'
•••✿❒ ነብዩሏህ ሉጥ ዐለይሂ ሰላም ❒✿•••

#ክፍል 2

ከሓዲያኑ የሰዶም ሕዝቦች ሉጥ ላይ ማፌዛቸውንና ማስቸገራቸውን አጠናክረው ቀጠሉ።

#ውዶቼ በባለፈው ትምህርታችን ላይ ታስታውሱ እንደሆነ መላእክት ነቢዩላህ ኢብራሂም ቤት ሄደው ዘይሯዋቸው ከዚያም መላእክት ራሳቸውን ለኢብራሂም አስተዋወቁ።

“እኛ አዋቂ ልጅ እንደምታገኝ ልናበስርህ ከጌታህ ዘንድ የተላክን መልዕከተኞች ነን።” አሏቸው። «አሁን ከአንተ ቤት ወጥተን ወደ ሉጥ ሕዝቦች በመሄድ ሉጥን እንረዳዋለን።
የሕዝቦቹ መጥፊያ በዚህች ሌሊት ነው። ቀጠሯቸው ጐህ ሲቀድ ነው። በማለት መላእክቱ የመጡበትን ዓለማ ለኢብራሂም (ዐ.ሰ) አስረዱ።
ኢብራሂም በሁኔታው ተደናግጠው ነገሩ እንዲዘገይ ለማድረግ ሞከሩ። መላእክቱ ግን የአላህ ትእዛዝ ስለሆነ ሳይዘገይ የሚፈጸም መሆኑን አስረዷቸው።
መላእክቱ ከነብዩ ኢብራሂም ቤት ወጥተው ወደ ሰዶም መንደር አመሩ። አስር ሶላት ወቅት ሲሆን ሰዶም መንደር ዳርቻ ደረሱ።
እዚያ ቦታ ላይ በደን ውስጥ የሚፈስ ወንዝ ነበር። ከወንዙ ዳርቻ አንዲት ልጅ ውሃ ለመቅዳት ቆማ አገኟት። ይህች ልጅ የሉጥ (ዐ.ሰ) ልጅ ነበረች።

4ቱን ወጣቶች ስታይ ለየት ያለ ውበት ስለነበራቸው ተደናገጠች። ከ4ተኛው አንደኛው የሉጥ ቤት የት እንደሆነና እንግዳም ይቀበሉ እንደሆነ ጠየቃት።
ልጅቷም የሰዶም ሰዎችን አስፀያፊ ተግባር ስለምታውቅ «ለአባቴ ነግሬ መልሱን እስከምነግራችሁ ድረስ እዚሁ ቆዩ። ወደ ሰዶም እንዳትገቡ» ብላ አስጠነቅቃቸው የውሃ እቃዋን ወንዙ ዳር ተወችና ፈጥና ወደ አባቷ ሉጥ (ዐ.ሰ) ዘንድ በመሄድ ሦስት ወጣቶች እሳቸውን ፈልገው እንደመጡ ነገረቻቸው።

ሉጥ ይህን መልዕክት ሲሰሙ ተደሰቱ ወይስ አዘኑ? ስለሁኔታው አላህ (ሱ.ወ) በሁድ ምዕራፍ ውስጥ እንዲህ ይላል፦

وَلَمَّا جَآءَتْ رُسُلُنَا لُوطًۭا سِىٓءَ بِهِمْوَضَاقَبِهِمْ ذَرْعًۭا وَقَالَ هَـٰذَا يَوْمٌ عَصِيبٌۭ ﴿٧٧﴾
“መልዕክተኞቻችን ሉጥን በመጡት ጊዜ በነሱ (ምክንያት) አዘነ። ልቡም በነሱ ተጨነቀ። ይህ ብርቱ ቀን ነውም አለ።“ (ሁድ፥ 77)

ሉጥ (ዐ.ሰ) «ዛሬ አስቸጋሪ ቀን ነው። አሉና ፈጥነው ወደ እንግዶቹ ሄዱ። እንግዶቹን ሲያዩ ለሰዶም ሰዎች መጥፎ ተግባር እንዳይጋለጡ በመፍራት ይበልጥ አዘኑ።

ሉጥ እንግዶቹን ከየት እንደመጡ ጠየቋቸው። መልስ ሰጧቸው። ወደ የት እንደሚሄዱ ሲጠይቋቸው ግን መልስ አልሰጧቸውም ነበር። ይልቁንም በእንግድነት እንዲቀበሏቸው ጠየቋቸው። ሉጥ (ዐ.ሰ) እንግዶቹን ለማስተናገድ ስስት አልነበረባቸውም።

ነገር ግን መላእክት መሆናቸውን ስላላወቁ የመንደሩ ሰዎች አስፀያፊ ተግባራቸውን እንዳይፈጽሙባቸው ፈርተው ነበር ያዘኑት።
ከዚያም ፊት ለፊት እየመሩ እንግዶቻቸውን አስከትለው ወደ ሰዶም መንደር ገቡ።
በመንገድ ላይ እያሉ ሉጥ (ዐ.ሰ) ቆም አሉና «ከዚህ አገር ሰዎች አስጠንቅቃችኋለሁ። በመሬት ላይ እንደነዚህ ሰዎች ቆሻሻ ሰው የለም» አሏቸው። መላእክቱ ሉጥ በሰጧቸው ማስጠንቀቂያ ላይ ምንም አስተያየት ሳይሰጡ ዝም ብለው መንገዳቸውን ቀጠሉ።

ሉጥ (ዐ.ሰ) ለእንግዶቹ ይህን ያሏቸው ከሰዶማዊያን ዓይን እንዲርቁ ፈልገው ነበር። እንግዶቹ ግን ምንም ሳይናገሩ ፀጥ ብለው ቆዩ።
በዚህን ጊዜ ሉጥ (ዐ.ሰ) ወደ ሰዶም መንደር በሌሊት ተደብቀው እንዲገቡ ጠየቋቸው።

እንግዶቹ ይህን ተቀብለው ማንም ሳያያቸው ከሉጥ ጋር በመሆን በሌሊት ወደ ከተማዋ ገቡ።

ሉጥ (ዐ.ሰ) እንግዶቹ ሌሊት ገብተው ጠዋት ጐህ ሲቀድ ማንም ሳያያቸው ይወጣሉ በሚል አስበው ነበር።
ሉጥ (ዐ.ሰ) አሁን ካሁን መጥፎዎቹ ሰዎች እነዚህን እንግዶች እንዳያይዋቸው እየተጨነቁ ከ4ቱ እንግዶቻቸው ጋር

እንደምንም ወደ ቤታቸው ገቡ።ከመንደሩ ሰዎች ማንም አላያቸውም ነበር።
ነገር ግን በቤት ውስጥ የነበረችው ከሓዲዋ ሚስታቸው እንግዶቹን እንዳየች ተደብቃና ድምጽዋን አጥፍታ ከቤት ወጣች።

★ የሉጥ (ዐ.ሰ) ሚስት በፍጥነት ወደ ሰዶማዊያኑ በመሄድ በሉጥ ቤት ከሰዶም ያልሆኑ እንግዶች እንዳሉ ነገረቻቸው።

ብልሹዎቹ ሰዎች ይህን ሲሰሙ ተደስተው እየተጠራሩ ወጡ። ከዚያም በአንድ ላይ ተሰብስበው ወደ ሉጥ ቤት አመሩ።
ሉጥ (ዐ.ሰ) ማን እንደነገራቸው ሲያስቡ፡ ሚስታቸው ቤት ውስጥ አለመኖሯን አወቁ። ሐዘናቸው በጣም ጠና።
ከየአቅጣጫው የተሰበሰቡት ሰዶማዊያን የሉጥን ቤት ከበቡ። ቀጥሎም በሩን መቆርቆር ጀመሩ። ሉጥ (ዐ.ሰ) ምን እንደምፈልጉ ጠየቋቸው።
በፊታቸው ላይ መጥፎ ነገር ይነበብ ነበር። ሉጥ (ዐ.ሰ) ተንኮለኞችን ለመመለስ ቢሞክሩም አልቻሉም። ከዚያም፦

وَجَآءَهُۥ قَوْمُهُۥ يُهْرَعُونَ إِلَيْهِ وَمِن قَبْلُ كَانُوا۟يَعْمَلُونَ ٱلسَّيِّـَٔاتِ ۚ قَالَ يَـٰقَوْمِ هَـٰٓؤُلَآءِ بَنَاتِى هُنَّ أَطْهَرُ لَكُمْ ۖ فَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَلَا تُخْزُونِ فِى ضَيْفِىٓ ۖأَلَيْسَ مِنكُمْ رَجُلٌۭ رَّشِيدٌۭ ﴿٧٨﴾
“ሕዝቦቼ ሆይ! እኝህ ሴቶች ልጆቼ ናቸው። እነሱ ለእናንተ ይልቅ በጣም የጸዱ ናቸው። (አግቧቸው)።

አላህንም ፍሩ። በእንግዶቼም አታሳፍሩኝ። ከናንተ ውስጥ ቅን ሰው የለምን?” (ሁድ፥ 78)በማለት አናገሯቸው።
ሉጥ (ዐ.ሰ) ሰዎቹ ሐራምን ትተው ወደ ሐላል እንዲዞሩ መንገድ ቢያሳዩዋቸውም አሻፈረኝ በማለት መጥፎ የመሥራት ፍላጎታቸውን ለማሳካት መሞከራቸውን ቀጠሉ።
በዚህን ጊዜ ሉጥ (ዐ.ሰ) በራቸውን ዘጉ። ሰዎቹም በሩን በኃይል ነቀነቁት። ሉጥ (ዐ.ሰ) በሁኔታው ተስፋ ቆረጡ።

قَالَ لَوْ أَنَّ لِى بِكُمْ قُوَّةً أَوْ ءَاوِىٓ إِلَىٰ رُكْنٍۢ شَدِيدٍۢ ﴿٨٠﴾
“ በናንተ ላይ ለኔ ኃይል በኖረኝ ወይም ወደ ብርቱ ወገን ቢጠጋ ኖሮ (የሚሠራውን በሠራሁ ነበር)።” (ሁድ፥ 80)

አሏቸው። ሉጥ (ዐ.ሰ) የተንኮለኞቹን ክፋት ለመከላከል በቂ ኃይል በነበረኝ ብለው ተመኙ ።
በዚህን ጊዜ መልአኩ ጅብሪል ቆመና፦ይህን የሉጥን ሁኔታ እና እንግልት የተመለከቱት በወጣቶች የተመሰሉት መላዕክት ሉጥን ጠሩት'ና ሁሉንም ነገር ግልፅ አደረጉለት። መላዕክት መሆናቸውንም አክለው ነገሩት።
1፦ጂብሪል
2፦ሚካኢል
3፦ኢስራፊል
4መለከል ሞት....ነበሩ።
በመጨረሻም ይህችን ከተማ ሊያጠፏት እንደሆነ እና ሉጥ ቤተሰቦቹን እና ተከታዮቹን ሁሉ ሰብስቦ ሱብሂ ሰዐት ከተማይቱን ለቅቆ እንዲወጣ አዘዙት።በዚህ ሁኔታ ሉጥ እንግዶቹን እያወራ ሳለ ህዝቡ በሩን ሊገነጥል ተቃረበ ያን ግዜ ጂብሪልም አላህን አስፈቀደ'ና አንድ ግዜ በሩን ከፍቶ በመውጣት በክንፉ ፊት ፊታቸውን ክፉኛ መታቸው አይኖቻቸውም እዛው መፍሰስ ጀመሩ።

ጠዋት ሲነጋ ሉጥን እንደሚገድሉት እየዛቱ ሁሉም ከበሩ እየተተራመሱ ሄዱ።ከዚያም ሉጥ መላዕክቱን፦መቼ ነው እነዚህን ህዝቦች ምታጠፉት አላቸው።
እነሱም፦"ሱብሂ ላይ ነው" አሉት።

ሉጥም፦"አሁኑኑ ብታጠፏቸውስ" ሲላቸው...

መላዕክቱም፦"እንዴ ሱብሂ ቅርብ አይደል ወይ!!!" አሉት።

በነጋታው ሉጥ ተከታዮቹን፣ቤተሰቦቹን እና አመፀኛዋን ሚስቱን ይዞ ከመቅሰፍቱ ሽሽት ከከተማይቱ መውጣት ጀመረ። ሲወጣም ለተከታዮቹ በከተማይቱ የሚወርደውን መቅሰፍት ማንም ዞሮ ማየት እንደሌለበት አስጠንቅቆ ተናገረ።

አሁም ጉዞ ጀምረዋል...መላዕክቱ እዛው ከተማ ውስጥ ናቸው...ሉጥ እና ተከታዮቹ ከተማይቱን ልክ ለቀው እንደወጡ ከወደ ከተማይቱ በኩል ከፍተኛ ድምፅ ሰሙ።