Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ
92.8K subscribers
8.31K photos
401 videos
18 files
19.1K links
አል-አይን የአማርኛ ዜና ድረ-ገፅ ሲሆን ፖለቲካዊ፡ኢኮኖሚያዊና ስፖርታዊ ዜና በዓለምአቀፍ ደረጃ በተአማኒነት የሚያቀርብ አንዱ የአል-አይን ሚዲያ ፕላት ፎርም ኔትወርክ ነው፡
Download Telegram
ብሪታንያ “የደም ቅሌት” ተብሎ ለሚጠራው ስህተት 12 ቢሊዮን ዶላር ካሳ ልትከፍል ነው፡፡

በ1970ዎቹ እና 1980ዎቹ በብሪታንያ ጤንነቱ ያልተጠበቀ ደም እና የደም ውጤቶች በህክምና ተቋማት ህክምና ፈልገው ለመጡ ሰዎች የተሰጠበት ክስተት “የደም ቅሌት” የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።

ለታካሚዎች የተሰጠው ደም በርካቶች በኤችአይቪ እና ጉበት በሽታ አምጪ ቫይረስ እንዲጠቁ ምክንያት ሆኖ ለውስብስብ የጤና ችግሮች እንደዳረጋቸው ዘግይቶ የተደረገ ምርመራ ማረጋገጡ የሚታወስ ነው።

ለንደን 30 ሺህ ገደማ ዜጎች ለተጎዱበትና 3 ሺህ ሰዎች ለሞቱበት “የደም ቅሌት” በፈረንጆቹ 2015 በይፋ ይቅርታ የጠየቀች ሲሆን፥ የሪሺ ሱናክ አስተዳደርም 12 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ካሳ ለመክፈል ማቀዱ ተዘግቧል።

ዝርዝሩን ያንብቡ፦ https://bit.ly/3URi4h8
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሃማስ መሪዎች የእስር ማዘዣ ወጣባቸው።

አለም አቀፉ የጦር ወንጀል ፍርድ ቤት በቤንያሚን ኔታንያሁ እና ኢስማኤል ሃኒየህ ላይ የእስር ማዘዣውን ያወጣው በጋዛ የንጹሃን ዜጎች ግድያ ተጠያቂ ናቸው በሚል ነው።

የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትሩ ዮቭ ጋላንት እና በጋዛ የሃማስ የፖለቲካ ክንፍ ሃላፊው ሀላፊ ያህያ ሲንዋር እና የቡድኑ ጦር አዛዥ መሀመድ አል ማስሪም የእስር ማዘዣው ወጥቶባቸዋል።

እስራኤልም ሆነች ሃማስ የጦር ወንጀሎችን እንዳልፈጸሙ በመጥቀስ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ፍርድ ቤት ያወጣውን የእስር ማዘዣ ውድቅ አድርገዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ያንብቡ፦ https://bit.ly/4axTCY2
ኢራን ለ5 ቀናት የሚቆይ የሀዘን ቀን አወጀች

ራይሲ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሆሴን አሚር አብሎላሂያን ባለፈው እሁድ በተራራማው የሰሜን ምዕራብ ኢራን በደረሰው የሄሊኮፕተር መጋጨት አደጋ ነበር ህይወታቸው ያለፈው።
https://bit.ly/44RNrgj
አሜሪካ በኔታንያሁ ላይ የእስር ማዛዣ ለማውጣት የሚደረገው ጥረት “አሳፋሪ” ነው አለች

ፕሬዝዳንት ባይደን አለማቀፉ የወንጀለኞች ፍርድቤት እስራኤልና ሃማስን በእኩል መመልከት የለበትም ሲሉ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል።

https://bit.ly/44Mpyqx
ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ የእስር ማዘዣ እንዲወጣባቸው ጥያቄ መቅረቡን ተቃወሙ

የአለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይሲሲ) በእሰራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር እና በሀማስ ከፍተኛ መሪዎች ላይ የእስር ማዘዣ እንዲያወጣ አቃቤው ለፍርድ ቤቱ ጥያቄ ማቀረባቸውን ይፋ አድርገዋል።
https://bit.ly/4awkvvB
አሜሪካ የኢራኑን ፕሬዝዳንት ህይወት ለቀጠፈው የሄሊኮፕተር አደጋ ለምን ድጋፍ ማቅረብ ተሳናት?

አሜሪካ የሄሌኮፕተር አደጋውን ተከትሎ “ከኢራን የድጋፍ ጥያቄ ቀርቦልኝ ነበር” ብላለች። አሜሪካ “በሄሌኮፕተር አደጋው ውስጥ እጇ የለበትም” በማለት አስታውቃለች።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመለክቱ፤ https://bit.ly/3UNwmzn
“ሰሜን ኮሪያ በሙዚቃ የስነልቦና ጦርነት አውጃብኛለች” - ደቡብ ኮሪያ

ሴኡል በቲክቶክ በርካቶች እየተቀባበሉት ያለውን ኪም ጆንግ ኡንን የሚያወድስ ሙዚቃ እንዳይታይ ወስናለች።

https://bit.ly/3QTp78a
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ ለምርጫ እንዳይወዳደሩ በፍርድ ቤት ታገዱ

ከ8 ቀናት በኋላ እንደሚካሄድ በሚጠበቀው ምርጫ የደቡብ አፍሪካው ዙማ የተቀላቀሉት አዲሱ ኤ ም ኬ ፓርቲ የራማፎሳን ኤ ኤን ሲ ፓርቲን የመገዳደደር አቅም እንዳለው ከፍተኛ ግምት አግኝቷል፡፡
https://bit.ly/3WP1Vvu
ከእስር ለማምለጥ ለ20 አመታት መስማት የተሳነው መስሎ የኖረው ቻይናዊ ተያዘ

ጎረቤቱን ገድሎ ከመኖሪያ ቀዬው የጠፋው ግለሰብ ያለፈ ታሪኩን ለመደበቅ በምልክት ቋንቋ ሲግባባ ቆይቷል።

https://bit.ly/4bCKCBY
መንገደኞችን የናጠው የሲንጋፖር አየርመንገድ አውሮፕላን ያለመዳረሻው ለማረፍ ተገዷል

211 ሰዎችን አሳፍሮ የነበረው አውሮፕላን በገጠመው ችግር አንድ መንገደኛ ህይወቱ ማለፉና 30 ሰዎች መቁሰላቸው ተገልጿል።

https://bit.ly/4dNtKu8
አሜሪካ ወታደራዊ አሰልጣኞችን ወደ ዩክሬን የመላክ እቅድ የለኝም አለች

ሩሲያ በፈረንጆቹ የካቲት 2022 በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ወታራዊ ዘመቻ ከማወጇ በፊት አሜሪካ ዩክሬን ውስጥ 150 ወታደራዊ አሰልጣኞች ነበሯት።
https://bit.ly/4auvKVj
በኬንያ የወንጀል ምጣኔ በ19 በመቶ መጨመሩ ተሰማ

በሀገሪቱ ያለው አስቸጋሪ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ለወንጀል መጨመር ዋነኛ ምክንያት ነው ተብሏል።
https://bit.ly/3wLHncI
የ14 አመት እስር የተፈረደባቸው ሩሲያዊ የሃይፐርሶኒክ ሚሳይል ሳይንቲስት ማን ናቸው?

የ77 አመቱ ማስሎቭ ክሳቸው በዝግ ችሎት ሲታይ ከቆየ በኋላ በሴንትፒተርስብግ ከተማ የሚገኝ ፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።
https://bit.ly/4azhKtg
በ5 ዓመት ውስጥ 107 ደቂቃዎች ብቻ ተጫውቶ 11 ዋንጫዎችን ማንሳት የቻለው ሲቲ ተጫዋች

ስኮት ካርሰን የተባለው የማንቸስተር ሲቲ ተጫዋች በ5 የውድድር ዘመን ውስጥ 2 ጊዜ ብቻ ሜዳ ገብቷል። ማንቸስተር ሲቲ የ2023/24 የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑ ይታወቃል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመለክቱ፤ https://bit.ly/4bNvu4Q
በ5 ዓመት ውስጥ 107 ደቂቃዎች ብቻ ተጫውቶ 11 ዋንጫዎችን ማንሳት የቻለው ሲቲ ተጫዋች

ስኮት ካርሰን የተባለው የማንቸስተር ሲቲ ተጫዋች በ5 የውድድር ዘመን ውስጥ 2 ጊዜ ብቻ ሜዳ ገብቷል። ማንቸስተር ሲቲ የ2023/24 የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑ ይታወቃል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመለክቱ፤ https://bit.ly/4bNvu4Q
ህጻናትን ከግጭት እና ጦርነት ዜናዎች ስነልቦናዊ ተጽእኖ እንዴት መጠበቅ እንችላለን?

የግጭት እና ጦርነት መረጃዎች በተደጋጋሚ በሚነገርባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ህጻናት ለጭንቀት፣ ፍርሀት እና ድብርት ሊጋለጡ ይችላሉ ተብሏል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመለክቱ፤ https://bit.ly/44VavL1
የኢራኑ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ የአስክሬን ሽኝት በመካሄድ ላይ ይገኛል

ኢራናዊያን ፕሬዝዳንታቸውን ለመሰናበት በአደባባይ ተገኝተዋል። በፕሬዝዳንት ራይሲ ላይ ተቃውሞ ያላቸው ዜጎች በፕሬዝዳንቱ ሞት መደሰታቸውን የሚገልጽ ምልክት ቢያሳዩ ጥብቅ ቅጣት ይጠብቃቸዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመለክቱ፤ https://bit.ly/4bi92AV
አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ከቼልሲ ጋር በስምምነት ተለያዩ

አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ከምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ጋር በጋራ ስምምነት መለያየታቸው ተሰምቷል።

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ እና አርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ ነው የተለያዩት።

በአሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ሲመራ የነበረው ቼልሲ የንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የ2023/24 የውድድር ዘመንን 6ኛ ደረጃን በመያዝ ነው ያጠናቀቀው።

አርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ እንደ አውሮፕያኑ አቆጣጠር ሐምሌ 1 ቀን 2023 ነበር ቼልሲን ለማሰልጠን የሁለት ዓመት ኮንትራት የተፈራረሙት።

ሆኖም ግን የኮንትራት ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት ነው ፖቼቲኖ እና ቼልሲበጋራ ስምምነት መለያየታቸውን ክለቡ ይፋ ያደረገው።

የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@alainnewsamharic
X (ትዊተር): https://twitter.com/AlAinAmharic
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የርችት ፋብሪካ ላይ የደረሰ የእሳት አደጋ

በህንድ በርችት ፋበሪካ መጋዝን ላይ የደረሰ የእሳት አደጋን ተከትሎ ፍንዳታ አጋጥሟል።

እሳት አደጋው በፋብሪካው ውስጥ ሲካሄድ ከነበረ ብየዳ አማካኝነት የተነሳ ሲሆን፤ በዚህም የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታውቋል።

የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@alainnewsamharic
X (ትዊተር): https://twitter.com/AlAinAmharic
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic
አሜሪካ የኢራኑን ፕሬዝዳንት ህይወት ለቀጠፈው የሄሊኮፕተር አደጋ ለምን ድጋፍ ማቅረብ ተሳናት?

"ከኢራን መንግስት እርዳታ ጥያቄ ቀርቦልን ነበር” ያሉት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማቲው ሚለር “በዚህ አይነት ሁኔታ የውጭ መንግስት ለሚቀርብልን ማንኛውንም ጥያቄ ምላሽ እንደምንሰጥ ግልፅ አድርገንላቸው ነበር” ብለዋል።
“በአብዛኛው በሎጂስቲክስ ምክንያት ከኢራን መንግስት ለቀረበልን ጥያቄ እርዳታ ልንሰጥ አልቻልንም” ሲሉም ሚለር ተናግሯል።
ኢራን አሜሪካን እና የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ኦሊይድ ኦስቲንን ተጠያቂ ልታደርግ ትችል ይሆናል በሚል ጥያቄ የቀረበላቸው ቃል አቀባዩ፤ ከዚህ አደጋ ጋር በተያያዘ ዩናይትድ ስቴትስ ምንም ድርሻ የላትም ብለዋል።
ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመለክቱ፤ https://am.al-ain.com/article/us-iran-helicopter-crash
ደቡብ ኮሪያ “ሰሜን ኮሪያ በሙዚቃ የስነልቦና ጦርነት አውጃብኛለች” በማለት ከሰሰች

ደቡብ ኮሪያ ለጎረቤቷ ሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን የተቀንቀነውንና በቲክቶክ ተወዳጅነትን ያተረፈውን ሙዚቃ በሀገሪቱ እንዳይታይ ልታግድ ነው።

የሀገሪቱ የሚዲያ ተቆጣጣሪ ተቋም በሚያዚያ ወር የተለቀቀው ሙዚቃ የሴኡልን የብሄራዊ ደህንነት ህግ የሚቃረን ነው ብሏል።

የደህንነት ህጉ የሰሜን ኮሪያን ድረገጾች እና መገናኛ ብዙሃን መመልከት የሚያግድ ሲሆን፥ የኪም ጆንግ ኡን አስተዳደርን የሚደግፍ ንግግር ማድረግና ይህንኑ የሚያንጽባርቅ ባህሪ ማሳየትም እንደሚያስቀጣ ያስቀምጣል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመለክቱ፤ https://bit.ly/3QTp78a