Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ
78.1K subscribers
7.99K photos
398 videos
18 files
17.7K links
አል-አይን የአማርኛ ዜና ድረ-ገፅ ሲሆን ፖለቲካዊ፡ኢኮኖሚያዊና ስፖርታዊ ዜና በዓለምአቀፍ ደረጃ በተአማኒነት የሚያቀርብ አንዱ የአል-አይን ሚዲያ ፕላት ፎርም ኔትወርክ ነው፡
Download Telegram
በሁለት ቀናት 6 ኪ.ግ ያህል ኮኬይን በቦሌ ኤርፖርት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት ጋር በመተባበር በዛሬው እለት ጥቅምት 19 ቀን 2013 ዓ.ም ወደ ዱባይ ሊጓዝ የነበረ 3.35 ኪሎ ግራም የሚመዝን ኮኬይን የተሰኘ አደገኛ ዕፅ በአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ተገለፀ፡፡
የፌደራል ፖለስ በፌስቡክ ገጹ እንደገለጸው ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ላይ ፣ የታይላንድ ዜግነት ያላት ተጠርጣሪ ከአዲስ አበባ ወደ ዱባይ ለመጓዝ ሻንጣዋን ስታስፈትሽ ነው አደገኛ ዕፁ እና ግለሰቧ በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡
ከትናንት በስቲያ ከምሽቱ አራት ሰዓት ደግሞ ከአዲስ አበባ ወደ ታይላንድ ባንኮክ ሊጓዝ የነበረ 2.6 ኪ.ግ የሚመዝን ኮኬይን የታይላንድ ዜግነት ካላት ተጠርጣሪ ጋር እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ተገልጿል፡፡ በድምሩ በሁለቱ ቀናት 5.95 ኪ.ግ. ኮኬይን ተይዟል፡፡
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሶማሌ ክልልን እና ድሬዳዋ ከተማን ጎብኝተዋል


በዛሬው ዕለት በሶማሌ ክልል የተለያዩ አካባቢዎችን የጎበኙት ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው በሶስት ፕሮጄክቶች ተከፋፍሎ የሚገነባውን የጎዴ ቀላፎ - ፈርፈር የመንገድ ፕሮጀክት ጨምሮ ከ300 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው እና ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት የተያዘላቸውን የመንገድ ፕሮጄክቶች ግንባታ አስጀምረዋል፡፡ ከጅግጅጋ - ገለልሽ የተገነባው 56 ኪ.ሜ መንገድም ተመርቆ ለአገልግሎት ተከፍቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ 2,000 ሄክታር የቆላ ስንዴ ሰብል የለማበትን የጎዴ የመስኖ ግድብን እና በሶማሌ ክልል አውባሬ ወረዳ የበርሃ አንበጣ ያደረሰውን ጉዳት እንዲሁም በወረዳው በ100,000 ሄ. መሬት ላይ የሚለማውን የስንዴ ማሳ ጎብኝተዋል፡፡
ከሶማሌ መልስ ወደ ድሬዳዋ ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ልዑካቸው በ150 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባውን የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ መርቀው ከፍተዋል።
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
አሜሪካ የኮሮና ተጠቂዎች ቁጥር እለታዊ ክበረወሰን ሰበረ

በአሜሪካ በትናንትናው እለት 91ሺ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ በሀገሪቱ ሲመዘገብ የነበረውን እልታዊ ክብረወሰን ሰብሯል፡፡ይህ ቁጥር የተመዘገበው በአሜሪካ በመጭው ማክሰኞ የሚካሄደው ምርጫ ሳምንት እየቀረው ነው፡፡

በቫይረሱ በከፍተኛ መጠን ከተጠቁት መካከል ኦሂዎ፣ ሚችጋን፤ኖርዝ ካሮሊና፣ፔኒስሊቫኒያና ዊስኮንሲን መሆናቸውን ሮተርስ ዘግቧል፡፡ እነዚህ ግዛቶች ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሁለተኛ የስልጣን ዘመን የሚያሸንፉበት ወይንም የዲሞክራቱ ተቀናቃኝ ዶ ባይደን የሚያሽንፉበትን የሚወስኑ ግዛቶች ናቸው፡፡ አሜሪካ በኮሮና ከተጠቁ ሀገራት ግንባር ቀደም ነች፡፡
የተራዘመው ምርጫው እስከ ሰኔ ይደረጋል ተባለ

ምርጫውን በግንቦት የመጨረሻዎቹ ሁለት ሳምንታት አልያም በሰኔ ወር የመጀመሪያ ሁለት ሳምንታት ለማካሄድ የመነሻ ሃሳብ አቀረበ፡፡የጤና ሚኒስቴር አሁን ላይ ያለሁ ሁኔታ ምርጫ ማከሄድ ያስችላል ማለቱን ተከትሎ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች እያከናወነ ይገኛል፡፡https://am.al-ain.com/article/extended-ethiopian-election-is-expected-to-be-held-until-june
ዩኬ በታሰረችው የዩኬና ኢራን ዜግነት ባለት ሰራተኛ ምክንያት የኢራንን አምባሳደር ጠራች
የዩናይትድ ኪንግደም መንግስት(ዩኬ) የዩናይትድ ኪንግደምና ኢራን ጥምር ዜግነት ባለው ናዛኒን ዛጋሪ ራትክሊፌ በተባለችው የእርዳታ ሰራተኛ እስር ምክንያት የኢራንን አምባሳደር መጥራቷን የውጭ ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል፡፡
የዩኬ ባለስልጣናት ለኢራኑ ዲፕሎማት ሃሚድ ቤይድነጃድ የናዛኒን ዛጋሪ ራትክሊፌ በደፈናው መታሰር እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል፡፡ የውጭ ገዱይ ቢሮው የታሳሪዋ አያያዝ ምክያታዊ ያልሆነና ተቀባይነት የሌለው መሆኑን መግለጻቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ዛጋሪ ራትክሊፌ በመጋቢት ወር የተለቀቀች ቢሆንም እንደገና በአዲስ ክስ በመስከረም ወር ታስራለች፡፡
በመተከል ዞን “ከጸረ ሠላም ኃይሎች” ጋር ሲሳተፉና ሲያብሩ የነበሩ 15 ግለሰቦች እጃቸውን ሰጡ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ወረዳዎች የጸረ ሰላም ኃይሎችን ተልዕኮ በመፈጸም ሲሳተፉ እና ሲተባበሩ የነበሩ 15 ግለሰቦች በሠላማዊ መንገድ እጃቸውን መስጠታቸውን የክልሉ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
በዞኑ የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት እየተካሄደ ባለው ውይይትና በተደረሰው የጋራ መግባባት በወምበራ ወረዳ 14 እንዲሁም በማንዱራ ወረዳ ደግሞ 1 በድምሩ 15 ግለሰቦች በሠላማዊ መንገድ እጃቸውን መስጠታቸው ነው የተገለጸው፡፡ የክልሉ መንግስት ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመሆን በዞኑ በተደጋጋሚ የሚፈጠሩ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት እየሰራ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የፌዴራልና የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች አካባቢውን ወደ ሠላማዊ ሁኔታ ለመመለስ እየሰሩ ነው ተብሏል፡፡
52 ግብጻውያን የኮሮና ምርመራ ውጤት ሳይዙ አዲስ አበባ ገቡ

የኮሮና ምርመራ ውጤት ሳይዙ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ግብጻውያን በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲቆዩ መደረጉን በአዲስ አበባ የግብፅ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡ግብጻውያኑ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ለ14 ቀናት ያህል ቆይተው ወደ ኩዌት ለመሄድ ነበር ብሏል ኢምባሲው፡፡https://am.al-ain.com/article/52-egyptians-who-don-t-hold-covid-19-free-certificate-quarantined-at-bole-airport
በኤጂያን ባህር የተነሳ የመሬት መንቀጥቀጥ ቱርክና ግሪክን አንቀጠቀጠ

በኤጂያን ባህር የተከሰተ ጠንካራ የመሬት መንቀጥቀጥ ቱርክና ግሪክ ደርሶ ህንጻዎች እንዲደረመሱ ምክንያት ሆኗል፤በፈረንጆቹ 1999 በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ በእዝመር ከ17ሺ በላይ ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል፡፡https://am.al-ain.com/article/earth-quake-erupted-at-aegean-sea-cause-damage-in-greek-turkey
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 488 ሰዎች በኮሮና ሲያዙ 960 ሰዎች አገገሙ

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5866 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 488 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በዛሬው እለት 960 ሰዎች ሲያገግሙ 7 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
እስካሁን በአጠቃላይ 95,789 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህም 51713 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን የ 1,464 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።
ቴሌግራም https://web.telegram.org/#/im?p=@alainamharic
#አል_ዐይን_ዜና #AlAinAmharic
#ዐይንዎት_በዓለም_ላይ_ነው
የታንዛኒያው ፕሬዘዳንት በድጋሚ ምርጫ ማሸነፋቸውን ምርጫ ኮሚሽን አስታወቀ
የታንዛኒያው ፕሬዘዳንት ጆን ማጉፉሊ አምስት አመት በስልጣን ለመቆየት የሚችሉበትን ሁለተኛ ዙር ምርጫ አሸንፈዋል፤ በውድድሩ ትልቅ ድል ቢያስመዘግቡም ተቃዋሚ ፓርቲው ምርጫው መጠነሰፊ ችግር ነበረበት እውነት የማይመስል ነው በማለት ተቃውመውታል፡፡
ማጉፉሊ12.5 ሚሊዮን ድምጽ ሲያገኙ ዋና ተቀናቃኛቸው የቻደማ ፓርቲ መሪ ቱንዱ ሊሱ 1.9 ሚሊዮን ድምጽ ማግኘታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ሁለተኛ ዙር ምርጫ ለማሸነፍ ማጉፉሊ ታላላቅ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን በመጨረስ ኢኮኖሚውን እንደሚያሳድጉ ቃል ገብተው ነበር፡፡
ሊሱ ቀደም ብለው የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበሉት ገልጸው ነበር፡፡
ቴሌግራም https://web.telegram.org/#/im?p=@alainamharic