Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ
75K subscribers
7.88K photos
395 videos
18 files
17.4K links
አል-አይን የአማርኛ ዜና ድረ-ገፅ ሲሆን ፖለቲካዊ፡ኢኮኖሚያዊና ስፖርታዊ ዜና በዓለምአቀፍ ደረጃ በተአማኒነት የሚያቀርብ አንዱ የአል-አይን ሚዲያ ፕላት ፎርም ኔትወርክ ነው፡
Download Telegram
መከላከያ ሚኒስቴር የትግራይ ክልል ስለሰራዊቱ ያወጣውን መግለጫ እንዲያርም ጠየቀ

ሚኒስቴሩ የትግራይ ክልል መንግስት “የሰራዊቱን ተልዕኮ ያላገናዘበ፣ ግዳጁንም ተንቀሳቅሶ እንዳይፈጽም የሚያስተጓጉል ሀገራዊና ክልላዊ ተግባሮቹንም በአግባቡ እንዳይወጣ የሚያደናቅፍ ሃላፊነት የጎደለው መግለጫ” ማውጣቱን ገልጿል፡፡

የትግራይ ክልል ከሰሞኑ “የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሃይሎች ተወያይተው ከሚያስቀምጧቸው ቀጣይ መፍትሄዎች ውጪ” የመከላከያ ሃይሎችን አደረጃጀትና ስምሪትን የተመለከቱ ወሳኔዎች“ተቀባይነትም ሆነ ተፈፃሚነት የላቸውም” ሲል መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ https://am.al-ain.com/article/ministry-of-defense-demands-tigray-region-to-correct-its-statement-issued-about-defense-force

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ማዕከላዊና ሰሜን ምዕራብ የተሰኙ ተጨማሪ ዕዞችን ማደራጀቱ ይታወቃል፡፡ዝርዝሩን ለማንበብ https://am.al-ain.com/article/ministry-of-defense-demands-tigray-region-to-correct-its-statement-issued-about-defense-force
የሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሥልጣን ለመልቀቅ ያነሱትን ሀሳብ ቀለበሱ

በተመድ እውቅና ያለው የሊቢያ መንግሰት ጠቅላይ ሚኒስትር ፋይዝ አልሳራጅ ከኃላፊነት ለመልቀቅ የወሰኑት ባለፈው መስከረም ወር ነበር፡፡https://am.al-ain.com/article/libya-s-un-recognized-government-pm-retracts-for-his-idea-of-resignation
በቅርቡ ግብፅን የጎበኙት የሱዳኑ አልቡርሃን ነገ አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሏል

አልቡርሃን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢትዮጵያ ግድብ ላይ ከሰጡትና ኢትዮጵያውያንን ካስቆጣው አስተያየታቸው በኋላ ወደ አዲስ አበባ የመጡ የመጀመሪያ መሪ ያደርጋቸዋል፡፡https://am.al-ain.com/article/sudanese-alburhan-to-visit-ethiopia-after-his-cairo-visit
ሁለቱ የታንዛኒያ መሪ ተቃዋሚዎች የምርጫውን ውጤት አንቀበልም አሉ

ሁለቱ የታንዛኒያ መሪ ተቃዋሚዎች በዛሬው እለት እንዳስታወቁት ለፕሬዘዳንት ጆን ማጉፉሊ ተጨማሪ የስልጣን ዘመን ያጎናጸፈውን የፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ውጤት እንደማይቀበሉት ተናግረዋል፡፡
የቻደማ ፓርቲ መሪ የሆኑት ፍሪማን ምብዌ በትዊተር ገጻቸው አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ እንደሚፈልጉ ጽፈዋል፡፡
ኢትዮጵያ የትራምፕ ንግግርን አስመልክቶ ዓለም አቀፍ የተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰብ ልትጀምር ነው

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የታላቁ ህዳሴ ግድብ በተመለከተ ባደረጉት ንግግር ላይ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰብ ልትጀምር መሆኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የድጋፍ አሰባሰብ ሥነ ስርዓቱ ዛሬ 10 ሰዓት ይጀምራል
ፕሬዚዳንት ትራምፕ እስራኤልና ሱዳን ዲፕሎማሲያዊ ግንኑነት መጀመራቸውን አስመልክቶ ከመሪዎቹ ጋር በስልክ ንግግር ባደረጉት ወቅት የሕዳሴ ግድብን ግብጽ ልታፈርሰው እንደምትችል ማውራታቸው ይታወሳል፡፡ ይህም ኢትጵያውያንን እና የኢትጵያን ወዳጆች ማስቆጣቱ ይታወሳል፡፡
የሕዳሴ ግድብ የሶስትዮች ድርድር ነገ ይቀጥላል

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ድርድር ነገ እንደሚቀጥል የሱዳን የመስኖ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በሦስቱ ሀገራት የውሃ ጉዳዮች ሚኒስትሮች ደረጃ ድርድር እንደገና እንደሚጀመር ገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ፣ሱዳንና ግብጽ መካከል ከሰሞኑ የተደረገው የሶስትዮሽ ድርድር ነገ ዳግም እንደሚጀመር ነው ካርቱም ያስታወቀችው፡፡

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ድርድር ከቀናት በፊት በወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር እና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲርል ራማፎዛ አነሳሽነት ከሰባት ሳምንታት በኋላ መጀመሩ ይታወሳል፡፡
በድርድሩ ሕብረቱ ድጋፍ እንደሚያደርግ ለተደራዳሪዎች ያረጋገጡት ራማፎዛ ቴክኒካዊ እና ህጋዊ ጉዳዮችን ጨምሮ ስምምነት ባልተደረሰባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ሀገራቱ እንደሚስማሙ ያላቸውን እምነት ገልጸው ነበር፡፡
በቱርክና በግሪክ ደሴት በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ 19 ሰዎች ሞቱ

በኤጊያን ባህር በተከሰተው 7.6 መጠን ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ 19 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ መንቀጥቀጡ ብዙ ህንጻዎች እንዲደረመሱና ንዝረቱ ወደ ወደብ ከተሞች መስፋፋቱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የመሬት መንቀጥቀጥ በተከሰተበት ወቅት በቱርኳ የወደብ ከተማ እዝመር ሰዎች በድንጋጤ ወደ መንገድ መውጣታቸውን ነዋሪዎች ገልጸው ነበር፤ አካባቢውም በፍርስራሽና በውሃ ተጥለቅልቆ ነበር በማለት የአይን እማኞች ለሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ህይወት የማዳን ስራው በተደረመሱ 17 ህንጻዎች ላይ መቀጠሉ ታውቋል፡፡
በቱርክ እና ግሪክ የመሬት መንቀጥቀጥ የሟቾች ቁጥር እየጨመረ ነው

መነሻውን በኤጂያን ባህር የቱርክ እና የግሪክ አዋሳኝ አካባቢ በማድረግ በተለይ በቱርክ ኢዝሚር ከተማ አርብ ዕለት በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ እስከ ትናንት ምሽት የሟቾች ቁጥር 39 መድረሱን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡ ከሟቾቹ 37ቱ በቱርክ ሁለቱ ደግሞ በግሪክ የተከሰተ መሆኑን የአካባቢው ባለስልጣናት ገልጸዋል፡፡
ቢያንስ በቱርክ 885 ሰዎች በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን የነፍስ አድን ሰራተኞች ከ 100 በላይ ሰዎችን ከፍርስራሽ ውስጥ በህይወት ማውጣታቸውን ዘገባው ያመለክታል፡፡
በኢዝሚር ከተማ 20 ህንጻዎች መፈራረሳቸውንም ነው ሲኤንኤን በዘገባው ያመለከተው፡፡
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
የሱዳኑ አልቡርሃን አዲስ አበባ ገቡ

ከሰሞኑ በካይሮ ጉብንት አድርገው የነበሩት የሱዳን የሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ዛሬ ኢትዮጵያ ገብተዋል፡፡ አል ቡርሃን ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
አል ቡርሃን በኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት በሚኖራቸው ቆይታ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በሁለትዮሽና በተለያዩ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡
ፎቶ ፋይል
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
የሕዳሴ ግድብ ድርድር በሚቀጥልበት በዛሬው ቀን አል-ቡርሃን ኢትዮጵያ ገብተዋል
የሱዳን የሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር አል-ቡርሃን በኢትዮጵያ የተለያዩ ስፍራዎችን የሚጎበኙ ሲሆን በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ የሚያደርጉት ውይይት ይጠበቃል፡፡
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በሕዳሴው ግድብ ላይ ኢትዮጵያን ያስቆጣ አስተያየት ከሰጡ በኋላ አል-ቡርሃን ቀድመው ግብፅን ጎብኝተዋል፡፡ https://am.al-ain.com/article/lt-gen-abdel-fattah-al-burhan-arrives-in-ethiopia-for-2-day-visit
ኮሮና እንግሊዝን ዳግም እገዳ እንድትጥል አስገደደ

ሰዎች ለተፈቀደላቸው ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ከቤታቸው እንዳይወጡ የ 4 ሳምንታት እገዳው ይከለክላል፡፡
ለሁለተኛ ጊዜ ያገረሸውን የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ሌሎች የተለያዩ የአውሮፓ ሀገራትም እገዳዎችን እየጣሉ ነው፡፡
https://am.al-ain.com/article/england-to-start-new-four-week-lockdown
በቱርክ የ 70 ዓመት አዛውንት ከ34 ሰዓታት በኋላ ከፍርስራሽ ውስጥ ወጡ

አርብ ዕለት የተከሰተውን የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ በቱርክ ኢዝሚር ከተማ እየተካሔደ ባለው የነፍስ አድን ስራ የ 70 ዓመት አዛውንት ከ34 ሰዓታት በኋላ ከፍርስራሽው ውስጥ መውጣታቸውን ዘ ናሺናል ዘግቧል፡፡
ቱርክን እና ግሪክን በመታው የመሬት መንቀጥቀጥ እስካሁን በትንሹ 60 ሰዎች መሞታቸው ሲረጋገጥ ከ900 በላይ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ከሟቾቹ 58ቱ ቱርካውያን ናቸው፡፡ የነፍስ አድን ስራው አሁንም የቀጠለ ሲሆን ከ100 በላይ ሰዎችን ከህንጻ ፍርስራሽ ውስጥ በህይወት ማውጣት ተችሏል፡፡
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 414 ሰዎች በኮሮና ሲያዙ 935 ሰዎች አገገሙ

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5,901 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 414 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በዛሬው እለት 935 ሰዎች ሲያገግሙ 9 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። 336 ሰዎች በጽኑ ታመዋል።
እስካሁን በአጠቃላይ 96,583 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህም 53,452 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን የ 1,478 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።