#ኢብራሂም ነብዩሏህ_ዒስማኢል እና #ነብዩሏህ_ዒስሃቅ

ክፍል1⃣5⃣

አሁን ዒስማኢል (ዐሰ) ጎርምሷል፣ለሁሉ ነገር ብቁ የሆነ ወጣትም ሆኗል።ውሀ
ፍለጋ መጥተው እዛው ኑሮዋቸውን ያደረጉት የጁርሀም ብሄረሰቦችም
ኢስማዒልን እጅጉን ይወዱታልም።
ቋንቋቸውንም አስለምደውት ባህላቸውንም አላብሰውታል።ለአቅመ አዳም
መድረሱን በተመለከቱም ግዜ ከራሳቸው ዘር የሆነችን እንስትም ዳሩለት።
ኢስማዒል (ዐ ሰ) ትዳር እንደያዘ እናትየው ሀጀር ብዙም ሳትቆይ ነበር
ለፈጣሪዋ ነፍሷን ያስረከበችው።ኢስማዒልም ያለ አባት ያሳደገችው እናቱ
ስትለየው እጅጉን ቢያዝንም ምላሹ ግን ዱዓ ብቻ ነበር።
ምንም እንኳን የኢስማዒል አባት ኢብራሂም (ዐ ሰ) በዛ ግዜ ትልቅ ሽማግሌ
ቢሆኑም የአብራካቸውን ክፋይ ለመጎብኘት ከፊለስጢን ምድር መካ ድረስ
በየግዜው ይመላለሱ ነበር።ነገር ግን አሁን ትንሽ ሰንበትበት ብለዋል መካ
ከመጡ...
ልክ መካ እንደደረሱ ልጃቸው ቤት ሲገቡ የልጃቸውን ሚስት
ያገኟታል።ኢስማዒል የት እንዳለም ሲጠይቋት ለአደን ከከተማ እንደራቀ
ነገረቻቸው።
እሳቸውም ቀጠል አድርገው ፦"ልጄ ኑሯቸሁ እንዴት ነው?" ብለው ሲጠይቋት
እሷም፦"ኑሮዋችን በጣም ዝቅተኛ ነው..."በማለት ብዙ ስሞታ አቀረበች።
እሳቸውም፦"በይ ልጄ እኔ መሄዴ ነው።ኢስማዒል ሲመጣ ሰላምታዬን
አድርሺልኝ።በመቀጠልም የበሩን መዝጊያ እንዲቀይርም ንገሪው" ብለዋት
ትተው ሄዱ።
ኢስማዒልም ከአደን ሲመለስ ሚስቱ፦"አንድ ሽማግሌ ሰውዬ መጥቶ
ነበር።ሰላም በይልኝ ብሎ የበርህንም መዝግያ እንድትቀይር አዞሀል" ስትለው
አባቱ መሆኑን አውቆ የበር መዝጊያ ደሞ ሚስቱን እንደሆነ በመረዳት ሚስቱን
ፈታት።
ኢስማዒልም ሌላ አዲስ ሚስት አገባ።ከእለታት አንድ ቀንም የልጃቸው ናፍቆት
አላስቀምጥ ያላቸው ኢብራሂም ከ ፊለስጢን ምድር ልጃቸውን ሊያዩ ሲከንፉ
መጡ።
ቤት ሲደርሱ ሌላ ሴት ተመለከቱ'ና፦"ልጄ ኢስማዒል የት ነው" ብለው
ሲጠይቋት
እሷም፦"ለአደን ራቅ ወዳለ ቦያ ሄዷል ኑ ግቡ"አለቻቸው።
እሳቸውም፦" ኑሮዋችሁስ እንዴት ነው?" ሲሏት
እሷም፦"በጣም ጥሩ ነው ሁሌ ድሎት ሁሌ ምቾት ነው" ብላ መለሰችላቸው።
እሳቸውም፦" በይ ልጄ እኔ መሄዴ ነው።ኢስማዒል ሲመጣ ሰላምታዬን
አድርሺልኝ።በመቀጠልም የበሩን መዝጊያ ጠበቅ አድርጎ እንዲይዝ ንገሪልኝ"
ብለዋት ሄዱ።
ኢስማዒልም ከአደን ሲመለስ ሚስቱ፦"አንድ ሽማግሌ ሰውዬ መጥቶ
ነበር።ሰላም በይልኝ ብሎ የበርህንም መዝግያ ጠበቅ አድርገህ እንድትይዝ
አዞሀል" አለችው።
ኢስማዒልም አባቱ ይህችኛዋን ሚስቱን እንደወደዱለት ተረድቶ ይልቅ
ያከብራትም ጀመር።
ለዚያ አካባቢ እና በዙሪያዋ ላሉ ነገዶች፣ለአማሊቃዎች፣ለጁርሀሞች እና
ለየመኖች በነቢይነት ሲያገለግል የነበረው ኢስማዒል (ዐ ሰ) ቀደምት አባቶቹ
የቀመሱትን የሞት ፅዋ መቅመሻው ግዜ ሲደርስ ነስማ የተባለችውን ሴት
ልጁን የወንድሙ የኢስሀቅ ልጅ የሆነው ዒስ እንዲያገባት ተናዝዞ በተወለደ
በ173 አመቱ የሙታንን መንደር ተቀላቀለ።...{ዐለይሂ ሰላቱ ወሰላም}
አሁን እግረ መንገዳችን የኢስሀቅን ህይወት ጎራ ብለን እንመልከት...
ለኢስሀቅ አባቱ ኢብራሂም (ዐሰ) በህይወት ሳለ በ40 አመቱ ነበር ረፍቃ ቢንት
በትዋዪል ከተባለች እንስት ትዳር ያስያዘው።
ምንም እንኳን ረፍቃ መውለድ የማትችል መሃን ብትሆንም በባለቤቷ ያላሰለሰ
ዱዓ ሁለት መንታ ልጆችን ለመታደል በቅታለች።
አንደኛው፦ዒስ ሲሆን
ሁለተኛው፦ያዕቁብ (ዐሰ) ይባላል።
ዒስ የሮም ህዝቦች ቅድመ አያት ሲሆን፤ ያዕቁብ ደሞ የእስራኢላውያን ቅድመ
አያት ነው። የሁለቱም አባት ሁለቱንም ልጆቹን በጣም ቢወዳቸውም ከያዕቁብ
ይልቅ ለዒሱ ግን ለየት ያለ ቦታ ነበረው።
እናታቸው ረፍቃ ግን ያዕቁብ ታናሽ ስለሆነ ይበልጥ እሱን ነበር የምትወደው።
ኢስሀቅ ከእርጅና የተነሳ አይናቸው ማየት ካቆመ ትንሽ ሰንበትበት ብሏል።
ከእለታት አንድ ቀን ኢስሀቅ (ዐሰ) ስጋ ያምራቸውና የሚወዱትን ልጃቸውን
ዒስን አደን አድኖ ስጋ እንዲያመጣለቸው እናም ከባድ ዱዓም
እንደሚያደርጉለት ነግረውት እሱም ለአደን ሄደ።
ይህን በድብቅ ስትሰማ የነበረችውም የልጆቹ እናት ረፍቃ ለያዕቁብ ነግራው
ከፍየሎቹ ወፍራሙን ሙኩት እንዲያርድ ካደረገች በኋላ የወንድሙን ዒስን
ልብስ አልብሳው እራሱን(ዒስን) አስመስላ የሰራውን ስጋ ለአባቱ እንዲያቀርብ
አደረገች።
ያዕቁብም ያዘጋጀውን ምግብ ይዞ አባቱ ዘንድ ሲያቀርብ
አባቱ፦"ማን ነህ አንተ?" አሉት።
ያዕቁብም፦"ልጅዎት ነኝ"አለ።
አባቱም(ኢስሀቅ)፦"ድምፅህ የያዕቁብ ነው፤ልብስህ ግን የዒስ ነው" በማለት
የቀረበላቸውን ምግብ በሉት።
ምግቡን በልተው እንደጠገቡም ምግቡን ላቀረበው አላህ ክብሩን ከፍ
እንዲያደግለት፣ የበላይ ዘርም እንዲያደርገው፣ልጆቹንም ሪዝቁንም አላህ
እንዲያበረክትለት ዱዓ አደረጉ።
ልክ ዱዓውን እንዳጠናቀቁ ያዕቁብ አሚን ብሎ የአባቱን ክፍል ለቆ
ወጣ።ያዕቁብም ሲወጣ ዒስ በታዘዘው መልኩ ያደነውን ስጋ ጠባብሶ ለአባቶ
አመጣ'ና አቀረበ። አባቱ ግን ቅድሙኑ ጠግበዋል።
ዒስ ምግቡን ሲያቀርብላቸው፦"ልጄ ይህ ምንድነው?" አሉት።
ዒስ'ም፦"አምጣልኝ ያሉት ስጋ ነዋ" አላቸው።
አባትየውም፦"አሁን አምጥተህልኝ በልቼ ዱዓ አላደረግኩልም እንዴ!!!"ሲሉት
ወንድሙ ያዕቁብ እንደቀደመው እና ዱዓውንም ሸውዶ እንደተቀበለ በመረዳት
ሀይለኛ እልህ ያዘው።
ዒስ አባታቸው ኢስሀቅ ከሞተ ያዕቁብን እንደሚገድለውም ይዝትበት
ጀመር።ያን ግዜ አባት ለልጃቸው ዒስ ማስተዛዘኛ ይሆም ዘንድ፦"አላህ
ዝርያዎችህን ጠንካሮች ያድርጋቸው፣ፍራፍሬዎችን እና ሪዝቆቹንም አላህ ሰፋ
አድርጎ ይስጥህ" በማለት ዱዓ አደረጉለት።
ነገር ግን እናት ልጇ ያዕቁብ ላይ ሚዛተው ዛቻ እረፍት ነስቷት ስለነበር የዒስ
ቁጣ እስኪበርድለት ድረስ ያዕቁብን ሀራን በሚባል አካባቢ ወደሚገኘው
ወንድሟ (ላባን) ላከችው።
ያዕቁብም ስንቁን ይዞ ወደ አጎቱ ላባን እየተጓዘ ሳለ መንገድ ላይ መሸበት እና
አንድ ድንጋይ ተንተርሶ ፏ ያለ እንቅልፍ ተኛ።
እዛው በተኛበትም በህልሙ ወደ ሰማይ መወጣጫ ይመለከታል።በዚያ
መወጣጫ መላዕክት ይወጣሉ...ይወርዳሉ።በዚያ መሀከል አላህም፦"እኔ
አንተን እባርክሀለሁ።ዝሪያዎችህንም አበዛልሀለሁ...ምድርንም ላንተ እና
ለዝርያዎችህ አደርጋታለሁ" አለው። በህልሙ ማለት ነው....
ልክ ይሄን እንዳየ ከእንቅልፉ ነቃ። ባየው ነገርም በጣሙን ተደሰተ'ና፦"ጌታዬ
አሁን ከምሄድበት በሰላም ከመለስከኝ እዚህ ቦታ ላይ ላንተ አምልኮ እሚሆን
ቤት እገነባለሁ።ከሚኖረኝም ሀብት አንድ አስረኛውን ባንተ መንገድ አውላለሁ"
በማለት እዛ ቦታ ላይ የሆነ ምልክት አድርጎ ስለት ገብቶ ጎዞውን ቀጠለ።
ብዙ ተጉዞ የሀራንን ምድር ደረሰ'ና ከአጎቱም ተገናኘ።ለአጎቱ ሁለት ሴት ልጆች
ነበሩት አንዷ (ለያ) ስትባል ታናሿ ደሞ (ራሂል) ትባላለች።
ምነው ለያ ራሂል...ስል የዩሱፍ ፊልም ትዝ አላችሁ ሀ....!!! ቆይ ዩሱፍንም
ደርሰነዋል ትንሽ ነው የቀረን።
ትንሸኛዋ ራሂል ቆንጅዬ ነገር ስትሆም ትልቋ ግን እስከዚህም ነገር
ነበረ።ከዚያም ያዕቁብ ትንሸኛዋ ራሂል በልቡ መግባቷን ሲያውቅ አጎቱን ላባንን
እንዲድረው ጠየቀው።
አጎቱም፦"7 አመት በጎችን ካገድክልኝ እድርሀለሁ" በማለት ቃል ገባለት'ና
ያዕቁብም ቆንጂዬዋን ራሂልን ለማግኘት ለ7 ተከታታይ አመታት እረኛ ሆኖ
አሳለፈ።
የማይደርስ የለም'ና ሰባቱ አመት ተጠናቅቆ የቀጠሮው ቀን ብቅ አለ።ላባንም
ድል ያለ ድግስ ደግሶ ዘመድ አዝማድ ከጠራ በኋላ ኒክህ እስሮ ሙሽሪትንም
ለያዕቁብ አስረከበው።
በማግስቱ ጠዋት ላይ ጨለማው በብርሀን መገፈፍ ሲጀ
#ነብዩሏህ_ያዕቆብ(ዐ,ሰ)

ክፍል 1⃣6⃣

ያዕቁብ ሙሽሪትን ተመለከታት ነገር ግን 7 አመት ለሷ ብሎ በግ የጠበቀላት
ራሂል ሳትሆን ብዙም ማታምረዋ ለያ ሆና አገኛት።
ያዕቁብ በጣም ተናደደ በጠዋት አጎቱ ጋ በመሄድ፦"አንተ ቃል ኪዳንን
አፍርሰሀል።እኔ የተዋዋልኩት ልጅህን ራሂልን ሀኖ ሳለ እንዴት ለያን
ትሞሽርልኛለህ" በማለት ወቀሰው።
የያዕቁብ አጎትም ላባን ብልጣ ብልጥ ነገር ነበር'ና፦"ይህማ በኛ ባህል ነውር
ነው...እንዴት ታላቅ እያለች ታናሽ ትዳራለች!!! በል ራሂልን ምትፈልግ እንደሆን
ለ7 አመት በጎችን አግድልኝ" አለው።
ያዕቁብም ራሂልን በጣም ወዷት ስለነበር 7 አመታትን ለመጠበቅ
ተገደደ።የማይደርስ የለም'ና ይህም ቀን ደረሰ።ያዕቁብም ለ14 አመት
የጠበቃትን ራሂልን በእጁ አስገባት።
(በነገራችን ላይ ሁለት እህትማማቾችን በአንድ ግዜ ማግባት በነሱ ህግ/ሸሪዓ
ክልክል አልነበረም።ከዚያ በኋላ ነው ተውራት ሲወርድ ይህ ህግ የተሻረው።)
ከዚያ ያዕቁብ ሁለት እህትማማቾችን አግብቶ ሳለ አጎቱ ላባን ለሁለት ለልጆቹ
ሁለት አገልጋዮችን በስጦታ መልኩ ጀባ አላቸው።
ለያ ለምትባለዋ፦ዘልፋ የምትባል አገልጋይ ሲሰጣት
ራሂል ለምትባለዋም፦በልሃ የምትባል አገልጋይ ሰጣት።
አላህም ለያ የምትባለዋን(ፉንጋዋን) 4 ወንድ ልጆችን በመስጠት
ካሳት።ልጆቿም
1፦ረውቢል
2፦ሸምዑን
3፦ላዊ
4፦የሁዳ...ናቸው።
ትንሿ ረሂል ምንም እንኳም ቆንጅዬ ብትሆንም ልጅ መውለድ ግን
አትችልም።በታላቅ እህቷ መውለድ በጣም ቅናት ይይዛት'ና እራሷ ዘንድ
የምትገኘውን በልሀ የተባለችውን አገልጋይ ለገዛ ባለቤቷ ዳረችው'ና
አገልጋይዋም ከያዕቁብ
5፦ዳን
6፦ኒፍታሊ...የተባሉ ልጆችን ወለደች።
ያን ግዜ ለያ ከእህቷ ረሂል እልህ ተያያዘች'ና እሷም ዘልፋ የምትባል
አገልጋይዋን ለያዕቁብ ዳረችለት'ና ያዕቁብም ከዘልፋ
7፦ጃድ
8፦ዐሺር...የተባሉ ልጆችን ወለደችለት። ኧረ የሌላ ይደላል ያዕቁብ ዐ ሰ
በመሀል ተመቻቸው እኮ...ሱብሀን አላህ የአላህ ተርቲብ
ከዚያም ለያ(ታላቋ) አምስተኛ አረገዘች'ና
9፦ያሳካር...የተባለ ልጅ ወልዳ ብዙም ሳትቆይ
10፦ዛብሎን... የተባለ ልጅ ደገመች።አሁንም አላረፈችም
11፦ዲና... የምትባል ሴት ልጅ ለያዕቁብ አሳቀፈችው።ያ ማለት ለያ
ከያዕቁብ 7 ልጆችን ወለደች ማለት ነው።
ይህን ስታይ መቋቋም ያቃታት ራሂል አላህን ልጅ እንዲሰጣት መማፀን
ጀመረች።አላህም በሩን ያንኳኳውን በከንቱ ማይመልስ ጌታ ነው'ና ዱዓዋን
ተቀብሎ
12፦ዩሱፍ (ዐሰ) የሚባል ውብ እና ገራሚ የሆነ ልጅ ጀባ አላት።
ይህ ሁሉ የሚሆነው በአጎቱ ሀገር በሀራን ምድር ላይ ነው።አሁን ያዕቁብ
የትውልድ ሀገሩን ፊለስጢንን ለቅቆ የሀራንን ምድር ከረገጠ 20 አመታትን
አስቆጥሯል።
ያዕቁብም አጎቱ ዘንድ በመሄድ፦"አጎቴ አሁን ፍቀድልኝ'ና ሚስት ልጆቼን
ሰብስቤ ቤተሰቦቼ ጋር ልሂድ" ይለዋል።
አጎቱ ላባንም፦"ያዕቁብ እኔ ባንተ ሰበብ ብዙ ንብረቴ በረካ ሆኖልኛል።ስለዚህ
የፈለግከውን ያህል ንብረት ጠይቀኝ" አለው።
ላባን በጣም ለቁጥር ሚያዳግት የእንስሳት መዐት ስለነበረው
ያዕቁብም፦"በዚህ አመት የሚወለዱትን ሁሉ ባጎች ስጠኝ።
ከተቀረው እንስሳቶችህ መልካቸው ጥቁር በነጭ የሚወልዱትንም ስጠኝ።
ነጭ ዳማዎችን እና ቀይ ዳማዎችንም ስጠኝ" አለው።
አጎቱ ላባንም፦"እሺ" አለው።
ያዕቁብም ይህን ሀላፊነት ልጆቹ እንዲወጡ አዘዘ።በመጀመርያ ያዕቁብ እርጉዝ
የሆኑ እንስሳቶችን ከሌሎቹ እንስሳት የሶስት ቀን መንገድ ያህል ርቀት
አራራቃቸው።
ነጭ ዳማዎችን እና ቀይ ዳማዎችን እንደዚያው አራራቃቸው።ይህን ካደረገ
በኋላ እርጉዞቹም ወለዱ ያዕቁብም ድርሻውን ለይቶ በአላህ ትዕዛዝ ለጉዞ
ተዘጋጀ።
አሁን ያዕቁብ የብዙ ሺህ በጎች...እንስሳቶች...እና የብዙ አገልጋዮች ባለቤት
ሆኗል።ወደ ፊለስጢን ጉዞ ሲዝጀምሩ ራሂል የተባለችዋ የያዕቁብ ሚስት
የአባቷን ጣኦት ደብቃ ይዛ ወጣች።
ያዕቁብ ልጆቹን፣ሚስቶቹን፣አገልጋዮቹን፣እንስሳቶቹን...ሁሉ ሰብስቦ በረሀውን
እያቋረጠ ብዙ ተጎዞ የሀራንን ምድር ካጋመሰ በኋላ አጎቱ ላባን እና የሀራን
ከተማ ነዋሪዎች ተከትለውት ደረሱበት።
ልክ እንዳገኙት አጎቱ ላባን በወቀሳ መልኩ፦"ያዕቁብ ለምን ሳትነግረኝ ትተህ
ትሄዳለህ!!! ምነው በደስታ ተሰነባብተን ከአከባቢው ህዝብ ጋር ጨፍረን
ብንሸኛቹስ" በማለት አንድ ጣኦት ይዘው እንደመጡም አክሎ ጠየቀው።
ያዕቁብ ዐ ሰ ምንም አይነት ከጣኦት ጋር ግንኙነት ባይኖረውም ለአጎቱ ሲል
የሚስቶቹን እቃ ሀሉ ፈተሸለት ምንም አላገኘም።
ራሂል ግን ጣኦቱን ይዛው ስለነበር ለፍተሻ ፍቃደኛ አልሆነችም ነበር አሞኛል
አልነሳም አለች።ያን ግዜ ያ ጣኦት ምናልባት ጀልዓድ በተባለ ዳገት ላይ
ይኖራል በሚል ግምት ላባን ልጆቹን እና የእህቱን ልጅ ያዕቁብን ተሰናብቷቸው
ተመለሰ።
ያዕቁብ የትውልድ ሀገሩን ሊገባ ጥቂት ሲቀራው መላዕክት እየወረዱ እንኳን
ደህና መጣህ እያሉት ያልፉ ነበር።
አሁን ያዕቁብ ሳዒር የምትባል ቦታ ላይ ደርሷል ግን ሀገሩ ሊገባ የወንድሙን
በቀል ፈርቷል።እዛው ሆኖ እንደማለማመጥ አይነት ነገር ፅፎ ደብዳቤ
ለወንድሙ ላከለት።
በነጋታው ሌላ የዛቻ ደብዳቤ የያዘች ወረቀት ዒስ(የያዕቁብ ወንድም) 400
እግረኛ ጦር አሰልፎ እየመጣ መሆኑን የሚያስረዳ መልዕክት ከወደ ፊለስጢን
በኩል ለያዕቁብ መጣችለት።
ያዕቁብም ፈራ...አላህንም ከወንድሙ ተንኮል እንዲታደገው
ተማፀነ...ለአላህም ስለት ገባ።
ያዕቁብም ፈራ...አላህንም ከወንድሙ ተንኮል እንዲታደገው
ተማፀነ...ለአላህም ስለት ገባ።
ከዚያም ወንድሙን ሊያስደስት በርከት ያለ ስጦታም አዘጋጀለት...
200 ሴት ፍየሎችን እና 20 ወንድ ፍየሎች
200 ሴት በጎችን እና 20 ወንድ በጎች
30 (ኮርማ)በሬዎችን እና 40 ላሞች
20 ሴት ግመሎችን እና 10 ወንድ ግመሎች
እና አራቱንም የስጦታ አይነቶችን ለያይቶ ሊልክ በአራት ቡድን የተደራጀ
አገልጋዮችን አዘጋጀ እና ቀድሞ አንዱን ቡድን ለከ።
የመጀመርያው ቡድን ስጦታን ይዞ ሄዶ ትንሽ ራቅ ሲል ሁለተኛውን ይልካል
ሁለተኛውም ትንሽ ራቅ ሲል ሶስተኛውን ይልካል....እንዲ እንዲ እያለ
አራቱንም የስጦታ አይነት ከነ አገልጋዮቻቸው ጨምሮ፦"ማንም የማን ነው
ብሎ ከጠየቃችሁ ከያዕቁብ ለዒስ የተላከ ስጦታ ነው በሉ" ብሎ ላካቸው።
ይህንንም ሊያደርግ የቻለው ወንድሙ ዒስ ስጦታዎች በተከታታይ ሲመጡለት
ደስታው የላቀ ይሆናል በሚል ነው።
ከዚያም የመጀመሪያውን ስጦታ የያዘው የአገልጋልይ ቡድን ዒስ እና ወታደሮቹ
ያሉበትን ቦታ ሲደርሱ
ዒስ፦"ይህ የማን ነው?" ብሎ ጠየቀ።
አገልጋዮቹም፦" ከያዕቁብ ለዒስ የተላከ ስጦታ ነው" አሉት።
እሱን ተቀበላቸውና ሁሉም የስጦታ ነጂ ቡድኖች ስጦታዎቻቸውን ተራ በተራ
እየነዱ አስረከቡት።
ያዕቁብም ሚስቶቹን ልጆቹን እና የተቀሩ አገልጋዮቹን አስከትሎ በሌሊት ወደ
ወንድሙ ጉዞ ጀመረ።(በነገራችን ላይ በዚህች የሌሊት ጉዞ ነበር ክርስቲያን
ወገኖች ያዕቁብ እና እግዚአብሄር ተደባድበው ያዕቁብ አሸነፈው የሚሉት።)
ሌሊቱን ተጉዞ ፀሀይ ጀንበሯን አምልጣ መውጣት ስትጀምር ለ20 አመታት
ያህል የተለያዩ ወንድማሞች አይን ለአይን ተገጣጠሙ።
ዒስ 400 ጦረኛዎችን አሰልፏል።ያዕቁብም ወንድሙን ሲያየው 7 ግዜ
አጎበደደለት(ይህ በዘመናቸው ሀራም አልነበረም የዘመናቸውም ሰላምታ
ነበር።በቀጣይ ክፍላችን ለዩሱፍ ሲሰግዱ እንዳስሳለን"
ዒስ ዱዓውን ከአባቱ የዘረፈውን ወንድሙን ሲያይ ሄዶ ተጠምጥሞበት
ወንድሙን እየሳመ ያለቅስ ጀመር።በዚህ አጋጣሚ ከአጠገቡ ያሉትን ሴቶችን
ልጆችን እና አገልጋዮችን ሲመለከት፦"ይሄም
#ነብዩሏህ_ሉጥ_(ዐ.ሰ)
#ክፍል 1⃣7⃣

★ የሉጥ ሕዝቦች ነብያቸውን በማስተባበል በምድር ላይም ብልሹነትን አነገሱ፥ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፦
ﻭَﻟُﻮﻃًﺎ ﺇِﺫْ ﻗَﺎﻟَﻠِﻘَﻮْﻣِﻪِۦٓ ﺃَﺗَﺄْﺗُﻮﻥَ ﭐﻟْﻔَـٰﺤِﺸَﺔَ ﻭَﺃَﻧﺘُﻢْ ﺗُﺒْﺼِﺮُﻭﻥَ ﴿٥٤﴾ ﺃَﺋِﻨَّﻜُﻢْ ﻟَﺘَﺄْﺗُﻮﻥَ ﭐﻟﺮِّﺟَﺎﻝَ ﺷَﻬْﻮَﺓًۭ ﻣِّﻦ
ﺩُﻭﻥِ ﭐﻟﻨِّﺴَﺎٓﺀِ ۚ ﺑَﻠْﺄَﻧﺘُﻢْ ﻗَﻮْﻡٌۭ ﺗَﺠْﻬَﻠُﻮﻥَ ﴿٥٥ ﴾
#“ሉጥንም_ለሕዞቦቹ_ባለ_ጊዜ_(አስተውስ)_እናንተ_የምታዩ_ስትኾኑ_ጸያፍን_ነገር_ትሠራላችሁን። #እናንተ_ከሴቶች_አልፋችሁ_ወንዶችን_ለመከጀደል_ትመጣላችሁን_በውነቱ_እናንተ_የምትሳሳቱ_ሕዝቦች_ናችሁ። (አን-ነምል፥ 54-55)

እነዚህ ሕዝቦች በምሥራቃዊ ዮርዳኖስ ይኖሩ ነበር። ይህ ቦታ በሙት ባህር
አቅራቢያ ይገኛል። በአካባቢው አምስት መንደሮች ነበሩ። እነሱም;- “ሰዱም፣
ዑመራ” “አደመህ” “ሱወይም” “ባሊ’ዕ” ናቸው። ሉጥ (ዐ.ሰ) በዋናው
መንደር ሰዱም ይኖሩ ነበር። መጥፎና ርካሽ ተግባራትን ትፈፅም የነበረችውም
መንደር እሷ ነች።
የሰዱም ነዋሪዎች እርኩሶችና መጥፎ ከመሥራት የማይፈሩ ነበሩ። አስፀያፊ
ተግባራቸውን በግልጽ የሚፈጽሙበት መሰብሰቢያ ቦታ ነበራቸው። መንገደኛን
ይዘርፋሉ። ከሌላ አካባቢ ነጋዴዎች ከመጡ ተሰብስበው ዕቃቸውን ይቀማሉ።
የሉጥ ሕዝቦች ነፍሳቸውንም በእጅጉ የሚበድሉ እጅግ ቆሻሾች ነበር።
ካቆሻሻነታቸው የተነሳ በፆታ ግንኙነት ከሴት ይልቅ ወንድ ከወንድ ጋር መገናኘት
ይመርጡ ነበር።
እነዚህ ሰዎች መጥፎ ተግባራቸው ወሰን ያለፈ ስለሆነ ይህ አስፀያፊ ተግባር
ወደ ሌሎችም አካባቢዎች እንዳይዛመት እነሱን በማስተካከል ወይም
በማጥፋት ይህን መጥፎ ተግባራቸውን ማስወገድ የግድ ነበር። ምክንያቱም
ሲባል ነው።
# የሉጥ_ጥሪ
★ ሉጥ (ዐ.ሰ) ሕዝቦቻቸው የሚሠሩትን አስፀያፊ ነገር ሲያዩ የወገኖቻቸው
በዚህ ሁኔታ መገኘት አሳሰባቸው። ሥነ-ምግባራቸው እንዲስተካከል
በማሰብም ምክር መለገስ ጀመሩ። የሉጥ ጥሪ ሥነ-ምግባራቸው በጅጉ
ለተበላሹና ቀልባቸው ለደረቀ ሰዎች የሚደረግ በመልካም ተግባር ማዘዝና
ከመጥፎ መከልከል ነበር። እነዚህ ሰዎች ምንም ሐያእ /ሐፍረት/ የሌላቸውና
አስጸያፊ ወንጀልን በጠራራ ፀሐይ የሚፈፅሙ ነበሩ። ከዚህም በላይ ሴት
በማግባት አላህ የፈቀደላቸውን ግንኙነት መፈጸም ትተው ከወንዶች ጋር
በመገናኘት ማንም አድርጎት የማያውቀውን አስጸያፊ ተግባር ይፈፅሙ ነበር።
ስለዚህም አላህ (ሱ.ወ) ሉጥ (ዐ.ሰ) ወደ እነዚህ ሕዝቦች ሄደው ከቆሻሻ
ተግባራቸው እንዲፀዱ ጥሪ እንዲያደርጉላቸው ላካቸው።
ሉጥ (ዐ.ሰ) የነበዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) የወንድም ልጅ ሲሆኑ በኢራቅ ባቢል
ነበር የተወለዱት። ነቢዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ወደ ተውሂድ ጥሪ ሲያደርጉ
አምነው ከሳቸው ጋር ወደ ሻም አካባቢ ስደት በመሄድ በምሥራቅ ዮርዳኖስ
በሚገኘው ሱዲም ሸለቆ አካባቢ ሰፈሩ። በአካባቢው ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት
የምትፈጽስም ሰዱም የምትባል መንደር ነበረች። አላህ (ሱ.ወ) ነቢዩላህ
ሉጥን ወደ ሰዶምና አካባቢዋ ሕዝቦች፣ አላህን ብቻ እንዲያመልኩና ከመጥፎ
ተግባራቸው እንዲርቁ ለማስተማርና ወንድ ለወንድ ግንኙነት መፈጸማቸውን
ትተው አላህ የፈቀደላቸውን ሴቶቻቸውን በማግባት ግንኙነት እንዲፈፅሙ
እንዲያዟቸው አላህ ሉጥን ላካቸው። ይህ ዓይነቱ ወንጀል ከሰዶም ሕዝቦች
በፊት ማንም ያልሠራው አስጸያፊ ወንጀል ነበር
ነቢዩላህ ሉጥ (ዐ.ሰ)
ﺇِﺫْ ﻗَﺎﻝَ ﻟَﻬُﻢْ ﺃَﺧُﻮﻫُﻤْﻠُﻮﻁٌ ﺃَﻟَﺎ ﺗَﺘَّﻘُﻮﻥَ ﴿١٦١﴾ ﺇِﻧِّﻰ ﻟَﻜُﻢْ ﺭَﺳُﻮﻝٌ ﺃَﻣِﻴﻦٌۭ ﴿١٦٢﴾ ﻓَﭑﺗَّﻘُﻮﺍ۟ ﭐﻟﻠَّﻪَ
ﻭَﺃَﻃِﻴﻌُﻮﻥِ﴿١٦٣﴾
#“አትጠነቀቁምን? #እኔ_ለናንተ_ታማኝ_መልዕክተኛ_ነኝ።_አላህንም_ፍሩ።_ታዘዙኝም” (አሽ-ሹዐራእ፥ 161-163)
አሏቸው።
እንዲሁም ሉጥ እያዘኑላቸው ለዘብ ባለ ቃል!
ﻭَﻣَﺎٓ ﺃَﺳْـَٔﻠُﻜُﻢْ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﻣِﻦْ ﺃَﺟْﺮٍ ۖ ﺇِﻥْ ﺃَﺟْﺮِﻯَ ﺇِﻟَّﺎ ﻋَﻠَﻰٰ ﺭَﺏِّ ﭐﻟْﻌَـٰﻠَﻤِﻴﻦَ﴿١٦٤ ﴾
#“በርሱም_ላይ_ምንም_ዋጋ_አልለምናችሁም። #ዋጋዬ_በዓለማት_ጌታ_ላይ_እንጅ_በሌላ_አይደለም።” (አሽ-ሹዐራእ፥ 164) በማለት አስገነዘቧቸው።

በዚህ ቃላቸው ውስጥ ሉጥ (ዐ.ሰ) ከነሱ ዓለማዊ ጥቅም እንደማይሹና
ብቸኛው ፍላጐታቸው የነሱ መስተካከልና አላህን ብቻ ማምለካቸው እንደሆነ
አስረዷቸው።
በመቀጠልም ሉጥ (ዐ.ሰ) ወደነዚህ ሰዎች አስፀያፊ ተግባር በመዞር
የሚከተለውን ተናገሯቸው።

ﻭَﻟُﻮﻃًﺎ ﺇِﺫْ ﻗَﺎﻝَ ﻟِﻘَﻮْﻣِﻪِۦٓ ﺃَﺗَﺄْﺗُﻮﻥَ ﭐﻟْﻔَـٰﺤِﺸَﺔَﻭَﺃَﻧﺘُﻢْ ﺗُﺒْﺼِﺮُﻭﻥَ ﴿٥٤﴾ ﺃَﺋِﻨَّﻜُﻢْ ﻟَﺘَﺄْﺗُﻮﻥَ ﭐﻟﺮِّﺟَﺎﻝَ ﺷَﻬْﻮَﺓًۭ ﻣِّﻦ
ﺩُﻭﻥِ ﭐﻟﻨِّﺴَﺎٓﺀِ ۚ ﺑَﻠْﺄَﻧﺘُﻢْ ﻗَﻮْﻡٌۭ ﺗَﺠْﻬَﻠُﻮﻥَ ﴿٥٥ ﴾ ۞
#“ሉጥንም_ለሕዝቦቹ_ባለ_ጊዜ_(አስተውስ)_እናንተ_የሚታዩ_ስትኾኑ_ጸያፍን_ነገር_ትሠራላችሁን። #እናንተ_ከሴቶች_ወንዶችን_ለመከጀል_ትመጣላችሁን_በውነት_እናንተ_የምትሳሳቱ_ሕዝቦች_ናችሁ። (አን-ነምል፥ 54-55)

የሰዶም ሰዎች አስፀያፊ ተግባራቸውን በግልጽና በስብሰባ ቦታዎች ሁሉ
ሳይቀር መፈጸማቸው ሉጥን በጣም አሳዘነ። #ሉጥ (ዐ.ሰ) ከዚህ አስፀያፊ
ተግባር ቢከለክሏቸውም «አንተ ሴቶችን አስተናግድ ወንዶችን ተውልን።»
በማለት አስፀያፊ መልስ ሰጧቸው።
ይህ ሁሉ ቢሆንም ነቢዩላህ #ሉጥ (ዐ.ሰ) ተስፋ ባለመቁረጥ የተለያዩ
ማስረጃዎችን በመጥቀስ ጥሪያቸ እውነት መሆኑን ሊያሳምኗቸው ሞከሩ።
ነገር ግን ድካማቸው በከንቱ ነበር። ቀናት ወራትን ወራት ዓመታትን እየተኩ
ዘመኑ ሄደ። #ሉጥም ዳዕዋቸውን ቀጠሉ። ነገር ግን ከቤተሰባቸው ውጭ
አንድም ሰው አላመነላቸውም ነበር። ከቤተሰባቸውም ውስጥ ሚስታቸው
አላመነችም ነበር። ከከሓዲያን ጐን ተሰለፈች። ይህም ሁኔታ #ሉጥ (ዐ.ሰ)
ከቤታቸው ውጭ ከሓዲያንን፣ በቤት ውስጥ ደግሞ ከሓዲት ሚስታቸውን
መታገል አስገደዷቸው። ስለሆነም በጣም ድካም ይሰማቸው ነበር። ቢሆኑም
ግን ትዕግስት እያደረጉ ያለ መሰላቸት ወደ አላህ ጥሪ ማድረጋቸውን ቀጠሉ።
ሕዝባቸው ግን ማመናቸው ቀርቶ በዳዕዋቸው በማላገጥ #“ከእውነተኞቹ_እንደሆንክ_የአላህን_ቅጣት_አምጣብን።” (አል-ዐንከቡት፥ 29)

ሉጥ (ዐ.ሰ) ሕዝባቸው ቢቀልዱባቸውም ታግሰውና ችለው አሁንም
ማስተማራቸውን ቀጠሉ። ከሓዲያኑ የሰዶም ሕዝቦች ሉጥ ላይ ማፌዛቸውንና
ማስቸገራቸውን አጠናክረው ቀጠሉ። ሉጥ (ዐ.ሰ) በአላህ (ሱ.ወ)
እንደሚጠበቁ በመዘንጋት የሰዶም ሕዝቦች ሊያጠቋቸው ሞከሩ።
ሉጥንና ቤተሰባቸውን በመናቅም።
#ﻭَﻣَﺎ ﻛَﺎﻥَ ﺟَﻮَﺍﺏَ ﻗَﻮْﻣِﻪِۦٓ ﺇِﻟَّﺎٓ ﺃَﻥ ﻗَﺎﻟُﻮٓﺍ۟ ﺃَﺧْﺮِﺟُﻮﻫُﻤﻢِّﻥ ﻗَﺮْﻳَﺘِﻜُﻢْ ۖ ﺇِﻧَّﻬُﻢْ ﺃُﻧَﺎﺱٌۭ ﻳَﺘَﻄَﻬَّﺮُﻭﻥَ ﴿٨٢ ﴾
#“ሉጥንና_ተከታዮቹን_ከከተማችሁ_አውጧቸው። አሉ። #እነሱ፡_የሚጥራሩ_ሰዎች_ናቸውና።” (አል-አዕራፍ፥ 82)
አሉ። የሰዶም ሕዝቦች ቆሻሾች ስለነበሩ ነቢያቸው ሉጥ «ከመጥፎ ነገር
ተመለሱ። በተመሳሳይ ፆታ መካከል ግብረ ሥጋ ግንኙነት አትፈጽሙ።» ብለው ሲመክሯቸው በሉጥና ተከታዮቻቸው ንፁህነት በመቀለድ “እነሱ ንፁሃን ናቸው”
ሲሉ አሾፉባቸው።
★ ሉጥ (ዐ.ሰ) ሕዝባቸው ቢቀልዱባቸውም ታግሰውና ችለው አሁንም ማስተማራቸውን ቀጠሉ።

ክፍል1⃣8⃣ ኢንሽአላህ
ይ..ቀ.ጥ.ላ.ል
#share
@alahu_akber1
#ነብዩሏህ_ሉጥ_ (አለይሂ ሰላም)

ክፍል1⃣8⃣

★ ሉጥ (ዐ.ሰ) ሕዝባቸው ቢቀልዱባቸውም ታግሰውና ችለው አሁንም
ማስተማራቸውን ቀጠሉ። ከሓዲያኑ የሰዶም ሕዝቦች ሉጥ ላይ ማፌዛቸውንና
ማስቸገራቸውን አጠናክረው ቀጠሉ። ሉጥ (ዐ.ሰ) በአላህ (ሱ.ወ)
እንደሚጠበቁ በመዘንጋት የሰዶም ሕዝቦች ሊያጠቋቸው ሞከሩ።
ውዶች በባለፈው ትምህርታችን ላይ ታስታውሱ እንደሆነ መላእክት ነቢዩላህ
ኢብራሂም ቤት ሄደው ዘይሯዋቸው ከዚያም መላእክት ራሳቸውን ለኢብራሂም
አስተዋወቁ። “እኛ አዋቂ ልጅ እንደምታገኝ ልናበስርህ ከጌታህ ዘንድ የተላክን
መልዕከተኞች ነን።” አሏቸው። «አሁን ከአንተ ቤት ወጥተን ወደ ሉጥ ሕዝቦች
በመሄድ ሉጥን እንረዳዋለን። የሕዝቦቹ መጥፊያ በዚህች ሌሊት ነው።
ቀጠሯቸው ጐህ ሲቀድ ነው። በማለት መላእክቱ የመጡበትን ዓለማ
ለኢብራሂም (ዐ.ሰ) አስረዱ። ኢብራሂም በሁኔታው ተደናግጠው ነገሩ
እንዲዘገይ ለማድረግ ሞከሩ። መላእክቱ ግን የአላህ ትእዛዝ ስለሆነ ሳይዘገይ
የሚፈጸም መሆኑን አስረዷቸው።
መላእክቱ ከነብዩ ኢብራሂም ቤት ወጥተው ወደ ሰዶም መንደር አመሩ። አስር
ሶላት ወቅት ሲሆን ሰዶም መንደር ዳርቻ ደረሱ። እዚያ ቦታ ላይ በደን ውስጥ
የሚፈስ ወንዝ ነበር። ከወንዙ ዳርቻ አንዲት ልጅ ውሃ ለመቅዳት ቆማ አገኟት።
ይህች ልጅ የሉጥ (ዐ.ሰ) ልጅ ነበረች። ሦስቱን ወጣቶች ስታይ ለየት ያለ
ውበት ስለነበራቸው ተደናገጠች። ከሦስተኛው አንደኛው የሉጥ ቤት የት
እንደሆነና እንግዳም ይቀበሉ እንደሆነ ጠየቃት። ልጅቷም የሰዶም ሰዎችን
አስፀያፊ ተግባር ስለምታውቅ «ለአባቴ ነግሬ መልሱን እስከምነግራችሁ ድረስ
እዚሁ ቆዩ። ወደ ሰዶም እንዳትገቡ» ብላ አስጠነቅቃቸው የውሃ እቃዋን ወንዙ
ዳር ተወችና ፈጥና ወደ አባቷ ሉጥ (ዐ.ሰ) ዘንድ በመሄድ ሦስት ወጣቶች
እሳቸውን ፈልገው እንደመጡ ነገረቻቸው።
ሉጥ ይህን መልዕክት ሲሰሙ ተደሰቱ ወይስ አዘኑ? ስለሁኔታው አላህ (ሱ.ወ)
በሁድ ምዕራፍ ውስጥ እንዲህ ይላል፦
ﻭَﻟَﻤَّﺎ ﺟَﺎٓﺀَﺕْ ﺭُﺳُﻠُﻨَﺎ ﻟُﻮﻃًۭﺎ ﺳِﻰٓﺀَ ﺑِﻬِﻤْﻮَﺿَﺎﻕَ ﺑِﻬِﻢْ ﺫَﺭْﻋًۭﺎ ﻭَﻗَﺎﻝَ ﻫَـٰﺬَﺍ ﻳَﻮْﻡٌ ﻋَﺼِﻴﺐٌۭ ﴿٧٧ ﴾
“መልዕክተኞቻችን ሉጥን በመጡት ጊዜ በነሱ (ምክንያት) አዘነ። ልቡም በነሱ
ተጨነቀ። ይህ ብርቱ ቀን ነውም አለ።“ (ሁድ፥ 77)
ሉጥ (ዐ.ሰ) «ዛሬ አስቸጋሪ ቀን ነው። አሉና ፈጥነው ወደ እንግዶቹ ሄዱ።
እንግዶቹን ሲያዩ ለሰዶም ሰዎች መጥፎ ተግባር እንዳይጋለጡ በመፍራት
ይበልጥ አዘኑ።
ሉጥ እንግዶቹን ከየት እንደመጡ ጠየቋቸው። መልስ ሰጧቸው። ወደ የት
እንደሚሄዱ ሲጠይቋቸው ግን መልስ አልሰጧቸውም ነበር። ይልቁንም
በእንግድነት እንዲቀበሏቸው ጠየቋቸው።
ሉጥ (ዐ.ሰ) እንግዶቹን ለማስተናገድ ስስት አልነበረባቸውም። ነገር ግን
መላእክት መሆናቸውን ስላላወቁ የመንደሩ ሰዎች አስፀያፊ ተግባራቸውን
እንዳይፈጽሙባቸው ፈርተው ነበር ያዘኑት። ከዚያም ፊት ለፊት እየመሩ
እንግዶቻቸውን አስከትለው ወደ ሰዶም መንደር ገቡ። በመንገድ ላይ እያሉ
ሉጥ (ዐ.ሰ) ቆም አሉና «ከዚህ አገር ሰዎች አስጠንቅቃችኋለሁ። በመሬት ላይ
እንደነዚህ ሰዎች ቆሻሻ ሰው የለም» አሏቸው። መላእክቱ ሉጥ በሰጧቸው
ማስጠንቀቂያ ላይ ምንም አስተያየት ሳይሰጡ ዝም ብለው መንገዳቸውን
ቀጠሉ።
ሉጥ (ዐ.ሰ) ለእንግዶቹ ይህን ያሏቸው ከሰዶማዊያን ዓይን እንዲርቁ ፈልገው
ነበር። እንግዶቹ ግን ምንም ሳይናገሩ ፀጥ ብለው ቆዩ። በዚህን ጊዜ ሉጥ
(ዐ.ሰ) ወደ ሰዶም መንደር በሌሊት ተደብቀው እንዲገቡ ጠየቋቸው።
እንግዶቹ ይህን ተቀብለው ማንም ሳያያቸው ከሉጥ ጋር በመሆን በሌሊት ወደ
ከተማዋ ገቡ። ሉጥ (ዐ.ሰ) እንግዶቹ ሌሊት ገብተው ጠዋት ጐህ ሲቀድ
ማንም ሳያያቸው ይወጣሉ በሚል አስበው ነበር።
ሉጥ (ዐ.ሰ) አሁን ካሁን መጥፎዎቹ ሰዎች እነዚህን እንግዶች እንዳያይዋቸው
እየተጨነቁ ከሦስቱ እንግዶቻቸው ጋር እንደምንም ወደ ቤታቸው ገቡ።
ከመንደሩ ሰዎች ማንም አላያቸውም ነበር። ነገር ግን በቤት ውስጥ
የነበረችው ከሓዲዋ ሚስታቸው እንግዶቹን እንዳየች ተደብቃና ድምጽዋን
አጥፍታ ከቤት ወጣች።
★ የሉጥ (ዐ.ሰ) ሚስት በፍጥነት ወደ ሰዶማዊያኑ በመሄድ በሉጥ ቤት
ከሰዶም ያልሆኑ እንግዶች እንዳሉ ነገረቻቸው። ብልሹዎቹ ሰዎች ይህን ሲሰሙ
ተደስተው እየተጠራሩ ወጡ። ከዚያም በአንድ ላይ ተሰብስበው ወደ ሉጥ ቤት
አመሩ። ሉጥ (ዐ.ሰ) ማን እንደነገራቸው ሲያስቡ፡ ሚስታቸው ቤት ውስጥ
አለመኖሯን አወቁ። ሐዘናቸው በጣም ጠና።
ከየአቅጣጫው የተሰበሰቡት ሰዶማዊያን የሉጥን ቤት ከበቡ። ቀጥሎም በሩን
መቆርቆር ጀመሩ። ሉጥ (ዐ.ሰ) ምን እንደምፈልጉ ጠየቋቸው። በፊታቸው ላይ
መጥፎ ነገር ይነበብ ነበር። ሉጥ (ዐ.ሰ) ተንኮለኞችን ለመመለስ ቢሞክሩም
አልቻሉም። ከዚያም፦
ﻭَﺟَﺎٓﺀَﻩُۥ ﻗَﻮْﻣُﻪُۥ ﻳُﻬْﺮَﻋُﻮﻥَ ﺇِﻟَﻴْﻪِ ﻭَﻣِﻦ ﻗَﺒْﻞُ ﻛَﺎﻧُﻮﺍ۟ﻳَﻌْﻤَﻞَﻥﻭُ ﭐﻟﺴَّﻴِّـَٔﺎﺕِ ۚ ﻗَﺎﻝَ ﻳَـٰﻘَﻮْﻡِ ﻫَـٰٓﺆُﻟَﺎٓﺀِ ﺑَﻨَﺎﺗِﻰ ﻫُﻦَّ
ﺃَﻃْﻬَﺮُ ﻟَﻜُﻢْ ۖ ﻓَﭑﺗَّﻘُﻮﺍ۟ ﭐﻟﻠَّﻪَ ﻭَﻟَﺎ ﺗُﺨْﺰُﻭﻥِ ﻓِﻰ ﺿَﻴْﻔِﻰٓ ۖﺃَﻟَﻴْﺲَ ﻣِﻨﻜُﻢْ ﺭَﺟُﻞٌۭ ﺭَّﺷِﻴﺪٌۭ ﴿٧٨ ﴾
“ሕዝቦቼ ሆይ! እኝህ ሴቶች ልጆቼ ናቸው። እነሱ ለእናንተ ይልቅ በጣም የጸዱ
ናቸው። (አግቧቸው)። አላህንም ፍሩ። በእንግዶቼም አታሳፍሩኝ። ከናንተ
ውስጥ ቅን ሰው የለምን?” (ሁድ፥ 78)
በማለት አናገሯቸው። ሉጥ (ዐ.ሰ) ሰዎቹ ሐራምን ትተው ወደ ሐላል እንዲዞሩ
መንገድ ቢያሳዩዋቸውም አሻፈረኝ በማለት መጥፎ የመሥራት ፍላጎታቸውን
ለማሳካት መሞከራቸውን ቀጠሉ። በዚህን ጊዜ ሉጥ (ዐ.ሰ) በራቸውን ዘጉ።
ሰዎቹም በሩን በኃይል ነቀነቁት። ሉጥ (ዐ.ሰ) በሁኔታው ተስፋ ቆረጡ።
ﻗَﺎﻝَ ﻟَﻮْ ﺃَﻥَّ ﻟِﻰ ﺑِﻜُﻢْ ﻗُﻮَّﺓً ﺃَﻭْ ﺀَﺍﻭِﻯٓ ﺇِﻟَﻰٰ ﺭُﻛْﻦٍۢ ﺷَﺪِﻳﺪٍۢ ﴿٨٠ ﴾
“ በናንተ ላይ ለኔ ኃይል በኖረኝ ወይም ወደ ብርቱ ወገን ቢጠጋ ኖሮ
(የሚሠራውን በሠራሁ ነበር)።” (ሁድ፥ 80)
አሏቸው። ሉጥ (ዐ.ሰ) የተንኮለኞቹን ክፋት ለመከላከል በቂ ኃይል በነበረኝ
ብለው ተመኙ ።
በዚህን ጊዜ መልአኩ ጅብሪል ቆመና፦ይህን የሉጥን ሁኔታ እና እንግልት
የተመለከቱት በወጣቶች የተመሰሉት መላዕክት ሉጥን ጠሩት'ና ሁሉንም ነገር
ግልፅ አደረጉለት። መላዕክት መሆናቸውንም አክለው ነገሩት።
1፦ጂብሪል
2፦ሚካኢል
3፦ኢስራፊል....ነበሩ።
በመጨረሻም ይህችን ከተማ ሊያጠፏት እንደሆነ እና ሉጥ ቤተሰቦቹን እና
ተከታዮቹን ሁሉ ሰብስቦ ሱብሂ ሰዐት ከተማይቱን ለቅቆ እንዲወጣ አዘዙት።
በዚህ ሁኔታ ሉጥ እንግዶቹን እያወራ ሳለ ህዝቡ በሩን ሊገነጥል ተቃረበ ያን
ግዜ ጂብሪልም አላህን አስፈቀደ'ና አንድ ግዜ በሩን ከፍቶ በመውጣት በክንፉ
ፊት ፊታቸውን ክፉኛ መታቸው አይኖቻቸውም እዛው መፍሰስ ጀመሩ።
ጠዋት ሲነጋ ሉጥን እንደሚገድሉት እየዛቱ ሁሉም ከበሩ እየተተራመሱ
ሄዱ።ከዚያም
ሉጥ መላዕክቱን፦"መቼ ነው እነዚህን ህዝቦች ምታጠፉት" አላቸው።
እነሱም፦"ሱብሂ ላይ ነው" አሉት።
ሉጥም፦"አሁኑኑ ብታጠፏቸውስ" ሲላቸው...
መላዕክቱም፦"እንዴ ሱብሂ ቅርብ አይደል ወይ!!!" አሉት።
በነጋታው ሉጥ ተከታዮቹን፣ቤተሰቦቹን እና አመፀኛዋን ሚስቱን ይዞ ከመቅሰፍቱ
ሽሽት ከከተማይቱ መውጣት ጀመረ። ሲወጣም ለተከታዮቹ በከተማይቱ
የሚወርደውን መቅሰፍት ማንም ዞሮ ማየት እንደሌለበት አስጠንቅቆ ተናገረ።
አሁም ጉዞ ጀምረዋል...
#ነብዩሏህ_ዩሱፍ(ዐለይሂ_ሰላም) ታሪክ

ክፍል 1⃣9⃣

ያዕቁብ ልጆቹን ሚስቶቹን እና አገልጋዮቹን ይዞ ከንዓን ምድር ላይ ኑሯቸውን
ጀምረዋል።ያዕቁብ ልጆቹን ሁሉ እላፊ በመውደዱ የሚታወቅ አባት ቢሆንም
ለየቲሞቹ #ለዩሱፍ እና #ለቢንያሚን ያለው ቦታ ልዩ ነበር።
ከእለታት አንድ ቀን #ዩሱፍ በሌሊት ተነስቶ ለአባባቱ ያየውን ድንቅ ህልም
እንዲህ ሲል ይነግረዋል፦" አባቴ ሆይ! እኔ ዐስራ አንድ ከዋክብትን ፀሐይንና
ጨረቃንም (በሕልሜ) አየሁ፡፡ ለእኔ ሰጋጆች ሆነው አየኋቸው"
አባትየውም፦"ልጄ ሆይ! ሕልምህን ለወንድሞችህ አታውራ፡፡ ላንተ ተንኮልን
ይሰሩብሃልና፡፡ ሰይጣን ለሰው ግልጽ ጠላት ነውና..... እንደዚሁም
(እንዳየኸው) ጌታህ ይመርጥሃል፡፡ ከንግግሮችም ፍች ያስተምርሃል፡፡
ጸጋውንም ከአሁን በፊት በሁለቱ አባቶችህ በኢብራሂምና በኢስሐቅ ላይ
እንዳሟላት በአንተ ላይና በያዕቆብ ዘሮችም ላይ ይሞላታል፡፡ ጌታህ ዐዋቂ
ጥበበኛ ነውና" ብሎ አብስሮት ህልሙንም ለማንም እንዳይናገር
አስጠነቀቀው።
አባትየው ያዕቁብ የዩሱፍን ህልም ከሰሙ በኋላ ለዩስፍ ያላቸው ፍቅር ወደ
አክብሮት እና ለሱ ወደ መተናነስ ያደላም ጀመር።ይህ ግን ለዩሱፍ ለአባቱ
ልጆች የእግር እሳት ሆኖባቸው ቅናት እረፍት ነስቷቸዋል።
ከእለታት አንድ ቀን የዩሱፍ የአባት ልጆች በዩሱፍ እና በአባቱ መካከል ያለውን
ፍቅር እንዴት በአጭሩ ማኮላሸት እንዳለባቸው ሊመካከሩ አንድ ቦታ
ተሰበሰቡ።ብዙ ሀሳቦችን አንስተው በመጨረሻም ዩሱፍን በአንድ ውሀው
ጨዋማ በሆነ ስምጥ ጉድጓድ ውስጥ ሊጨምሩት ወሰኑ።
ማታ ላይ አባታቸው ዘንድ በመሄድም፦" አባታችን ሆይ! በዩሱፍ ላይ ለምን
አታምነንም እኛም ለእርሱ በእርግጥ አዛኞች ነን።
ነገ ከእኛ ጋር ላከውና ይደሰት፤ ይጫወትም፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎች ነን"
በማለት ዩሱፍ ከነሱ ጋር እንዲሄድ አባታቸው ያዕቁብን ተማፀኑት።
ያዕቁብም፦" እኔ እርሱን (ዩሱፍን) ይዛችሁ መሄዳችሁ በእርግጥ ያሳዝነኛል፡፡
እናንተም ከእርሱ ዘንጊዎች ስትሆኑ ተኩላ ይበላዋል ብዬ እፈራለሁ" በማለት
መለሰላቸው።
ከዚህም ከዚያም ብለው አባታቸውን ካሳመኑት በኋላ የልባቸውን ሊፈፅሙ
ዩሱፍን ወዳጅ መስለው አቅፈው ወሰዱት።ያሰቡበትም ጉድጓድ ውስጥም
እየለመናቸው እጅ እግሩን አሳስረው ቀሚሱን አውልቀው ወረወሩት።
ማታ ሲሆንም የሁዳ ባመጣው ሀሳብ መሰረት ያወለቁትን የዩሱፍን ቀሚስ አንድ
ፍየል አርደው ቀሚሱን በፍየሏ ደም ለወሱት።በመጨረሻም ምሽቱ ሲደምቅ
እንስሳቶቹን እየነዱ መንደር ከደረሱ በኋላ የዩሱፍን በደም የተለወሰ ቀሚስ
ይዘው እዬዬዬ....በማለት እያለቀሱ ሰፈሩን ቀወጡት።
ይህን ሲያይ ያዕቁብ እግሩ ተብረከረከ ተንኮለኛ ልጆቹ በውዱ ልጁ ሴራቸውን
ተግባር ላይ እንዳዋሉ ተረዳ።
እሱም፦"ልጄ ምን ሆነ" ሲላቸው...
እነሱም፦" አባታችን ሆይ! እኛ (ለሩጫና ለውርወራ) ልንሽቀዳደም ሄድን፡፡
ዩሱፍንም ዕቃችን ዘንድ ተውነው፡፡ ወዲያውም ተኩላ በላው፡፡ አንተም
እውነተኞች ብንሆንም የምታምነን አይደለህም" አሉት (እነዚህ ቀልበ ደረቆች)
አባታቸውም፦" አይደለም፤ ነፍሶቻችሁ (ውሸት) ነገርን ለእናንተ ሸለሙላችሁ፡፡
ስለዚህ መልካም ትዕግስት (ማድረግ አለብኝ) በምትሉትም ነገር ላይ
መታገዣው አላህ ብቻ ነው" ብሎ ጉዳዩ ለአላህ የወው።
ዩሱፍም እዚያ ጉድጓድ ውስጥ ሳለ ወደ ግብፅ የሚሄድ ቅፍለት(ተጓዥ
ነጋዴዎች) በዚያ ጉድጓድ ሲያልፉ ውሀ ለመቅዳት ባልዲያቸውን ወደ ውስጥ
ወርውረው ውሀ ለማውጣት ወደ ላይ ሲጎትቱ ቆንጅዬ ልጅ ባልዲው ላይ
ተንጠልጥሎ ወጣ።
በዚህ ሁኔታ ላይ ውሀውን ሚቀዳው ሰውዬ ልጅ አገኘሁ እያለ ሲጮኽ የዩሱፍ
ወንድሞች ሰምተው መጡ'ና፦"ከኛ ያመለጠ ባሪያ ነው ከፈለጋችሁ ግዙን
እንጂ በነፃ አትወስዱም" በማለት ወንድማቸውን በርካሽ ዋጋ ለነጋዴዎቹ
ሸጡላቸው።
ነጋዴዎቹ ደግሞ ሸቀጣቸውን ከሚገዙባት ግብፅ ከተማ ሲደርሱ ለግብፅ
አስተዳዳሪ በውድ ዋጋ ሸጡለት።የሀገሪቱ አስተዳዳሪም ዩሱፍን ለሚስቱ
በስጦታ ምልኩ አበርክቶላት ልጅ ስለሌላት እንድ ልጇ አድርጋ እንድታየውም
ነገራት።
ሚስቱም እጅጉን ተደሰተች የልጁ ውበትም ከልጅነቱ ጋር አጓጊነቱም ማረካት።
ግዚያት ነጎዱ ቀን ሌሊትን ክረምት በጋን እየተተካኩ ብዙ አመታት
ተቆጠሩ።ዩሱፍም ወጣትነቱ እና የአዕምሮ ብስለቱ ይልቅ ውበቱን
ጨምሮበታል።የአስተዳዳሪው ሚስት ይህን ስታይ ሁኔታዋ እየተቀያየረ
መምጣት ጀመረ።
ከእለታት አንድ ቀንም ለዝሙት እራሷን አዘጋጅታ ክፍሏ አስጠራችው'ና በሩን
ዘጋጋች።ከዚያም፦"ተዘጋጅቼልሀለሁ ናልኝ" ስትለው
ዩሱፍም፦" በአላህ እጠበቃለሁ እርሱ (የገዛኝ) ጌታዬ ኑሮዬን ያሳመረልኝ
ነውና፤ (አልከዳውም)፡፡ እነሆ! በደለኞች አይድኑም" አላት።
በዚህ አጋጣሚ ዩሱፍ በሩን ከፍቶ ሲወጣ የሴትየዋ ባል፣የከተማይቷ
አስተዳዳሪ፣የራሱ አለቃ....በር ላይ ተገጣጠሙ።ሚስቱ ዩሱፍን ተከትላም
ስትወጣ ባሏን በር ላይ አገኘችው።ለትንሽ ሰዐት በሶስቱም መሀከል ዝምታ
ሰፈነ።በመቀጠልም ምን እየተከሰተ እንደነበር አስተዳዳሪው ሲጠይቃቸው
ሚስትየው ቀደም ብላ፦" በባለቤትህ መጥፎን ያሰበ ሰው ቅጣቱ መታሰር
ወይም አሳማሚ ስቃይ እንጂ ሌላ አይደለም" አለች።
ዩሱፍም ንግግሯ ውሸት እንደሆነ አስተባበለ በዚህ መሀልም አንድ በወራት
ቤት ያለ የዙለይካ የዘመዷ ህፃን ልጅ ሊዳኛቸው አላህ በመሀል አስገባው።
ህፀኑም፦" ቀሚሱ ከበስተፊት ተቀድዶ እንደሆነ (እሷ)እውነት ተናገረች፡፡
እርሱም ከውሸታሞቹ ነው
ቀሚሱም ከበስተኋላ ተቀድዶ እንደሆነ እሷ ዋሸች፡፡እርሱም ከእውነተኞቹ
ነው"በማለት ፍርዱን ሰጠ።
አስተዳዳሪውም በመገረም ቀሚሱን ሲመለከት የተቀደደው ከኋላ ነው።ወደ
ሚስቱ ዞር በማለት፦" እርሱ (የተናገርሺው) ከተንኮላችሁ ነው (ሴቶች)
ተንኮላችሁ በእርግጥ ብርቱ ነውና" ብሎ ወቀሳት።
ለዩሱፍም ወሬውን እንዳያሰራጭ ነገረው።
ነገር ግን በጥቂት ቀናት ውስጥ ወሬው በከተማይቱ እጅጉን ተሰራጨ።(ወይ
dire tube የለ...ወይ ethiopian dj የለ...)ግን ብቻ ወሬው ከአጥናፍ
እስካጥናፍ ተሰራጨ።ይንህ የወሬውን መሰራጨት ዙለይካ ስትሰማ አንድ ሴራ
ጠነሰሰች'ና አንድ ትልቅ ዝግጅት በማዘጋጀት የከተማውን የመሳፍንት እና
የከበርቴ ሚስቶችን ባጠቃላይ ጠራች።
ከዚያም በዝግጅቱ ሁሉም ሴት መገኘቱን ስታረጋግጥ ፍራፍሬ እና ቢለዋ
በመስጠት እሷ መብላት ጀምሩ ሳትል ማንም እንዳይበላ አዘዘቻቸው።
በዚህ መሀል አሁን መብላት ትችላላችሁ ብላ ሴቶቹ የያዙትን ፍራፍሬ
መቆራረጥ ሲጀምሩ፦"ዩሱፍ ና ግባ" በማለት ድምጿን ከፍ አድርጋ
ጠራችው።ዩሱፍም ያማረ ልብስ አስለብሳው ነበር'ና ልክ የሌሊት ጨረቃ
መስሎ ወደ ውስጥ ሲገባ ሴቱ ሁሉ አይናቸው በሱ ፈዘዘ'ና ፍራፍሬውን
ረስተው እጆቻቸውን በያዙት ቢለዋ በመሸረካከት፦" አላህም ጥራት ይገባው፡፡
ይህ ሰው አይደለም፡፡ ይህ ያማረ መልአክ እንጅ ሌላ አይደለም" ማለት
ጀመሩ።
እሷም፦"ታዲያ ይህ ያ በርሱ (ፍቅር) የዘለፋችሁኝ ነው፡፡ በእርግጥም ከነፍሱ
አባበልኩት፡፡ እምቢ አለም፡፡ የማዘውንም ነገር ባይሠራ በእርግጥ ይታሰራል፡፡
ከወራዶቹም ይሆናል" አለቻቸው።
ዩሱፍም፦"ጌታዬ ሆይ! ወደርሱ ከሚጠሩኝ ነገር (ከዝሙት) ይልቅ መታሰር
ለእኔ የተወደደ ነው፡፡ ተንኮላቸውንም ከእኔ ላይ ባትመልስልኝ ወደነሱ
እዘነበላለሁ፡፡ ከስህተተኞቹም እሆናለሁ" ሲል አላህን ተማፀነው።
የከተማይቱ አስተዳዳሪም በሚስቱ ሰበብ የጠፋውን ስሙን ለማደስ ሲል
ዩሱፍን እስር ቤት ለመጣል ወሰነ።ዩሱፍም እስር ቤት በገባ ግዜ እሱን
በፊትም የሚያውቁት ሁለት እስረኞች(አንዱ የንጉስ የምግብ ሰራተኛ ሲ
#ነብዩሏህ_ዩሱፍ(ዐለይሂ ሰላም)

ክፍል 2⃣0⃣

የከተማይቱ አስተዳዳሪም በሚስቱ ሰበብ የጠፋውን ስሙን ለማደስ ሲል
ዩሱፍን እስር ቤት ለመጣል ወሰነ።ዩሱፍም እስር ቤት በገባ ግዜ እሱን
በፊትም የሚያውቁት ሁለት እስረኞች(አንዱ የንጉስ የምግብ ሰራተኛ ሲሆን
አንዱ ደሞ የንጉስ ጠጅ ጠማቂ ነው።)
ለዩሱፍም እንዲህ ሲል አንደኛው ጠየቀው፦" እኔ በህልሜ የወይን ጠጅን
ስጠምቅ አየሁ" ሁለተኛውም፡-"እኔ በራሴ ላይ ዳቦ ተሸክሜ ከእሱ በራሪ
(አሞራ) ስትበላ አየሁ፡፡ ፍቹን ንገረን፡፡ እኛ ከአሳማሪዎች ሆነህ እናይሃለን'ና"
በማለት ጠየቀው።
ዩሱፍም እችን አጋጣሚ በመጠቀም እስር ቤት ውስጥ ላሉ እስረኞች ዳዕዋ
ለማድረግ አሰበ'ና፦"ማንኛውም የሚመጣላችሁ ምግብ ለናንተ ከመምጣቱ
በፊት ፍቹን የምነግራችሁ ቢሆን እንጂ አይመጣላችሁም፡፡ ይኸ ጌታዬ
ካሳወቀኝ ነገር ነው፤ እኔ በአላህ የማያምኑን እነርሱም መጨረሻይቱን ዓለም
እነርሱ ከሓዲዎች የሆኑትን ሕዝቦች ሃይማኖት ትቻለሁ።
የአባቶቼን የኢብራሂምንና፣ የኢስሐቅን፣
የያዕቆብንም ሃይማኖት ተከትያለሁ፤ ለኛ በአላህ
ምንንም ማጋራት አይገባንም፤ ያ (አለማጋራት)
በኛ ላይና በሰዎቹ ላይ የአላህ ችሮታ ነው፤ ግን አብዛኞቹ ሰዎች
አያመሰግኑም።
የእስር ቤት ጓደኞቼ ሆይ! የተለያዩ አምላኮች
ከብርና ከወርቅ ከእንጨት የተሠሩ...?
ይሻላሉን ወይንስ አሸናፊው አንዱ አላህ?
ከርሱ ሌላ እናንተና አባቶቻችሁ (አማልክት
ብላችሁ) የጠራችኋቸውን ስሞች እንጅ
አትግገዙም፤ አላህ በርሷ ምንም አስረጅ
አላወረደም ፍርዱ የአላህ እንጅ የሌላ አይደለም
እርሱን እንጅ ሌላን እንዳትግገዙ አዟል፤ ይህ
ትክክለኛው ሃይማኖት ነው፤ ግን አብዛኞቹ ሰዎች
አያውቁም" በማለት ወደ አላህ ከጠራቸው በኋላ
የሁለቱንም ህልም እንዲህ ሲል ፈታላቸው፦"የእስር ቤት ጓደኞቼ አንደኛችሁ ለ
ንጉሱ ጠጁን በመጥመቅ ወደ ቀድሞ ስራው ሲመለስ ሁለተኛችሁ ደግሞ
ስቅላት ተፈርዶበት ከተሰቀለ በኋላም ጭንቅላቱን አዕዋፍ ይበሉታል። ይህ
የህልማችሁ ፍቺ ጥርጥር የለውም ተፋፃሚ ነው።"
ይህን ካላቸው በኋላ ዩሱፍ ዐ ሰ ህልማቸውን በፈታው መልኩ አንደኛው
ተወስዶ ሲሰቀል አንደኛውም ወደ መጀመርያ ስራው ተመልሶ ለንጉሱ ጠጅ
እንዲጠምቅለት ተወሰነ።
ለንጉሱ ጠጅ እንዲጠምቅለት የተወሰነለት ሊወጣ ሲል ዩሱፍ
አስቆመው'ና፦"ንጉሱ ዘንድ ስትሄድ አንድ ንፁህ ሰው ያለ ወንጀሉ
በአስተዳዳሪው አማካኝነት ታስሯል ብለህ በደሌን ንገርልኝ" አለው።
እሱም እሽ ብሎ ከወጣ በኋላ ንጉሱ ዘንድ ወደ ስራ ገበታው ሲቀላቀል ዩሱፍን
ከነአካቴው ረሳው።በዚህ ሁኔታ ላይ ዩሱፍ ለረጅም አመታት ያለጥፋቱ እስር
ቤት ከረመ።
ከእለታት አንድ ቀን የሀገሪቱ ንጉሱ(በነገራችን ላይ ንጉስ እና አስተዳዳሪ ስል
እንዳይመሳሰልባችሁ እሺ...! አስተዳዳሪው ዩሱፍን የገዛው ሲሆን ንጉሱ ደሞ
ገና ዩሱፍን አያውቀውም።የአስተዳዳሪው የበላይ ነው) እናላችሁ ይህ ንጉስ
በደረቅ ሌሊት ህልም አየው ብሎ ተነስቶ ቤተ መንግስቱ በአንድ እግር
አቆመው።
በአስቸኳይ የኮከብ አዋቂዎችን እና ካህናትን በዚያ ሌሊት እንዲሰበሰቡ
አደረገ።ከዚያ ህልሙንም እንዲህ ሲል ተረከላቸው፦" እኔ ሰባትን የሰቡ ላሞች
ሰባት
ከሲታዎች ሲበሉዋቸው፣ ሰባትንም ለምለም
ዘለላዎች ሌሎችንም ደረቆችን
(ሲጠመጠሙባቸው በሕልሜ) አያለሁ፤ እናንተ
ታላላቅ ሰዎች ሆይ! ሕልምን የምትፈቱ
እንደሆናችሁ ሕልሜን ፍቱልኝ "
ካህናቱ እና ጠንቋይዎቹ የንጉሱን ህልም ሊፈቱ እጅጉን ተቸገሩ። ቢያወጡ
ቢያወርዱ በቃ ምንም ሊያውቁት አልቻሉም'ና፦"ንጉስ ሆይ! የዚህን ህልም
ፍቺ ልናውቅ ስላልቻልን ይህ ህልም ቅዠት ነው" አሉት።
ያን ግዜ ጠጅ ጠማቂው ያ የድሮ የእስር ቤቱን ህልም ፈቺ ጓደኛውን ዩሱፍን
አስታወሰ።ከመሀከል ብድግ በማለትም፦"እኔ የህልሙን ፍቺ ይዤ እመጣለሁ
ግን የእስር ቤት ፍቃድ አውጡልኝ" ሲል ለንጉሱ ተናገረ።
ንጉስም አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግለት በማዘዝ ጠጅ ጠማቂውም ዩሱፍ
ወደሚገኝበት እስር ቤት ብቅ አለ።
ዩሱፍንም ስለረሳው ይቅርታ በመጠየቅ ንጉሱ ያየውን ህልም ተረከለት'ና
ፍቺውን ጠየቀው።ዩሱፍም፦" ሰባትን የተከታተሉ ዓመታት
ትዘራላችሁ፤ ያጨዳችሁትንም ሁሉ ከምትበሉት
ጥቂት በስተቀር በዘለላው ውስጥ ተዉት።
ከዚያም ከነዚያ በኋላ፣ ካከማቻችሁት ጥቂት
ሲቀር፣ ለነሱ ያከማቻችሁትን ሁሉ የሚበሉ ሰባት
የችግሮች ዓመታት ይመጣሉ።
ከዚያም ከነዚያ በኋላ ሰዎቹ በርሱ የሚዘነቡበት፣
በርሱም (ወይንን) የሚጨምቁበት የጥጋብ ዓመት ይመጣል" በማለት
ህልሙን ብቻ ሳይሆን መፍትሄውንም ጭምር ዘረዘረለት።
ጠጅ ጠማቂውም የህልሙን ፍቺ ይዞ በደስታ ወደ ቤተ መንግስት ይገሰግስ
ጀመር ልክ እንደደረሰም ለንጉሱ ፍቺውን ከነ መፍትሄው ሲተርክለት ንጉሱ
ዩሱፍን አሁኑኑ አምጡልኝ አለ።
ዩሱፍንም ከእስር ቤት አውጥቶ የሚያመጣ ሰው ተመድቦ እስር ቤት ሲደርስ
ዩሱፍ፦" ወደ
ንጉሱ ተመለስ፤ የነዚያንም እጆቻቸውን
የቆረጡትን ሴቶች ሁኔታ ጠይቀው፤ ጌታዬ
ተንኮላቸውን አዋቂ ነውና" በማለት ይህ ጉዳይ ሳይጣራ ለመውጣት ፍቃደኛ
እንዳልሆነ ለንጉሱ ለከ።
ይህን ግዜ ንጉሱም በዚያ ቀን ያን ዝግጅት ተካፍለው የነበሩ
የመሳፍንት፣የከበርቴ እና የአስተዳዳሪውንም ሚስት አንድ ላይ እንዲ ቀርቡ
ካደረገ በኋላ፦" ዩሱፍን ከነፍሱ ባባበላችሁት ጊዜ፣ነገራችሁ(ምክንያታችሁ)
ምንድነው?" ብሎ ሲጠይቃቸው...
ሴቶቹም በአንድ አፍ፦"ለአላህ ጥራት
ይገባው፤ በርሱ ላይ ምንም መጥፎን ነገር
አላወቅንም" አሉት።
ያን ግዜ ከመሀል የአስተዳዳሪው ሚስት ቀበል አድርጋ፦" አሁን እውነቱ
ተገለጸ፤ እኔ ነኝ ከነፍሱ ያባበልኩት፤ እርሱም
ከውነተኞቹ ነው" በማለት በህዝብ ፊት የዩሱፍን ንፁህነት መሰከረች።
ንጉስ ይህን በሰማ ግዜ እውነተኛውን ዩሱፍን ለማየት እጅጉን ጉጉት
አደረበት።ነፃነትህን አስመስክረሀል ና ብሎ ጠርቶት የግል አማካሪው
ከማድረግም ባሻገር የሀገሪቱን ጉዳይ ሙሉ በሙሉ ፈላጭ ቆራጭ አደረገው።
አሁን ዩሱፍ ህዝቡ ዘንድ ልዩ ቦታ አለው።አብዝሀኛውም የሀገሪቱ ነዋሪ
የዩሱፍን ጥሪ ተቀብሏል...እንዲህ እንዲህ እያሉ 7 አመታት ካሳለፉ በኋላ
የድርቁ ዘመን ከች አለ።
ድርቁን ተከትሎ ከተለያዩ ሀገራት በድርቅ የተመቱ እህል ሸማቾች ወደ ግብፅ
ምድርም ይተሙ ጀመር።በዚያ መሀል በከንዓን ይኖሩ የነበሩ የዩሱፍ
ቤተሰቦችም የድርቁ ሰለባ ነበሩ'ና 10 ወንድሞቹ እህል ፍለጋ የግብፅን ምድር
ረግጠው በማያውቁት ወንድማቸው መጋዘን ለእህል ተሰለፉ።
____
ክፍል2⃣1⃣ ኢንሽአላህ
ይ.....ቀ......ጥ.....ላ........ል፡፡

ሌሎች የነብያት፣ የሰሃቦች ታሪክ ና የተለያዪ ትምህርታዊ ፅሁፉች ቶሎ ቶሎ
እንዲደርሶ ከስር ሊንኩን በመክፈት ግሩፑን ይቀላቀሉ እርሶ ጋር እንዲቀመጥ
አይፍቀዱ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ።
👉 https://t.me/alahu_akber1
#ነብዩሏህ_ዩሱፍ (ዐለይሂ ሰላም)

ክፍል2⃣1⃣

በዚያ መሀል በከንዓን ይኖሩ የነበሩ የዩሱፍ ቤተሰቦችም የድርቁ ሰለባ ነበሩ'ና 10 ወንድሞቹ እህል ፍለጋ የግብፅን ምድር
ረግጠው በማያውቁት ወንድማቸው መጋዘን ለእህል ተሰለፉ።
ድርቁን ተከትሎ ከተለያዩ ሀገራት በድርቅ የተመቱ እህል ሸማቾች ወደ ግብፅ
ምድርም ይተሙ ጀመር።በዚያ መሀል በከንዓን ይኖሩ የነበሩ የዩሱፍ
ቤተሰቦችም የድርቁ ሰለባ ነበሩ'ና 10 ወንድሞቹ እህል ፍለጋ የግብፅን ምድር
ረግጠው በማያውቁት የወንድማቸው መጋዘን ለእህል ተሰለፉ።
በግዜው ከመንግስት መጋዘን ሁሉም እህል ሲሸምት ስሙን እና የመጣበትን
ሀገር እያስመዘገበ ነበር የሚሸምተው።እነዚህም ወንድሞቹ ስማቸውን
እስመዝግበው እህላቸውን ከመረከባቸው በፊት ዩሱፍ የከንዓን ሰዎች
መጥተዋል የሚል ወሬ ሰምቶ ሊያጣራ ሲሄድ ወንድሞቹን ተመለከታቸው።
ምንም እንኳን እሱ ቢያውቃቸውም እነሱ ግን በፍፁም ሊያውቁት
አልቻሉም።ግን ዝም ብለው በግምት፦" ይህ ፊት አዲስ አልሆነብኝም
ይባባላሉ" እርስ በርስ....
ዩሱፍም ከተለያዩ ሀገራት ከመጡ ቁጥር ስፍር ከሌለው ሰልፈኛ መሀል ለ40
አመት የተለያያቸውን ወንድሞቹን የሰሩበትን ተንኮል ወደ ጎን አድርጎ በናፍቆት
ተሸንፎ ስለማንነቱ ምንም ሳይነግራቸው ወደሚኖርበት ቤተ መንግስት ይዟቸው
ሄድ።
ይህችን ሌሊትም እሱ ጋር አሳልፈው በነጋታው እንደሚሄዱ ካሳመናቸው በኋላ
በጥሩ መስተንግዶ እራት አብልቷቸው ያዕቁብ ስለተባለው ነቢይ መጠየቅ
ጀመረ።በህይወት እንዳለ እና ዩሱፍ በተባለው ልጁ ሀዘን ምክንያት በጣሙን
እንደተጎዳ ነገሩት።ዩሱፍ ይህን ሁሉ ሲሰማ ሆድ እየባሰው ከእንባው ጋር
ትንቅንቅ ቢገጥምም ይህን ሀዘኑን ግን ለወንድሞቹ ግልፅ ሊያደርግ
አልፈለገም።ያውቁኛል ብሎ ሰግቶ.....
በነጋታው ዩሱፍ አገልጋዮቹን ጠርቶ፦"ለእህሉ የከፈሉትን ገንዘብ
በየከረጢታቸው ውስጥ ደብቁትና ሳያውቁ ስጧቸው" ብሎ አዘዘ። ዩሱፍ
ባዘዘውም መልኩ የከፈሉት ገንዘብ ተመልሶ በየከረጢታቸው ተጨመረላቸው።
በመጨረሻም ሲሸኛቻው፦"በሚቀጥለው ዙር ስትመጡ ከንዓን ትታችሁት
የመጣችሁትን ትንሹን ወንድማችሁን ይዛችሁ ኑ። እሱን ካላመጣችሁት ግን
ምንም አይነት እህል አንሰፍርላችሁም" ብሎ ሸኛቸው።
እነሱም እንደሚሞክሩ ቃል ገብተውለት ጉዞ ወደ ከንዓን ጀመሩ።ረጅም
ተጉዘው ከንዓንም ሲደርሱም በግብፅ ከተማ የገጠማቸውን ሁሉ ለአባታቸው
ያዕቁብ ተረኩለት'ና በቀጣይ ዙር ግን ታናሽ ወንድማቸውን ቢንያሚንን
ካላመጡ ምንም አይነት ስፍር እንደማይሰፈርላቸው ነገሩት።
አባታቸው ያዕቁብ ግን ልጆቹ ከዚህ በፊት በልጁ ዩሱፍ የፈፀሙትን በማስታወስ
ዳግም ልጁን ቢንያሚንን ለነሱ አምኖ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆነም
ነበር።ይሁን እንጂ ያዕቁብ ምንም እንኳን ውድ ልጁን ቢንያሚንን ከአጠገቡ
ማራቅ ቢከብደውም ከፊትለፊቱ የተደቀነው ድርቅ እና ቸነፈር ቢንያሚንን ወደ
ግብፅ ለመላክ አስገድዶታል።
ከመላኩ በፊትም ያዕቁብ ልጆቹን ሰብስቦ፦"ካልተከበባችሁ በስተቀር እርሱን
(ቢንያሚንን) በእርግጥ
የምታመጡልኝ ለመሆናችሁ ከአላህ የሆነን ቃል
ኪዳን መተማመኛ እስከምትሰጡኝ ድረስ ከናንተ
ጋር ፈፅሞ አልልከውም" አላቸው።
መተማመኛቸውንም ቃል ኪዳን በሰጡት ጊዜ ፦"አላህ
በምንለው ሁሉ ላይ ምስክር ነው" አላቸው።
በገቡት ቃል ኪዳን መሰረትም ቢንያሚንን ከአባታቸው እቅፍ አውጥተው
ከከንዓን ምድር ነዋሪዎች ጋር ጉዞ ወደ ግብፅ ከመጀመራቸው በፊትያዕቁብ
ልጆቹን ነጥሎ፦" ልጆቼ ሆይ! ባንድ በር አትግቡ፤ ግን
በተለያየ በሮች ግቡ፤ ከአላህም (ፍርድ)
በምንም አልጠቅማችሁም፤ (አልመልስላችሁም)፤
ፍርዱ የአላህ እንጅ የሌላ አይደለም፤ በርሱ ላይ
ተመካሁ፤ ተመኪዎችም ሁሉ በርሱ ብቻ ይመኩ" ብሎ መከራቸው።
በከንዓን እና በግብፅ መሀከል ያሉትን በረሃማ እና አሸዋማ መንገዶችን
ካቋረጡ በኋላ የዩሱፍን ታናሽ ወንድም ይዘው ቤተ መንግስት ገቡ።ዩሱፍም
ከመጀመርያው በተሻለ መልኩ ካስተናገዳቸው በኋላ ታናሽ ወንድሙን ለግል
አውጥቶ፦"እነሆ እኔ ወንድምህ ነኝ ይሠሩት
በነበሩትም ሁሉ አትቆጭ" ብሎት ነገ እሱን ግብፅ ሊያስቀረው የንጉስ ዋንጫ
በሱ ከረጡት እንደሚሸጉጥበትም ጨምሮ ነግሮት ለአዳር ወንድሞቹ ጋ
አቀላቀለው።
ጠዋትም ለጉዞ በተዘጋጁ ግዜ ዩሱፍ እቃዎቻቸውን አስጭኖላቸው
ሸኛቸው።ብዙም ሳይርቁም ዩሱፍ እና ወታደሮቹ ከአንድ ኮረብታ ላይ ሆነው፦"
እናንተ ባለ ግመሎች ሆይ! እናንተ በርግጥ ሌቦች ናችሁ" በማለት
ተጣሯቸው።
እነሱም ዞረው፦" ምንድነው የጠፋችሁ?" አሉ።
ዩሱፍም፦" ፦ የንጉሡ መስፈሪያ ጠፍቶናል፤ እርሱንም ላመጣ ሰው የግመል
ጭነት ሽልማት አለው፤ እኔም በርሱ ተያዥ
ነኝ" አላቸው።
እነሱም፦" በአላህ እንምላለን በምድር ላይ ለማጥፋት
እንዳልመጣን በእርግጥ ዐውቃችኋል፤ ሌቦችም
አልነበርንም" አሉት።
ዩሱፍም፦" ውሸታሞች ብትሆኑ ቅጣቱ ምንድነው?" አላቸው።
እነሱም፦"ቅጣቱ (በያዕቆብ ሕግ) ዕቃው በጓዙ ውስጥ
የተገኘበት ሰው (ራሱን አገልጋይ አድርጎ መወሰድ) ነው፤ እርሱም
ቅጣቱ ነው። እንደዚሁ በደለኞችን እንቀጣለን" ብለው መለሱለት።
(ፍተሻውን) ከወንድሙም ዕቃ በፊት
በዕቃዎቻቸው ጀመረ፤ ከዚያም (ዋንጫይቱን)
ከወንድሙ ዕቃ ውስጥ አወጣት።ሁሉም ደነገጡ ሚሉት ጠፋባቸው በዚህ
አጋጣሚ እራሳቸውን ለማዳን፦"እሱ ቢሰርቅ ምንም አይደንቅም አንድ ታላቅ
ወንድሙም እንዲህ ይሰርቅ ነበር" አሉ።
ዩሱፍም በውስጡ፦"እናንተ ሥራችሁ የከፋ
ነው፤ አላህም የምትሉትን ሁሉ ዐዋቂ ነው" አለ።
ከዚያም እነሱ ራሳቸው በተስማሙት መሰረት እቃውን የሰረቀውን ቢንያሚንን
ዩሱፍ እና ወታደሮቹ ይዘውት ሊሄዱ ሲሉ፦"አንተ የተከበርከው ሆይ! ፦ ለርሱ
(ለቢንያሚን) በእርግጥ ትልቅ
ሽማግሌ አባት አለው፤ ስለዚህ በርሱ ፋንታ
አንደኛችንን ያዝ፤( ይህን ከፈፀምክ) እኛ ከመልካም ሠሪዎች ሆነህ
እናይሃለንና" አሉት።
ዩሱፍም፦"ዕቃችንን እርሱ ዘንድ ካገኘነው ሰው ሌላን ሰው ከመያዝ በአላህ
እንጠበቃለን፤ እኛ ያን ከፈፀምን በእርግጥ በዳዮች ነን" አለ።
ዩሱፍንም ለምነው ለምነው ተስፋ ሲቆርጡ ወደ ጎን ነጠል ብለው መመካከር
ጀመሩ።በመሀልም ታላቅ ወንድማቸው፦" አባታችሁ በናንተ ላይ
ከአላህ የሆነን መታመኛ ቃል ኪዳን በእርግጥ
የያዘባችሁ መሆኑን ከዚህም በፊት በዩሱፍ ላይ
ግፍ የሠራችሁትን አታውቁምን? ስለዚህ አባቴ
ለኔ እስከሚፈቅድልኝ ወይም አላህ ለኔ
እስከሚፈርድልኝ ድረስ የግብፅን ምድር
አልለይም፤ እርሱ ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነው።
ወደ አባታችሁ፣ ተመለሱ፤ እንዲህ በሉትም፦ አባታችን
ሆይ! ልጅህ ሰረቀ ባወቅነውም ነገር እንጂ
አልመሰከርንም፤ ሩቁንም ነገር (ምስጢሩን)
ዐዋቂዎች አልነበርንም፤
ያችንም በውስጧ የነበርንባትን ከተማ ያችንም
በውስጧ የመጣነውን ባለ ግመል ጓድ ጠይቅ፤
እኛም በእርግጥ እውነተኞች ነን በሉ" ብሏቸው እነሱን ትቶ ወደ ከተማይቱ
ገባ።
እነሱም ምንም አማራጭ አልነበራቸውምና የጫኑትን እህል ጭነው ወደ
ከንዓን ተጓዙ።ልክ ከንዓን ሲደርሱ አባታቸው መንገድ ላይ እየጠበቃቸው
ነበር።ሁሉንም ሰላም ብሎ የልጁ ቢንያሚንን መምጣት በጉጉት ሲጠብቅ
ቢንየሚን የውሀ ሽታ ሆነበት።ልጄስ ብሎ ሲጠይቃቸውም የሆነውን ሁሉ
ነገሩት።....
(አባታቸው ቢንያምን ትተው በመምጣታቸው ምን ያደርጋቸው ይመስላችሇል)፡፡

ክፍል 2⃣2⃣ ኢንሽአላህ
ይ........ቀ.. ....ጥ......ላ.....ል፡፡
👉 https://t.me/alahu_akber1
#ነብዩሏህ_ዩሱፍ (ዐለይሂ ሰላም)

ክፍል 2⃣2⃣

ሁሉንም ሰላም ብሎ የልጁ ቢንያሚንን መምጣት በጉጉት ሲጠብቅ
ቢንየሚን የውሀ ሽታ ሆነበት።ልጄስ ብሎ ሲጠይቃቸውም የሆነውን ሁሉ
ነገሩት።
ይህን ግዜ አባታቸው በተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ሆኖ፦"አይደለም
ነፍሶቻችሁ አንዳች ነገርን
ለናንተ ሸለሙላችሁ፤ (ሠራችሁትም) መልካምም
ትዕግሥት (ማድረግ) አለብኝ፤ እነርሱን፣
(ሦስቱንም ልጆቼን) የተሰበሰቡ ሆነው አላህ ሊያመጣልኝ ይከጀላል፤ እነሆ
እርሱ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና"
አላቸው።
ያዕቁብም ከአጠጋባቸው ዘወር ብሎ፦" በዩሱፍ ላይ ዋ ሐዘኔ!" እያለ
የድሮውን ዩሱፍን በማስታወስ ይንሰቀሰቅ ጀመር።
እነርሱም ፦ "በአላህ እንምላለን፤ ለጥፋት
የቀረብክ እስከምትሆን ወይም ከጠፊዎቹ
እስከምትሆን ድረስ፣ ዩሱፍን ከማውሳት
አትወገድም" አሉ።
ያዕቁብም፦"ጭንቀቴንና ሐዘኔን የማስማው፣ ወደ አላህ
ብቻ ነው፤ ከአላህም በኩል የማታውቁትን ነገር ዐውቃለሁ" አላቸው።
ቀን ቀንን እየተካ ቀስ በቀስ ልጆቹ ከግብፅ ይዘው የመጡት ቀለብ
አለቀ።ቤተሰቡም አደጋ ላይ ወደቀ። ይህን ግዜ ያዕቁብ ልጆቹን
ሰብስቦ፦"ልጆቼ ሆይ! ሂዱ፤ ስለ ዩሱፍና ስለ ወንድሙም ፊንጭ ሰብስቡ፤
ከአላህም እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፤
እነሆ ከአላህ እዝነት ከሐዲዎች ሕዝቦች እንጂ፣
ተስፋ አይቆርጥም" አላቸው።
እነሱም አባታቸው ባላቸው መልኩ ዩሱፍን እና ወንድሞቹን ፍለጋ ወደ ግብፅ
ምድር ለሶስተኛ ግዜ ብቅ አሉ። ዩሱፍ ዘንድም በመግባት፦" አንተ
የተከበርከው ሆይ!
እኛንም ቤተ ሰቦቻችንንም ጉዳት ደረሰብን፤ ርካሽ
ሸቀጥም ይዘን መጥተናል፤ ስፍርንም ለኛ
ሙላልን፤ በኛም ላይ መጽውት አላህ መጽዋቾችን
ይመነዳልና" እያሉ ሲማፀኑት...
ዩሱፍም ማንነቱን ሊነግራቸው ወሰነ'ና፦" እናንተ ባለማወቅ በዩሱፍ እና
በወንድሙ የፈፀማችሁትን አውቃችኋልን?" አላቸው።
ይህን ግዜ እነሱም ይህ ሰው ዩሱፍ ይሆን ብለው በመጠትጠር፦" አንተ ግን
ዩሱፍ ነህ እንዴ?" አሉት።
ዩሱፍም፦"እኔ ዩሱፍ
ነኝ ይህም ቢንያሚን ወንድሜ ነው አላህ በኛ ላይ በእርግጥ
ለገሰልን፤ እነሆ! የሚጠነቀቅና የሚታገሥ ሰው
(አላህ ይክሰዋል)፤ አላህ የበጎ አድራጊዎችን ዋጋ
አያጠፋምና" አለ።
ያን ግዜ ህፍረትን ተከናነቡ በመተናነስም፦" በአላህ እንምላለን፤ አላህ በኛ ላይ
በእርግጥ
አበለጠህ፤ እኛም በእርግጥ አጥፊዎች ነበርን" አሉ።
ዩሱፍም፦"ዛሬ በናንተ ላይ ወቀሳ የለባችሁም፤ አላህ ለናንተ ይምራል፤
እርሱም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነው።አሁን ይህንን ቀሚሴን ይዛችሁ
ከንዓን ሂዱ፤ በአባቴ ፊትም
ጣሉት አይኑም ተፈውሶ የሚያይ ሆኖ ይመጣልና
ቤተሰቦቻችሁንም ሰብስባችሁ አምጡልኝ" አላቸው።
ልጆቹም እህሉን እና የዩሱፍን ቀሚስ ይዘው ወደከንዓን ጉዞ ሲጀምሩ
ያዕቁብም፦"እኔ የዩሱፍ ሽታ በእርግጥ እየሸተተኝ ነው፤ ባታቀሉኝ
ኖሮ (ታምኑኝ ነበር)" አለ እዛው ከንዓን ሆኖ።
ልጆቹም ከንዓን ምድር ከገቡ በኋላ ቀሚሱን በያዕቁብ ፊትለፊት ሲጥሉት
ያዕቁብም አይኑ በራለት።
ያን ግዜ፦"እኔ ለናንተ
ከአላህ በኩል የማታውቁትን ዐውቃለሁ
አላልኳችሁምን?" አላቸው።
ልጆቹም በዩሱፍ ላይ የፈፀሙትን ጥፋት ሁሉ አምነው አባታቸው አላህን
ይቅርታ እንዲለምንላቸው ለመኑት።
አባታቸውም፦"ወደፊት ለናንተ ጌታዬን ምሕረትን
እለምንላችኋለሁ እነሆ! እርሱ መሐሪው አዛኙ
ነውና" አላቸው።
አሁን የዩሱፍ ቤተሰቦች ሁሉም ከንዓንን ትተው ወደ ግብፅ ጉዞ
ጀምረዋል።ሁሉም ተሰብስበው ግብፅን ከደረሱ ብኋላ ዩሱፍም መንገድ ላይ
ከሀገሪቷ መሳፍንት ጋር ሆኖ ትልቅ አቀባበል አደረገላቸው።
ዩሱፍም ወላጆቹን ለያን እና ያዕቁብን ዙፋን ላይ ሲያወጣቸው ያዕቁብም
ልጆቹን ይዞ ለተከበረው ልጁ ለዩሱፍ ሱጁድ አደረጉለት።
ዩሱፍም፦አየህ አባቴ ያኔ ድሮ ህፃን ሳለሁ በህልሜ ያየሁትን ነገር
ጌታዬ በእርግጥ
እውነት አደረጋት፤ ከወህኒ ቤትም ባወጣኝና
ሰይጣንም በኔና በወንድሞቼ መካከል ከአበላሸ
በኋላ እናንተን ከገጠር ባመጣችሁ ጊዜ፣
በእርግጥ ለኔ መልካም ዋለልኝ፤ ጌታዬ
ለሚሻው ነገር እዝነቱ ረቂቅ ነው፤ እነሆ እርሱ
ዐዋቂው ጥበበኛው ነው" ብሎ ከተናገረ በኋላ ለዚህ ደረጃ ላበቃው ጌታም
እንዲህ ሲል አወደሰ፦" ጌታዬ ሆይ! ከንግስና በእርግጥ ሰጠኸኝ፤
ከሕልሞችም ፍች አስተማርከኝ፤ የሰማያትና
የምድር ፈጣሪ ሆይ! አንተ በቅርቢቱና
በመጨረሻይቱ ዓለም ረዳቴ ነህ፤ ሙስሊም ሆኜ
ግደለኝ፤ በመልካሞቹም አስጠጋኝ"
ከዚህ በኋላ ያዕቁብ እና መላ ቤተሰቦቹ መንፊስ በተባለች ከተማ ዩሱፍ
ባዘጋጀላቸው አከባቢ ፍፁም ምቾት እና ድሎት በሞላበት ኖሮ ይኖሩ
ጀመሩ።ያኔ ያዕቁብ እድሜው 130 ነበር።
በመጨረሻም ያዕቁብ በመንፊስ ከተማ ለ17 አመታት ከኖረ በኋላ በ147
አመቱ ይህችን አለም በሞት ተለየ።
ያዕቁብም ሲሞት የግብፅ ህዝብ ለ70 ቀናት ያህል ለቅሶ ከያዘ በኋላ ዩሱፍ
የግብፅ ከበርቴዎችን ባለአባቶችን የሀገር ሽማግሌዎችን አስከትሎ በአባቱ
ኑዛዜ መሰረት የኢብራሂም መቃብር ወደሚገኝበት ምድር አባቱ ያዕቁብን
ወስዶ ቀበረው።
ዩሱፍም ከዚያ በኋላ ብዙ አመታትን ቆይቶ ከሞተ ሬሳውን የአያቶቹ መካነ
መቃብር በሚገኝበት ወስደው እንዲቀብሩት ተናዝዞ በተወለደ በ120 አመቱ
ነፍሱን ለጌታዋ አስረከባት።ይሁን እንጂ ኑዛዜውን አልፈፀሙለትም ነበር።
የአላህ ሰላም እና እዝነት በያዕቁብ እና በዩሱፍ ላይ ይስፈን።
__
ምንጮች
:-
ﺍﻟﻘﺮﺀﺍﻥ ﺍﻟﻜﺮﻳﻢ
ﺍﻟﺒﺪﺍﻳﺔ ﻭﺍﻟﻨﻬﺎﻳﺔ / ﺍﻟﺠﺰﺀ ﺍﻷﻭﻝ /

♻️ #የ'ነብዩሏህ_ሹዐይብ (ዐለይሂ ሰላም ታሪክ

ክፍል 2⃣3⃣ ኢንሽአሏህ
ይ.......ቀ.....ጥ.....ላ.....ል፡፡

ሌሎች የነብያት፣ የሰሃቦች ታሪክ ና የተለያዪ ትምህርታዊ ፅሁፉች ቶሎ ቶሎ
እንዲደርሶ ከስር ሊንኩን በመክፈት ግሩፑን ይቀላቀሉ እርሶ ጋር እንዲቀመጥ
አይፍቀዱ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ፡፡

👉 https://t.me/alahu_akber1
#ነብዩሏህ_ሹዐይብ_ዐለይሂ_ሰላም

ክፍል2⃣4⃣

ከዚህም አልፈው፦"ሹዐይብ አንተ የምትለንን ምንም አናውቅም...በዛ ላይ
አንተ ደካማ ነህ ጎሳዎችህ በጎንህ ባይኖሩ እንገድልህ ነበር ምንም
አታቅተንም" እስከማለት ደረሱ።
ሹዐይብም እጅግ ስነ ምግባርን በተሞላ መልኩ፦"ህዝቦቼ ሆይ! ጎሳዎቼን
የምትፈሩ ስትሆኑ ለምንስ አላህን አትፈሩም...!!! እኔ እኮ ለእናንተ ቅኑን
መንገድ ልመራችሁ እንጂ ሌላን አስቤ አይደለም።በዚህም ከናንተ ምንም
ክፍያ አልፈልግም።
ህዝቦቼ ሆይ! በዚህ በምትፈፅሙት እኩይ ተግባር የምትዘወትሩ እንደሆን
የአላህ ቁጣ እንዳይወርድባችሁ አስጠነቅቃችኋለሁ" አላቸው።
እነሱም፦"እኛ መብታችን ነው በብራችን የፈለግነውን ማድረግ
እንችላለን።አንተ ግን ይህ ዘውትር የምትሰግደው ሰላት ነው እንዴ በብራችን
እንደፈለግን እንድንሆን እና አማልክቶቻችንንም እንድንተው የሚያዝህ?"
በማለትም ያላግጡበት ጀመር።
ሹዐይብም፦" እኔ ምንም ነገር አልከለከልኳችሁም።ግን እናንተ ነፃነት ብላችሁ
የምታስቡት ሚዛንን በማጉደል፣የሰውን ሀቅ በመብላት፣አንዱ ሌላኛውን
በመበደል....ነው እንዴ!!!
እኔ እንኳን ሚዛን ላይ ታማኝ እንድትሆኑ የሰውን ሀቅ እንዳትበሉ እና አንዱ
ሌላኛውን እንዳይበድል ነው የመከርኳችሁ።
ህዝቦቼ ሆይ! የአንድ ሀገር ልጆች ሆናችሁ ሳለ ለምን እርስ በርስ
ትሸዋወዳላችሁ!!!
እባካችሁ እርስ በርስ በመከባበር አንዳችሁ የአንዳችሁን መብት ጠብቁ።
ህዝቦቼ ሆይ! ጌታችሁን ማርታ በመጠየቅ ወደ እሱም ተመለሱ እሱ አዛኝ ጌታ
ሲሆን ወደ እርሱ የሚመለሱ ባሪያዎቹን ይወዳል።አላህም ለእናንተ መልካምን
ይሻል...ለዚህም ነው እኔን በመልዕክተኝነት ወደ እናንተ የላከኝ" አላቸው።
ህዝቡም፦"ሹዐይብ አንተ ድግምት የተሰራብህ ሰው ነህ። እኚህ ወገኖችህ
(ጎሳዎችህ) ባይኖሩ ድራሽህን እናጠፋህ ነበር" አሉት።
ይህን ግዜ ሹዐይብ ከህዝቦቹ ዛቻን እና ማላገጥን ሲመለከት ተስፋ
ቆረጠ።ህዝቡንም፦"ህዝቦቼ ሆይ! እናንተ የታያችሁን ስሩ እኔም የታየኝን
እሰራለሁ።ከዚያም ማናችንን አሳፋሪ ቅጣት እንደሚያገኘን እንመለከታለን"
አላቸው።
ይህን ግዜ ህዝቦቹ፦"እንደውም ቅጣት ስትል ትዝ አለን እውነት መልዕክተኛ
ከሆንክ እስቲ ቅጣት አስወርድብን" በማለት አሾፉበት።
ሹዐይብም፦" እሽ ማን ውሸታም እንደሆነ ታዩታላችሁ!!" ብሎ ህዝቡን ትቶ አል
አይካ ወደተባለች አጎራባች ሀገር ሄደ።
ሹዐይብም አል አይካ የተባለችውን ሀገር ሲገባ ህዝቡን ልክ የሀገሩን
(የመድየንን )አይነት ኑሮ ሲኖሩ ተመለከታቸው።በሀገሪቱ ሲዘዋወርም
ቅርንጫፎቻቸውን ያንጋለሉ ፍራፍሬዎችን፣የእርሻ ማሳዎችን እያቋረጡ የሚፈሱ
ጅረቶችን እና የተንደላቀቁ ቤቶችን ተመለከተ።
ነገር ግን እነዚህም ህዝቦች እንደ መድየን አቻዎቻቸው ሁላ የጣኦታት
ተገዢ፣እርስ በርስ አጭበርባሪ፣የሚዘን ዘራፊ እና እራስ ወዳድ ህዝቦች ሁነው
አገኛቸው።
ሹዐይብ ምንም እንኳን ለከተማይቱ እንግዳ ቢሆንም ወደ አላህ ለመጣራት
ምንም አላፈገፈገም ነበር።እንዲህም ሲል ጥሪ አደረገላቸው፦" አላህን
ተጠንቀቁ...ቁጣውንም ፍሩ። አላህ ብክለትን አይወድም ወንጀለኛ ህዝቦንም
አይወድም። ስለዚህም በእኩይ ተግባሮቻችሁ ምድርን አትበክሏት"
ይህን ሲሰሙ ጥሪውን ሙሉ በሙሉ ውድቅ በማድረግ፦"አንተ ውሸታም
የምትናገረው ነገር እውነት ከሆነ እስቲ የጌታህን ቅጣት አምጣ" አሉት።
ሹዐይብም፦"እናንተ የምትሰሩትን አላህ ያውቀዋል እኔ ስራዬ መልዕክቱን
ማድረስ ብቻ ነው። የቻልኩትን ያህል እናንተንም አስተካክ
ላለሁ ረዳቴም አላህ ብቻ ነው" አላቸው።
እነሱም፦"አንተ ግልፅ ድግምተኛ ነህ።ቆይ አንተ ከኛ በምን ተለይተህ ነው
የፈጣሪ መልዕክተኛ የምትሆነው!!!" አሉት።
ይህን ሲመለከት ሹዐይብ የ አል አይካ ህዝቦችን ባሉበት ትቶ ወደመጣበት
የትውልድ ሀገሩ መድየን ተመልሶ ሄደ።
መድየን ሲደርስ የመድየን አመፀኛ ህዝቦች ሹዐይብን ማስተባበል አንሷቸው
በሱ መልዕክተኝነት ያመኑትን ሲያንከራትቷቸው አገኘ።
ሹዐይብም ወደ አላህ የሚያደርሰውን መንገድ ህዝቦቹ እንዳያቋርጡ እና
ካቋረጡም ቅጣታቸው የከፋ እንደሆነም አክሎ ለህዝቡ ነገራቸው።
ከእለታት አንድ ቀን የመድየን ህዝቦች ሹዐይብ ዘንድ በመምጣት፦"ይህን
ሀይማኖትህን ልቀቅ እንቢ ያልክ እንደሆን አንተንም ተከታዮችህንም ከሀገር
እናባርራችኋለን" ሲሉት
አንድ ሙዕሚን ከሹዐይብ ዘንድ ነበር እና፦"ሰዎች! ከሀገር የሚያስባርር
ተግባር እኮ እኛ አልፈፀምንም። ለምንድነው ምታባርሩን!!!" አላቸው።
እነሱም፦"እንግዲያውስ ወደ ድሮው ሀይማኖታችሁ እንድትመለሱ
እናስገድዳችኋለን" አሉ።
ሹዐይብም፦"ይሄን መንገዳችሁን ጠማማ መሆኑን አውቀን፤አላህ ትክክለኛውን
መንገድ ከመራን በኋላ ወደ ጨለማ የምንመለስ ይመስላችኋልን!!!" አላቸው።
ከዚያም ሹዐይብ በመተናነስ እጁን ወደላይ ዘርግቶ፦"ጌታችን ሆይ! በእኛ እና
በህዝባችን መሀክል በእውነት ፍረድ፤ አንተም እውነተኛ ፈራጅ ነህ'ና" ብሎ
አላህን ተማፀነ።
ሹዐይብም ከህዝባቸው ጋር ያለውን ንትርክ እርግፍ አድርገው ተዉት።ያመኑትን
ብቻ በአንድ ቤት ሰብስበው ትምህርት መስጠት ጀመሩ።ይሁን እንጂ ህዝቦቹ
ግን ሹዐይብን'ና ተከታዮቹን መተናኮል አልተዉም።
በመጨረሻም የቁርጥ ቀን ደረሰ።ህዝቡ ሀገር ሰላም ብሎ ለአማልክቱ
ከሰገዱ በኋላ በሌሊት ለስራ ወጡ።እርስ በርስ እየተጭበራበሩ እየተሸዋወዱ
ቀኑ ካሳለፉ በኋላ ፀሀይ ገብታ ለተረኛው ጨለማ ቦታ ለቀቀች።
ያን ቀን ማታው ይከብድ ጀመር ሰዉ ሁሉ እርካታ ርቆታል።ሁሉም
ተጫጭኖታል...በዚህ ሁኔታ ላይ ሰሉ ከከርሰ ምድር ውስጥ ከፍተኛ ድምፅ
ወጣ። መሬት በከፍተኛ ሁኔታ ድምፁን እያስተጋባች መንቀጥቀጥ
ጀመረች።መድየንም በጥቂት ደቂቃዎች ልክ እንደፈራረሰ ቤት ድምጥማጧ
ጠፋ።
ከምንም በላይ የነዚህን ለየት የሚያደርገው የመድየን ምድር ስትንቀጠቀጥ
ሙእሚኖችም እዛው ከተማዋ ውስጥ ነበሩ።ነገር ግን በአላህ ጥበብ
በነጋታው በሰላም ከሀገሪቱ ወጡ።
ሹዐይብም የከተማይቱን መውደም እና በህዝቡ ላይ የደረሰውን መቅሰፍት ባየ
ግዜ፦"ህዝቦቼ ሆይ! የጌታዬን መልዕክት አድርሼላችሁ መክሪያችሁም
ነበር።ታዲያ በከሀዲያን ህዝቦች መጥፋት እንዴት አዝናለሁ" አለ።
ሹዐይብም ከዚያ በኋላ በወደመችው መድየን ኑሮውን ከሁለት ሴት ልጆቹ ጋር
ይኖር ጀመር።በዚያ ግዜ ሹዐይብ ይተዳደር የነበረውም በጎችን በማርባት
ስለነበር ትንሽ እርጅና ሲጫጫነው በጎቹን የማርባቱን ሀላፊነት ሁለቱ ሴት
ልጆቹ ተረከቡ።
ብዙ ግዜ በጎችን ውሀ ለማጠጣት ወደ ወንዝ ሲወስዱ እነዚህ ሴቶች
አይናፋር ስለሆኑ ሁሌም ከሰዉ በስተመጨረሻ ነበር በጎቹን የሚያጠጡት።
እችን ቦታ የሙሳን ትረካ ስንጀምር በሰፊው እንዳስሳታለን።
ሹዐይብ ከዚያ በኋላ ብዙ አመታትን ከኖረ በኋላ በጆርዳን ምድር ዋዲ ሹዐይብ
ተብሎ በሚያወቀው ተራራ ላይ ተቀብሯል።
ግን አንዳንድ የታሪክ መዛግብት ሹዐይብ መሞቻው አካባቢ ከተከታዮቹ ጋር
መካ መጥቶ ከሞተ በኋላ በካዕባ በስተ ምዕራብ በኩል በሚገኙት በ ዳረ-
ነድዋ እና በ ዳሩ በኒ ሳህም መካከል እንደተቀበሩ ይዘግባሉ። #አላሁ_አዕለም.....

(የአላህ ሰላም እና እዝነት #በሹዐይብ ላይ ይስፈን)
_________

የ'#ነብዩሏህ_አዩብ_አለይሂ_ሰላም ታሪክ

ክፍል2⃣5⃣ ኢንሽአሏህ
ይ.....ቀ......ጥ......ላ......ል፡፡

#share
@alahu_akber1
#ነብዩሏህ_አዩብ ዐለይ ሂሰላም

ክፍል2⃣5⃣

የዛሬው እንግዳችን #አዩብ_ኢብን_ሙስ_ኢብን_ራዚኽ_ኢብን_ዒስ_ኢብን_ኢስሀቅ_ኢብን_ኢብራሂም ይባላል፡፡
#እናቱም_የነቢዩላህ_ሉጥ ልጅ ስትሆን ባለቤቱ ደግሞ #ራህማ ትባላለች::
#የነቢዩላህ_ዩሱፍ_የልጅ_ልጅ ናት
ይህ #ነቢይ በጣም ሚገርመው ዙሪያው በነቢያት የታጠረ ነው።እራሱ የነቢያት
የልጅ ልጅ ሲሆን #ሚስቱ እና እናቱም #የነቢያት_ልጆች ናቸው።
እናላችሁ ይህ ነቢይ የዘር ሀረጉ በከበርት ቤተሰቦች የተከበበ ከመሆኑም
ባሻገር ዱንያ ላይም አላህ ሰፋ አድርጎለት ነበር።
#አዩብ የብዙ አገልጋዮች እና የብዙ ማሳዎች ባለቤት ብቻ ሳይሆን በጣም
የብዙ ልጆችም አባት ነበር።በሀገሩ ካሉ ባለሀብቶች ውስጥ በደግነቱ እና
በላጋስነቱም የሚታወቅ ምርጥ ነቢይም ነው።
በዚህ በተመቻቸ የኖሮ ደረጃ ላይ እሱ እና ቤተሰቦቹ ህይወትን እያጣጣሙ ስላ
ነበር #አላህ በአንድ ሌሊት ውስጥ ሚስቱ ስትቀር መላ ልጆቹን እና ሙሉ
ንብረቱን ያጠፋበት።(ፈተናው ተጀመረ)
ይህም ብቻ አልበቃም #አዩብ በቅፅበት በአደገኛ በሽታ ላይም ወድቆ ሰውነቱ
እየቆሳሰለ #ስጋው ከአከላቱ መራገፍ ጀመረ።
በሰውነቱ ላይም እንደ ሴት ጡት ያለ ነገር ያብጥበት'ና እብጠቱ ሲፈነዳም
ምግል እና እዥ ይወጣል።ሽታው ይከብድ ነበር....
ይህን የተመለከቱ የከተማይቱ ነዋሪዎችም ተላላፊ በሽታ ነው በሚል አዩብን
ከከተማ በማግለል አንድ ተራራ ላይ ወስደው ጣሉት።
ምንም እንኳም አዩብ በበሽታ ተኮማትሮ የከተማይቱ ህዝብ ተፀይፈው
ከመሀከላቸው ቢያገሉትም በፍፁም ፍቅር እና እዝነት የተሞላችው ውድ
ባለቤቱ ግን ልክ እናት ለልጇ የምታደርገውን እንክብካቤ አይነት በዚያ ተራራ
ላይ ያለ አጋዥ ታደርግለት ነበር።
ቀን ወደ ከተማ ወርዳ በየቦታው ተቀጥራ በመስራት ሲመሽ ለአዩብ #ምግብ
ገዝታለትም ትመጣ ነበር።
አዩብ የበሽታ ዘመኑ እጅግ ዘገየበት። ይሁን እንጂ #አዩብ በዚህ ሁኔታውም ቀን
እና ማታ ጌታውን ከማጥራራት ጋር ማመስገንን አልተወም።ትዕግስት
አስጨራሽ የሆኑ #7 #የእንግልት_አመታትን በዚያ #ተራራ ላይ ካሳለፉ በኋላ
ከእለታት አንድ ቀን ይህች መከራዋ የበዛባት #የአዩብ_ሚስት ተንሰቅስቃ
ማልቀስ ጀመረች።
#አዩብም፦"ምን ሆንሽ?" ሲላት...
እሷም፦"መከራህ በዛ። #ያለ_እረፍት_7_የእንግልት_አመታትን_አሳለፍን_እባክህ_ጌታህን_ለምን_ይህን_በላእ_እንዲያነሳልም" አለችው።
#አዩብም፦"ከዚህ በፊት በድሎት ስንት አመታት አሳልፈናል?" አላት።
#እሷም፦"70 አመታት አሳልፈናል" አለችው
#አዩብም፦"70 አመታትን በድሎት ሲያንደላቅቀን ከርሞ አሁን ለ7 አመታት
ስላሳመመኝ ሰብር አናደርግም እንዴ.. #ወላሂ_አላህ_አፊያ_ካደረገኝ_100_ግዜ_እገርፍሻለሁ!!!?" አላት።
ከእለታት አንድ ቀን ከተማ ስራ ፍለጋ በወጣችበት በጣም ጣፋጭ ምግብ ይዛ
ተመለሰች።እንዲህ አይነት ምግብ ከየት አገኘሽ ሲላት ምንም መልስ
ሳትሰጠው አበላችው።
ዳግም በሁለተኛ ቀንም ከተማ ወጥታ የትናንቱ አይነት ጣፋጭ ምግብ ይዛ
ስትመጣ ከየት ነው ያመጣሽው ብሎ አጥብቆ ሲጠይቃት ያን ግዜ ፀጉሯን
ሸጣ እንዳመጣችለት ነግራው ፀጉሯን ስትገልጥለት አዩብ እጅጉን አዘነ
አላህንም ሊማፀን ወሰነ።
በማግስቱ እሷ እንደተለመደው ምናምን ፍለጋ ከተማ በወረደችበት #አዩብ እጁን
ዘርግቶ ሀራም አይተው በማያውቁት አይኖቹ እንባ እያዘነበ፦"(#ጌታዬ_ሆይ!!)#እኔን_መከራ_አገኘኝ_አንተም_ከአዛኞች_ሁሉ_ይበልጥ_አዛኝ_ነህ" በማለት
#አላህን ተማፀነ።
አላህም የታጋሾችን ጥሪ ምላሽ ይሰጣል'ና፦" #በእግርህ (#ምድርን) #ምታ፡፡ #ይህ_ቀዝቃዛ_መታጠቢያ_እና_መጠጥም_ነው" አለው። #አዩብም ምድሪቱን በእግሩ
ሲመታ ሁለት ምንጮች ወጡ፤አንዱን ጠጥቶ በአንዱ ሲታጠብ አዩብ ሙሉ
በሙሉ ከበሽታው በመፅዳት የድሮ ውበቱ እና ግርማ ሞገሱ ተመለሰ።
#አዩብ በዚያ ሁኔታ ላይ ሳለ በአጠገቡ ከሰማይ የአንበጣ መንጋዎች መጡ'ና
ወርቅ ሆነው መዝነብ ጀመሩ። አዩብም እየተሯሯጠ የሚዘንበውን ወርቅ
በልብሱ መሰብሰብ ሲጀምር #አላህም፦"#አንተ_አዩብ_ከዚህ_ከምትሰበስበው_ወርቅ_አላብቃቃሁክም_እንዴ!!!" #ብሎ_ተጣራው።
አዩብም አራዳ ነበር'ና፦"#ልክ_ነህ_ጌታዬ፤#ግን_ካንተ_በረከት_እንዴት_እብቃቃለሁ።
#አንተ_እይጎድልብህ እባክህ ተወኝ ልሰብስብ" ብሎ መሰብሰቡን
ቀጠለ።
ከዚያም ሚስት የቀን ስራ ስትሰራ ውላ ለባሏ ምግብ ሸምታ አዩብ የሚገኝበት
ቦት ስትደርስ አዩብን አጣችው።እዛ ጋር አንድ ሰው ተመልክታም፦"እዚህ ጋር
አንድ በሽተኛ ትቼ ሄጄ ነበር አይተኸዋል? ደሞ ድሮ ከመታመሙ በፊት ልክ
አንተን ይመስል ነበር" ስትለው እዛ ጋር የነበረውም ሰው፦"እኔ እኮ አዩብ ነኝ"
አላት።
ተቃቅፈው ከተለቃቀሱ በኋላ ያኔ ቃል የገባውንም 100 ግርፊያ እንዲገርፋት
አላህም አዘዘው። ነገር ግን፦"ትንሽ አርጩሜ ይዘህ አንድ ግዜ ትንሽ መታ
አድርጋት እኔም በመቶ እቆጥርልሀለሁ" አለው።
ከዚያም አላህ ለአዩብ ድሮ ከነበረው ሀብት እጥፍ ድርብ አድርጎ
ካሰው።ጠፍተው የነበሩትንም ልጆቹን ሁሉ ሰበሰበለት'ና ድሮ ይኖሩ ከነበረው
የድሎት ኑሮ በላይ መኖርም ጀመሩ።
(የአላህ ሰላም እና እዝነት በአዩብ እና በባለቤቱ ላይ ይሁን)
__________
(በታሪካቸው ውስጥ ለአእምሮ ባለ ቤቶች በእርግጥ መገሰጫ ነበረ፡፡ (ይህ
ቁርኣን) የሚቀጣጠፍ ወሬ አይደለም፡፡ ግን ያንን በስተፊቱ ያለውን አረጋጋጭ
ለነገርም ሁሉ ገላጭ ለሚያምኑ ሕዝቦችም መሪና ችሮታ ነው።) [#ሱረቱ_ዩሱፍ]
_______
ምንጮቻችን፦"
ﺍﻟﻘﺮﺀﺍﻥ ﺍﻟﻜﺮﻳﻢ
ﺻﺤﻴﺢ ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱ
ﻣﺴﻨﺪ ﺇﻣﺎﻡ ﺃﺣﻤﺪ
ﺍﻟﺒﺪﺍﻳﺔ ﻭﺍﻟﻨﻬﺎﻳﺔ ﻹﺑﻦ ﻛﺜﻴ

በቀጣይ (#የዙል-ኪፍልን) ታሪክ ይዤላችሁ እስክንገናኝ ድረስ ሰላማችሁ ብዝት
ይበልልኝ በያላችሁበት አላህ ይጠብቃችሁ

ክፍል2⃣6⃣ ኢንሽዓሏህ
ይ.....ቀ....ጥ.....ላ....ል፡፡

☞የተለያዩ የተውሂድ ትምህርቶች የነብያትና የሰሀባዎች ሙሉ ታሪክ የሚቀርብበት ቻናል
ለምንለቃቸውን ትምህርቶች ለመከታተል ቻናላችንን join አድርጉ☞ @alahu_akber1
#የነብያት_ታሪክ

#ነብዩሏህ_ዙል_ኪፍል

ክፍል2⃣6⃣

እርግጠኛ ነኝ አብዝሀኛዎቻችን ይሄን ነብይ በስም ብቻ ነው የምናውቀው።
አይደል እንዴ...!!!
ነገሩ እንዲህ ነው...
ለአንድ አካባቢ ተልኮ ህዝቡን ሲያገለግል የከረመ አንድ ነቢይ ነበር።ይህም
ነብይ መሞቻው ሲቃረብ የአከባቢውን ህዝብ ሰብስቦ፦"እኔ ስሞት የህዝቡን
ሀላፊነት ከእናንተ ውስጥ ለአንድ ሰው አስረክቤ መሞት ነው ምፈልገው።ያም
ሀለፊነቱን የማስረክበው ሰው 3 ተግባራትን የሚፈፅም ሰው መሆን
አለበት።እነሱም...
1፦ቀኑን በፆም የሚያሳልፍ
2፦ሌሊቱን በሰላት የሚያሳልፍ
3፦የማይቆጣ
ስለዚህ ከእናንተ ውስጥ እነዚህን ተግባራት የሚፈፅም ማን ነው" አለ።
ሁሉም ዝም አለ...ነገር ግን ዙል ኪፍል እጁን አውጥቶ፦"እኔ" አለ።
ያ ነቢይም ሀለፊነቱን ለዙል ኪፍል አስረክቦ ዱንያን ተሰናበተ።ዙልኪፍልም
ሀገሪቱን በፍትህ ይመራ ጀመር።
ከእለታት አንድ ቀን ኢብሊስ ዙል ኪፍልን በስህተት ሊጥለው ፈልጎ ሸይጣኖችን
ሰብስቦ፦"እያንዳንዳችሁ ዙል ኪፍልን በስህተት የመጣል ግዴታ
አድርጌባችኋለሁ" አላቸው።
ሸይጣኖችም ዙል ኪፍልን ለማሳሳት ብዙ ከታገሉ በኋላ ተስፋ በመቁረጥ
ኢብሊስ ዘንድ በመሄድ፦"አልቻልንም" አሉት።
ኢብሊስም፦"እሽ እኔ እንዴት እንደማሳስተው አሳያችኋለሁ" ብሏቸው ወደ ዙል
ኪፍል ዘንድ ሄደ።
ዙል ኪፍል ማታ እየሰገደ ስለሚያድር እንቅልፍ እሚተኛው ከዙህር በኋላ ነው።
እና ዙል ኪፍል ቀይሉላ (ከዙህር በኋላ የሚተኛ እንቅልፍ) ሊተኛ ዝግጅት ላይ
ሳለ ኢብሊስ በትልቅ ሽማግሌ ሰው ተመስሎ እቤቱን አንኳኳ።
ዙል ኪፍልም፦"ማን ነው?" አለ።
ኢብሊስም፦"እኔ በእድሜ የገፋው ሽማግሌ ነኝ። አንድ ጉዳይ ገጥሞኝ ነው"
አለ።
ዙል ኪፍልም ተነስቶ ከፈተለት'ና ጉዳዩን ጠየቀው።ኢብሊስም፦"የሆኖ ሰዎች
እንዲ በድለውኝ እንዲ አድርገውኝ....."እያለ የቆጥ የባጡን ለረጅም ሠዐት
ማውራት ጀመረ።ዙል ኪፍልም እንቅልፉን ተቋቁሞ በጥሞና ካደመጠው በኋላ
ሽማግሌውን፦ነገ ችሎት ላይ ቅረብ'ና እዛ ጉዳይህን እናይልሀለን" ብሎ
ሸኘው።ያን ቀን ዙል ኪፍል የእንቅልፍ ሰዐቱ ሳይተኛም አለቀችበት።
በሁለተኛው ቀን ጠዋት ላይ ዙል ኪፍል ችሎት ላይ ሆኖ ያን ሽማግሌ ረጅም
ሰዐት ቢጠብቀውም ሊመጣ አልቻለም።ዙል ኪፍልም ብዙ ከጠበቀው በኋላ
ትቶት ሄደ።
ከዚያም ማታ ሲሰግድ ያደረው ዙል ኪፍል ጎኑን ሊያሳርፍ ፍራሹ ላይ ገና
ከመቀመጡ በሩ ተንኳኳ።
ዙል ኪፍልም፦"ማን ነህ?" ሲል
ኢብሊስ፦"የትናንቱ ሽማግሌ ነኝ" አለው።
ዙል ኪፍል ተነስቶ በሩን ከከፈተ በኋላ፦"ችሎት ላይ ቅረብ ብዬህ አልነበር
ለምን ቀረህ?" አለው።
ኢብሊስም፦"አረ በጣም መጥፎ ሰዎች ናቸው የበደሉኝን ላንተ ነግሬ ችሎት
ላይ ጉዳያችንን እንደምታይ ሲሰሙ ሀቅህን እንሰጥሀለን አሉኝ።ከዚያም ችሎቱ
ሲያልቅ ከለከሉኝ" አለው።
ዙል ኪፍልም፦"በቃ አሁን ሂድ ነገ ችሎት ላይ ግን እንዳትቀር" ብሎ ሸኘው'ና
የዛሬዋንም እንቅልፍ መስዋዕት አደረገ።
በማግስቱ ዙል ኪፍል ችሎት ላይ ይሄን ሽማግሌ ቢጠብቀው... ቢጠብቀው
ሊመጣ አልቻለም።የቀኑን ችሎት ካጠናቀቀ በኋላ ሌሊት ሲግድ ያደረውን'እና
ከሁለት ቀን አንስቶ እረፍት ያጣውን ወገቡን ሊያሳርፍ እቤት ገባ።
ለዘበኞቹም፦"ማንም ሰው ቢመጣ እንቅልፌን ሳልጨርስ በሩን እንዳያንኳኳ"
ብሎ ክፍሉን ዘግቶ ተኛ።
ልክ ዙል ኪፍል እንደተኛውም ሽማግሌው ከች አለ'ና ሊየንኳኳ ሲል ዘበኞች
ከለከሉት።
ኢብሊስም፦"አይ እኔ ትናንት መጥቼ ጉዳዬን ነግሬዋለሁ አሁን ቀጥሮኝ ነው
የመጣሁት" አላቸው።እነሱም በምንም ተዐምር አናስገባህም አሉት።
የን ግዜ ኢብሊስ ከርቀት አንዲት ቀለበት የምታክል ቀዳዳ በሩ ላይ
ተመለከተ'ና ተወርውሮ በሷ ሾልኮ ገባ።ከዚያው ከውስጥ በኩል ሆኖ ሲያንኳኳ
ዙል ኪፍል ደንግጦ ተነሳ።
ዙል ኪፍል ሽማግሌውን ክፍሉ ውስጥ ሲመለከተው ዘበኛውን ጠርቶ፦"ማንም
እንዳይገባ ብዬህ አልነበር!!! ለምን ፈቀድክለት?" ብሎ ሲጠይቀው
ዘበኛውም፦"እኔ አልፈቀድኩለትም ነገር ግን በዚህች ቀዳዳ ነው የገባው"
ብሎ የበሩን ቀዳዳ አሳየው።ያን ግዜ ዙል ኪፍል ሽማግሌውን ነቃበት'ና፦"አንተ
የአላህ ጠላት ኢብሊስ ነሃ...!!" አለው።
ሽማግሌውም፦"አዎ እኔ ኢብሊስ ነኝ በተለያዩ ነገሮች ፈትኜክ ስላልቻልኩህ
ይሄን ስልት ተጠቅሜ ላስቆጣህ ነበር።ይሁን እንጂ አላህ ጠብቆህ አሁንም
አልቻልኩህም" አለው።
ለዚያ ነው እንግዲህ አላህም ዙል ኪፍል(ሀላፊነትን የመወጣት ባለቤት) ብሎ
የሰየመው።
ማሳሰቢያ፦በሙስነድ የተዘገበው ዙል ኪፍል ይህ እንዳይመስላችሁ።ይኼኛው
ዙል ኪፍል እና ዙል ኪፍል (የበኒ ኢስራኢሉ ዓቢድ) ይለያያሉ።
_______
ምንጭ፦
ﺍﻟﺒﺪﺍﻳﺔ ﻭﺍﻟﻨﻬﺎﻳﺔ / ﺍﻟﺠﺰﺀ ﺍﻷﻭﻝ /

የ'#ነብዩሏህ_ዩኑስ_ዐለይሂ_ሰላም ታሪክ

ክፍል2⃣7⃣ኢንሽዓሏህ
ሊ.....ቀ.........ጥ....ላ....ል፡፡

☞የተለያዩ የተውሂድ ትምህርቶች የነብያትና የሰሀባዎች ሙሉ ታሪክ የሚቀርብበት ቻናል
ለምንለቃቸውን ትምህርቶች ለመከታተል ቻናላችንን join አድርጉ☞ @alahu_akber1
✅ #የነብያት_ታሪክ ✅

🐬#ነብዩሏህ_ዩኑስ_ዐለይሂ_ሰላም🦈

ክፍል2⃣7⃣

በድሮ ዘመን አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ #ነይነዋ ወደተባለች ምድር #ዩኑስ የተባለን
ሰው #በነቢይነት ይልከዋል።
ዩኑስም አላህ እሱን ነቢይ አድርጎ ስለመረጠውም በጣም ተደስቶ ተልዕኮውን
መፈፀም ጀመረ።
ምንም እንኳም #ዩኑስ ያለ እረፍት የነይነዋን ህዝቦች ወደ አላህ ቢጣራም
ለጥሪው ምላሽ የሰጠ አንድም #ፍጥረት አላገኘም።
ዩኑስ ተስፍ ቆረጠ...የህዝቡን አመፅ እና እንቢተኝነት ሲመለከት #የነይነዋን
ምድር ትቶ ወደማያውቅበት ሀገር ለመሄድም ወሰነ።ነገር ግን #የአላህን_ፍቃድ አልጠየቀም ነበር እንዲሁ በብስጭት ነበር ዩኑስ ሀገሩን ሊለቅ የወሰነው።
ዩኑስም በማግስቱ ባህር ዳርቻ በመሄድ #መርከብ ጠብቆ መርከቢቱ የትም
ትሂድ የት ብቻ መርከቢቱ ወደምትሄድበት ሊሄድ #ሂሳብ_ከፍሎ ተሳፈረ።
ሰዐቱ ፀሀይ ልትጠልቅ ጀንበርን በመሰነባበት ላይ ነበረች....ጨለማውም
ምድርን ሊሸፍን ዝግጅት ላይ ነው።ይሄን ግዜ ዩኑስን እና በርካታ ተሳፋሪዎችን
የጫነችው መርከብ በጨለማ ባህሩን እየሰነጠቀች መጓዝ ጀመረች።
ሁሉም ነገር በመርከቢቷ ረግቷል..ሰላም እና ሰጥታም እጅጉን ሰፍኗል።በዚህ
ሁኔታ ላይ ሳሉ መርከቢቷ ብዙ ከተጓዘች በኋላ ባልታሰበ መልኩ በድቅድቅ
ጨለማ መርከቢቷን ከየት እንደመጣ ያልታወቀ #ማዕበል ከየአቅጣጫው
#ያናውጣት ጀመር።
ሁሉም ግራ ተጋባ የመርከቧ ሰራተኞች ሁኔታውን ሊያረጋጉ ቢሞክሩም ምንም
ሊረጋጋ ባለመቻሉ የመርከቧ ክብደት እንዲቀንስ እያንዳንዱ ሰው የጫነውን
ጭነት ከመርከቧ እንዲጥል አዘዙ።
ምንም እንኳን ተሳፋሪው ሁሉ የያዘውን እቃ ወደ ባህር ቢወረውርም
የመርከቢቷ መናወጥ ሊቆም አልቻለም።በመጨረሻም መርከቧ ላይ ያሉ
ተሳፋሪዎች፦"እዚህ መሀከላችን አንድ ከአሳዳሪው ያመለጠ ባሪያ አለ ማለት
ነው።ስለዚህ ያን ወንጀለኛ ለማወቅ እጣ እንጣል" በማለት ተስማሙ።
እጣው ተጀመረ....ወረቀቱ ሲከፈት ዩኑስ የሚል ስም ወጣ።ዳግም እጣ
ጣሉ፤አሁንም ዩኑስ የሚል ስም ወጣ። ለሶስተኛ ግዜም እጣ ሲጥሉ የዩኑስ
ስም ወጣ...። ያን ግዜ ዩኑስ እራሱን ከመርከቢቱ ሲወረውር አንድ አሳ ነባሪ
አፉን ከፍቶ ጎረሰው'ና ወደ ባህሩ ዝቅተኛ ክፍል ይዞት ወረደ።
አላህም አሳ ነባሪውን፦"አንድም አጥንት እንዳትሰብር አንድም ስጋ እንዳታኝክ"
አለው።
ዩኑስም በአሳነባሪው ጉሮሮ ተሽሎክልኮ ሆዱ ላይ እንዳረፈም ያን አሳ ነባሪ
እራሱ ሌላ አሳ ነባሪ ዋጠው።ዩኑስም እራሱን የአሳ ነባሪው ሆድ ውስጥ
ሲያገኝ የሞተ መስሎት ነበር፤ ድንገት እግሩን ሲያንቀሳቅስ በህይወት እንዳለ
ተረድቶ መዘከር ጀመረ።
አስቡ ሌሊት ነው፣በዛ ላይ ዩኑስ አሳ ነባሪው ሆድ ውስጥ ነው፣በዛ ላይ ዩኑስን
የዋጠው አሳ ነባሪ እራሱ ሌላ አሳ ነባሪ ሆድ ውስጥ ገብቷል፣ ጨለማ ላይ
ጨለማ ተደራርቧል።
ዩኑስ እዛው በአሳ ነባሪዎቹ ሆድ ውስጥ ሆኖ የሆነ ጫጫታ ይሰማል...እና
በልቡ፦"የምን ጫጫታ ነው ምሰማው ...!!!" እያለ ሲያሰላስል
አላህም፦"የባህር ውስጥ ፍጥረታት ለኔ የሚያደርጉት ውዳሴ ነው" ብሎ
ወህይ አወረደለት።

ያን ግዜ ዩኑስ፦"#ላ_ኢላሀ_ኢላ_አንተ_ሱብሀነከ_ኢኒ_ኩንቱሚነ_ዟሊሚን

(ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ጥራት ይገባህ፡፡ እኔ በእርግጥ ከበዳዮቹ ነበርኩ)"
ሲል ወደ አላህ ተጣራ።

#ዩኑስ እንዲህ ሲል #ከሰባት_ሰማያት በላይ ያሉ መላዕክት ይሄን ጥሪ ሰምተው
አላህን
እንዲህ አሉት፦ያ አላህ አንድ የሚታወቅ ደካማ ድምፅ ከሩቅ ቦታ ይሰማናል"
አላህም፦"እሱ እኮ ዩኑስ ነው። አምፆኝ በአሳ ነባሪ ሆድ ውስጥ አስሬው ነው"
አላቸው።
መላዕክቱም፦"እንዴ! ያ ቀን እና ማታ መልካም ስራዎቹ ወደ ሰማይ
የሚወጡለት ዩኑስ?"ብለው ሲጠይቁት
አላህም፦" አዎን" አላቸው።
ያን ግዜ መላዕክቱ ለዩኑስ አማላጅ ሆኑለት'ና ዩኑስን የዋጠው #አሳ_ነባሪ ከአንድ
ደሴት ዳርቻ ሄዶ በአላህ ትዕዛዝ #ዩኑስን_ተፋው።
ዩኑስ ከአሳ ነባሪው ሆድ ወጥቶ ሲወድቅ የአሳ ነባሪው የሆዱ ሙቀት ዩኑስን
እጅጉን አሞቅሙቆት ስለነበር ዝንቦች ይረባረቡበት ጀመር።ያን ግዜ አላህ
የዱባ ቅጠልን ዩኑስ በተኛበት ቦታ አበቀለለት።
አላህም ዩኑስ እዛው ሳለ ተውበቱን እንደተቀበለው ወህይ አወረደለት'ና ወደ
ህዝቡ እንዲመለስ አዘዘው።
(እሺ አሁን አንዴ ወደኋላ ልመልሳችሁ ነው...አንድም ሰው እንዳይቀር ግርርር
ብላችሁ ኑ።)
ዩኑስ መጀመሪያ ህዝቡን ትቶ ሲወጣ አላህ በእነዚያ ህዝብ ላይ ከባድ ቅጣትን
አምጥቶ አንዣበበባቸው።ሰማዩ ጠቁሯል...ብቻ ከባድ ቅጣት እንደመጣባቸው
ታውቋቸዋል ዩኑስን ማስተባበላቸው በጣሙን ፀፅቷቸዋል።
አሁን ሁሉም ጥፋቱን አምኖ የሀዘን ልብስ ለብሰ፣ላሞችን ከጥጃዎቻቸው
ለይተው፣በጎችን እና ፍየሎችን ከግልገሎቻቸው ለይተው፣ ግመሎችንም
ከግልገሎቻቸው ልይተው፣ ህፃናት ልጆችንም ከእናቶቻቸው ለይተው ሁሉም
ኡኡኡ ብሎ ሲጮህ አላህ ያዝንልናል በሚል ሚዳ ላይ ወጥተው
ኡኡኡ...እያሉ አላህን በፀፀት እንባ ለመኑት።
አላህም ተውበታቸውን ተቀብሎ ያመጣባቸውን መቅሰፍት መለሰላቸው።
ከዚያም ያ የጠፋውን ነቢያቸውን ይቅርታ ሊጠይቁት በጉጉት ይጠባበቁት
ጀመር።
(እሺ አሁን ወደ ቅድሙ ቦታ ኑ...አንድም ስው እንዳይቀር...፤ዩኑስን አጅበን
እንመጣለን።)
ከዚያም ዩኑስ እዛች የዱባ ቅጠል ስር ሆኖ ካገገመ በኋላ የቀድሞው ህዝቡ
ወደሚገኝበት #የነይነዋ_ምድር ዳግም ዳዕዋ ለማድረግ ጉዞ ጀመረ።
#ዩኑስም ልክ ነይነዋ ከተማ ውስጥ ሲገባ ከ 100,000(መቶ ሺህ) ህዝብ በላይ
ተገልብጦ በመውጣት ደማቅ አቀባበል አደረጉለት።በህዝቡ መለወጥ
በጣምም ተገረም....እነሱም የተከሰተውን ሁሉ በዝርዝር ነግረውት ይቅርታም ጠየቁት።
እሱም ሰላሳለፋቸው አሰቃቂ ግዜያት አወጋላቸው።
ከዚያ በኋላ የዩኑስን ትምህር እየተቀበሉ ለረጅም አመታት በሰላም ከኖሩ በኋላ
ዩኑስ ይህ ነው ተብሎ በማይታወቅ #እድሜው ይህችን አስቸጋሪ አለም በሞት
ተገላገለ።

(የአላህ ሰላም እና እዝነት #በዩኑስ ላይ ይሁን)
___________
ምንጮች፦
ﺍﻟﻘﺮﺀﺍﻥ ﺍﻟﻜﺮﻳﻢ
ﺍﻟﺒﺪﺍﻳﺔ ﻭﺍﻟﻨﻬﺎﻳﺔ / ﺍﻟﺠﺰﺀ ﺍﻷﻭﻝ /
ﺝﺤﺢ ﺴ
ﻣﺴﻨﺪ ﺍﻹﻣﺎﻡ ﺃﺣﻤﺪ
_______
የ'#ኢሳ_ዐለይሂ_ሰላም_ታሪክ
_______
ክፍል2⃣8⃣ ኢንሽዓሏህ
ይ ......ቀ......ጥ......ላ......ል፡፡

☞የተለያዩ የተውሂድ ትምህርቶች፣ የነብያትና የሰሀባዎች ሙሉ ታሪክ የሚቀርብበት ቻናል
ለምንለቃቸውን ትምህርቶች ለመከታተል ቻናላችንን join አድርጉ☞ @alahu_akber1
_______
✅#የነብያት_ታሪክ✅

〰〰⭐️#ኢሳ_እየሱስ_ዐለይሂ_ሰላም〰〰⭐️

ክፍል3⃣1⃣

ዒሳም ብድግ ብሎ የማዕዱን ሽፋን፦"በአላህ ስም መልካም ለጋሽ በሆነው" በማለት ከፈተው።
በውስጧም የዓሳ ስጋ ፣ዳቦ ፣የተለያዩ መጠጦችን እና የተለያዩ ፍራፍሬዎችን ተመለከቱ።
ከዚያም ዒሳ ሀዋሪያቱን እንዲበሉ ሲያዛቸው፦"አይ
በውስጧም የዓሳ ስጋ ፣ዳቦ ፣የተለያዩ መጠጦችን እና የተለያዩ ፍራፍሬዎችን ተመለከቱ።
ከዚያም ዒሳ ሀዋሪያቱን እንዲበሉ ሲያዛቸው፦"አይ!!! ቀድመህ አንተው ብላ"አሉት።
ዒሳም፦"ማዕድ ከሰማይ እንዲወርድላችሁ ያዘዛችሁት እኮ እናንተ ናችሁ" አላቸው።
ይሁን እንጂ ሀዋሪያቱ ቀድመው መብላት እንቢ በማለታቸው ዒሳ ወደ 1300 (አንድ ሺህ ሶስት መቶ) የሚሆኑ በሽተኞችን፣ ድሆችን እና ሚስኪኖችን ሰብስቦ መብላት ሲጀምር በሽታቸው ካለያቸው መነሳት ጀመረ።ይሄን ሲመለከቱ እንቢ ያሉት ሀዋሪያቱ ተፀፀቱ።
ከዚያም በኋላ ለተከታታይ ቀናት ያለ መቋረጥ ማዕዱ እየወረደ ሀዋሪያቱም መብላት ጀመሩ።በመጨረሻም አላህ ማዕዱን ድሆች እና ሚስኪኖች ብቻ እንዲበሉ አዘዘ።
ያን ግዜ ሀብታሞች እና ሙናፊቆቹ ማጉረምረም ሲጀምሩ አላህም ከነጭራሹ ማዕዱን አቋረጠው።
(ወይኔ በአላህ ! አበዛሁባችሁ አይደል...ያው ሊነጋ ሲል ይጨልማል አይደል ተረቱ!!! ሊያልቅ ሲልም ይረዝማል።ደሞ ከማዕዱ እየበላችሁ...ሀሀሀ)
ከዚያ ቀን በኋላ ዒሳ በሀዋሪያቱ ተሰወረባቸው።ሲያፈላልጉትም ወደ ባህር እንደሄደ ሰምተው ተከትለውት ሲሄዱ እሱ ባህር ላይ ሲራመድ እና ማዕበል አንዴ ከፍ ሲያደርገው አንዴም ዝቅ ሲያደርገው ተመለከቱት።
ከሀዋሪያቱ መሀከልም አንዱ ሳሊህ፦"አንተ የአላህ ነቢይ ሆይ ወዳንተ ልምጣ?" ብሎ ሲጠይቀው፤ ዒሳም ጠራው።
ከዚያም ሰውዬው አንድ እግሩን ባህሩ ላይ አሳረፈ'ና ሁለተኛዋን ሲደግም ኡኡ... ብሎ ጮሆ ሰመጠ።ዒሳም፦"እጅህን አሳየኝ አንተ የኢማን ደከማ" አለው'ና ከባህሩ አውጥቶት፦"የአደም ልጅ የገብስ ፍሬ ያህል ኢማን ቢኖረው ኖሮ ባህር ላይ ይራመድ ነበር" አለ።
ከዚያም ዒሳ ሀዋሪያቱን ከባህር ዳርቻ ሰብስቦ ሁለት እጆቹን አሸዋ ውስጥ በመክተት በአንድ እጁ ወርቅ እና በአንድ እጁ አሸዋ አወጣ።ከዚያም ሁለቱንም ለነሱ እያሳያቸው፦" የቱን ትመርጣላችሁ" ሲላቸው ወርቁን አሉት።
እሱም፦"እኔ ዘንድ ግን ሁለቱም እኩል ናቸው።" አለ።
ከዚያም አላህ ለዒሳ፦"ዒሳ ሆይ! ሰዎች ሲያውቁህ አዛ እንዳያደርጉህ ከቦታ ወደ ቦታ ተዘዋወር። በልቅናዬ እና በልዕልናዬ እምላለው። አንድ ሺህ ሁረል ዒኖችን እዘውጅሀለሁ...ከዚያም አርባ አመት ያህል እደግስልሀለሁ" አለው።
ዒሳም ይህችን ምድር ለቆ ወደ ሰማይ የሚያርግበት ግዜ ሲቃረብ ዒሳ አስራ ሁለቱን ሀዋሪያት ቤቱ ሰብስቧቸው፦"ከእናንተ ውስጥ በኔ ነቢይነት ካመነ በኋላ አስራ ሁለት ግዜ የሚክድ አለ። እስቲ ማናችሁ ነው ዛሬ በኔ ምስል ተመስሎ በኔ ቦታ በመሞት በጀነት ደረጃዬ እኩል ሚሆን?" ብሎ ጠየቃቸው።
ሁሉም ዝም ብለው አንድ ወጣት፦"እኔ" ብሎ ቆመ።
ዒሳም፦"ቁጭ በል" አለው። ልጁም ቁጭ አለ።
አሁንም ዒሳ የመጀመሪያውን ጥያቄ ዳግም አቀረበላቸው። ሁሉም ዝም ሲሉ ልጁ አሁንም፦"እኔ" አለ።ዒሳም ቁጭ በል አለው።
በዚህ ሁኔታ ሶስቴ ካስቀመጠው በኋላ በዒሳ ምስል ተመስሎ ለመሞት ይህ ልጅ ታጨ።ከዚያም አላህ የዒሳን ምስል በዚያ ወጣት ልጅ አደርገበት'ና ዒሳን በተወለደ በ33 አመቱ ወደ ሰማይ ሰቀለው።
ልክ ዒሳ ወደ ሰማይ እንዳረገውም ዒሳን ሊገድሉ የንጉሱ ወታደሮች ሲመጡ በዒሳ የተመሰለውን ወጣት አግኝተው ዒሳ ነው በማለት ሰቀሉት።
ከዚያም በኋላ በዒሳ አምነው የነበሩ ሰዎች ለሶስት ተከፋፈሉ።
1፦ጌታ የተወሰነ ግዜ ከኛ ቆይቶ ከዚያ ወደ ሰማይ ወጣ።
2፦የአላህ መልዕክተኛ የተወሰነ ግዜ ከኛ ቆይቶ ወደ ሰማይ ወጣ።
3፦የአላህ ልጅ የተወሰነ ግዜ ከኛ ቆይቶ ወደ ሰማይ ወጣ።
በማለት ሶስት ቡድን ከሆኑ በኋላ ቡድን አንድ እና ቡድን ሶስት በመተባበር ቡድን ሁለትን ጨፍጭፈው ጨረሷቸው ከዚያም ዒሳ የአላህ ልጅ ነው እና ዒሳ አላህ ነው እያሉ በማምለክ ረጅም አመታትን ዘለቁ።
(የአላህ ሰላም እና እዝነት በመልዕክተኛው ዒሳ እና በእናቱ ላይ ይስፈን)
__________
ምንጮች፦
1 القرءان الكريم
2ﺍﻟﺒﺪﺍﻳﺔ ﻭﺍﻟﻨﻬﺎﻳﺔ /ﺍﻟﺠﺰﺀ ﺍﻟﺜﺎﻧﻲ/
3 ﺍﻟﻜﺎﻣﻞ ﻓﻲ ﺍﻟﺘﺎﺭﻳﺦ ﻋﺰ ﺍﻟﺪﻳﻦ ﺃﺑﻮ ﺍﻟﺤﺴﻦ ﻋﻠﻲ ﺍﻟﻤﻌﺮﻭﻑ ﺑﺎﺑﻦ ﺍﻷﺛﻴﺮ
------------------------------------------------
አል-ኒሳዕ 4:157
وَقَوْلِهِمْ إِنَّا قَتَلْنَا ٱلْمَسِيحَ عِيسَى ٱبْنَ مَرْيَمَ رَسُولَ ٱللَّهِ وَمَا قَتَلُوهُ وَمَا صَلَبُوهُ وَلَٰكِن شُبِّهَ لَهُمْ ۚ وَإِنَّ ٱلَّذِينَ ٱخْتَلَفُوا۟ فِيهِ لَفِى شَكٍّۢ مِّنْهُ ۚ مَا لَهُم بِهِۦ مِنْ عِلْمٍ إِلَّا ٱتِّبَاعَ ٱلظَّنِّ ۚ وَمَا قَتَلُوهُ يَقِينًۢا
«እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም (ረገምናቸው)፡፡ አልገደሉትም አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነሱ (የተገደለው ሰው በዒሳ) ተመሰለ፡፡ እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ (መገደል) በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም አልገደሉትም፡፡
አል-ኒሳዕ 4:171
يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْحَقَّ ۚ إِنَّمَا ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ ٱللَّهِ وَكَلِمَتُهُۥٓ أَلْقَىٰهَآ إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌۭ مِّنْهُ ۖ فَـَٔامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ ۖ وَلَا تَقُولُوا۟ ثَلَٰثَةٌ ۚ ٱنتَهُوا۟ خَيْرًۭا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا ٱللَّهُ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ سُبْحَٰنَهُۥٓ أَن يَكُونَ لَهُۥ وَلَدٌۭ ۘ لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ ۗ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًۭا
እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ፡፡ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ዒሳ የአላህ መልክተኛ ወደ መርየም የጣላት «የኹን» ቃሉም ከእርሱ የኾነ መንፈስም ብቻ ነው፡፡ በአላህና በመልክተኞቹም እመኑ፡፡ « (አማልክት) ሦስት ናቸው» አትበሉም፡፡ ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱ ልጅ ያለው ከመኾን የጠራ ነው፡፡ በሰማያትና በምድር ያለ ሁሉ የርሱ ነው፡፡ መመኪያም በአላህ በቃ፡፡
________
የ'#ነብዩሏህ_የህያ_እና_ዘከርያ ታሪክ
~~~~~

ክፍል 3⃣2⃣ኢንሽዓሏህ
ይ......ቀ.......ጥ.......ላ......ል፡፡

☞የተለያዩ የተውሂድ ትምህርቶች የነብያትና የሰሀባዎች ሙሉ ታሪክ የሚቀርብበት ቻናል
ለምንለቃቸውን ትምህርቶች ለመከታተል ቻናላችንን join አድርጉ☞alahu_akber1
'
•••✿ ❒ ነብዩሏህ አደም ዐለይሂ ሰላም ❒✿•••

#ክፍል 3

የቃቢልም ቅጣቱ ከዱንያ ጀመረ ሁለቱ ታፋዎቹ ተጣበቁ።ፀሀይ ወደዞረችበት ሁሉ አላህ የቃቢል አይን እንድታፈጥ አደረገ መቃጣጫ ይሆነው ዘንድ።
አደም እና ሀዋ በልጃቸው ሀቢል ሀዘን በጣሙን ስለተጎዱ አላህ ሸይስ የሚባል መልካም ልጅ ሰጥቶ ሀዘናቸውን አስረሳቸው።

ሸይስ ማለት የ አላህ ስጦታ ማለት ነው።እንደዛ ብለው ሊሰይሙት የቻሉትም ሀቢል ከሞተ በኋላ አላህ እሱን በምትኩ ስለሰጣቸው ነው።

በሰው ልጅ ታሪክ አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ /104 አንድ መቶ አራት መለኮታዊ መፃህፍትን ወደተለያዩ መልዕክተኞች አውርዷል።ከዛ ውስጥ 50 ሀምሳው በሸይስ ነበር የተወረደው።

ለመጀመሪያ ግዜ በጥበብ የተናገረውም ሸይስ ነው።

ለመጀመርያ ግዜ በወርቅ እና በአልማዝ ንግድ የጀመረውም ሸይስ ነው።

ለመጀመርያ ግዜ በሚዛን መገበያየትንም የጀመረው ሸይስ ነው።

ለመጀመርያ ግዜ ከምድር ማዕድናትን ማውጣት ያስተማረውም ሸይስ ነበር...

በነገራችን ላይ የሰው ልጆች ሁሉ የዘር ሀረጋቸው ከሸይስ ጋር ነው ሚገናኙት።ምክንያቱም ሌሎቹ የአደም ልጆች ተበታትነው ቀሩ እንጂ አልተዋለዱም።

በዚህ ሁኔታ ሳለ አንድ ቀን መለከል መውት ቀጠሮዋን ጠብቆ አደምን ነፍሱን ለማውጣት ሲመጣ አደም አልሰማህም ገና 40 አመት ይቀራኛል ብሎ ተሟገተ።

መለከል መውትም፦" በርግጥ እድሜህ 1000 ነበር ግን ያኔ ለዳዉድ ከኔ 40 ቀንሳችሁ 100 ሙሉለት ብለህ ነበር" አለው።

አደምም ምንም ማውቀው ነገር የለም እንዲ ብዬም አላውቅም ብሎ ድርቅ አለ።ያን ግዜ አላህም የምስክር ወረቀቱን እና ምስካሪ ያደረጋቸውን መላዕክትን እንደ ማስረጃ አቀረበበት።

አደምም አመነ ነገር ግን አላህ የቀረችውንም 40 አመት በእዝነቱ እንዲኖር

ፈቀደለት። ይሁን እንጂ የማይደርስ የለም'ና 40 አመቷ ተጠናቅቃ አሁንም አደም ሞት አፋፍ ላይ ደረሰ።

ያን ግዜ አደም ምክራዊ ኑዛዜውን ለልጁ ሸይስ ይናዘዝ ጀመር።የቀን እና የሌሊትን ክፍለ ግዜ አስተማረው...በሁለቱ ክፍለ ግዜ ውስጥም የሚደረጉ አምልኮዎችንም በዝርዝር አስተማረው።

ቀኑ ጁምዓ ነው...አደም በጣም ታሟል...ልጆቹ የሚያደርጉት ጠፍቷቸዋል...በዚህ መሀል አደም ለልጆቹ የጀነት ፍራፍሬ እንዲያመጡለት አዘዛቸው።

እነሱ የጀነት ፍራፍሬ የት ይሁን፤ምን አይነት ይሁን ሚያውቁት ነገር የለም።ብቻ ሰብሰብ ብለው ፍለጋ ወጡ።በፍለጋ ላይ ሳሉ መላዕክትም ሰብሰብ ብለው ከፈን፣የሬሳ ሽቶ፣መቆፈሪያ፣አካፋ...ምናምን ይዘው ሲያልፉ ተገጣጠሙ።

ከዚያም መላዕክቶቹም ለአደም ልጆች፦"ወደ የት ነው ምትሄዱት?" አሏቸው። ልጆቹም፦"አባታችን ታሟል። የጀነት ፍራፍሬ ስላሰኘው ልንፈልግለት እየሄድን ነው" አሏቸው

መላዕክቶቹም፦"አባታችሁ ሙቷል ኑ ተመለሱ" ብለው ልጆቹን ይዘው መለሷቸው።

ለአደም መሞት በአጥናፈ አለሙ ያሉ ፍጥረተት በሙሉ ነበር ያለቀሱት ምድርና ሰማያትም ሳይቀሩ።

መላዕክትም የአደምን የቀብር ስነ ስርዐት ለመፈፅም ሲመጡ እናታችን ሀዋ አለቀሰች።አትውሰዱብኝ እያለችም እዬዬ ትል ጀመር።

ከዚያም መላዕክት የአደምን አስክሬን ወሰዱት'ና አጥበው ከፍነው ሽቶ ቀብተው.....ባዘጋጁለት ቀብር ውስጥ(ህንድ ላይ በሚገኝ ተራራ ላይ ነው ቀብሩ) ልጆቹ እያዩ አስገብተውት አፈር መለሱበት።

ከዚያም መላዕክት፦"እናንተ የአደም ልጆች ሆይ! ይህ ከአሁን በኋላ ሙታኖቻችሁን የምትቀብሩበት ስነ ስርዐት ነው" ብለዋቸው ሄዱ።

አደም ከሞተ በኋላ ዋሀ'ም ከአንድ አመት በኋላ ባለቤቷን ተከተለችው።

ከዚህ በኋላ ዱንያ መስመሯን ይዛ የአደምን ልጆች ችግር ልታስተምራቸው ነው።

አደም እና ሀዋ ከሞቱ በኋላ የአድም ልጆች ሀላፊነት ሙሉ በሙሉ ሸይስ ላይ ወደቀ። ሸይስ በጥሩ ሁኔታ የአደምን ልጆች ካስተዳደራቸው በኋላ የሱም የሞት ፅዋ መቅመሻ ግዜው ደረሰ'ና ለልጁ አኑሽ ኑዛዜውን ተናዝዞ ነፍሱን ለፈጣሪው አስረከበ።

የ ሸይስ ልጅ አኑሽ'ም በጥሩ ሁኔታ ሀላፊነቱን ከተወጣ በኋላ የሱም ከዱንያ መሰናበቻ ግዜው ይደርስ'ና እሱም ለልጁ ቀይኑን ሀላፊነቱን አስረክቦ ዱንያን ተሰናበተ።

አሁን የአድም ልጆች በጣም እየተበራከቱ መጥተዋል።ቀይኑን'ም ከባዱን ሀላፊነቱን ተሸክሞ ከቆየ በኋላ ለልጁ መህላዪል መሪነቱን አስረክቦ አያቶቹ የቀመሱትን ፅዋ ቀመሰ።

አሁን ተራው የመህላዪል ነው። መህላዪል በጣም ጀግና ነበር...ወንዳ ወንድነት ይታይበታል ለመጀመርያ ግዜ ዛፍ የቆረጠውም እሱ ነበር።ትላልቅ ህንፆዎችን ከእንጨት በመገንባት ምርጥ ከተማም መስርቷል።የባቢሎንን ከተማ እና አቅሳን የቆረቆረውም መህላዪል ነው።

በነገራችን ላይ መህላዪል ከአመፀኛ የጅን ነገዶች ጋር ከፍተኛ ጦርነት በመክፈት እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ ካደረገ በኋላ ከምድር አባሯቸው ወደ ባህር ዳርቻ እና ወደ ተለያዩ ደሴቶች በታትኗቸዋል።

በጣም የሚያምር ዘውድም ነበረው።ንግግሩም ማራኪ ነበር...ንግስናውም ለ40 አመታት ያህል ከከረመ በኋላ ነፍሱን ለፈጣሪዋ አስረከበ።

መህላዪል ከሞተ በኋላ ልጁ የርድ የአባቱን ዙፋን ያዘ።እሱም ለተወሰነ ግዜ አስተዳደረ'ና ቦታውን ለልጁ (ኸኑኽ) ኢድሪስ ዐ.ሰ አስረክቦ የሙታንን መንደር ተቀላቀለ።

•••✿ ❒ ተ_ፈ_ፀ_መ ❒✿•••

በቀጣይ #ነብዩሏህ_እድሪስ(ዐ.ሰ) ታሪክ እንጀምራለን 🥰
#share
@alahu_akber1
'
•••✿ ❒ የነብዩሏህ ኑህ ዐለይሂ ሰላም ❒✿•••

#ክፍል 2

ከሰማይ የወረደው ውሀ እና ከምድር የወጣው ውሀ ሲገናኝ ምድር ከአቅሟ በላይ መጥለቅለቅ ጀመረች።ያን ግዜ መርከቧ ቀስ እያለች መንሳፈፍ ጀመረች።

ውሀው በየሰዐቱ እየጨመረ ነው አጋጣሚ ኑህ ዐ ሰ ሁኔታውን ለማጣራት ወደ ምድር ሲመለከቱ የአብራካቸው ክፋይ የሆነው ልጃቸው አንዴ ሲወድቅ አንዴ ሲነሳ ውሀው ሲያንከራትተው ተመለከቱት።

እንዲህም ሲሉ ተጣሩ፦"ልጄ ና ከኛ ጋር ተሳፈር ከካሀዲያን ህዝብም አትሁን"

ልጁ ግን በትዕቢት የተሞላ ነው'ና፦"ከውሀው ይጠብቀኝ ዘንድ ወደ ተራራ እወጣለሁ" ብሎ መለሰላቸው።

እሳቸውም፦" ዛሬ ከአላህ ትዕዛዝ ምንም ጠባቂ የለም (እርሱ) ያዘነለት ካልሆነ በቀር" ብለው ንግግራቸውን ሳይጨርሱ እንደ ትልቅ ተራራ ያለ ማዕበል መጣና ልጁን ጠራርጎ ወሰደው።

ኑህም ልጄ እያሉ ወደ አላህ ሲጮሁ አላህም፦" ኑሕ ሆይ! እርሱ ከቤተሰብህ አይደለም፤ እርሱ መልካም ያልሆነ ሥራ ነው፤ በርሱ ዕውቀት የሌለህንም ነገር አትጠይቀኝ፤ እኔ ከሚሳሳቱት ሰዎች እንዳትሆን እገስጽሀለሁ" አለው።ወዲያውኑ ኑህ ተፀፀተና ተመለሰ፡፡አለም ጌታዬ ሆይ በሱ እውቀት የለለኝን ነገር የምጠይቅህ ከመሆን ኤኔ በንተ አጠበቃለሁ ዓለ፡፡ ለኔም በትመረኝ እና በታዝነልኝ ከከሳረመዎች እሆናለሁ ዓለ፡፡

ውሀውም ምድርን ለ40 ቀናት ያህል ካጥለቀለቀ በኋላ ምንም አይነት ነፍስ ያለው ነገር ከምድረ ገፅ ጠፋ።

እብኑ አባስ በወሩት ሀዲስ ኑህ እና ተከታዬቹ በመርከቧዎ ውስጥ ለ6ወራት ቆይተዋል፡፡ በቡዙ ዘገባወች እንደተጠቀሰው ኑህ እና አማኞቹ ከመርከቢቱ የወረዱት በአሹራ እለት ነው፡፡በሙሀረም በ10ኛው ቀን ማለት ነው፡፡በቡዙ ዘገባወች እንደተጠቀሰው ነቢያችን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ይህነን አሏህ ሙሳን ዐ ሰ ከመስመጥ ያደነበትን አና ኑህን አለይሂሰላም ከመጥለቅለቅ ያደነበትን ያአሹራ እለት በፆም አክበረዋል፡፡

መጥለቅለቁ በአሏህ ሲበሀነሁ ወተዓላ በወረደ ትዕዛዝ ተጠናቀቀ፡፡

ያን ግዜ አላህም ምድርን፦"ምድር ሆይ! ውሃሽን ዋጪ፡፡ ሰማይም ሆይ (ዝናብሽን) ያዢ፡፡" ብሎ ምድርን ከመጥለቅለቅ አስቆመ።ቅጣቱም ተጠናቀቀ፤

ምድር ትንሽ ጠፈፍ ማለት ስትጀመር ኑህን እና ተከታዮቹን የተሸከመችው መርከብ በሰላም ጁዲይ በተባለ ተራራ ላይ አረፈች።

ከዚያነም፡አሏህ ሱ ወ እንዲህ ዓለው ኑህ ሆይ ከኛ በሆነ ሰላም በንተ ለይ እና አንተምጋ ባሉት ህዝቦች፣ ትውልድ ላይ በሆኑ በረከቶችን የተጎናጠፉክ ሁነህ ውረድ፡፡

ከነሱ ዘሮች የሆኑ ህዝቦችም በቅርቢቱ አለም በርግጥ እናስመቻችዋለን።ከዝህ ብሇላ መልሰው ወደ ክህደት ለሚገቡ ደግሞ ከዚያም ከኛ የሆነ አሳማሚ ቅጣት ይነካችዋል ተባለ፡፡

ኑህ በመርከቢቷዋ በቆየበት ቆይታ ውሃው ቶሎ እንዲሰርግ ይፈልግ ነበር፣ በዚሂም ግዜ እርግበን አዲስ ነገር ታመላክተው ዘንድ ይልካት ነበር፣

ምነም ነገር ሰትይዝ ተመለስ ነበር፡፡

ከእለታት አንድ ቀን የዘይቱን ቅረጫፉ አመጣቺለት፣ በዚህም ወሃው የሰረገና አተክልቶች መብቀል እንደጀመረ አወቀ፡፡

እንደገና መልሶ ሲልካት በግሮቿዋ ላይ የጭቃ ቅሬት የዛ ተመለሰች፡፡ ፉቺው በመሬት ላይ አረፈች ማለት ነው፡፡

የበዚህም መጥለቅለቁ እንዳበቃ አወቀ፡፡

ይህ እኛ ዘንድ በታረክ መዛግብት ውስጥ ይገኛል፡፡ከዚህ ተነስተው ነው ሌሎች የሰላም እርግብ የሚሉት፡፡
በግሮቻ የምታዝለውም የዘይቱን ቀንዘል ያነን የሚጦቅም ነው፡፡

ኑህ ዐ ሰ ከአደም ልጆች መካከል እነዚያ ከሱጋ የቀሩት ብቻ እንጂ ሌሎች የሌሉ ሲሆን ወረድ፡፡በምደር ላይ የሉ ሰወች ሁሉ አለቀዋል፡፡በረግጥ መደር እንዳዐሁኑ ግዜ የሰው ልጆች አልተሰረጬባትም፡፡
በተወሰነች ስፉራ በአረብ ደሴት ፣ በፊሊስጢን፣ና በዙሯዋ ብቻ ነበር የሰው ልጆች ሰፈረውባት የነበረው እነኝህ ክልል ብቻ ነበሩ፡፡የተቀሩ ምድሮች የሰው ልጆች፡አልነበሩባትም፡፡ግን የተጥለቀለቀቺው ምደር ሁላ ነበር፡፡

ከዚያን አሏህ ከኑህ ዐ ሰ ጋ የነበረትን ህዝቦች በሙሉ መሀን አደረጋቸው፡፡ መውለድ የማይቺሉ፤ ለኑህ ና ለባለቤቱ በስተቀር ለሌሎች ልጅ ሊወለድ አልቻለም፡፡ከመደር ላይ ከዘለቀው ከኑህ ዝሪያ በስተቀር ሌላ አልቀረም ፡፡

ከዚህም የተነሳ ኑህ ዐ ሰ ሁለተኛው አደም በመባል ይጠራል፡፡ሁለተኛ የሰው ልጅች አባት በመባል ተሰይሞል፡፡

በመጨረሻም አላህ ኑህን ዐ ሰ፦"ኑህ ሆይ! እኔ ፍጥረታትን የፈጠርኩት እንዲገዙኝ ነው።እኔ ያዘዝኳቸውንም እንዲታዘዙኝ ነው።ነገር ግን አመፁኝ፤ከኔ ሌላ የሆነንም አካል ጌታ አድርገው ያዙ። ያን ግዜ ቁጣዬም እነሱ ላይ ተፈፃሚ ሆነ በውሀም አጥለቀለቅኳቸው" ብሎ ወህይ አወረደለት።

አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ የ ኑህን (ዐ ሰ) ህዝብ በውሀ ካጥለቀለቀ በኋላ በምድር ላይ ከ ኑህ(ዐ ሰ) ጋር አብረው ከዳኑት ምዕመናን ውጭ ምንም አይነት የሰው ልጅ አልቀረም ነበር።ኑህ ከወሃው መጥለቅለቅ ቡሇላ 350ዓመት ኖረ፡፡

አሏህ ሱበሃነሁ ወተዓላ እንደጠቀሰው፤ለ350አመታት አሏህን ተገዢና አመስጋኝ ሆኖ ነው የኖረው፡፡

እብኑ ማጀህ በዘገቡት ሀዲስ፣ ነቢዩ (ሰዐወ) የኑህን ፆምን ሲገልፁ ኑህ ዐ ሰ ከኢድ ቀናት ውጭ ያሉትን የዓመቱ ቀናትን ሁሉ የፆሙ ነበር በለዋል፡፡በኢድ ለት ያፈጥራል እንጂ በተቀሩት ቀናት ሁሉ በፆም ላይ ነው፡፡ ኑህ ዐ ሰ የሆን ዓመት ከቆየ ቡሇላ ሞቴ፡፡

ስለሱ ከተዘገቡ ዘገባወች አመዛኙ መካ እንደተቀበረ የሚናገረው ነው፡፡በዐንዳድ ዘገባዎች ደግሞ ሉብናን ሊባኖስ ሀገር በሚገኘው ከርከር በቃ በተባለ ስፉራ የተቀበረ መሆኑን ተነግሯል፡፡ይህም ዘገባ ሚዛን ያለው ነው፡፡ኑህ አለይሂሰላም 3ልጆች ነበሩት ፣ ሳም ፣ሃም ና ያፌስ!!

በሳም ልጆች ውስጥ፦ነጭ ነት ና ትነሽ ጡቁረነት ነበረበት፡፡ ወደ ጠይምነተም የሚያመዝን መልክም አለ፣ነጭነትም ቀይነትም ነበረበት፡፡

በሀም ልጆች ዉስጥ ደግሞ፦ጡቅረት የሚሃይል ሲሆን፣ ጢቂትነጭነት ይገኝበታል፡፡አብዛኛቸው ግን ጡቅረት አለበት፤
የያፌስልጆች ደግሞ፦ነጭነት ና ቀይነት የለባቸው ናቸው፡፡አረቦች እና ኢስሪዒላዊያን የሳም ዝሪያወች ናቸው፡፡

አፍሪካዊያን ደግሞ፦ የሃም ዝሪያ ናቸው፡፡ቱርኮች ፣ምስረቅ ኢሲያወች ና አውሮፓዊያኖች ደግሞ የያፌስ ዝሪያወች ናቸው፡፡

•••✿ ❒ ተ_ፈ_ፀ_መ ❒✿•••

በቀጣይ #ነብዩሏህ ሁድ(ዐ.ሰ) ታሪክ እንጀምራለን 🥰
#share
@alahu_akber1
'
•••✿❒ ነብዩሏህ ሁድ ዐለይሂ ሰላም ❒✿•••

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኑህ ዐ ሰ እና በዘመኑ የነበሩት ሰዎች ከሞቱ በኋላ አንዱ አንዱን ሲተካ ምድር ዳግም በሰዎች ትሞላ ጀመር።

ያ ዘመን ካለፈ በኋላ የነበሩ ህዝቦችም ማንም አምልኮ ከምያውቀው በላይ ጣኦትን ማምለክ ተያያዙት።የህዝቡ መለያ ስማቸውም (ዓድ) ይባላል።

በመጀመርያ የዓድን ህዝቦች ላስተዋውቃችሁ...

የዓድ ህዝቦች በዐረቢያ ምድር በየመን ግዛት አህቃፍ በሚባል አካባቢ ኢረም በተባለች ከተማ የሚኖሩ በጣም ትላልቅ ቁመና ያላቸው ህዝቦች ሲሆኑ፤አላህ ስፍር ቁጥር የሌለውን የፀጋ አይነት ያትረፈረፈባቸው ህዝቦች ናቸው።

ከፀጋዎቻቸውም የሚኖሩበት ምድር በጣም ለቡቃያ አመቺ እና ለም አፈር ያለበት አካባቢ ነው።

ሰውነታቸውም በጣም ግዙፎች እና ረጃጅሞችም ነበሩ።

ከሰውነታቸው መግዘፍ የተነሳ አንድን የቴምር ዘንባባ በሁለት ጣታቸው ይነቅሉ ነበር።(የተምር ዛፎች ምን ያህል ግዙፍ እንደሆኑ ዐረብ ሀገር ያላችሁ ውዶች ታውቁታላችሁ)

ነገር ግን አላህ ለዋለላቸው እንዲህ አይነት ኒዕማ ምላሻቸው ምስጋና ሳይሆን ድንበር ያለፈ አመፅ እና መኩራራት ነበር።

የኑህ ህዝቦች ያደርጉት የነበረውን የጣኦት አምልኮ አሟሙቀው ጀመሩት።ያም አላንስ ብሏቸው ምድርን በተለያዩ የወንጀል አይነቶች ይሞሏትም ጀመር።

ነገር ግን ለቅጣት የማይቸኩለው አላህ በእዝነት አዘል ጥበቡ ከመጥፎ ከልክሎ ወደ መልካም የሚመራቸውን (ሁድ) የተባለውን መልዕክተኛ ከመሀከላቸው ላከላቸው።

ሁድ ዐ ሰ መልካም፣ቁጥብ፣የተረጋጉ እና አንደበተ ርቱዕ እና ዐረብኛ ቋንቋን ለመጀመርያ ግዜ የተናገሩ ሰው ናቸው።አላህም እሳቸውን ወደ ህዝባቸው በመሄድ የጌታቸውን ተልዕኮ እንዲያደርሱ አዘዛቸው።

ሁድ'ም ዐ ሰ የጌታቸውን ትዕዛዝ በመቀበል ወደ ዝባቸው ሄደው፦"እኔ ከጌታችሁ የተላክሁ ነብይ ስሆን፤በዚህ አለምም አላህ የሚባል ጌታ አላ።ከሱ ሌላ አምላክ የለም እነዚህ ከተለያዩ ድንጋይ እና እንጨት ጠርባችሁ ምታመልኳቸው ጣኦታት መጥቀምም መጉዳትም የማይችሉ ደካማ ሲሆኑ ከናንተ ጥበቃን ይሻሉ እንጂ እራሳቸውንም አይጠብቁም።

እኔን የታዘዘኝ ከሞት በኋላ ጀነት ይገባል እኔንም ያስተባበለኝ ጀሀነም መቀመጫው ስትሆን መቀመጫነቷስ ምንኛ ከፋ።" ብለው ማስጠንቀቅ ጀመሩ።

እነሱም ነቢያቸው በሚናገረው ግራ በመጋባት፦"እንዴት ነው አማልክቶቻችንን ትተን አንድን ፈጣሪ ብቻ ምንገዛው!!! ይህ ሰውዬ ምን አይነት ቂልነት ነው ይዞብን የመጣው" ይሉ ነበር።

ሁድ ዐ ሰ ህዝቦቹ የሚያሳዩት የመልስ ምት ለቅፅበት እንኳን ተስፋ አላስቆረጣቸውም ነበር። ይልቁኑ፦"እኔ ከናንተ ዘንድ የፈጣሪያችሁን ጥሪ ለማድረስ ከመሀከላችሁ የተመረጥኩ ስሆን፤የተላክሁበትንም ተልዕኮ ያለመሰላቸት በተደጋጋሚ ወደ እናንተ አደርሳለሁ።

እስቲ ፀሀይን እና ጨረቃን ተመልከቱ...ማን ነው የሚያፈራርቃቸው!!!

ማን ነው'ስ የፈጠራቸው!!!

ምድርንና ሰማይንም ተመልከቱ ማን ነው ምድርን አንጥፎ ሰማይን ያለ መሶሶ ያንጣለለው!!!

ተዉ ህዝቦቼ ጌታችሁን አምልኩት።ተጠንቀቁ እናንተ ከሞታችሁ በኋላ ትቀሰቀሱ'ና በሰራችሁት ትተሳሰባላችሁ።መልካም የሰራ ለነፍሱ ነው መጥፎ የሰራም ከከሳሪዎችም ይሆናል" እያሉ ይጠሯቸው ነበር።

ይህን የነቢያቸውን ጥሪ በሰሙ ግዜ፦"ይህን ሰው ከአማልክቶቻችን አንዱ በመጥፎ ተመልክቶታል(አብዷል)" በማለትም ይተቹት ጀመር።

አንዳንዴም፦"ይሄ ሂሳብ፣ጀነት፣ጀሀነም፣መቀስቀስ....ምናምን ምትለው ምን ማለት ነው?" እያሉም ይከራከሩታል።

የዓድ ህዝቦችም በምድር ላይ ያለ አግባብ ኮሩ፡፡ «ከእኛ ይበልጥ በኀይል ብርቱ ማን ነው?» አሉም፡፡ ያ የፈጠራቸው አላህ እርሱ በኀይል ከእነርሱ ይበልጥ የበረታ መኾኑን አያዩምን? በተዓምራታችንም ይክዱ ነበሩ። (ሱረቱል ፉሲለት)

ሁድ ዐ ሰ የህዝቡ ሁኔታ ተስፋ ሲያስቆርጠው፦"እናንተ ከምትሰሩት ሁሉ እኔ ነፃ መሆኔን ምስካሪ ሁኑ" እያለ የሱን ጥሪ ባለመቀበላቸው በዱንያ የሚወርድባቸውንም ቅጣት ያበስራቸውም ጀመር።

እነሱም፦"ምንድነው ዝም ብለህ ቅጣት ቅጣት...እያልክ ምታስፈራራን!!! እንደውም እስቲ ቅጣት ምትለውን አምጣው" እያሉ ሲያሾፉ

ሁድም ዐ ሰ፦"ይህ የማስጠንቅቃችሁ ቅጣት በናንተ ላይ ተፈፃሚ ይሆናል። አትጠራጠሩ" አሏቸው። በመጨረሻም ሁድ ዐ ሰ በህዝባቸው ላይ ዱዓ ማድረግ ጀመሩ።

ከዚያም አላህ የቅጣቱን አርጩሜ በህዝቡ ላይ ሊያወርድ መጀመርያ ለረጅም አመታት ዝናብ በማቋረጥ ምድሪቱን አድርቆ እንስሳቶቻቸውን አጠፋባቸው።

ሁድም ዐ ሰ፦"ከዚህ ሁሉ እንግልት ሊያድናችሁ እሚችለው በጌታችሁ ማመን ብቻ ነው" አላቸው።

እነሱም፦"በረሀብ እና በጥማት እንሞታታለን እንጂ ከጣኦቶቻችን ሌላ ማንንም አንለምንም" በማለት ጣኦታት ዘንድ እየሄዱ ኡኡኡ... ይሉ ጀመር።

ጣኦቶቻቸው ዘንድ ሄደው እሪ ብለው ሲወጡ ሰማይን በደመና ተሞልቶ አገኙት።በጣምም ተደሰቱ አማልክቱ ፀሎቶቻቸውንም እንደሰሙ አመኑ ጥሩ ዝናብ ሊዘንብልን ነው በማለትም ተመፃደቁ።

ያን ግዜ ሁድ ዐ ሰ፦"ይህ እኮ አምጣልን ያላችሁት የቅጣት ደመና ነው እንጂ እናንተ እንደምትሉት ዝናብ አይደለም" አላቸው።

ከዚያም ከፍተኛ ጉልበት የለው ንፋስ ከተማቸውን ያናውጥላቸው ጀመር።ቀስ በቀስ ንፋሱ አስፈሪ ድምፅን እየቀላቀለ በክፍተኛ ጩሀት ህዝቡን ወደ ሰማይ ማፈናጠር ጀመረ።

በዚህ ሁኔታ ለ 7 ሌሊቶች እና ለ 8 ቀናት

ያህል ንፋሱ ዘለቀ። በነዚያ የቅጣት ቀናት ሰውም እንስሳትም ምንም አይነት ፍጥረት አልቀረም ነበር።በሁድ ዐ ሰ ያመኑት ምዕመናን ሲቀሩ ሁሉም የመቅሰፍቱ ሰለባ ሆኑ.....

አሏህ ሱበሃነሁ ወተዓላ ነቢዩሏህ ሁድን ዐ ሰ እና ከሱጋ ያመኑት አዳነቸው፡፡

•••✿ ❒ ተ_ፈ_ፀ_መ ❒✿•••

በቀጣይ #ነብዩሏህ ሉጥ(ዐ.ሰ) ታሪክ እንጀምራለን 🥰
#share
@alahu_akber1
ማንም ወደ ከተማዋ እንዳይዞር ማስጠንቀቂያ ስለተሰጠ ማንም አልዞረም ነበር።የሉጥ ሚስት ግን ወደኋላ በመዞር፦"ወይኔ ወገኔ,,,,!!!" በማለት ጮኸች።
ትልቅ የድንጋይ ፍንጣሪ መጣና እራሷን ለሁለት ከፈለላትና የመቅሰፍቱ ሰለባ ሆነች።

አላህም ይህን ዘግናኝ ክስተት ሲተርክ እንዲህ ይላል፦
"ትዕዛዛችንም በመጣ ግዜ (የከተማይቱን) ላይዋን ከታች አደረግን(ገለባበጥናት) ተከታታይም የሆነ የሸክላ ድንጋይ በርሷ ላይ አዘነብን" (ሱረቱል ሁድ)

እንዴት አድርጎ እንደገለባበጣቻው ታውቃላችሁ...!!!
መጀመሪያ ጂብሪል ክንፉን በከተማይቱ መሬት ውስጥ ዘቅዝቆ አስገባው።
ከዚያም ከተማይቱን ከነ ህንፃዎቿ ነቅሎ ወደ ሰማይ ከፍ ካደረገ በኋላ ገለበጠው'ና መልሶ ወደ ምድር ተከለው።

ሉጥ ከነ ተከታዮቹ ብዙ ርቀት ከተጓዘ በኋላ ሱዒር የተባለ አከባቢ በመስፈር ይህ ነው ተብሎ በታሪክ መዛግብት እድሜው ባይሰፍርም እዛው ሱዒር ላይ ህይወቱ አልፏል። (ዐለይሂ ሰላቱ ወሰላም)

•••✿ ❒ ተ_ፈ_ፀ_መ ❒✿•••

በቀጣይ #ነብዩሏህ ሷሊህ(ዐ.ሰ) ታሪክ እንጀምራለን 🥰
#share
@alahu_akber1
ሁለተኛው ቀን ደርሶ በነጋታው ሰዉ ሲነቃ ሁሉም ፊቱ ደም መስሏል።በድንጋጤ የሞቱትም ብዙ ነበሩ።ያን ቀን በትካዜ እና በፍራቻ ካሳለፉ በኋላ የማይደርስ የለም'ና ሶስተኛዋ ቀን መጣች።

ፊቶቻቸውን ጥቁረት ወረረው፣ተስፋም ቆረጡ ሁሉም በመሰባሰብ ከፈናቸውን ለብሰው ሽቶ ተቀብተው ሞታቸውን መጠባበቅ ጀመሩ።
ልክ ፀሀይ ጀንበሯን ተሻግራ ብቅ ማለት ስትጀመር ከወደ ሰማይ በኩል እንደመብረቅ ያለ፣ ከፍተኛ ድምፅ ያለው ነገር መጣ።ምድርም በሀል መንቀጥቀጥ ጀመረች...ጂብሪልም በከፍተኛ ድምፁ ጮኸባቸው።ያን ግዜ ልቦቻቸው ከደረታቸው መበጣጠስ ጀመረ።አይኖቻቸውን ወደ ሰማይ ያፈጣሉ...

መቅሰፍቱ ከየት በኩል እንኳን እንደመጣ ማወቅ እየተሳናቸው ነፍሶቻቸው ወደ ሰውነታቸው ዳግም ላትመለስ ተነጠለቻቸው።
የከተማይቱ ህዝብ ሁሉም በያሉበት በድን ሁነው ሲሞቱ አንዲት ሴት ብቻ ቀረች ስሟም ከልባ ቢንት ሰለቅ ይባላል።

ለሳሊህ ዐ ሰ ከፍተኛ ጥላቻ ሲኖታት የክህደትን ዘውድ ከራሷ አኑራለች። ይህን ስትመለከት እግሬ አውጭኝ ብላ ከሀገሩ ሸሸች። ብዙ ከተጓዘችም በኋላ አንድ የዐረብ ነገድ የሚኖሩበትን መንደር ደረሰችና የሆነውን ሁሉ ነገረቻቸው።
በመጨረሻም ውሀ እንዲያጠጧት ጠይቃ ልክ ውሀውን ስትቀምሰው ነፍሷ የሙታንን መንደር ተቀላቀለች።
ሳሊህ ዐለይሂሰላም ወደ ሌላ ቦታ ተሰደደ ሷሊህ እና ከሱጋ ያመኑት ሰወች ወደ ተከበረቺው ወደ ተባረከቺው ፊለስጢን ሀገር ተሰደደ፡፡
ከዚያንም በረምላ ከተማ መኖር ጀመረ፡፡ ቆይቶም ሷሊህ ዐለይሂሰለም በ58 አመታቸው በዛው በረምላ ከተማ የዚህችን አለም ጣጣ አጠናቅቀው ነፍሳቸውን ለጌታቸው አስረከቡ።

በነገራችን ላይ ረሱላችን (ሰዐወ) አንድ ቀን ለተቡክ ዘመቻ ባልደረቦቻቸውን ይዘው በመሄድ ላይ ሳሉ የሳሊህ ህዝቦች የጠፉበትን ከተማ ደረሱ። ማንም አይኖርበትም..የተወሰኑ ሶሃቦች በሷሊህ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ምንጮች ውስጥ ሊቀዱ ሄዱ፣ የተወሰኑት፣ ደግሞ መገልገያ እቃወችን አመጡ፥

የአሏህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መገልገያ መሰረያወቹ እንዲሰበሩ እና የተቀዳም ውሃ እንዲደፋ አዘዙ፡፡ከዚያ ውሃ የተሰረው ምግብ ሁሉ እንድደፋ አዘዙ፦ከዚያም ነቢያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፦

"ይህችን ከተማ ስትገቡ እያለቀሳችሁ ፣መልቀስ እንኳዋ ባትችሉ ለማልቀስ የዳዳቹህ ሁናቹህ እንጂ ዝም ብላችሁ እንዳትገቡ።
እኔ በነሱ የወረደው በላእ እናንተን እንዲያገኝብኝ አልፈልግም" አሏቸው።ፊዳከ አቢ ወ ኡም ወነፍሲ ወደሚ ወዒርዲ ያ ረሱሉላህ

በዚያ አከባቢም ያሉ ነገሮችን ሁሉ ለባልደረቦቻቸው አሳይዋቸው።ግመሏም የወጣችበትን እና የተገደለችበትንም ቦታ ወስደው አሳይዋቸው።

•••✿ ❒ ተ_ፈ_ፀ_መ ❒✿•••

በቀጣይ #ነብዩሏህ_ኢብራሂም(ዐ.ሰ) ታሪክ እንጀምራለን 🥰
#share
@alahu_akber1
•••✿ ❒ የነቢዩሏህ_እስሃቅ_ና_የአቆብ_ዐለይሂሰላም_ታረክ ❒ ✿•••

#ክፍል 2

አሁን ያዕቁብ የትውልድ ሀገሩን ፊለስጢንን ለቅቆ የሀራንን ምድር ከረገጠ 20 አመታትን አስቆጥሯል።

ያዕቁብም አጎቱ ዘንድ በመሄድ፦"አጎቴ አሁን ፍቀድልኝ'ና ሚስት ልጆቼን ሰብስቤ ቤተሰቦቼ ጋር ልሂድ" ይለዋል።

አጎቱ ላባንም፦"ያዕቁብ እኔ ባንተ ሰበብ ብዙ ንብረቴ በረካ ሆኖልኛል።ስለዚህ የፈለግከውን ያህል ንብረት ጠይቀኝ" አለው።

ላባን በጣም ለቁጥር ሚያዳግት የእንስሳት መዐት ስለነበረው

ያዕቁብም፦"በዚህ አመት የሚወለዱትን ሁሉ ባጎች ስጠኝ።

ከተቀረው እንስሳቶችህ መልካቸው ጥቁር በነጭ የሚወልዱትንም ስጠኝ።

ነጭ ዳማዎችን እና ቀይ ዳማዎችንም ስጠኝ" አለው።

አጎቱ ላባንም፦"እሺ" አለው።

ያዕቁብም ይህን ሀላፊነት ልጆቹ እንዲወጡ አዘዘ።

በመጀመርያ ያዕቁብ እርጉዝ የሆኑ እንስሳቶችን ከሌሎቹ እንስሳት የሶስት ቀን መንገድ ያህል ርቀት አራራቃቸው።

ነጭ ዳማዎችን እና ቀይ ዳማዎችን እንደዚያው አራራቃቸው።ይህን ካደረገ በኋላ እርጉዞቹም ወለዱ ያዕቁብም ድርሻውን ለይቶ በአላህ ትዕዛዝ ለጉዞ ተዘጋጀ።

አሁን ያዕቁብ የብዙ ሺህ በጎች...እንስሳቶች...እና የብዙ አገልጋዮች ባለቤት ሆኗል።

ወደ ፊለስጢን ጉዞ ሲዝጀምሩ ራሂል የተባለችዋ የያዕቁብ ሚስት የአባቷን ጣኦት ደብቃ ይዛ ወጣች።

ያዕቁብ ልጆቹን፣ሚስቶቹን፣አገልጋዮቹን፣እንስሳቶቹን...ሁሉ ሰብስቦ በረሀውን እያቋረጠ ብዙ ተጎዞ የሀራንን ምድር ካጋመሰ በኋላ አጎቱ ላባን እና የሀራን ከተማ ነዋሪዎች ተከትለውት ደረሱበት።

ልክ እንዳገኙት አጎቱ ላባን በወቀሳ መልኩ፦"ያዕቁብ ለምን ሳትነግረኝ ትተህ ትሄዳለህ!!!

ምነው በደስታ ተሰነባብተን ከአከባቢው ህዝብ ጋር ጨፍረን ብንሸኛቹስ" በማለት አንድ ጣኦት ይዘው እንደመጡም አክሎ ጠየቀው።

ያዕቁብ ዐ ሰ ምንም አይነት ከጣኦት ጋር ግንኙነት ባይኖረውም ለአጎቱ ሲል የሚስቶቹን እቃ ሀሉ ፈተሸለት ምንም አላገኘም።

ራሂል ግን ጣኦቱን ይዛው ስለነበር ለፍተሻ ፍቃደኛ አልሆነችም ነበር አሞኛል አልነሳም አለች።

ያን ግዜ ያ ጣኦት ምናልባት ጀልዓድ በተባለ ዳገት ላይ ይኖራል በሚል ግምት ላባን ልጆቹን እና የእህቱን ልጅ ያዕቁብን ተሰናብቷቸው ተመለሰ።

ያዕቁብ የትውልድ ሀገሩን ሊገባ ጥቂት ሲቀራው መላዕክት እየወረዱ እንኳን ደህና መጣህ እያሉት ያልፉ ነበር።

አሁን ያዕቁብ ሳዒር የምትባል ቦታ ላይ ደርሷል ግን ሀገሩ ሊገባ የወንድሙን በቀል ፈርቷል።

እዛው ሆኖ እንደማለማመጥ አይነት ነገር ፅፎ ደብዳቤ ለወንድሙ ላከለት።

በነጋታው ሌላ የዛቻ ደብዳቤ የያዘች ወረቀት ዒስ(የያዕቁብ ወንድም) 400 እግረኛ ጦር አሰልፎ እየመጣ መሆኑን የሚያስረዳ መልዕክት ከወደ ፊለስጢን በኩል ለያዕቁብ መጣችለት።

ያዕቁብም ፈራ...አላህንም ከወንድሙ ተንኮል እንዲታደገው ተማፀነ...ለአላህም ስለት ገባ።

ያዕቁብም ፈራ...አላህንም ከወንድሙ ተንኮል እንዲታደገው ተማፀነ...ለአላህም ስለት ገባ።

ከዚያም ወንድሙን ሊያስደስት በርከት ያለ ስጦታም አዘጋጀለት...

200 ሴት ፍየሎችን እና 20 ወንድ ፍየሎች

200 ሴት በጎችን እና 20 ወንድ በጎች

30 (ኮርማ)በሬዎችን እና 40 ላሞች

20 ሴት ግመሎችን እና 10 ወንድ ግመሎች

እና አራቱንም የስጦታ አይነቶችን ለያይቶ ሊልክ በአራት ቡድን የተደራጀ አገልጋዮችን አዘጋጀ እና ቀድሞ አንዱን ቡድን ለከ።

የመጀመርያው ቡድን ስጦታን ይዞ ሄዶ ትንሽ ራቅ ሲል ሁለተኛውን ይልካል ሁለተኛውም ትንሽ ራቅ ሲል ሶስተኛውን ይልካል....

እንዲ እንዲ እያለ አራቱንም የስጦታ አይነት ከነ አገልጋዮቻቸው ጨምሮ፦"ማንም የማን ነው ብሎ ከጠየቃችሁ ከያዕቁብ ለዒስ የተላከ ስጦታ ነው በሉ" ብሎ ላካቸው።

ይህንንም ሊያደርግ የቻለው ወንድሙ ዒስ ስጦታዎች በተከታታይ ሲመጡለት ደስታው የላቀ ይሆናል በሚል ነው።

ከዚያም የመጀመሪያውን ስጦታ የያዘው የአገልጋልይ ቡድን ዒስ እና ወታደሮቹ ያሉበትን ቦታ ሲደርሱ

ዒስ፦"ይህ የማን ነው?" ብሎ ጠየቀ።

አገልጋዮቹም፦" ከያዕቁብ ለዒስ የተላከ ስጦታ ነው" አሉት።

እሱን ተቀበላቸውና ሁሉም የስጦታ ነጂ ቡድኖች ስጦታዎቻቸውን ተራ በተራ እየነዱ አስረከቡት።

ያዕቁብም ሚስቶቹን ልጆቹን እና የተቀሩ አገልጋዮቹን አስከትሎ በሌሊት ወደ ወንድሙ ጉዞ ጀመረ።

(በነገራችን ላይ በዚህች የሌሊት ጉዞ ነበር ክርስቲያን ወገኖች ያዕቁብ እና እግዚአብሄር ተደባድበው ያዕቁብ አሸነፈው የሚሉት።)

ሌሊቱን ተጉዞ ፀሀይ ጀንበሯን አምልጣ መውጣት ስትጀምር ለ20 አመታት ያህል የተለያዩ ወንድማሞች አይን ለአይን ተገጣጠሙ።

ዒስ 400 ጦረኛዎችን አሰልፏል።ያዕቁብም ወንድሙን ሲያየው 7 ግዜ አጎበደደለት(ይህ በዘመናቸው ሀራም አልነበረም የዘመናቸውም ሰላምታ ነበር።

በቀጣይ ክፍላችን ለዩሱፍ ሲሰግዱ እንዳስሳለን"

ዒስ ዱዓውን ከአባቱ የዘረፈውን ወንድሙን ሲያይ ሄዶ ተጠምጥሞበት ወንድሙን እየሳመ ያለቅስ ጀመር።በዚህ አጋጣሚ ከአጠገቡ ያሉትን ሴቶችን

ልጆችን እና አገልጋዮችን ሲመለከት፦"ይሄም ሁሉ ኬት አምጥተህ ነው?" አለው።

ያዕቁብም፦"እነዚህ አላህ የሰጠኝ ስጦታዎቼ ናቸው" አለው።

ይህን ግዜ የያዕቁብ ልጆች እና ሚስቶች ተራ በተራ እየመጡ ዒስን ከዘየሩ በኋላ ያዕቁብ በአገልጋዮቹ አማካኝነት ለዒስ የላከውን ስጦታ ዒስ መቀበል እንቢ አለ።

ያዕቁብም ለምኖት እንዲቀበል አደረገው'ና አብረው በረሀውን እያቆራረጡ አባታቸው ወደሚገኝበት የፊለስጢን ምድር መትመም ጀመሩ።

በዚህ ጉዞ ላይም ሳሉ ያኔ....ያዕቁብ አጎቱ ጋ ሲሄድ ተኝቶ ህልም ያየበትን ቦታ ደረሱና እዛ ቦታ ያዕቁብ በ200 በግ ያንን ቦታ ከአንድ ገበሬ ገዛው'ና

አንድ ትልቅ የአምልኮ ቦታ ሰራ(ቁድስ) ከዚያ በኋላ ነው በሱለይማን ዘመን ሱለይማን ያደሰው።

በዚህ ጉዞ ላይም ሳሉ ነበር አንድ ደስታ እና ትልቅ ሀዘን በያዕቁብ ቤተሰብ የተከሰተው።

ነፍሰ ጡር የነበረችው ትንሿ ራሂል ምጥ አስቸገራት...ብዙ ከተጨነቀች በኋላ ቢንያሚን የተባለ ልጅ ተገላግላ ለራሷም ዱንያን ተገላገለቻት።


ያዕቁብም ባለቤቱን መንገድ ላይ ቀብሮ ሀዘኑን ታቅፎ ወደ አባቱ ጉዞ ቀጠለ።

ከአባቱም ተገናኝቶ በከንዓን ምድር ሀብሩን በምትባል(ኢብራሂም ይኖር በነበረበት) አካባቢ መኖር ጀመረ።

ኢስሀቅም እርጅና ተጫጭኖትም ስለነበር ጌታው የፃፈለትን 180 አመት ካጠናቀቀ በኋላ ነፍሱን ለጌታው አስረከበ።

የነበቢዩሏህ የኢስሃቅ ዐለይሂሰላም ታረክ አዚህ ላይ ተፈፀመ።

የነቢዩሏህ የአቆብ ዐለይሂሰላም ታሪክ የቀረውን የነቢዩሏህ ዩሱፍ ታረክ ውስጥ እናየወለንን!!


•••✿ ❒ ተ_ፈ_ፀ_መ ❒✿•••

በቀጣይ #ነብዩሏህ_የአቆብ_ና_ዩሱፍ(ዐ.ሰ) ታሪክ እንጀምራለን 🥰
#share
@alahu_akber1
•••✿ ❒ ነብዩሏህ_የአቆብ_ና_ዩሱፍ_ዐለይሂ_ሰላም_ታርክ ❒✿•••

#ክፍል 4

አሁን ያዕቁብ የትውልድ ሀገሩን ፊለስጢንን ለቅቆ የሀራንን ምድር ከረገጠ 20 አመታትን አስቆጥሯል።

ያዕቁብም አጎቱ ዘንድ በመሄድ፦"አጎቴ አሁን ፍቀድልኝ'ና ሚስት ልጆቼን ሰብስቤ ቤተሰቦቼ ጋር ልሂድ" ይለዋል።

አጎቱ ላባንም፦"ያዕቁብ እኔ ባንተ ሰበብ ብዙ ንብረቴ በረካ ሆኖልኛል።ስለዚህ የፈለግከውን ያህል ንብረት ጠይቀኝ" አለው።

ላባን በጣም ለቁጥር ሚያዳግት የእንስሳት መዐት ስለነበረው

ያዕቁብም፦"በዚህ አመት የሚወለዱትን ሁሉ ባጎች ስጠኝ።

ከተቀረው እንስሳቶችህ መልካቸው ጥቁር በነጭ የሚወልዱትንም ስጠኝ።

ነጭ ዳማዎችን እና ቀይ ዳማዎችንም ስጠኝ" አለው።

አጎቱ ላባንም፦"እሺ" አለው።

ያዕቁብም ይህን ሀላፊነት ልጆቹ እንዲወጡ አዘዘ።

በመጀመርያ ያዕቁብ እርጉዝ የሆኑ እንስሳቶችን ከሌሎቹ እንስሳት የሶስት ቀን መንገድ ያህል ርቀት አራራቃቸው።

ነጭ ዳማዎችን እና ቀይ ዳማዎችን እንደዚያው አራራቃቸው።ይህን ካደረገ በኋላ እርጉዞቹም ወለዱ ያዕቁብም ድርሻውን ለይቶ በአላህ ትዕዛዝ ለጉዞ ተዘጋጀ።

አሁን ያዕቁብ የብዙ ሺህ በጎች...እንስሳቶች...እና የብዙ አገልጋዮች ባለቤት ሆኗል።

ወደ ፊለስጢን ጉዞ ሲዝጀምሩ ራሂል የተባለችዋ የያዕቁብ ሚስት የአባቷን ጣኦት ደብቃ ይዛ ወጣች።

ያዕቁብ ልጆቹን፣ሚስቶቹን፣አገልጋዮቹን፣እንስሳቶቹን...ሁሉ ሰብስቦ በረሀውን እያቋረጠ ብዙ ተጎዞ የሀራንን ምድር ካጋመሰ በኋላ አጎቱ ላባን እና የሀራን ከተማ ነዋሪዎች ተከትለውት ደረሱበት።

ልክ እንዳገኙት አጎቱ ላባን በወቀሳ መልኩ፦"ያዕቁብ ለምን ሳትነግረኝ ትተህ ትሄዳለህ!!!

ምነው በደስታ ተሰነባብተን ከአከባቢው ህዝብ ጋር ጨፍረን ብንሸኛቹስ" በማለት አንድ ጣኦት ይዘው እንደመጡም አክሎ ጠየቀው።

ያዕቁብ ዐ ሰ ምንም አይነት ከጣኦት ጋር ግንኙነት ባይኖረውም ለአጎቱ ሲል የሚስቶቹን እቃ ሀሉ ፈተሸለት ምንም አላገኘም።

ራሂል ግን ጣኦቱን ይዛው ስለነበር ለፍተሻ ፍቃደኛ አልሆነችም ነበር አሞኛል አልነሳም አለች።

ያን ግዜ ያ ጣኦት ምናልባት ጀልዓድ በተባለ ዳገት ላይ ይኖራል በሚል ግምት ላባን ልጆቹን እና የእህቱን ልጅ ያዕቁብን ተሰናብቷቸው ተመለሰ።

ያዕቁብ የትውልድ ሀገሩን ሊገባ ጥቂት ሲቀራው መላዕክት እየወረዱ እንኳን ደህና መጣህ እያሉት ያልፉ ነበር።

አሁን ያዕቁብ ሳዒር የምትባል ቦታ ላይ ደርሷል ግን ሀገሩ ሊገባ የወንድሙን በቀል ፈርቷል።

እዛው ሆኖ እንደማለማመጥ አይነት ነገር ፅፎ ደብዳቤ ለወንድሙ ላከለት።

በነጋታው ሌላ የዛቻ ደብዳቤ የያዘች ወረቀት ዒስ(የያዕቁብ ወንድም) 400 እግረኛ ጦር አሰልፎ እየመጣ መሆኑን የሚያስረዳ መልዕክት ከወደ ፊለስጢን በኩል ለያዕቁብ መጣችለት።

ያዕቁብም ፈራ...አላህንም ከወንድሙ ተንኮል እንዲታደገው ተማፀነ...ለአላህም ስለት ገባ።

ያዕቁብም ፈራ...አላህንም ከወንድሙ ተንኮል እንዲታደገው ተማፀነ...ለአላህም ስለት ገባ።

ከዚያም ወንድሙን ሊያስደስት በርከት ያለ ስጦታም አዘጋጀለት...

200 ሴት ፍየሎችን እና 20 ወንድ ፍየሎች

200 ሴት በጎችን እና 20 ወንድ በጎች

30 (ኮርማ)በሬዎችን እና 40 ላሞች

20 ሴት ግመሎችን እና 10 ወንድ ግመሎች እና አራቱንም የስጦታ አይነቶችን ለያይቶ ሊልክ በአራት ቡድን የተደራጀ አገልጋዮችን አዘጋጀ እና ቀድሞ አንዱን ቡድን ለከ።

የመጀመርያው ቡድን ስጦታን ይዞ ሄዶ ትንሽ ራቅ ሲል ሁለተኛውን ይልካል ሁለተኛውም ትንሽ ራቅ ሲል ሶስተኛውን ይልካል....

እንዲ እንዲ እያለ አራቱንም የስጦታ አይነት ከነ አገልጋዮቻቸው ጨምሮ፦"ማንም የማን ነው ብሎ ከጠየቃችሁ ከያዕቁብ ለዒስ የተላከ ስጦታ ነው በሉ" ብሎ ላካቸው።

ይህንንም ሊያደርግ የቻለው ወንድሙ ዒስ ስጦታዎች በተከታታይ ሲመጡለት ደስታው የላቀ ይሆናል በሚል ነው።

ከዚያም የመጀመሪያውን ስጦታ የያዘው የአገልጋልይ ቡድን ዒስ እና ወታደሮቹ ያሉበትን ቦታ ሲደርሱ

ዒስ፦"ይህ የማን ነው?" ብሎ ጠየቀ።

አገልጋዮቹም፦" ከያዕቁብ ለዒስ የተላከ ስጦታ ነው" አሉት።

እሱን ተቀበላቸውና ሁሉም የስጦታ ነጂ ቡድኖች ስጦታዎቻቸውን ተራ በተራ እየነዱ አስረከቡት።

ያዕቁብም ሚስቶቹን ልጆቹን እና የተቀሩ አገልጋዮቹን አስከትሎ በሌሊት ወደ ወንድሙ ጉዞ ጀመረ።

(በነገራችን ላይ በዚህች የሌሊት ጉዞ ነበር ክርስቲያን ወገኖች ያዕቁብ እና እግዚአብሄር ተደባድበው ያዕቁብ አሸነፈው የሚሉት።)

ሌሊቱን ተጉዞ ፀሀይ ጀንበሯን አምልጣ መውጣት ስትጀምር ለ20 አመታት ያህል የተለያዩ ወንድማሞች አይን ለአይን ተገጣጠሙ።

ዒስ 400 ጦረኛዎችን አሰልፏል።ያዕቁብም ወንድሙን ሲያየው 7 ግዜ አጎበደደለት(ይህ በዘመናቸው ሀራም አልነበረም የዘመናቸውም ሰላምታ ነበር።

በቀጣይ ክፍላችን ለዩሱፍ ሲሰግዱ እንዳስሳለን"

ዒስ ዱዓውን ከአባቱ የዘረፈውን ወንድሙን ሲያይ ሄዶ ተጠምጥሞበት ወንድሙን እየሳመ ያለቅስ ጀመር።በዚህ አጋጣሚ ከአጠገቡ ያሉትን ሴቶችን

ልጆችን እና አገልጋዮችን ሲመለከት፦"ይሄም ሁሉ ኬት አምጥተህ ነው?" አለው።

ያዕቁብም፦"እነዚህ አላህ የሰጠኝ ስጦታዎቼ ናቸው" አለው።

ይህን ግዜ የያዕቁብ ልጆች እና ሚስቶች ተራ በተራ እየመጡ ዒስን ከዘየሩ በኋላ ያዕቁብ በአገልጋዮቹ አማካኝነት ለዒስ የላከውን ስጦታ ዒስ መቀበል እንቢ አለ።

ያዕቁብም ለምኖት እንዲቀበል አደረገው'ና አብረው በረሀውን እያቆራረጡ አባታቸው ወደሚገኝበት የፊለስጢን ምድር መትመም ጀመሩ።

በዚህ ጉዞ ላይም ሳሉ ያኔ....ያዕቁብ አጎቱ ጋ ሲሄድ ተኝቶ ህልም ያየበትን ቦታ ደረሱና እዛ ቦታ ያዕቁብ በ200 በግ ያንን ቦታ ከአንድ ገበሬ ገዛው'ና አንድ ትልቅ የአምልኮ ቦታ ሰራ(ቁድስ) ከዚያ በኋላ ነው በሱለይማን ዘመን ሱለይማን ያደሰው።

በዚህ ጉዞ ላይም ሳሉ ነበር አንድ ደስታ እና ትልቅ ሀዘን በያዕቁብ ቤተሰብ የተከሰተው።

ነፍሰ ጡር የነበረችው ትንሿ ራሂል ምጥ አስቸገራት...ብዙ ከተጨነቀች በኋላ ቢንያሚን የተባለ ልጅ ተገላግላ ለራሷም ዱንያን ተገላገለቻት።

ያዕቁብም ባለቤቱን መንገድ ላይ ቀብሮ ሀዘኑን ታቅፎ ወደ አባቱ ጉዞ ቀጠለ።

ከአባቱም ተገናኝቶ በከንዓን ምድር ሀብሩን በምትባል(ኢብራሂም ይኖር በነበረበት) አካባቢ መኖር ጀመረ።

ኢስሀቅም እርጅና ተጫጭኖትም ስለነበር ጌታው የፃፈለትን 180 አመት ካጠናቀቀ በኋላ ነፍሱን ለጌታው አስረከበ።

የነበቢዩሏህ የኢስሃቅ ዐለይሂሰላም ታረክ አዚህ ላይ ተፈፀመ።

የነቢዩሏህ የአቆብ ዐለይሂሰላም ታሪክ የቀረውን የነቢዩሏህ ዩሱፉ ታረክ ውስጥ እናየወለንን!!

      •••✿ ❒ ተ_ፈ_ፀ_መ ❒✿•••

በቀጣይ #ነብዩሏህ_አዩብ(ዐ.ሰ) ታሪክ እንጀምራለን 🥰
#share
@alahu_akber1