶማሌ መልስ ወደ ድሬዳዋ ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ልዑካቸው በ150 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባውን የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ መርቀው ከፍተዋል።
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
አሜሪካ የኮሮና ተጠቂዎች ቁጥር እለታዊ ክበረወሰን ሰበረ

በአሜሪካ በትናንትናው እለት 91ሺ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ በሀገሪቱ ሲመዘገብ የነበረውን እልታዊ ክብረወሰን ሰብሯል፡፡ይህ ቁጥር የተመዘገበው በአሜሪካ በመጭው ማክሰኞ የሚካሄደው ምርጫ ሳምንት እየቀረው ነው፡፡

በቫይረሱ በከፍተኛ መጠን ከተጠቁት መካከል ኦሂዎ፣ ሚችጋን፤ኖርዝ ካሮሊና፣ፔኒስሊቫኒያና ዊስኮንሲን መሆናቸውን ሮተርስ ዘግቧል፡፡ እነዚህ ግዛቶች ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሁለተኛ የስልጣን ዘመን የሚያሸንፉበት ወይንም የዲሞክራቱ ተቀናቃኝ ዶ ባይደን የሚያሽንፉበትን የሚወስኑ ግዛቶች ናቸው፡፡ አሜሪካ በኮሮና ከተጠቁ ሀገራት ግንባር ቀደም ነች፡፡
የተራዘመው ምርጫው እስከ ሰኔ ይደረጋል ተባለ

ምርጫውን በግንቦት የመጨረሻዎቹ ሁለት ሳምንታት አልያም በሰኔ ወር የመጀመሪያ ሁለት ሳምንታት ለማካሄድ የመነሻ ሃሳብ አቀረበ፡፡የጤና ሚኒስቴር አሁን ላይ ያለሁ ሁኔታ ምርጫ ማከሄድ ያስችላል ማለቱን ተከትሎ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች እያከናወነ ይገኛል፡፡https://am.al-ain.com/article/extended-ethiopian-election-is-expected-to-be-held-until-june
ዩኬ በታሰረችው የዩኬና ኢራን ዜግነት ባለት ሰራተኛ ምክንያት የኢራንን አምባሳደር ጠራች
የዩናይትድ ኪንግደም መንግስት(ዩኬ) የዩናይትድ ኪንግደምና ኢራን ጥምር ዜግነት ባለው ናዛኒን ዛጋሪ ራትክሊፌ በተባለችው የእርዳታ ሰራተኛ እስር ምክንያት የኢራንን አምባሳደር መጥራቷን የውጭ ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል፡፡
የዩኬ ባለስልጣናት ለኢራኑ ዲፕሎማት ሃሚድ ቤይድነጃድ የናዛኒን ዛጋሪ ራትክሊፌ በደፈናው መታሰር እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል፡፡ የውጭ ገዱይ ቢሮው የታሳሪዋ አያያዝ ምክያታዊ ያልሆነና ተቀባይነት የሌለው መሆኑን መግለጻቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ዛጋሪ ራትክሊፌ በመጋቢት ወር የተለቀቀች ቢሆንም እንደገና በአዲስ ክስ በመስከረም ወር ታስራለች፡፡