Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ
83.5K subscribers
8.08K photos
398 videos
18 files
18.1K links
አል-አይን የአማርኛ ዜና ድረ-ገፅ ሲሆን ፖለቲካዊ፡ኢኮኖሚያዊና ስፖርታዊ ዜና በዓለምአቀፍ ደረጃ በተአማኒነት የሚያቀርብ አንዱ የአል-አይን ሚዲያ ፕላት ፎርም ኔትወርክ ነው፡
Download Telegram
የሰው ህይወት በቀጠፈው የሲንጋፖር አየርመንገድ አውሮፕላን ችግር ምንድን ነው?

ከለንደን የተነሳውና መዳረሻውን ሲንጋፖር ያደረገው ቦይንግ 777 አውሮፕላን በባንኮክ በድንገት ለማረፍ ተገዷል።

የሲንጋፖር አየርመንገድ ንብረት የሆነው አውሮፕላን 211 መንገደኞችና 18 የበረራ ቡድን አባላትን አሳፍሮ ነበር ተብሏል።

ከለንደን ከተነሳ ከ11 ስአት በኋላ ሲበርበት ከነበረው 37 ሺህ ጫማ ከፍታ በአምስት ደቂቃ ውስጥ ወደ 31 ሺህ ጫማ መውረዱን የፍላይትራዳር መረጃ ያመለክታል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመለክቱ፤ https://bit.ly/4dNtKu8
የ14 አመት እስር የተፈረደባቸው ሩሲያዊ የሃይፐርሶኒክ ሚሳይል ሳይንቲስት ማን ናቸው?

በሩሲያ የሃይፐርሶኒክ ሚሳይል ማበልጸግ ወሳኝ ሚና የነበራቸው ሩሲያዊው የፊዚክስ ባለሙያ አናቶሊ ማስሎቭ በሀገር ክህደት ወንጀል ተከሰው የ14 አመት እስር ተፈርዶባቸዋል ተብሏል።

የ77 አመቱ ማስሎቭ ክሳቸው በዝግ ችሎት ሲታይ ከቆየ በኋላ በሴንትፒተርስብግ ከተማ የሚገኝ ፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ እንደተላለፈባቸው ሮይተረስ ዘግቧል።

ማስሎቭ ጥፋተኛ አይደለሁም ሲሉ ፍርዱን ተቃውመዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመለክቱ፤ https://bit.ly/4azhKtg
በ5 ዓመት ውስጥ 107 ደቂቃዎች ብቻ ተጫውቶ 11 ዋንጫዎችን ማንሳት የቻለው ሲቲ ተጫዋች

የማንቸስተር ሲቲው ተጫዋች ስኮት ካርሰን በ5 ዓመት ውስጥ 107 ደቂቃዎች ብቻ ተጫውቶ 11 ዋንጫዎችን ማንሳት መቻሉ ተነግሯል።

ስኮት ካርሰን የማንቸስተር ሲቲ ተጠባባቂ ግብ ጠባቂ ሲሆን፤ ከማንቸስተር ሲቲ ጋር በቆየበት 5 የውድድር ዘመን ወደ ሜዳ ገብቶ የተጫወተው በ2 ጨዋታዎች ላይ ብቻ ነው ተብሏል።

ስኮት ካርሰን ማነቸስተር ሲቲን የተቀላቀለው በፈረንጆቹ 2019 ሲሆን፤ ወደ ሜዳ ገብቶ የተጫወተው ግን በ2020/21 እና በ2021/22 የውድድር ዘመን በሁለት ጨዋታዎች ላይ ብቻ ነው ተብሏል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመለክቱ፤ https://bit.ly/4bNvu4Q
ሩሲያ በዩክሬን ድንበር የታክቲካል ኒዩክሌር መሳሪያ ልምምድ ጀመረች

ልምምዱ ምዕራባውያን በዩክሬኑ ጦርነት ይበልጥ ጣልቃ እንዳይገቡ ለማስጠንቀቅ ያለመ ነው ተብሏል።

https://bit.ly/4bsMTQi
ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ ቀጣዩ የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ?

የቀያይ ሰይጣኖቹ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ቀጣይ እጣፈንታ ከኤፍ ኤ ካፕ የዋንጫ ጨዋታ በኋላ ይታወቃል ተብሏል።

https://bit.ly/3ypjMyK
የሻይ ጤና በረከቶች ምን ምን ናቸው?


ሻይ በዓለማችን ከውሀ ቀጥሎ በሰው ልጆች የሚወሰድ ምርት ይወሰዳል


ቻይና፣ሕንድ እና ኬንያ የዓለማችን ቀዳሚ ሻይ አምራች ሀገራት ናቸው


ተጨማሪ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://bit.ly/3Kc0XBR
ኖርዌይ ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና ሰጠች

ቴልአቪቭ ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና መስጠት ማለት ሀማስ እንዲፈረጥም መፍቀድ ማለት ነው ትላለች።
https://bit.ly/3VdZnpC
ኖርዌይ፣አየርላንድ እና ስፔን ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና እንደሚሰጡ አስታወቁ

ኖርዌ፣ ከእስራኤል ጋር ሰላም ይፈጥራል በሚል ተስፋ ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና እንደምትሰጥ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጆኔስ ጋህር ስቶሬ ባለፈው ረቡዕ እለት ተናግረዋል።

አየርላንድ እና ስፔንም ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና እንደሚሰጡ ሮይተርስ ዘግቧል።

https://am.al-ain.com/article/norway-ireland-recognizes-israel
ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ኔቶ የሩሲያን ሚሳኤል መትቶ እንዲጥል ጠየቁ


የኔቶ አባል ሀገራት በራሳቸው የአየር ክልል ሆነው የሩሲያን ሚሳኤል ቢመቱ ምንም ችግር አያመጣባችሁም ብለዋል


ፕሬዝዳንቱ አክለውም ሀገራቱ ባሉበት ሆነው በዩክሬን ሰማይ ላይ የሚገቡ የሩሲያን ሚሳኤል ምቱልን ሲሉ ጠይቀዋል

ተጨማሪ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://bit.ly/4bsK95I
በሳኡዲ አረቢያ ታሪካዊ የተባለ የፋሽን ትርኢት ተዘጋጀ

"እውነት ነው፤ ሀገሪቱ ወግ አጥባቂ ነች። ነገርገን የአረቡን አለም የሚወክል የሚያምር የመዋኛ ልብስ ፋሽን አዘጋጅተናል" ስትል ሞሮኳዊቷ ዲዛይነር ቁንዛል ተናግራለች።
https://am.al-ain.com/article/saudi-arabia-held-historic-swimsuit-fashion-show
የሚወደውን ክለብ ለመጥቀም በሚል ሶስት ተጫዋቾችን በቀይ ካርድ ያስወጣው ዳኛ የእድሜ ልክ እገዳ ተጣለበት


ዳኛው ከቀይ ካርዶቹ በተጨማሪ 15 ጭማሪ ደቂቃዎችንም ያላግባብ ጨምሯል ተብሏል


ዋንጫውን ካሸነፈው ክለብ ጋር አብሮ ሲጨፍር የታየው ይህ ዳኛ የተላለፈብኝ እገዳ የተጋነነ ነው ብሏል


ተጨማሪ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ👉https://bit.ly/44SDLC6
የሃማስ የፖለቲካ መሪው ኢስማኤል ሃኒየህ ቴህራን ገቡ።

ሃኒየህ ከኢራኑ ሃይማኖታዊ መሪ አያቶላህ አሊ ሃሚኒ ጋር በመገናኘትም በቀድሞው ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።

የሃማስ መሪው በዚሁ ወቅት ፍልስጤማውያን በኢራን ባለስልጣናት ህልፈት ጥልቅ ሀዘን ተሰምቷቸዋል ብለዋል።

የሩሲያ፣ ኢራቅ፣ ኩዌትን ጨምሮ ከ40 በላይ የተለያዩ ሀገራት ልኡካን በሄሊኮተር አደጋ ህይወታቸውን ባጡት የኢራን ባለስልጣናት የአስከሬሽን ሽኝት ላይ ለመገኘት ቴህራን ገብተዋል።

የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@alainnewsamharic
X (ትዊተር): https://twitter.com/AlAinAmharic
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic
በቦሌ አየር መንገድ አካባቢ የተከሰተው የእሳት አደጋ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር መዋሉን ኮሚሽኑ ገለጸ


የኢትጽያ አየር መንገድ ባወጣው አጭር መግለጫ አደጋው የተከሰተው ከአየር መንገዱ ቅጥር ግቢ ውጭ መሆኑን እና በቃጠሎው ምክንያት በረራ አለመስተጓጎሉን አስታውቋል።

https://am.al-ain.com/article/fire-around-bole-airport-extinguished
ቻይና በ12 የአሜሪካ ኩባንያዎች ላይ ማዕቀብ ጣለች

ሀገሪቱ ማዕቀቡን የጣለችው ለታይዋን የጦር መሳሪያ አቅርበዋል በሚል ነው

አሜሪካ ከሰሞኑ ለሩሲያ ድጋፍ አድርገዋል በሚል በቻይና ኩባንያዎች ላይ ተመሳሳይ ማዕቀብ ጥላለች

ተጨማሪ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://bit.ly/3wHLdn7
ሻይ በብዛት የሚጠጣባቸው ሀገራት

ከ10 ቱርካውያን ዘጠኙ ሻይ ጠጪ መሆናቸውን ጥናት አመላክቷል።

ቻይና፣ ህንድ፣ ኬንያ እና ሲሪላንካ ቀዳሚዎቹ ሻይ አምራች ሀገራት ናቸው።

ዜጎቻቸው በብዛት ሻይ ጠጪ የሆኑባቸው ሀገራትን በዝርዝር ይመልከቱ፦https://bit.ly/3WSKKJf
ኤችአይቪ ኤድስን ጨምሮ በግብረ ስጋ ግንኝነት የሚተላለፉ በሽታዎች ገዳይነት እየጨመረ ነው ተባለ

በእነዚህ በሽታዎች በአለም አቀፍ ደረጃ ከ2 ሚልየን በላይ ሰዎች ህይወት እያለፈ መሆንን የአለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።
https://bit.ly/3KfccJG
እድሜ እና ካንሰር ያልበገረው የትምህርት ፍቅር

የቀድሞ የአሜሪካ ወታደር የነበሩት የ90 ዓመት አዛውንት ሞትን እየተጠባበቁበት ባለው አልጋቸው ላይ ሁነው የሁለተኛ ደረጃ ዲፕሎማቸውን ተቀብለዋል። ለአላማ ጽናት እና መሰጠት በ90 አመቱ አዛውንት ላይ ተገልጦ ታይቷል ተብሎላቸዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4bRW9NZ
እስራኤል በሰባት ወራት ዘመቻ ከሐማስ ታጣቂዎች መካከል 35 በመቶውን ብቻ መግደሏ ተገለጸ

ሐማስ በሺዎች የሚቆጠሩ አዲስ ታጣቂዎችን እየመለመለ መሆኑን የአሜሪካ ስለላ ተቋም አስታውቋል

65 በመቶው የሐማስ ታጣቂዎች አሁንም እንዳሉ ተገልጿል

ተጨማሪ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://bit.ly/4avYtcj
አሜሪካና ሳኡዲ የኒዩክሌር ሃይልና የደህንነት ትብብር ስምምነት ለመፈራረም ተቃርበዋል

ሳኡዲ ግን ከእስራኤል ጋር ግንኙነቷን ማደስ የሚያስችለው ስምምነት ፍልስጤም ነጻ ሀገር ሆና የምትመሰረትበትን ሂደት በግልጽ ማካተት አለበት ብላለች።

https://bit.ly/44Wtvck
በኢራኑ ፕሬዝዳንት የቀብር ስነ ስርዓት ላይ የተገኙ የሀገራት መሪዎች እነማን ናቸው?

የ68 ሀገራት መሪዎች እና ከፍተኛ ባለስልጣናት ኢራን ገብተዋል።

https://bit.ly/3WOMgMJ