'
•••✿❒ ነብዩሏህ ሁድ ዐለይሂ ሰላም ❒✿•••

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኑህ ዐ ሰ እና በዘመኑ የነበሩት ሰዎች ከሞቱ በኋላ አንዱ አንዱን ሲተካ ምድር ዳግም በሰዎች ትሞላ ጀመር።

ያ ዘመን ካለፈ በኋላ የነበሩ ህዝቦችም ማንም አምልኮ ከምያውቀው በላይ ጣኦትን ማምለክ ተያያዙት።የህዝቡ መለያ ስማቸውም (ዓድ) ይባላል።

በመጀመርያ የዓድን ህዝቦች ላስተዋውቃችሁ...

የዓድ ህዝቦች በዐረቢያ ምድር በየመን ግዛት አህቃፍ በሚባል አካባቢ ኢረም በተባለች ከተማ የሚኖሩ በጣም ትላልቅ ቁመና ያላቸው ህዝቦች ሲሆኑ፤አላህ ስፍር ቁጥር የሌለውን የፀጋ አይነት ያትረፈረፈባቸው ህዝቦች ናቸው።

ከፀጋዎቻቸውም የሚኖሩበት ምድር በጣም ለቡቃያ አመቺ እና ለም አፈር ያለበት አካባቢ ነው።

ሰውነታቸውም በጣም ግዙፎች እና ረጃጅሞችም ነበሩ።

ከሰውነታቸው መግዘፍ የተነሳ አንድን የቴምር ዘንባባ በሁለት ጣታቸው ይነቅሉ ነበር።(የተምር ዛፎች ምን ያህል ግዙፍ እንደሆኑ ዐረብ ሀገር ያላችሁ ውዶች ታውቁታላችሁ)

ነገር ግን አላህ ለዋለላቸው እንዲህ አይነት ኒዕማ ምላሻቸው ምስጋና ሳይሆን ድንበር ያለፈ አመፅ እና መኩራራት ነበር።

የኑህ ህዝቦች ያደርጉት የነበረውን የጣኦት አምልኮ አሟሙቀው ጀመሩት።ያም አላንስ ብሏቸው ምድርን በተለያዩ የወንጀል አይነቶች ይሞሏትም ጀመር።

ነገር ግን ለቅጣት የማይቸኩለው አላህ በእዝነት አዘል ጥበቡ ከመጥፎ ከልክሎ ወደ መልካም የሚመራቸውን (ሁድ) የተባለውን መልዕክተኛ ከመሀከላቸው ላከላቸው።

ሁድ ዐ ሰ መልካም፣ቁጥብ፣የተረጋጉ እና አንደበተ ርቱዕ እና ዐረብኛ ቋንቋን ለመጀመርያ ግዜ የተናገሩ ሰው ናቸው።አላህም እሳቸውን ወደ ህዝባቸው በመሄድ የጌታቸውን ተልዕኮ እንዲያደርሱ አዘዛቸው።

ሁድ'ም ዐ ሰ የጌታቸውን ትዕዛዝ በመቀበል ወደ ዝባቸው ሄደው፦"እኔ ከጌታችሁ የተላክሁ ነብይ ስሆን፤በዚህ አለምም አላህ የሚባል ጌታ አላ።ከሱ ሌላ አምላክ የለም እነዚህ ከተለያዩ ድንጋይ እና እንጨት ጠርባችሁ ምታመልኳቸው ጣኦታት መጥቀምም መጉዳትም የማይችሉ ደካማ ሲሆኑ ከናንተ ጥበቃን ይሻሉ እንጂ እራሳቸውንም አይጠብቁም።

እኔን የታዘዘኝ ከሞት በኋላ ጀነት ይገባል እኔንም ያስተባበለኝ ጀሀነም መቀመጫው ስትሆን መቀመጫነቷስ ምንኛ ከፋ።" ብለው ማስጠንቀቅ ጀመሩ።

እነሱም ነቢያቸው በሚናገረው ግራ በመጋባት፦"እንዴት ነው አማልክቶቻችንን ትተን አንድን ፈጣሪ ብቻ ምንገዛው!!! ይህ ሰውዬ ምን አይነት ቂልነት ነው ይዞብን የመጣው" ይሉ ነበር።

ሁድ ዐ ሰ ህዝቦቹ የሚያሳዩት የመልስ ምት ለቅፅበት እንኳን ተስፋ አላስቆረጣቸውም ነበር። ይልቁኑ፦"እኔ ከናንተ ዘንድ የፈጣሪያችሁን ጥሪ ለማድረስ ከመሀከላችሁ የተመረጥኩ ስሆን፤የተላክሁበትንም ተልዕኮ ያለመሰላቸት በተደጋጋሚ ወደ እናንተ አደርሳለሁ።

እስቲ ፀሀይን እና ጨረቃን ተመልከቱ...ማን ነው የሚያፈራርቃቸው!!!

ማን ነው'ስ የፈጠራቸው!!!

ምድርንና ሰማይንም ተመልከቱ ማን ነው ምድርን አንጥፎ ሰማይን ያለ መሶሶ ያንጣለለው!!!

ተዉ ህዝቦቼ ጌታችሁን አምልኩት።ተጠንቀቁ እናንተ ከሞታችሁ በኋላ ትቀሰቀሱ'ና በሰራችሁት ትተሳሰባላችሁ።መልካም የሰራ ለነፍሱ ነው መጥፎ የሰራም ከከሳሪዎችም ይሆናል" እያሉ ይጠሯቸው ነበር።

ይህን የነቢያቸውን ጥሪ በሰሙ ግዜ፦"ይህን ሰው ከአማልክቶቻችን አንዱ በመጥፎ ተመልክቶታል(አብዷል)" በማለትም ይተቹት ጀመር።

አንዳንዴም፦"ይሄ ሂሳብ፣ጀነት፣ጀሀነም፣መቀስቀስ....ምናምን ምትለው ምን ማለት ነው?" እያሉም ይከራከሩታል።

የዓድ ህዝቦችም በምድር ላይ ያለ አግባብ ኮሩ፡፡ «ከእኛ ይበልጥ በኀይል ብርቱ ማን ነው?» አሉም፡፡ ያ የፈጠራቸው አላህ እርሱ በኀይል ከእነርሱ ይበልጥ የበረታ መኾኑን አያዩምን? በተዓምራታችንም ይክዱ ነበሩ። (ሱረቱል ፉሲለት)

ሁድ ዐ ሰ የህዝቡ ሁኔታ ተስፋ ሲያስቆርጠው፦"እናንተ ከምትሰሩት ሁሉ እኔ ነፃ መሆኔን ምስካሪ ሁኑ" እያለ የሱን ጥሪ ባለመቀበላቸው በዱንያ የሚወርድባቸውንም ቅጣት ያበስራቸውም ጀመር።

እነሱም፦"ምንድነው ዝም ብለህ ቅጣት ቅጣት...እያልክ ምታስፈራራን!!! እንደውም እስቲ ቅጣት ምትለውን አምጣው" እያሉ ሲያሾፉ

ሁድም ዐ ሰ፦"ይህ የማስጠንቅቃችሁ ቅጣት በናንተ ላይ ተፈፃሚ ይሆናል። አትጠራጠሩ" አሏቸው። በመጨረሻም ሁድ ዐ ሰ በህዝባቸው ላይ ዱዓ ማድረግ ጀመሩ።

ከዚያም አላህ የቅጣቱን አርጩሜ በህዝቡ ላይ ሊያወርድ መጀመርያ ለረጅም አመታት ዝናብ በማቋረጥ ምድሪቱን አድርቆ እንስሳቶቻቸውን አጠፋባቸው።

ሁድም ዐ ሰ፦"ከዚህ ሁሉ እንግልት ሊያድናችሁ እሚችለው በጌታችሁ ማመን ብቻ ነው" አላቸው።

እነሱም፦"በረሀብ እና በጥማት እንሞታታለን እንጂ ከጣኦቶቻችን ሌላ ማንንም አንለምንም" በማለት ጣኦታት ዘንድ እየሄዱ ኡኡኡ... ይሉ ጀመር።

ጣኦቶቻቸው ዘንድ ሄደው እሪ ብለው ሲወጡ ሰማይን በደመና ተሞልቶ አገኙት።በጣምም ተደሰቱ አማልክቱ ፀሎቶቻቸውንም እንደሰሙ አመኑ ጥሩ ዝናብ ሊዘንብልን ነው በማለትም ተመፃደቁ።

ያን ግዜ ሁድ ዐ ሰ፦"ይህ እኮ አምጣልን ያላችሁት የቅጣት ደመና ነው እንጂ እናንተ እንደምትሉት ዝናብ አይደለም" አላቸው።

ከዚያም ከፍተኛ ጉልበት የለው ንፋስ ከተማቸውን ያናውጥላቸው ጀመር።ቀስ በቀስ ንፋሱ አስፈሪ ድምፅን እየቀላቀለ በክፍተኛ ጩሀት ህዝቡን ወደ ሰማይ ማፈናጠር ጀመረ።

በዚህ ሁኔታ ለ 7 ሌሊቶች እና ለ 8 ቀናት

ያህል ንፋሱ ዘለቀ። በነዚያ የቅጣት ቀናት ሰውም እንስሳትም ምንም አይነት ፍጥረት አልቀረም ነበር።በሁድ ዐ ሰ ያመኑት ምዕመናን ሲቀሩ ሁሉም የመቅሰፍቱ ሰለባ ሆኑ.....

አሏህ ሱበሃነሁ ወተዓላ ነቢዩሏህ ሁድን ዐ ሰ እና ከሱጋ ያመኑት አዳነቸው፡፡

•••✿ ❒ ተ_ፈ_ፀ_መ ❒✿•••

በቀጣይ #ነብዩሏህ ሉጥ(ዐ.ሰ) ታሪክ እንጀምራለን 🥰
#share
@alahu_akber1
«ያ ረቢ!
ይህ ሁሉ እያመፅኩህ አልቀጣኸኝም!» አለ።
እንዲህ ተባለ: ‐

«ይህን ሁሉ እየቀጣሁህ እስከሁን አላወቅክም!?…
ከኔ ጋር የማንሾካሾክን ጣዕም አልከለከልኩህም?!»

[ኢማም ኢብኑል‐ጀውዚይ፥ ሶይዱል‐ኻጢር]
:
@alahu_akber1
አንተ እየጠነከርክ ሂድ እንጅ::
ሕይወት እየቀለለች ትመጣለች ብለህ እንዳትጠብቅ!!

@alahu_akber1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
'
ያረብ ይሄን የላጤ ሂወት በቃ በለን 😭

@alahu_akber1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
'
ሷሊህ ሴት እና ሷሊህ ወንድ...
በዱአ ብዛት እንጂ በጅንጀና ዉጤት አይገናኙም 😎

@alahu_akber1
'
•••✿❒ ነብዩሏህ ሉጥ ዐለይሂ ሰላም ❒✿•••

#ክፍል 1

★ የሉጥ ሕዝቦች ነብያቸውን በምድር ላይም ብልሹነትን አነገሱ፥ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፦

وَلُوطًا إِذْ قَالَلِقَوْمِهِۦٓ أَتَأْتُونَ ٱلْفَـٰحِشَةَ وَأَنتُمْ تُبْصِرُونَ ﴿٥٤﴾ أَئِنَّكُمْ لَتَأْتُونَ ٱلرِّجَالَ شَهْوَةًۭ مِّن دُونِ ٱلنِّسَآءِ ۚ بَلْأَنتُمْ قَوْمٌۭ تَجْهَلُونَ ﴿٥٥﴾
“ሉጥንም ለሕዞቦቹ ባለ ጊዜ (አስተውስ) እናንተ የምታዩ ስትኾኑ ጸያፍን ነገር ትሠራላችሁን።

እናንተ ከሴቶች አልፋችሁ ወንዶችን ለመከጀደል ትመጣላችሁን በውነቱ እናንተ የምትሳሳቱ ሕዝቦች ናችሁ። (አን-ነምል፥ 54-55)

እነዚህ ሕዝቦች በምሥራቃዊ ዮርዳኖስ ይኖሩ ነበር።

ይህ ቦታ በሙት ባህር አቅራቢያ ይገኛል። በአካባቢው አምስት መንደሮች ነበሩ። እነሱም;- “ሰዱም፣ ዑመራ” “አደመህ” “ሱወይም” “ባሊ’ዕ” ናቸው።ሉጥ (ዐ.ሰ) በዋናው መንደር ሰዱም ይኖሩ ነበር። መጥፎና ርካሽ ተግባራትን ትፈፅም የነበረችውም መንደር እሷ ነች።

የሰዱም ነዋሪዎች እርኩሶችና መጥፎ ከመሥራት የማይፈሩ ነበሩ። አስፀያፊ ተግባራቸውን በግልጽ የሚፈጽሙበት መሰብሰቢያ ቦታ ነበራቸው። መንገደኛን ይዘርፋሉ። ከሌላ አካባቢ ነጋዴዎች ከመጡ ተሰብስበው ዕቃቸውን ይቀማሉ።

የሉጥ ሕዝቦች ነፍሳቸውንም በእጅጉ የሚበድሉ እጅግ ቆሻሾች ነበር።ካቆሻሻነታቸው የተነሳ በፆታ ግንኙነት ከሴት ይልቅ ወንድ ከወንድ ጋር መገናኘት ይመርጡ ነበር።

እነዚህ ሰዎች መጥፎ ተግባራቸው ወሰን ያለፈ ስለሆነ ይህ አስፀያፊ ተግባር ወደ ሌሎችም አካባቢዎች እንዳይዛመት እነሱን በማስተካከል ወይም በማጥፋት ይህን መጥፎ ተግባራቸውን ማስወገድ የግድ ነበር። ምክንያቱም ሲባል ነው።

#የሉጥ_ጥሪ

★ ሉጥ (ዐ.ሰ) ሕዝቦቻቸው የሚሠሩትን አስፀያፊ ነገር ሲያዩ የወገኖቻቸው በዚህ ሁኔታ መገኘት አሳሰባቸው።

ሥነ-ምግባራቸው እንዲስተካከል በማሰብም ምክር መለገስ ጀመሩ። የሉጥ ጥሪ ሥነ-ምግባራቸው በጅጉ ለተበላሹና ቀልባቸው ለደረቀ ሰዎች የሚደረግ በመልካም ተግባር ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል ነበር።

እነዚህ ሰዎች ምንም ሐያእ /ሐፍረት/ የሌላቸውና አስጸያፊ ወንጀልን በጠራራ ፀሐይ የሚፈፅሙ ነበሩ።

ከዚህም በላይ ሴት በማግባት አላህ የፈቀደላቸውን ግንኙነት መፈጸም ትተው ከወንዶች ጋር በመገናኘት ማንም አድርጎት የማያውቀውን አስጸያፊ ተግባር ይፈፅሙ ነበር።

ስለዚህም አላህ (ሱ.ወ) ሉጥ (ዐ.ሰ) ወደ እነዚህ ሕዝቦች ሄደው ከቆሻሻ ተግባራቸው እንዲፀዱ ጥሪ እንዲያደርጉላቸው ላካቸው።

ሉጥ (ዐ.ሰ) የነበዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) የወንድም ልጅ ሲሆኑ በኢራቅ ባቢል ነበር የተወለዱት።

ነቢዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ወደ ተውሂድ ጥሪ ሲያደርጉ አምነው ከሳቸው ጋር ወደ ሻም አካባቢ ስደት በመሄድ በምሥራቅ ዮርዳኖስ በሚገኘው ሱዲም ሸለቆ አካባቢ ሰፈሩ።በአካባቢው ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት የምትፈጽስም ሰዱም የምትባል መንደር ነበረች።

አላህ (ሱ.ወ) ነቢዩላህ ሉጥን ወደ ሰዶምና አካባቢዋ ሕዝቦች፣ አላህን ብቻ እንዲያመልኩና ከመጥፎ ተግባራቸው እንዲርቁ ለማስተማር ና

ወንድ ለወንድ ግንኙነት መፈጸማቸውን ትተው አላህ የፈቀደላቸውን ሴቶቻቸውን በማግባት ግንኙነት እንዲፈፅሙ እንዲያዟቸው አላህ ሉጥን ላካቸው።ይህ ዓይነቱ ወንጀል ከሰዶም ሕዝቦች በፊት ማንም ያልሠራው አስጸያፊ ወንጀል ነበር

إِذْ قَالَ لَهُمْ أَخُوهُمْلُوطٌ أَلَا تَتَّقُونَ ﴿١٦١﴾ إِنِّى لَكُمْ رَسُولٌ أَمِينٌۭ ﴿١٦٢﴾ فَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ﴿١٦٣﴾

“አትጠነቀቁምን? እኔ ለናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝ። አላህንም ፍሩ። ታዘዙኝም” (አሽ-ሹዐራእ፥ 161-163)

አሏቸው። እንዲሁም ሉጥ እያዘኑላቸው ለዘብ ባለ ቃል!

وَمَآ أَسْـَٔلُكُمْ عَلَيْهِ مِنْ أَجْرٍ ۖ إِنْ أَجْرِىَ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّ ٱلْعَـٰلَمِينَ﴿١٦٤﴾

“በርሱም ላይ ምንም ዋጋ አልለምናችሁም። ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጅ በሌላ አይደለም።” (አሽ-ሹዐራእ፥ 164) በማለት አስገነዘቧቸው።
በዚህ ቃላቸው ውስጥ ሉጥ (ዐ.ሰ) ከነሱ ዓለማዊ ጥቅም እንደማይሹና ብቸኛው ፍላጐታቸው የነሱ መስተካከልና አላህን ብቻ ማምለካቸው እንደሆነ አስረዷቸው።

በመቀጠልም ሉጥ (ዐ.ሰ) ወደነዚህ ሰዎች አስፀያፊ ተግባር በመዞር የሚከተለውን ተናገሯቸው።

وَلُوطًا إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِۦٓ أَتَأْتُونَ ٱلْفَـٰحِشَةَوَأَنتُمْ تُبْصِرُونَ ﴿٥٤﴾ أَئِنَّكُمْ لَتَأْتُونَ ٱلرِّجَالَ شَهْوَةًۭ مِّن دُونِ ٱلنِّسَآءِ ۚ بَلْأَنتُمْ قَوْمٌۭ تَجْهَلُونَ ﴿٥٥﴾ ۞

“ሉጥንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስተውስ) እናንተ የሚታዩ ስትኾኑ ጸያፍን ነገር ትሠራላችሁን። እናንተ ከሴቶች ወንዶችን ለመከጀል ትመጣላችሁን በውነት እናንተ የምትሳሳቱ ሕዝቦች ናችሁ። (አን-ነምል፥ 54-55)

የሰዶም ሰዎች አስፀያፊ ተግባራቸውን በግልጽና በስብሰባ ቦታዎች ሁሉ ሳይቀር መፈጸማቸው ሉጥን በጣም አሳዘነ።
ሉጥ (ዐ.ሰ) ከዚህ አስፀያፊ ተግባር ቢከለክሏቸውም «አንተ ሴቶችን አስተናግድ ወንዶችን ተውልን።»በማለት አስፀያፊ መልስ ሰጧቸው።

ይህ ሁሉ ቢሆንም ነቢዩላህ ሉጥ (ዐ.ሰ) ተስፋ ባለመቁረጥ የተለያዩ ማስረጃዎችን በመጥቀስ ጥሪያቸ እውነት መሆኑን ሊያሳምኗቸው ሞከሩ።

ነገር ግን ድካማቸው በከንቱ ነበር። ቀናት ወራትን ወራት ዓመታትን እየተኩ ዘመኑ ሄደ። ሉጥም ዳዕዋቸውን ቀጠሉ። ነገር ግን ከቤተሰባቸው ውጭ አንድም ሰው አላመነላቸውም ነበር። ከቤተሰባቸውም ውስጥ ሚስታቸው አላመነችም ነበር።

ከከሓዲያን ጐን ተሰለፈች። ይህም ሁኔታ ሉጥ (ዐ.ሰ) ከቤታቸው ውጭ ከሓዲያንን፣ በቤት ውስጥ ደግሞ ከሓዲት ሚስታቸውን መታገል አስገደዷቸው።ስለሆነም በጣም ድካም ይሰማቸው ነበር። ቢሆኑም ግን ትዕግስት እያደረጉ ያለ መሰላቸት ወደ አላህ ጥሪ ማድረጋቸውን ቀጠሉ።

ሕዝባቸው ግን ማመናቸው ቀርቶ በዳዕዋቸው በማላገጥ “ከእውነተኞቹ እንደ ሆንክ የአላህን ቅጣት አምጣብን።
” (አል-ዐንከቡት፥ 29)

ሉጥ (ዐ.ሰ) ሕዝባቸው ቢቀልዱባቸውም ታግሰውና ችለው አሁንም ማስተማራቸውን ቀጠሉ። ከሓዲያኑ የሰዶም ሕዝቦች ሉጥ ላይ ማፌዛቸውንና ማስቸገራቸውን አጠናክረው ቀጠሉ።

ሉጥ (ዐ.ሰ) በአላህ (ሱ.ወ) እንደሚጠበቁ በመዘንጋት የሰዶም ሕዝቦች ሊያጠቋቸው ሞከሩ። ሉጥንና ቤተሰባቸውን በመናቅም።

وَمَا كَانَ جَوَابَ قَوْمِهِۦٓ إِلَّآ أَن قَالُوٓا۟ أَخْرِجُوهُممِّن قَرْيَتِكُمْ ۖ إِنَّهُمْ أُنَاسٌۭ يَتَطَهَّرُونَ ﴿٨٢﴾
“ሉጥንና ተከታዮቹን ከከተማችሁ አውጧቸው። አሉ። እነሱ፡ የሚጥራሩ ሰዎች ናቸውና።” (አል-አዕራፍ፥ 82)

አሉ።የሰዶም ሕዝቦች ቆሻሾች ስለነበሩ ነቢያቸው ሉጥ «ከመጥፎ ነገር ተመለሱ። በተመሳሳይ ፆታ መካከል ግብረ ሥጋ ግንኙነት አትፈጽሙ።»

ብለው ሲመክሯቸው በሉጥና ተከታዮቻቸው ንፁህነት በመቀለድ “እነሱ ንፁሃን ናቸው” ሲሉ አሾፉባቸው።

★ ሉጥ (ዐ.ሰ) ሕዝባቸው ቢቀልዱባቸውም ታግሰውና ችለው አሁንም ማስተማራቸውን ቀጠሉ።


ክፍል 2 ይቀጥላል....

#share
@alahu_akber1
ምናልባት የአንድ ቀን ስህተት
ትክክለኛውን መንገድ ያሳይሃል!

@alahu_akber1
'
•••✿❒ ነብዩሏህ ሉጥ ዐለይሂ ሰላም ❒✿•••

#ክፍል 2

ከሓዲያኑ የሰዶም ሕዝቦች ሉጥ ላይ ማፌዛቸውንና ማስቸገራቸውን አጠናክረው ቀጠሉ።

#ውዶቼ በባለፈው ትምህርታችን ላይ ታስታውሱ እንደሆነ መላእክት ነቢዩላህ ኢብራሂም ቤት ሄደው ዘይሯዋቸው ከዚያም መላእክት ራሳቸውን ለኢብራሂም አስተዋወቁ።

“እኛ አዋቂ ልጅ እንደምታገኝ ልናበስርህ ከጌታህ ዘንድ የተላክን መልዕከተኞች ነን።” አሏቸው። «አሁን ከአንተ ቤት ወጥተን ወደ ሉጥ ሕዝቦች በመሄድ ሉጥን እንረዳዋለን።
የሕዝቦቹ መጥፊያ በዚህች ሌሊት ነው። ቀጠሯቸው ጐህ ሲቀድ ነው። በማለት መላእክቱ የመጡበትን ዓለማ ለኢብራሂም (ዐ.ሰ) አስረዱ።
ኢብራሂም በሁኔታው ተደናግጠው ነገሩ እንዲዘገይ ለማድረግ ሞከሩ። መላእክቱ ግን የአላህ ትእዛዝ ስለሆነ ሳይዘገይ የሚፈጸም መሆኑን አስረዷቸው።
መላእክቱ ከነብዩ ኢብራሂም ቤት ወጥተው ወደ ሰዶም መንደር አመሩ። አስር ሶላት ወቅት ሲሆን ሰዶም መንደር ዳርቻ ደረሱ።
እዚያ ቦታ ላይ በደን ውስጥ የሚፈስ ወንዝ ነበር። ከወንዙ ዳርቻ አንዲት ልጅ ውሃ ለመቅዳት ቆማ አገኟት። ይህች ልጅ የሉጥ (ዐ.ሰ) ልጅ ነበረች።

4ቱን ወጣቶች ስታይ ለየት ያለ ውበት ስለነበራቸው ተደናገጠች። ከ4ተኛው አንደኛው የሉጥ ቤት የት እንደሆነና እንግዳም ይቀበሉ እንደሆነ ጠየቃት።
ልጅቷም የሰዶም ሰዎችን አስፀያፊ ተግባር ስለምታውቅ «ለአባቴ ነግሬ መልሱን እስከምነግራችሁ ድረስ እዚሁ ቆዩ። ወደ ሰዶም እንዳትገቡ» ብላ አስጠነቅቃቸው የውሃ እቃዋን ወንዙ ዳር ተወችና ፈጥና ወደ አባቷ ሉጥ (ዐ.ሰ) ዘንድ በመሄድ ሦስት ወጣቶች እሳቸውን ፈልገው እንደመጡ ነገረቻቸው።

ሉጥ ይህን መልዕክት ሲሰሙ ተደሰቱ ወይስ አዘኑ? ስለሁኔታው አላህ (ሱ.ወ) በሁድ ምዕራፍ ውስጥ እንዲህ ይላል፦

وَلَمَّا جَآءَتْ رُسُلُنَا لُوطًۭا سِىٓءَ بِهِمْوَضَاقَبِهِمْ ذَرْعًۭا وَقَالَ هَـٰذَا يَوْمٌ عَصِيبٌۭ ﴿٧٧﴾
“መልዕክተኞቻችን ሉጥን በመጡት ጊዜ በነሱ (ምክንያት) አዘነ። ልቡም በነሱ ተጨነቀ። ይህ ብርቱ ቀን ነውም አለ።“ (ሁድ፥ 77)

ሉጥ (ዐ.ሰ) «ዛሬ አስቸጋሪ ቀን ነው። አሉና ፈጥነው ወደ እንግዶቹ ሄዱ። እንግዶቹን ሲያዩ ለሰዶም ሰዎች መጥፎ ተግባር እንዳይጋለጡ በመፍራት ይበልጥ አዘኑ።

ሉጥ እንግዶቹን ከየት እንደመጡ ጠየቋቸው። መልስ ሰጧቸው። ወደ የት እንደሚሄዱ ሲጠይቋቸው ግን መልስ አልሰጧቸውም ነበር። ይልቁንም በእንግድነት እንዲቀበሏቸው ጠየቋቸው። ሉጥ (ዐ.ሰ) እንግዶቹን ለማስተናገድ ስስት አልነበረባቸውም።

ነገር ግን መላእክት መሆናቸውን ስላላወቁ የመንደሩ ሰዎች አስፀያፊ ተግባራቸውን እንዳይፈጽሙባቸው ፈርተው ነበር ያዘኑት።
ከዚያም ፊት ለፊት እየመሩ እንግዶቻቸውን አስከትለው ወደ ሰዶም መንደር ገቡ።
በመንገድ ላይ እያሉ ሉጥ (ዐ.ሰ) ቆም አሉና «ከዚህ አገር ሰዎች አስጠንቅቃችኋለሁ። በመሬት ላይ እንደነዚህ ሰዎች ቆሻሻ ሰው የለም» አሏቸው። መላእክቱ ሉጥ በሰጧቸው ማስጠንቀቂያ ላይ ምንም አስተያየት ሳይሰጡ ዝም ብለው መንገዳቸውን ቀጠሉ።

ሉጥ (ዐ.ሰ) ለእንግዶቹ ይህን ያሏቸው ከሰዶማዊያን ዓይን እንዲርቁ ፈልገው ነበር። እንግዶቹ ግን ምንም ሳይናገሩ ፀጥ ብለው ቆዩ።
በዚህን ጊዜ ሉጥ (ዐ.ሰ) ወደ ሰዶም መንደር በሌሊት ተደብቀው እንዲገቡ ጠየቋቸው።

እንግዶቹ ይህን ተቀብለው ማንም ሳያያቸው ከሉጥ ጋር በመሆን በሌሊት ወደ ከተማዋ ገቡ።

ሉጥ (ዐ.ሰ) እንግዶቹ ሌሊት ገብተው ጠዋት ጐህ ሲቀድ ማንም ሳያያቸው ይወጣሉ በሚል አስበው ነበር።
ሉጥ (ዐ.ሰ) አሁን ካሁን መጥፎዎቹ ሰዎች እነዚህን እንግዶች እንዳያይዋቸው እየተጨነቁ ከ4ቱ እንግዶቻቸው ጋር

እንደምንም ወደ ቤታቸው ገቡ።ከመንደሩ ሰዎች ማንም አላያቸውም ነበር።
ነገር ግን በቤት ውስጥ የነበረችው ከሓዲዋ ሚስታቸው እንግዶቹን እንዳየች ተደብቃና ድምጽዋን አጥፍታ ከቤት ወጣች።

★ የሉጥ (ዐ.ሰ) ሚስት በፍጥነት ወደ ሰዶማዊያኑ በመሄድ በሉጥ ቤት ከሰዶም ያልሆኑ እንግዶች እንዳሉ ነገረቻቸው።

ብልሹዎቹ ሰዎች ይህን ሲሰሙ ተደስተው እየተጠራሩ ወጡ። ከዚያም በአንድ ላይ ተሰብስበው ወደ ሉጥ ቤት አመሩ።
ሉጥ (ዐ.ሰ) ማን እንደነገራቸው ሲያስቡ፡ ሚስታቸው ቤት ውስጥ አለመኖሯን አወቁ። ሐዘናቸው በጣም ጠና።
ከየአቅጣጫው የተሰበሰቡት ሰዶማዊያን የሉጥን ቤት ከበቡ። ቀጥሎም በሩን መቆርቆር ጀመሩ። ሉጥ (ዐ.ሰ) ምን እንደምፈልጉ ጠየቋቸው።
በፊታቸው ላይ መጥፎ ነገር ይነበብ ነበር። ሉጥ (ዐ.ሰ) ተንኮለኞችን ለመመለስ ቢሞክሩም አልቻሉም። ከዚያም፦

وَجَآءَهُۥ قَوْمُهُۥ يُهْرَعُونَ إِلَيْهِ وَمِن قَبْلُ كَانُوا۟يَعْمَلُونَ ٱلسَّيِّـَٔاتِ ۚ قَالَ يَـٰقَوْمِ هَـٰٓؤُلَآءِ بَنَاتِى هُنَّ أَطْهَرُ لَكُمْ ۖ فَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَلَا تُخْزُونِ فِى ضَيْفِىٓ ۖأَلَيْسَ مِنكُمْ رَجُلٌۭ رَّشِيدٌۭ ﴿٧٨﴾
“ሕዝቦቼ ሆይ! እኝህ ሴቶች ልጆቼ ናቸው። እነሱ ለእናንተ ይልቅ በጣም የጸዱ ናቸው። (አግቧቸው)።

አላህንም ፍሩ። በእንግዶቼም አታሳፍሩኝ። ከናንተ ውስጥ ቅን ሰው የለምን?” (ሁድ፥ 78)በማለት አናገሯቸው።
ሉጥ (ዐ.ሰ) ሰዎቹ ሐራምን ትተው ወደ ሐላል እንዲዞሩ መንገድ ቢያሳዩዋቸውም አሻፈረኝ በማለት መጥፎ የመሥራት ፍላጎታቸውን ለማሳካት መሞከራቸውን ቀጠሉ።
በዚህን ጊዜ ሉጥ (ዐ.ሰ) በራቸውን ዘጉ። ሰዎቹም በሩን በኃይል ነቀነቁት። ሉጥ (ዐ.ሰ) በሁኔታው ተስፋ ቆረጡ።

قَالَ لَوْ أَنَّ لِى بِكُمْ قُوَّةً أَوْ ءَاوِىٓ إِلَىٰ رُكْنٍۢ شَدِيدٍۢ ﴿٨٠﴾
“ በናንተ ላይ ለኔ ኃይል በኖረኝ ወይም ወደ ብርቱ ወገን ቢጠጋ ኖሮ (የሚሠራውን በሠራሁ ነበር)።” (ሁድ፥ 80)

አሏቸው። ሉጥ (ዐ.ሰ) የተንኮለኞቹን ክፋት ለመከላከል በቂ ኃይል በነበረኝ ብለው ተመኙ ።
በዚህን ጊዜ መልአኩ ጅብሪል ቆመና፦ይህን የሉጥን ሁኔታ እና እንግልት የተመለከቱት በወጣቶች የተመሰሉት መላዕክት ሉጥን ጠሩት'ና ሁሉንም ነገር ግልፅ አደረጉለት። መላዕክት መሆናቸውንም አክለው ነገሩት።
1፦ጂብሪል
2፦ሚካኢል
3፦ኢስራፊል
4መለከል ሞት....ነበሩ።
በመጨረሻም ይህችን ከተማ ሊያጠፏት እንደሆነ እና ሉጥ ቤተሰቦቹን እና ተከታዮቹን ሁሉ ሰብስቦ ሱብሂ ሰዐት ከተማይቱን ለቅቆ እንዲወጣ አዘዙት።በዚህ ሁኔታ ሉጥ እንግዶቹን እያወራ ሳለ ህዝቡ በሩን ሊገነጥል ተቃረበ ያን ግዜ ጂብሪልም አላህን አስፈቀደ'ና አንድ ግዜ በሩን ከፍቶ በመውጣት በክንፉ ፊት ፊታቸውን ክፉኛ መታቸው አይኖቻቸውም እዛው መፍሰስ ጀመሩ።

ጠዋት ሲነጋ ሉጥን እንደሚገድሉት እየዛቱ ሁሉም ከበሩ እየተተራመሱ ሄዱ።ከዚያም ሉጥ መላዕክቱን፦መቼ ነው እነዚህን ህዝቦች ምታጠፉት አላቸው።
እነሱም፦"ሱብሂ ላይ ነው" አሉት።

ሉጥም፦"አሁኑኑ ብታጠፏቸውስ" ሲላቸው...

መላዕክቱም፦"እንዴ ሱብሂ ቅርብ አይደል ወይ!!!" አሉት።

በነጋታው ሉጥ ተከታዮቹን፣ቤተሰቦቹን እና አመፀኛዋን ሚስቱን ይዞ ከመቅሰፍቱ ሽሽት ከከተማይቱ መውጣት ጀመረ። ሲወጣም ለተከታዮቹ በከተማይቱ የሚወርደውን መቅሰፍት ማንም ዞሮ ማየት እንደሌለበት አስጠንቅቆ ተናገረ።

አሁም ጉዞ ጀምረዋል...መላዕክቱ እዛው ከተማ ውስጥ ናቸው...ሉጥ እና ተከታዮቹ ከተማይቱን ልክ ለቀው እንደወጡ ከወደ ከተማይቱ በኩል ከፍተኛ ድምፅ ሰሙ።
ማንም ወደ ከተማዋ እንዳይዞር ማስጠንቀቂያ ስለተሰጠ ማንም አልዞረም ነበር።የሉጥ ሚስት ግን ወደኋላ በመዞር፦"ወይኔ ወገኔ,,,,!!!" በማለት ጮኸች።
ትልቅ የድንጋይ ፍንጣሪ መጣና እራሷን ለሁለት ከፈለላትና የመቅሰፍቱ ሰለባ ሆነች።

አላህም ይህን ዘግናኝ ክስተት ሲተርክ እንዲህ ይላል፦
"ትዕዛዛችንም በመጣ ግዜ (የከተማይቱን) ላይዋን ከታች አደረግን(ገለባበጥናት) ተከታታይም የሆነ የሸክላ ድንጋይ በርሷ ላይ አዘነብን" (ሱረቱል ሁድ)

እንዴት አድርጎ እንደገለባበጣቻው ታውቃላችሁ...!!!
መጀመሪያ ጂብሪል ክንፉን በከተማይቱ መሬት ውስጥ ዘቅዝቆ አስገባው።
ከዚያም ከተማይቱን ከነ ህንፃዎቿ ነቅሎ ወደ ሰማይ ከፍ ካደረገ በኋላ ገለበጠው'ና መልሶ ወደ ምድር ተከለው።

ሉጥ ከነ ተከታዮቹ ብዙ ርቀት ከተጓዘ በኋላ ሱዒር የተባለ አከባቢ በመስፈር ይህ ነው ተብሎ በታሪክ መዛግብት እድሜው ባይሰፍርም እዛው ሱዒር ላይ ህይወቱ አልፏል። (ዐለይሂ ሰላቱ ወሰላም)

•••✿ ❒ ተ_ፈ_ፀ_መ ❒✿•••

በቀጣይ #ነብዩሏህ ሷሊህ(ዐ.ሰ) ታሪክ እንጀምራለን 🥰
#share
@alahu_akber1
'
ውበትሽ ቤቴ ሊያስገባሽ ይችላል...
ነገር ግን ፀባይሽ አባትሽ ጋር ሊመልስሽ ይችላል እና ተጠንቀቂ 😁

@alahu_akber1
'
•••✿ ❒ ነብዩሏህ_ሷሊህ_ዐለይሂ_ሰላም_ታሪክ ❒✿•••



የሰሙድ ህዝቦች ከሁድ ህዝቦች በኋላ የመጡ ሲሆኑ በጣም ትዕቢተኛ እና ኩራተኛ ናቸው።
በሳውዲ ዐረቢያ ምድር በሂጃዝ እና በተቡክ መሀከል የሚገኝውን ግዙፍ ተራራ በመፈልፈል ከዘመኑ ጋር የማይመጣጠን ውብ ውብ... ህንፃዎችን ሰርተው ነበር የሚኖሩት።በጣም ትላልቅ ናቸው አሁን ያለው ትውልድ በጉልበትም ሆነ በግዝፈት ከነሱ አይስተካከልም።
ምንም እንኳን ድንጋያማ አካባቢ የሚኖሩ ህዝቦች ቢሆኑም አላህ ምድራቸውን ለቡቃያ ምቹ አድርጓት የምንጮቹንም ብዛት ለጉድ አድርጎታል።
ግዜው ከአባቶቻቸው የወረሱርትን የጣኦት አምልኮ አጧጡፈው የያዙበት ዘመን ነበር።

በዱንያ ሰክረው...አላህን ረስተው...በወንጀል ተጨማልቀው ሳለ አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ ሳሊህ ኢብን ዑበይድ ኢብን ሂሻም ኢብን.....ዓድ ኢብን ኣርም ኢብን ሳም ኢብን ኑህ (ዐ ሰ) የተባለን መልካም ነቢይ ከመሀከላቸው ላከላቸው።
ሳሊህ ዐ ሰ በነቢይነት ከመመረጣቸው በፊት ህዝቡ ዘንድ በምልካም ስነ ምግባራቸው የሚታወቁ፣ከከበርቴ ቤተሰብ የተወለዱ፣ከዚያም አልፎ ሰዎች ለፍርድ ሚያስቸግር ክርክር ሲገጥማቸው እሳቸው ጋር የሚሄዱ ምርጥ የአላህ ባርያ ናቸው።

ወደፊት ሀገሪቷን በንግስና ያስተዳድሯታል ተብሎም ይገመት ነበር።
በንዲህ አይነት ሁኔታ ላይ ሳለ ሳሊህ ዐ ሰ የጌታቸውን ተልዕኮ እንደተቀበሉ በትኩስነቱ፦" ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ ከዓድም በኋላ ምትኮች ባደረጋችሁና በምድሪቱም ላይ ባስቀመጣችሁ ጊዜ አስታውሱ፡፡ ከሜዳዎቿ (ሸክላ) ሕንጻዎችን ትገነባላችሁ፡፡ ከተራራዎችም ቤቶችን ትጠርባላችሁ፡፡ ስለዚህ የአላህን ጸጋዎች አስታውሱ፡፡ በምድርም ውስጥ አጥፊዎች ኾናችሁ አታበላሹ" በማለት ጥሪውን አስተጋባ።
ይህን በሰሙ ግዜ ትዕቢታቸው አናታቸው ላይ ወጣ...ኩራታቸው ገነፈለ...የከተማይቱ መሳፍንትም፦"አንተ ሳሊህ! ቆይ አንተ ከኛ በምን ተሽለህ ነው አላህ መልዕክተኛ አድርጎ ሊመርጥህ የቻለው? ይልቁኑ አማልክቶቻችን በመጥፎ አይን ሳያዩህ አልቀሩም'ና አብደሀል" አሉት።

ከዚያም እንደተለመደው ሳሊህ(ዐ ሰ) የድሆች እና ምስኪኖች ተከታይ ይበራከቱለት ጀመር።ይሁን እንጂ በለፀጋዎች እና ጉልበተኞቹ ዝም ማለትን አልመረጡም'ና ምእመናኑ ዘንድ በመሄድ፦"እናንተ ባመናችሁት ነገር እኛ ክደናል" በማለት ይሳለቁባቸው ነበር።

ከዛላችሁ እነዚህ አመፀኛ ህዝቦች አንደ ቀን የሳሊህን ዐ ሰ ጥሪ ለማስቆም እና ተከታዮቹን ከሱ ለማራቅ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሊመካከሩ አንድ ቦታ ተሰበሰቡ።ብዙ ከመከሩ በኋላ በመጨረሻም ሳሊህን (ዐ ሰ) ያለ ተከታይ ብቻውን ለማስቀረት አንድ መፍትሄ አገኙ።
እሱም፦"ሳሊህን የሚከተል ከአማልክቱ በኩል የማይድንን በሽታ ይይዘዋል።ከሳሊህም የሚርቅ ከነዚህ ነገሮች የተጠበቀ ይሆናል" በማለት ከተማይቷን ቀወጧት።

ነገር ግን ትክክለኛይቱ የዳዕዋ ጥሪ መንገዷን ይዛ ቀጥላለች።በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ አንድ ቀን ሳሊህ ዐ ሰ ጥሪያቸውን በህዝብ ፊት ሲያደርሱ ህዝቡም፦"አንተ ሳሊህ እውን አንተ ነቢይ ከሆንክ ማረጋገጫ ይሆነን ዘንድ እስቲ ተዐምር አምጣልን" አሉት።

የከተማይቱ ሹማምንት እና የተከበሩ ሰዎች በቦታው ነበሩ።የማይችለውን ነገር በመጠየቅ እንዳደናገሩት በማሰብ የማላገጥን ሳቅ ይስቁበትም ጀመር።(ወላሂ ነቢያቶች አላህ ምንዳቸውን ከፍ ያድርግላቸው።በገዛ ሀገራቸው ይሳቀቃሉ)

ከመሳፍንቱ መሀክል አንዱ ቆመ'ና፦"አንተ ሳሊህ ተዐምር ማሳየት እችላለሁ የምትል ከሆነ የተዐምሩን አይነት እኛ ነን ምንመርጠው ያንተ ስራ እኛ የመረጥነውን ተዐምር መተግበር ብቻ ነው" አሉት

እኛ እያየን ከዚህ ተራራ ውስጥ በግዝፈቷ አቻ የሌላት የአስር ወር እርጉዝ የሆነች፣መልኳም ቀይ የሆነ፣ከግዝፈቷ የተነሳ የከተማይቱ ይዝብ እና እንስሳት የሚጠጡትን ውሀ በአንዴው መጠጣት የምትችል ትልቅ ግመል አውጣልን"አሉት።

ነቢዩላህ ሳሊህም (ዐ ሰ) ህዝቡ ሁሉ ተዐምሩን አይተው በማመን ከጀሀነም ይድኑ ዘንድ የከተማይቱ ሰው ሁሉ እንዲሰበሰብ አዘዙ'ና ሁሉም ተሰበሰቡ።

ከዚያም ሳሊህ (ዐ ሰ) ለጌታቸው ሱጁድ በመውረድ ጌታቸውን ይማፀኑ ጀመር።አላህም የሱን መልዕክተኞች በህዝባቸው ፊት አያሳፍራቸውም'ና ተራራው በጣም መንቀጥቀጥ ጀመረ።

ህዝቡ ሁሉ አይኑን ተራራው ላይ ተክሏል።ካሁን አሁን ምን ሊከሰት ነው በማለት እርስ በርስ ይተያያሉ።

በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ ተራራው ከፍተኛ ጩኸት ካስተጋባ በኋላ በጣም በመሰንጠቅ ከመሀከሉ ህዝቡ በጠየቀው መልኩ ትልቅ እና እርጉዝ ቀይ ግመል ወጣች።

ይህን ባዩ ግዜ አይኖቻቸው ፈጠጠ፣ አንደበታቸው ደረቀ፣ምላሶቻቸው ተሳሰሩ።ሳሊህም ዐ ሰ፦"ህዝቦቼ ሆይ! ይህች ግመል የአላህ ተዐምር ናት።

ታይዋታላችሁ፤ ትዳስሷታላችሁም እናንተ ዘንድም ትኖራለች።

ባስቀመጣችሁት መስፈርት መሰረት ትልቅ እና እርጉዝ ሴት ግመል እንደመሆኗ መጠን ካሁን በኋላ ውሀችሁንም ለጋራ ነው ምትጠጡት።
አንድ ቀን ግመሊቱ ስትጠጣ ቀጣይ ቀን እናንተ ትጠጣላችሁ። ምክንያቱም መጀመርያ ያስቀመጣችሁት መስፈርት ይህ ነው'ና።

ነገር ግን ይህችን ግመል አንዳችሁ በመጥፎ ከተተናኮላችኋት የአላህ ፈጣኑ ቅጣት ይወርድባችኋል" በማለት አስረዳቸው።
ከዚያም ህዝቡ ለሳሊህ ዐ ሰ ያለው አመለካከት 100% ተቀየረ።ሁሉም ከማንም በላይ ሳሊህን ያከብር ጀመረ።ብዙ ሺህ ሰውም የሳሊህ ተከታይ ሆነ።
ይህ ያሳሰባቸው የከተማይቱ ሹማምንት አንድ ቀን ተሰብስበው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሲወያዩ ውለው በመጨረሻም ግመሊቱን በመግደል ተስማሙ።
ይህ የተወሰነውም በአንድ መጠጥ ቤት ውስጥ ሆነው ነበር።አጋጣሚ እዛው መጠጥ ቤት ሳሉ የመጠጥ ጥማቸው ሳይቋረጥም ከመጠጡ ቤት ጓዳ "መጠጥ አልቋል" የሚል መርዶ ደረሳቸው።
ሹመንቱም፦"ለምንድነው በርከት አድርጋችሁ ማትሰሩት" ብለው ሲጮሁባቸው
የመጠጥ ቤቱ ባለቤት፦
"ዛሬ ውሀ የግመሊቱ ተራ ስለሆነ ውሀ የለም'ና ብዙ መስራት አልቻንም" ብላ መለሰችላቸው።

ከመሀከላቸውም አንድ ቀዳር ኢብን ሳሊፍ ኢብን ጁንደዕ የተባለ አመፀኛ ከመሰል ጓደኛው ጋር ተነሳ'ና ግመሏን ሊገድል ጉዞ ጀመረ።
በጉዞ ላይ ሳሉም ሌላ ሰባት ሰዎችን መንገድ ላይ በመቀላቀል ዘጠኝ ሁነው ግመሏ ውሀ የምትጠጣበት ስፍራ ደረሱ።

ውሀው ዘንድም ደረሱ'ና በያዙት ሰይፍ ገደሏት።ከአጠገቧ ግልገሏ ነበር'ና ግልገሏንም አሳድደው በትልቅ ተራራ ላይ ይዘውት ገደሉት።ከሙጅሪምነታቸው የተነሳ የግመሊቱን ስጋ ቀኑኑ ተከፋፈሉት።

ሳሊህም ዐ ሰ ይህን በተመለከተ ግዜ፦"አሁን የጌታችሁን ቅጣት ተጠባበቁ።
የጌታችሁ ቅጣት ከመውረዱም በፊት ስጋውን ተሎ ተሎ በልታችሁ ጨርሱ" አላቸው።

ህዝቡም፦"አንተ ምን ዝም ብለህ ቅጣት ቅጣት እያልክ ትዝትብናለህ! እስቲ አምጣ ቅጣት ምትለውን" ሲሉት
ሳሊህም፦"በዚህ 3 ቀን ውስጥ የጌታችሁ ቅጣት እናንተ ላይ ተፈፃሚ ይሆናል።ለዚህም ማረጋገጫ ዛሬ ፊታችሁ ብጫ ይሆናል።
ነገ ደሞ ቀይ ይሆናል።ከነገ ወዲያ ደግሞ ጥቁር ይሆንና ትጠፋላችሁ ይህም ሀሰት የሌለው ዛቻ ነው" አላቸው።
እነዚህ የሀፅያትን ፅዋ ጠጥተው የማይጠግቡ ህዝቦችም ሳሊህን ዐ ሰ ለመግደል ወስነው ዝግጅታቸውን አጠናቀው ሳለ፣

በመጀመርያ ግመሏን በገደሉት ዘጠኙ ሰዎች ላይ እቤት ተደረመሰባቸው፣
አሁን የአመፀኞቹ ህዝቦች ፊታቸው መቀያየር ጀምሯል።ሀሉም የፊቱ ብጫ መሆን አስፈርቶት እርስ በርስ ይተያያል።
ሁለተኛው ቀን ደርሶ በነጋታው ሰዉ ሲነቃ ሁሉም ፊቱ ደም መስሏል።በድንጋጤ የሞቱትም ብዙ ነበሩ።ያን ቀን በትካዜ እና በፍራቻ ካሳለፉ በኋላ የማይደርስ የለም'ና ሶስተኛዋ ቀን መጣች።

ፊቶቻቸውን ጥቁረት ወረረው፣ተስፋም ቆረጡ ሁሉም በመሰባሰብ ከፈናቸውን ለብሰው ሽቶ ተቀብተው ሞታቸውን መጠባበቅ ጀመሩ።
ልክ ፀሀይ ጀንበሯን ተሻግራ ብቅ ማለት ስትጀመር ከወደ ሰማይ በኩል እንደመብረቅ ያለ፣ ከፍተኛ ድምፅ ያለው ነገር መጣ።ምድርም በሀል መንቀጥቀጥ ጀመረች...ጂብሪልም በከፍተኛ ድምፁ ጮኸባቸው።ያን ግዜ ልቦቻቸው ከደረታቸው መበጣጠስ ጀመረ።አይኖቻቸውን ወደ ሰማይ ያፈጣሉ...

መቅሰፍቱ ከየት በኩል እንኳን እንደመጣ ማወቅ እየተሳናቸው ነፍሶቻቸው ወደ ሰውነታቸው ዳግም ላትመለስ ተነጠለቻቸው።
የከተማይቱ ህዝብ ሁሉም በያሉበት በድን ሁነው ሲሞቱ አንዲት ሴት ብቻ ቀረች ስሟም ከልባ ቢንት ሰለቅ ይባላል።

ለሳሊህ ዐ ሰ ከፍተኛ ጥላቻ ሲኖታት የክህደትን ዘውድ ከራሷ አኑራለች። ይህን ስትመለከት እግሬ አውጭኝ ብላ ከሀገሩ ሸሸች። ብዙ ከተጓዘችም በኋላ አንድ የዐረብ ነገድ የሚኖሩበትን መንደር ደረሰችና የሆነውን ሁሉ ነገረቻቸው።
በመጨረሻም ውሀ እንዲያጠጧት ጠይቃ ልክ ውሀውን ስትቀምሰው ነፍሷ የሙታንን መንደር ተቀላቀለች።
ሳሊህ ዐለይሂሰላም ወደ ሌላ ቦታ ተሰደደ ሷሊህ እና ከሱጋ ያመኑት ሰወች ወደ ተከበረቺው ወደ ተባረከቺው ፊለስጢን ሀገር ተሰደደ፡፡
ከዚያንም በረምላ ከተማ መኖር ጀመረ፡፡ ቆይቶም ሷሊህ ዐለይሂሰለም በ58 አመታቸው በዛው በረምላ ከተማ የዚህችን አለም ጣጣ አጠናቅቀው ነፍሳቸውን ለጌታቸው አስረከቡ።

በነገራችን ላይ ረሱላችን (ሰዐወ) አንድ ቀን ለተቡክ ዘመቻ ባልደረቦቻቸውን ይዘው በመሄድ ላይ ሳሉ የሳሊህ ህዝቦች የጠፉበትን ከተማ ደረሱ። ማንም አይኖርበትም..የተወሰኑ ሶሃቦች በሷሊህ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ምንጮች ውስጥ ሊቀዱ ሄዱ፣ የተወሰኑት፣ ደግሞ መገልገያ እቃወችን አመጡ፥

የአሏህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መገልገያ መሰረያወቹ እንዲሰበሩ እና የተቀዳም ውሃ እንዲደፋ አዘዙ፡፡ከዚያ ውሃ የተሰረው ምግብ ሁሉ እንድደፋ አዘዙ፦ከዚያም ነቢያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፦

"ይህችን ከተማ ስትገቡ እያለቀሳችሁ ፣መልቀስ እንኳዋ ባትችሉ ለማልቀስ የዳዳቹህ ሁናቹህ እንጂ ዝም ብላችሁ እንዳትገቡ።
እኔ በነሱ የወረደው በላእ እናንተን እንዲያገኝብኝ አልፈልግም" አሏቸው።ፊዳከ አቢ ወ ኡም ወነፍሲ ወደሚ ወዒርዲ ያ ረሱሉላህ

በዚያ አከባቢም ያሉ ነገሮችን ሁሉ ለባልደረቦቻቸው አሳይዋቸው።ግመሏም የወጣችበትን እና የተገደለችበትንም ቦታ ወስደው አሳይዋቸው።

•••✿ ❒ ተ_ፈ_ፀ_መ ❒✿•••

በቀጣይ #ነብዩሏህ_ኢብራሂም(ዐ.ሰ) ታሪክ እንጀምራለን 🥰
#share
@alahu_akber1
'
የሆነ ሰዐት ላይ ሁሉም ሰው ደስተኛ ነበር 🥀
ነገ ሐሙስ ነው የቻለ ይፁም ያልቻለ ለሌሎች ያስታውስ😊


መፆም የምትችሉም share አድርጉ እሺ 😁
ደግሞ በ ዱአ አትርሱን
🥹
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
'
ፍላጎታችን በጣም በዛና የተፃፈውን ቀደር ረሳን
መንገደኞች መሆናችንን ዘነጋንና
የጥቂት ቀናት ፈተና የልብ ሰላም ነሳን::

@alahu_akber1
.
እናትህ ያንተን ሰላም መሆን ለማረጋገጥ ብላ
እንድትረግጣት ትመኝ ነበር!🥹

@alahu_akber1
“በኔ ላይ አንድን ሰለዋት ያወረደ አላህ አስር ሰለዋትን ያወርድለታል። አስር ሀጢያቱን ይሰርዝለታል። ደረጃውን በአስር ከፍ ያደርግለታል።”

ረሱል (ﷺ)

@alahu_akber1
ቆይ ግን የምር ማለት ነው የምር
" ቆይ አባቷ ቢድሯትስ?"
" ቆይ ሀብታም አግኝታ ብትሸመጥጠኝስ ?"
"በትንሽ ነገር ተጣልተን ብንለያይስ ?"
"እእ ግን የኔና የሷ ግንኙነት ሀራም ነው ? አይ አይደለም እኛኮ ጊዜያችን ገና ስለሆነ ነው እንጂ እንጋባለን ደሞኮ ከኒካህ በፊት ላለመነካካት ተማምለናል ። ቆይ ብንማማልስ ምን ለውጥ ያመጣል😫!"

ወዘተ በሚል ርዕሶች ሌትተቀን ከራስህ ጋር እየተከራከርክ እንዴት አስችሎህ ነው የወር ደሞዝህን እሷ ላይ ምትጨርሰው አኺ 😑 እንዴት ልበደንዳና ብትሆኑ ነው ከካፌ ካፌ እየዞራቹ የከተማቹን አስፓልት ምታሰረጉዱት? ደሞ እኮ አብራቹ ስትሄዱ ኩራታቹ የሆነ ከጂሀድ የተመለሰ ሙጃሂድ ነው ምትመስሉት ።

እና ደሞ ሀራም ነገር ፍቅር ላይም ሀራም ነው ከጊዜ በኋላ ሀላል ሊሆን ይችላልና እናግራራው የሚባል ነገር የለም ። 

ብቻ አደብ!😁

Copy
'
ለማንም ሰው ቢሆን ከሚገባው በላይ ዋጋ አትስጡ ።

@alahu_akber1