𝐑𝐢𝐨 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜✌️
21.8K subscribers
433 photos
192 videos
8 files
476 links
...................꧁﷽꧂.....................

🕋"ከአላህ በስተቀር በሀቅ የሚመለክ አምላክ የለም" 🕋
#ኢስላማዊ_መረጃዎች
#ኢስላማዊ_ታሪኮች
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረቱ_ታሪኮች
#አጫጭር_ዳዕዋዎች እና
#የተለያዩ_ሀዲሶችን_ያገኛሉ
#owner 👉 #riyad (#rio)
for any comment @rio_comment_bot
Download Telegram
'
•••✿ ❒ ነብዩሏህ አደም ዐለይሂ ሰላም ❒✿•••

#ክፍል 2

አደምም እማያውቀው ቦታ ላይ አንድ አጫዋች በሌለበት ቁጭ ብሎ የድብርት ስሜት ተሰማው። ከዝያም ጋደም ባለበት ድንገት እንቅልፍ ሸለብ አደረገው። ልክ ከእንቅልፉ ሲነቃ እራስጌው ላይ አንዲት ሴት ተመለከት ከአይኖቿ ፍቅር እና እዝነት ይነበብባታል።

አደም፦"ከመተኛቴ በፊት እዚህ አልነበርሽም"

ሀዋ፦"አዎ"

አደም፦"በተኘሁበት ነው የመጣሽው ማለት ነዋ!!!"

ሀዋ፦"አዎ"

አደም፦"ኬት ነው የመጣሽው"

ሀዋ፦"ካንተ ውስጥ ነው የመጣሁት።አንተ በተኛህበት ነው አላህ ካንተ የፈጠረኝ።

አደም፦"ለምንድነው አላህ የፈጠረሽ?"

ሀዋ፦"አንተ እኔ ላይ ልትረጋ"

አደም አላህን አመሰገነ'ና፦'ብቸኝነት እየተሰማኝ ነበር" አለ።

ከዚያም መላዕክት መጡ'ና፦"ስሟ ማን ነው?" አሉት።

አደምም፦"ሀዋ" አለ።

መላዕክትም፦"ለምንድነው ሀዋ ተብላ የተሰየመችው" ብለው ሲጠይቁት

አደምም፦'እሷ ከኔ ነው የተፈጠረችው እኔ ደግም ህያው ነኝ ለዛ ነው ሀዋ ያልኳት"ብሎ መለሰላቸው።

ከዚያም አድም እና ሀዋ በጀነት ውስጥ ሳሉ አላህ አደምን እንዲህም አለው፦"አንተ አደም ጀነት ውስጥ ላንተ ሁሉ ነገር ሀላል ሲሆን ይህችን ቅጠል ላንተም ለሚስትህም ሀራም አድርጌያለሁ'ና እንዳትቀርቧት"

ከዚያም ሁለቱም በጀነት እየተዝናኑ ሳለ ኢብሊስ መጣ'ና አጠገባቸው ማልቀስ ጀመረ። ፦"ምን ሁነሀል?" ብለው ሲጠይቁት እንዲህ በማለት መለሰላቸው፦

"እንዲህ ስትዝናኑ በጣም ታምራላችሁ ግን በጣም እኔ ሚያሳዝነኝ ይሄ ደስታችሁ ዘለቄታ አይኖረውም።ግን ይህ ደስታችሁ ዘላለማዊ እንዲሆን ምትፈልጉ እንደሆን ይህችን ቅጠል ብሏት።ምክንያቱም አላህ ጌታችሁም መልኣኮች እንዳትኾኑ ወይም ከዘላለም ነዋሪዎች እንዳትኾኑ እንጂ ከዚህች ዛፍ አልከለከላችሁም" ብሎ በመወስወስ አሳስቶ ቅጠሏን አበላቸው።

(በነገራችን ላይ አንዳንድ ሰዎች በውድቅ ንግግሮቻቸው ሴቶችን መውቀስ ሲፈልጉ ፨ሀዋ ናት አደምን ያሳሳተችው፨ ይላሉ ይህ ከእውነት የራቀ ነው ሀዋ አይደለችም ቅጠሉን እንዲበሉ የገፋፋችው።ሁሉቱም ናቸው ተሳስተው የበሉት።)

አደም በስህተት የቀመሳትን ቅጠል መብላት ሲጀምር ልቡን እያመመው መጣ...ፍርሀት እና አለመረጋጋት ነገሰበት።

ዞር ብሎ ሚስቱን ሲያይ እርቃኗን ናት። እራሱንም ሲመለከት እርቃኑን መሆኑ ታወቀው። ከዚያም ቅጠል በመበጠስ ሀፍረተ ገላዎቻቸውን መሸፈን ጀመሩ። በፈፀሙትም ሀፅያትም ተፀፅተው እንዲህ በማለት አላህን ይማፀኑ ጀመር፦" ጌታችን ሆይ! ነፍሶቻችንን በደልን፡፡ አንተ ለእኛ ባትምር ባታዝንልንም በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንኾናለን"

አላህም ወደ ምድር እንዲወርዱትዕዛዙን አስተላለፈ እንዲህም አላቸው፦" ከፊላችሁ ለከፊሉ ጠላት ሲኾን ውረዱ፡፡ ለእናንተም በምድር ላይ እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ መርጊያና መጠቀሚያ አላችሁ።

በእርሷ/በምድር ላይ ትኖራላችሁ፡፡ በእርሷም ላይ ትሞታላችሁ፡፡ ከእርሷም ውስጥ ትወጣላችሁ" አሁን አደም እና ሀዋም ጉዞ ወደ ምድር....

አላህ ሁለቱንም ወደ ምድር ሲያወርዳቸው አደም ትካዜ ተቆጣጠረው፣ እጅጉን ሀሳብ ገባው...ሀዋ ደሞ ማልቀስ የሌት ተቀን ተግባሯ ሆነ።

ከዚያም አላህ ለሁለቱም፦"ምድር እኮ እናንተ የመጣችሁበት ምንጫችሁ ናት።ከአፈር ነው የተፈጠራችሁት ወደአፈር ነው ምትመለሱት...ከአፈርም ነው ምትቀሰቀሱት" እያለ አፅናናቸው።

ከዚያም አደም እና ሀዋ መሬት ላይ ቁጭ ብለው ሳለ ጂብሪል( ዐ.ሰ ) 7 የስንዴ ፍሬዎችን ይዞለት መጣ እያንዳንዱ ፍሬ 70ሺህ ዘለላ ያበቅል ነበር።አደምም ለጅብሪል፦"ምን ላድርገው" አለው።

ጂብሪልም፦"መሬት ላይ ዝራው" አለው።

አደምም ዘራው'ና ጂብሪል እያሳየው አጨደ።

አዚያም ፈጨው...ከዚያም አቦከው...ከዚያም ጋገረው እና ሲቀዘቅዝ ከባለቤቱ ጋር በመብላት የህይወትን ውጣ ውረድ ይላመድ ጀመር...

ሁለቱም ሚለብሱት ነገር ስላልነበራቸው በግ አረደ'ና ቆዳውን ለራሱም ለሷም ልብስ ሰርቶ ለበሱ። እንዲ እንዲ እያሉ የህይወትን ውጣ ውረዶች ለመዱት ልጆችም መውለድ ጀመሩ።ሀዋ ሁሌ ምትወልደው መንታ መንታ ነበር አንድ ወንድ እና አንድ ሴት...ልጆቻቸውን ሲያጋቡ በአንድ ላይ የተወለዱትን አያጋቡም ነበር አንድ ላይ የተወለዱት ሴቷ በሌላ ግዜ የተወለደውን ወንድ ስታገባ ወንዱም እንደዛው።

እናላችሁ አንድ ግዜ ሀቢል እና ቃቢል የተባሉ የአደም ልጆች ሁለቱም መንትያ እህቶች አሏቸው እና ሀቢል የቃቢልን እህት(አብራው የተወለደችውን) ማግባት ፈልጎ ሲጠይቅ ቆንጆ ስለነበረች ቃቢል ለራሱ ፈልጓት ለሀቢል ከለከለው።

አደምም ቃቢል እህቱን ለሀቢል እንዲድርለት ሲጠይቅም ፍቃደኛ አልሆን አለ።ከዚያም አደምም ለሁለቱ ልጆችቁርባን እንዲያዘገጁ አዘዛቸው'ና አድም ሀጅ ሊያደርግ ወደ መካ ተነሳ(ሀጅ በኢብራሂ ግዜ የተጀመረ እንዳይመስላችሁ ድሮም ቦታዋ ትታወቃለች)

ከዚያም አደም ልጆቹን የሚያስጠብቀው አካል የለም'ና ሰማያትን ልጆቹን እንዲጠብቁ አደራ ሲል እንቢ አሉ...ምድርንም ሲጠይቃት እንቢ አለች ተራራዎችንም ሲለምን ሀላፊነት መውሰድ ሀሉም ፈሩ።ግን ልጁ ቃቢል እኔ እወስዳለሁ ብሎ የአደምን ልጆች ሀላፊነት ቃቢል ተሸከመ። አደምም ጉዞውን ቀጠለ..

አደም ከሄደ በኋላ ልጆቹ ሀቢል እና ቃቢል ልጅቷን ለማግባት ለአላህ ቁርባን አቀረቡ።ሀቢል እረኛ ነገር ስለነበር ጥሩ የሚያምር ለአይን ሚማርክ ሙኩት አቀረበ...ቃቢል ደሞ ገበሬ ነበር ግን ተራ ውዳቂ እህል ነው ያቀረበው።

የሁለቱም ቁርባኖች አንድ ቦታ ሳሉ ከሰማይ እሳት ወረደች'ና የሀቢልን ቁርባን በላች(ቁርባኑ ተቀባይነት አግኝቷል ማለት ነው) የቃቢልን ግን ተወችው።(አላህ አልተቀበለውም ማለት ነው)

ያን ግዜ ቃቢልም፦"እህቴን ምታገባ እንደሆን እገድልሀለሁ" አለው ሀቢልን።

ሀቢልም፦"አላህ የሚቀበለው ከጥንቁቆች(እሱን ከሚፈሩት) ነው" አለው።

ያን ግዜ ቃቢልም ወንድሙን ሀቢልን በያዘው ብረት ጭንቅላቱን መቶት ጣለው።(ስለአገዳደሉ የኡለማኦች ልዩነት አለ እሱን ልዘረዝር አልፈልግም)

ቃቢል ወንድሙን ከገደለው በኋላ ሬሳውን ምን እንደሚያደርግ ጠፍቶበት አንድ አመት ሙሉ በጀርባው ተሸክሞ ሲዞር ከርሟል ይባላል።

በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለ አንድ ቀን የወንድሙን ሬሳ እንዴት እንደሚሸሽግ ያሳየው ዘንድ አላህ መሬትን የሚጭር ቁራ ላከለት፡፡ ቃቢልም፦«ወይ እኔ የወንድሜን ሬሳ እሸሽግ ዘንድ እንደዚህ ቁራ ብጤ መኾን አቃተኝን» አለ፡፡ ቃቢል ወንድሙን ሀቢል ከቀበረው በኋላ በመግደሉ በጣም ተፀፀተ። አደምም የልጁን ሞት ሲሰማ በከፍተኛ ሁኔታ አዘነ።

ክፍል 3 ይቀጥላል .....

#share
@alahu_akber1
'
•••✿ ❒ ነብዩሏህ አደም ዐለይሂ ሰላም ❒✿•••

#ክፍል 3

የቃቢልም ቅጣቱ ከዱንያ ጀመረ ሁለቱ ታፋዎቹ ተጣበቁ።ፀሀይ ወደዞረችበት ሁሉ አላህ የቃቢል አይን እንድታፈጥ አደረገ መቃጣጫ ይሆነው ዘንድ።
አደም እና ሀዋ በልጃቸው ሀቢል ሀዘን በጣሙን ስለተጎዱ አላህ ሸይስ የሚባል መልካም ልጅ ሰጥቶ ሀዘናቸውን አስረሳቸው።

ሸይስ ማለት የ አላህ ስጦታ ማለት ነው።እንደዛ ብለው ሊሰይሙት የቻሉትም ሀቢል ከሞተ በኋላ አላህ እሱን በምትኩ ስለሰጣቸው ነው።

በሰው ልጅ ታሪክ አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ /104 አንድ መቶ አራት መለኮታዊ መፃህፍትን ወደተለያዩ መልዕክተኞች አውርዷል።ከዛ ውስጥ 50 ሀምሳው በሸይስ ነበር የተወረደው።

ለመጀመሪያ ግዜ በጥበብ የተናገረውም ሸይስ ነው።

ለመጀመርያ ግዜ በወርቅ እና በአልማዝ ንግድ የጀመረውም ሸይስ ነው።

ለመጀመርያ ግዜ በሚዛን መገበያየትንም የጀመረው ሸይስ ነው።

ለመጀመርያ ግዜ ከምድር ማዕድናትን ማውጣት ያስተማረውም ሸይስ ነበር...

በነገራችን ላይ የሰው ልጆች ሁሉ የዘር ሀረጋቸው ከሸይስ ጋር ነው ሚገናኙት።ምክንያቱም ሌሎቹ የአደም ልጆች ተበታትነው ቀሩ እንጂ አልተዋለዱም።

በዚህ ሁኔታ ሳለ አንድ ቀን መለከል መውት ቀጠሮዋን ጠብቆ አደምን ነፍሱን ለማውጣት ሲመጣ አደም አልሰማህም ገና 40 አመት ይቀራኛል ብሎ ተሟገተ።

መለከል መውትም፦" በርግጥ እድሜህ 1000 ነበር ግን ያኔ ለዳዉድ ከኔ 40 ቀንሳችሁ 100 ሙሉለት ብለህ ነበር" አለው።

አደምም ምንም ማውቀው ነገር የለም እንዲ ብዬም አላውቅም ብሎ ድርቅ አለ።ያን ግዜ አላህም የምስክር ወረቀቱን እና ምስካሪ ያደረጋቸውን መላዕክትን እንደ ማስረጃ አቀረበበት።

አደምም አመነ ነገር ግን አላህ የቀረችውንም 40 አመት በእዝነቱ እንዲኖር

ፈቀደለት። ይሁን እንጂ የማይደርስ የለም'ና 40 አመቷ ተጠናቅቃ አሁንም አደም ሞት አፋፍ ላይ ደረሰ።

ያን ግዜ አደም ምክራዊ ኑዛዜውን ለልጁ ሸይስ ይናዘዝ ጀመር።የቀን እና የሌሊትን ክፍለ ግዜ አስተማረው...በሁለቱ ክፍለ ግዜ ውስጥም የሚደረጉ አምልኮዎችንም በዝርዝር አስተማረው።

ቀኑ ጁምዓ ነው...አደም በጣም ታሟል...ልጆቹ የሚያደርጉት ጠፍቷቸዋል...በዚህ መሀል አደም ለልጆቹ የጀነት ፍራፍሬ እንዲያመጡለት አዘዛቸው።

እነሱ የጀነት ፍራፍሬ የት ይሁን፤ምን አይነት ይሁን ሚያውቁት ነገር የለም።ብቻ ሰብሰብ ብለው ፍለጋ ወጡ።በፍለጋ ላይ ሳሉ መላዕክትም ሰብሰብ ብለው ከፈን፣የሬሳ ሽቶ፣መቆፈሪያ፣አካፋ...ምናምን ይዘው ሲያልፉ ተገጣጠሙ።

ከዚያም መላዕክቶቹም ለአደም ልጆች፦"ወደ የት ነው ምትሄዱት?" አሏቸው። ልጆቹም፦"አባታችን ታሟል። የጀነት ፍራፍሬ ስላሰኘው ልንፈልግለት እየሄድን ነው" አሏቸው

መላዕክቶቹም፦"አባታችሁ ሙቷል ኑ ተመለሱ" ብለው ልጆቹን ይዘው መለሷቸው።

ለአደም መሞት በአጥናፈ አለሙ ያሉ ፍጥረተት በሙሉ ነበር ያለቀሱት ምድርና ሰማያትም ሳይቀሩ።

መላዕክትም የአደምን የቀብር ስነ ስርዐት ለመፈፅም ሲመጡ እናታችን ሀዋ አለቀሰች።አትውሰዱብኝ እያለችም እዬዬ ትል ጀመር።

ከዚያም መላዕክት የአደምን አስክሬን ወሰዱት'ና አጥበው ከፍነው ሽቶ ቀብተው.....ባዘጋጁለት ቀብር ውስጥ(ህንድ ላይ በሚገኝ ተራራ ላይ ነው ቀብሩ) ልጆቹ እያዩ አስገብተውት አፈር መለሱበት።

ከዚያም መላዕክት፦"እናንተ የአደም ልጆች ሆይ! ይህ ከአሁን በኋላ ሙታኖቻችሁን የምትቀብሩበት ስነ ስርዐት ነው" ብለዋቸው ሄዱ።

አደም ከሞተ በኋላ ዋሀ'ም ከአንድ አመት በኋላ ባለቤቷን ተከተለችው።

ከዚህ በኋላ ዱንያ መስመሯን ይዛ የአደምን ልጆች ችግር ልታስተምራቸው ነው።

አደም እና ሀዋ ከሞቱ በኋላ የአድም ልጆች ሀላፊነት ሙሉ በሙሉ ሸይስ ላይ ወደቀ። ሸይስ በጥሩ ሁኔታ የአደምን ልጆች ካስተዳደራቸው በኋላ የሱም የሞት ፅዋ መቅመሻ ግዜው ደረሰ'ና ለልጁ አኑሽ ኑዛዜውን ተናዝዞ ነፍሱን ለፈጣሪው አስረከበ።

የ ሸይስ ልጅ አኑሽ'ም በጥሩ ሁኔታ ሀላፊነቱን ከተወጣ በኋላ የሱም ከዱንያ መሰናበቻ ግዜው ይደርስ'ና እሱም ለልጁ ቀይኑን ሀላፊነቱን አስረክቦ ዱንያን ተሰናበተ።

አሁን የአድም ልጆች በጣም እየተበራከቱ መጥተዋል።ቀይኑን'ም ከባዱን ሀላፊነቱን ተሸክሞ ከቆየ በኋላ ለልጁ መህላዪል መሪነቱን አስረክቦ አያቶቹ የቀመሱትን ፅዋ ቀመሰ።

አሁን ተራው የመህላዪል ነው። መህላዪል በጣም ጀግና ነበር...ወንዳ ወንድነት ይታይበታል ለመጀመርያ ግዜ ዛፍ የቆረጠውም እሱ ነበር።ትላልቅ ህንፆዎችን ከእንጨት በመገንባት ምርጥ ከተማም መስርቷል።የባቢሎንን ከተማ እና አቅሳን የቆረቆረውም መህላዪል ነው።

በነገራችን ላይ መህላዪል ከአመፀኛ የጅን ነገዶች ጋር ከፍተኛ ጦርነት በመክፈት እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ ካደረገ በኋላ ከምድር አባሯቸው ወደ ባህር ዳርቻ እና ወደ ተለያዩ ደሴቶች በታትኗቸዋል።

በጣም የሚያምር ዘውድም ነበረው።ንግግሩም ማራኪ ነበር...ንግስናውም ለ40 አመታት ያህል ከከረመ በኋላ ነፍሱን ለፈጣሪዋ አስረከበ።

መህላዪል ከሞተ በኋላ ልጁ የርድ የአባቱን ዙፋን ያዘ።እሱም ለተወሰነ ግዜ አስተዳደረ'ና ቦታውን ለልጁ (ኸኑኽ) ኢድሪስ ዐ.ሰ አስረክቦ የሙታንን መንደር ተቀላቀለ።

•••✿ ❒ ተ_ፈ_ፀ_መ ❒✿•••

በቀጣይ #ነብዩሏህ_እድሪስ(ዐ.ሰ) ታሪክ እንጀምራለን 🥰
#share
@alahu_akber1
'
•••✿ ❒ ነብዩሏህ_እድሪስ ዐለይሂ ሰላም ❒ ✿•••

#ክፍል 1

በግዜው አባታችን አደም (ዐ ሰ) ከሞተ 15 ክፍለ ዘመናት(1500 አመት) ተቆጥሯዋል።የአደም ልጆች ቁጥር ምንም እንኳን ቢጨምርም በአደም ልጆች ዘንድ እስካሁን ምንም አይነት የኩፍር እንቅስቃሴ የለም ያን ዘመናት ሁሉ የአደም ልጆች አላህን በብቸኝነት እያመለኩት ነው።

አሁን አሁን ግን ሰዎች አስተሳሰባቸው እየተቀየረ መጣ፣ትንሽ ትንሽ የሸይጣን ኮቴ ያንሸራትታቸውም ጀምሯል።
ነቢዩላህ ኢድሪስ (ዐ ሰ) ይባላሉ። ረጅም ሰዐት ዝምታ ያሚያስደስታቸው ሰው ናቸው።ከተናገሩም ሒክማ ያላትን እና አጠር ያለች ንግግር ነበር ሚናገሩት።

ለመጀመርያ ግዜ በቀለም መፃፍን የጀመሩትም እሳቸው ናቸው።

ለመጀመርያ ግዜ ልብስ ሰፍተው መልበስ የጀመሩትም ኢድሪስ ዐ ሰ ናቸው።

ሁሌም ልብስ ሲሰፉ መርፌዋን ባስገቡ'ና ባወጡ ቁጥር ሱብሀን አላህ ይሉ ነበር።

አላህም የኮከብ እውቀትን እና ስለ ሰነ ፈለክ አስተምሯቸዋል።

የእውቀትንም ሁሉ ቁልፍም አላህ ሰጥቷቸዋል።

በዘመናቸው የነበሩትን ሰዎች ስለ አፃፃፍም ያስተምሩ ነበር።

ሀገሪቷ ባቢሎን ትባላለች ዘመኑ ገና የስልጣኔ ጀምበር ብቅ ብቅ የሚልበት ዘመን ነበር። የከተማዋ ህዝብ ለሽርክ እና ለፈሳድ ገና ፍሬሽ ስለሆኑ ኢድሪስ ከዚህ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ ቢመክሯቸውም ጥቂት ሰዎች ሲቀሩ ሰዉ ሁሉ አሻፈረኝ ብሎ ጥመት ላይ መፅናትን መረጠ።

ከብዙ እልህ አስጨራሽ የዳዕዋ ትግል በኋላ ኢድሪስ ዐ ሰ ሀገሪቱን ለቀው ወደ ሌላ ቦታ ለመሰደድ ወሰኑ።ጥቂት ተከታዮቻቸውንም ሲያማክሩ ምንም እንኳን ሀገራቸውን ጥለው ለመውጣት ትንሽ ቢያንገራግሩም በኢድሪስ ዐ ሰ አንደበተ ርቱዕነት በሀሳባቸው ሊስማሙ ቻሉ።

ኢድሪስ ዐ ሰ ከባቢሎን ከተማ ተከታዮቻቸውን ይዘው ወጡ'ና ብዙ ከተጓዙ በኋላ አፍሪካዊቷ ቀደምት ከተማ የሆነችውን ግብፅን ገና ስትቆረቆር ከህዝቧ ጋር ተቀላቀሉ።ገና ከተማዋን ከመግባታቸው ነበር ወደ አላህ እና ወደ መልካም ስነ ምግባር ዳዕዋ ማድረግ የጀመሩት።


በዛም መሀል ወደ ሻም/ሶርያ አከባቢ እና ወደ ፊለስጢን በመሄድ ሰዎችን ወደ አላህ ይጣሩ ነበር።ይሁን እንጂ ለመቀመጫነት ግን ግብፅን ነበር የመረጡት።እዛው ለልጆቻቸውም የተለያዩ ዱንያዊ እና አኺራዊ ትምህርት ይሰጡም ነበር።

በኢድሪስ ዐ ሰ ዘመን ዐለም ላይ ያለው ቋንቋ ብዛት 72 ነበር።የፈለጉበት በመሄድ ዳዕዋ ያደርጉ ዘንድም አላህ ሀሉንም ቋንቋዎች አሳውቋቸውም ነበር።

እንዲህ እንዲህ እያሉ ኢድሪስ ዐ ሰ እድሚያቸው 865 ደረሰ።አላህም እንዲህ ሲል ለኢድሪስ ወህይ አወረደላቸው፦"በያንዳንዱ ቀን የአደም ልጆች ሁሉ የሚሰሩትን አጅር ያህል ላንተም እፅፍልሀለሁ።"

ኢድሪስም ዐ ሰ ግን እድሜያቸው እንዲጨመርላቸው እና ሌላም ብዙ መልካም ስራ መስራት ነበር ፍላጎታቸው።ይሁን እንጂ ፍላጎታቸውን በምኞት ብቻ ሊገድቡት አልፈለጉም ነበር።

አንድ መልዓክ ጓደኛ ነበራቸው'ና እሱን ወደ አላህ ዘንድ እንዲወስዳቸው እና አላህ በእድሚያቸው ላይም ይጨምርላቸው ዘንድ ሊጠይቁት እንደሆነም አስረድተውት ከመልዐኩ ጋር መልዓኩ በሁለት ክንፉ መካከል ይዟቸው አየሩን እየሰነጣጠቁ ጉዞ ወደ ሰማያት ጀመሩ።

ሰማያትን በመልዓኩ ክንፎች እየቀዘፉ በከፍተኛ ፍጥነት 1ኛ ሰማይ ደረሱ...2ኛ....3ኛ....4ኛ ሰማይ ላይ እንደረሱ መለከል መውት ወደ ምድር እየተምዘገዘገ አገኙት'ና ኢድሪስን ዐ ሰ የያዘው መልዓክ መለከል መውትን አስቆሞ የኢድሪስን ዐ ሰ እድሜ ስንት እንደቀረው መዝገቡን እንዲያይለት ጠየቀው።

መለከል መውትም መዝገቡን ተመለከተ'ና፦"ኢድሪስ የታለ" አለው።

መልዓኩም፦"እዚህ ክንፌ ውስጥ ነው" አለው።

ክፍል 2 ይቀጥላል....

#share
@alahu_akber1
'
•••✿ ❒ ነብዩሏህ_እድሪስ ዐለይሂ ሰላም ❒ ✿•••

#ክፍል 2

መለከል መውትም፦"ይገርማል! አሁን እኮ የሱ ቀጠሮ ደርሶ እሱ ጋ ነበር ምከንፈው። እኔ ልገረም የቻልኩት አላህ የኢድሪስን ሩህ በ4ኛ ሰማይ ላይ ሄደህ አውጣ ሲለኝ ግራ ተጋብቼ ነበር ምክንያቱም ኢድሪስ በምድር ላይ ሳለ እንዴት አላህ ከአራተኛ ሰማይ ሩሁን እንዳወጣ ያዘኛል ብዬ ነው።" አለ

መልዓኩም ትንሽ እንዲያቆየው ቢጠይቀውም መለከል መውትም፦"አሁን ነፍሱን እንዳወጣ እዚችው ነው'ና የታዘዝኩት እዚችው ነው ማወጣት" ብሎ ኢድሪስ ዐ ሰ በተወለዱ በ 865 አመታቸው በመልዓኩ እቅፍ ውስጥ ሳሉ ሩሀቸው በ4ኛ ሰማይ ላይ ወጣች።

ለዚህ ነው አላህ በሱረቱ መርየም እንዲህ ያለው፦"በመጽሐፉ ኢድሪስንም (ሄኖክን) አውሳ፡፡ እርሱ እውነተኛ ነቢይ ነበርና፡፡

ወደ ከፍተኛም ስፍራ አነሳነው" ሰደቀላሁል አዚም

ኢድሪስ ዐ ሰ ከሞቱ በኋላ ለተወሰኑ አመታት የሰው ዘሮች አላህን ያለማጋራት በብቸኝነት ያመልኩት ነበር።

ያው ትውልድ ትውልድን ይተካል'ና አላህን በማምለክ ወደር የሌላቸው መልካም'ና በዘመኑ ለነበሩ ሰዎች አርዐያ የሆኑት ውስን ሰዎች ህዝቡን በሞት ይለዩ ጀመር....በዘመኑ የነበሩ ህዝቦችም በነዚያ ደጋግ ሰዎች ህልፈት እጅጉን አዝነዋል።

ሀዘናቸውን ለማስታገስ እና እነዚህን ደጋግ የአላህ ባሮችን ለማስታወስ ሀውልት ሊሰሩላቸው ተነጋገሩበትና እቅዳቸውንም እውን በማድረግ በ5 ትላልቅ እና ደጋግ ሰዎች ስም 5 ሀውልት በከተማ መሀል አቆሙላቸው።

ስማቸውም፦

1፦ወድ

2፦ሱዋዕ

3፦የጉስ

4፦የዑቅ

5፦ነስር...እነዚህ ናችው።

በዚህ መልኩ እነዚህን ደጋግ ሰዎች ሁሌም ያወሷቸው ነበር...የከተማይቱ ሰዎች ለነዚያ ደጋግ የአላህ ባሮች ካላቸው ክብር አንፃር ሀውልቶቻቸውንም ወደር የለሽ ክብር ያከብሩ ነበር።

እንዲህ እንዲህ እያለ ሰዉ ለነዚህ ሀውልቶች ያለው ቦታ ሁኔታውን እየቀየረ መጣ።በሀውልቱ አጠገብ ሲያልፉ ለሀውልቱ ክብር በሚል እያጎበደዱም ማለፍ ጀመሩ።

ግዜው ይነጉዳል ክረምት እና በጋ ቀጠሮዋቸውን ጠብቀው በፍጥነት ይተካካሉ።ክረምት ሲመጣ ዝናቡ በጋ ሲመጣ ፀሀዩ የሀውልቶቹን ይዘት መቀየር ሲጀምር የከተማይቱ ነዋሪዎች ሀውልቶችን ከውድመት ለመታደግ አንድ ቤተ አምልኮ ውስጥ ሊያስገቧቸው ወስኑ።...እች ጠጋ ጠጋ እቃ ለማንሳት ሀ!!!

ሀውልቶቹን መጠለያ ውስጥ ካስገቡ በኋላ ለሀውልቶቹ ያላቸው ቦታ ይበልጥ ጨመረ።በገቡ እና በወጡ ቁጥር ለሀውልቶቹ ማጎብደድ ጀመሩ።

ያን ግዜ አላሁ ሱብሀነሁ አተዓላ ከነዝያ ህዝቦች ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራቸው ዘንድ ኑህ የተባሉ መልዕክተኛን አስነሳ።

•••✿ ❒ ተ_ፈ_ፀ_መ ❒✿•••

በቀጣይ #የነብዩሏህ_ኑህ(ዐ.ሰ) ታሪክ እንጀምራለን 🥰
#share
@alahu_akber1
'
•••✿ ❒ የነብዩሏህ ኑህ ዐለይሂ ሰላም ❒✿•••

#ክፍል 1

አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ ከነዝያ ህዝቦች ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራቸው ዘንድ ኑህ የተባሉ መልዕክተኛን አስነሳ።

ኑህም ህዝባቸውን ሰበሰቡ'ና፦" እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝ፡፡

አላህንም ፍሩ ታዘዙኝም፡፡

በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ(ክፍያ) አልጠይቃችሁም፡፡ ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም" ብለው ህዝባቸውን ተጣሩ።

ይህን ሲሰሙ አስተባበሉት ምንም ሊያምኑለት አላቻሉም።እንዲያውም ያፌዙበት ጀመር። ኑህ ዐ ሰ ያለመሰላቸት ዘወትር ጥሪም ያደርግላቸውም ነበር።

የህዝቦቹ ማፊዝ እና ማላገጥ በበዛበትም ግዜ፦" ወገኖቼ ሆይ! ምንም መሳሳት የለብኝም፡፡ ግን እኔ ከዓለማት ጌታ መልእክተኛ ነኝ፡፡

የጌታዬን መልክቶች አደርስላችኋለሁ፡፡ ለእናንተም እመክራችኋለሁ፡፡ ከአላህም በኩል የማታውቁትን ዐውቃለሁ።" አላቸው።

የኑህን ዐ ሰ ንግግር በሰሙ ግዜ በጣም በመገረም፦" አንተ ኑህ!!! አንተ እኮ እንደኛው ሰው ነህ እንዴት ነው መልዕክተኛ ነኝ ምትለው? በዛ ላይ ጥቂት ተከታዮች አሉህ ሁሉም ግን ድሀ እና ኮሳሳ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ናቸው።

ደግሞም በሀብትም ሆነ በክብር ከኛ ጋር አትመጣጠኑም" ብለውም አስተባበሉ።

ያም አላንስ ብሏቸው እርስ በርስ በሚፈፅሙት የሀውልት አምልኮ እንዲፀኑ ይመካከሩም ጀመር።

ኑህም የህዝቡ ሁኔታ ተስፋ ሲያስቆርጠው በመለማመጥ መልኩ፦አላህን ልትፈሩና ይታዘንላችሁም ዘንድ ከእናንተው (ጎሳ) በኾነ ሰው ላይ እንዲያስጠነቅቃችሁ ከጌታችሁ ግሳጼ ቢመጣላችሁ ትደነቃላችሁን" እያለ ቢያግባባቸውም ክህደታቸው ይበልጥ እየጨመረ እንጂ ምንም አይቀንስም ነበር።

ምንም እንኳን ኑህ ዐ ሰ የህዝቡ ነገር ተስፋ ቢያስቆርጣቸውም ተልዕኮዋቸውን በሚገባ በማድረስ ላይ ቀጥለዋል።

እናም ሁሌ ቀን እና ማታ ህዝባቸውን ስለ አላህ ሲያስታውሷቸው ህዝባቸው የነቢያቸውን ዳዕዋ ከመስማት ጆሮዋቸውን መያዝ ጀመሩ።ጆሮዋቸውን ይዘው መስማት እንቢ ሲሉ ኑህ ዐ ሰ በምልክት ይነግሯቸው ነበር። ኑህም በምልክት ሲነግሯቸው ህዥቡ ግን አይኖቻቸውን በልብሶቻቸው ይሸፍኑ ነበር።

ምንም ተስፋ አልቆርጥ ብሎ መቆም መቀመጥ ሲከለክላቸው፦"ድሆች እና ዝቅተኛ ሰዎች ያንተ ተከታይ ሆነው ሳለ እኛም ከነሱ ጋር እንድንከተልህ ትሻለህን!!! ይልቁንስ እኛ እንድንከተልህ ከፈለግክ እነዚህን ተራ ሰዎች ከጎንህ አርቃቸው።" አሉት።

ኑህ'ም ዐ ሰ፦"እነሱ የሚሰሩትን አላህ ነው ሚያውቀው። እኔ ላባርራቸው አልችልም።

እንዴትስ ረዳቶቼን፣አክባሪዎቼን አባርር ትሉኛላችሁ!!! ቆይ ባባርራቸውስ እኔን ከአላህ ማን ያተርፈኛል? አታስተውሉምን?" ብሎ ጠንከር አለባቸው።

ኑህ ዐ ሰ መልካም ነብይ ነበሩ። ሀብታም፣ድሀ ደከማ፣ጠንካራ፣ትልቅ፣ትንሽ ስይሉ ለሁሉም በክብር የተላኩትን ዳዕዋ አደረሱ።

ምንም እንኳም ለ950 አመታት ዳዕዋ ቢያደርጉም ዳዕዋቸውን ከ80 በላይ ሰው ሊቀበላቸው ባለመቻሉ ሁኔታው ከአቅማቸው በላይ መሆኑን ለጌታቸው ስሞታ ለማቅረብ ተገደዱ።

እንዲህም ሲሉ ለአላህ ነገሩት፦"ጌታዬ! ህዝቦቼ እኮ አስተባበሉኝ። በእኔና በእነርሱም መካከል (ተገቢ) ፍርድን ፍረድ፡፡ አድነኝም፡፡ ከእኔ ጋር ያሉትንም ምእምናን(አድን)፡፡"

ከዚህ በኋላ የኑህ ዐ ሰ የዳዕዋ ጥሪ ዛቻ አዘል መሆን ጀመረ።እነሱም ለኑህ ዐ ሰ ዛች ግድ አልነበራቸውም ይልቁኑ፦"የምትዝትብንን አምጣ እውነተኛ ከሆንክ" እያሉ ሲሳለቁበትም ጀመር።

ኑህም፦"ይህ እኮ በኔ ቁጥጥር ውስጥ አይደለም። ያ የአላህ ስልጣን ነው" ይላቸዋል።

አሁን ነገሩ መቋጫው ተቃርቧል አላህም አስፈሪ ወህይ እንዲህ ሲል ወደ ኑህ አወረደ፦" ከሕዝቦችህ በእርግጥ ካመኑት በስተቀር (ወደፊት ከአሁን በኋላ) አያምኑም፡፡ ይሠሩትም በነበሩት (ክህደት) አትዘን"

በመቀጠልም አላህ ኑህን ዐ ሰ የዘንባባ ችግኝ እንዲተክል አዘዘው።ያች ዛፍ ለማፍራት ስትበቃ የአላህ ቅጣትም በነዚያ ህዝቦች ላይ እንደሚፈፀም ቃል ገባለት።

የአላህ የተለምዶ እዝነቱ ይታወቀ ነው። ትልልቅ ሰዎች ባጠፉት ህፃናትን አይቀጣም'ና ህፃናት የቅጣቱ ሰለባ እንዳይሆኑ ቅጣቱ ከመፈፀሙ ከ40 አመታት በፊት የሴቶቹ ማህፀን ፅንስ መሸከም እንዳይችል አደረገው።

ለ40 አመት ያህል ምንም አይነት ህፃን ሳይወለድ ቀረ።በዚያ ዘመም ኑህ ዐ ሰ የታዘዘውን ዛፍ እንክብካቤ ሲያደርግ እነዚህ አመፀኛ ህዝቦች እንዲህ በማለት ይሳለቁበት ነበር፦"አንተ ኑህ ነቢይ ነኝ እያልክ ዘራፍ ብለህ አላዋጣ ሲልህ ወደ ግብርና ገባህ እንዴ!!!" ድንጋይም ይወረውሩባቸው ነበር።

የተተከለው ዛፍ 50 አመት ሲሞላው አላህም ለኑህ ዐ ሰ ወህይ በማውረድ ዛፎችን እንዲቆጣቸው አዘዛቸው።

ኑህም ዐ ሰ ዛፎቹን ከቆረጠ በኋላ አላህም ትልቅ መርከብ እንዲሰራ አዘዘው።ጂብሪልም መርከብ እንዴት እንደሚሰራ ሊያሳየው ከሰባት ሰማያት ወረደ።

አላህም እንዲህ ሲል ወህይ አወረደ፦

"የመርከቧ ርዝመት 1200 ክንድ

የጎን ስፋት 800 ክንድ

ከፍታው ደግሞ 80 ክንድ የሆነችን መርከብ ስራ"

በተንጣለለ አሸዋማ እና በረሀማ ቦታ ላይ ኑህ መርከቧን መስራት ጀመሩ።ህዝቦቹም ከአጠገቡ ሲያልፉ፦"አንተ ኑህ ከነብይነት አናፂነት ይሻላል ብለህ ነው?" እያሉ ያፌዙበታል።

ከፊሎቹ ደግሞ፦"አንተ ኑህ መርከብ እኮ ለባህር ነው ሚሰራው አንተ እልም ያለ በረሀ ላይ ትሰራለህ እንዴ!" ይሏቸዋል።

ኑህም ለስለስ ባለ አንደበት፦"ዛሬ በኛ ላይ ብትሳለቁብን ነገ እኛም በእናንተ ላይ እንሳለቅባችኋለን" ይላቸው ነበር።

የመርከቧ ስራ ከተጠናቀቀ በኋላ አላህ ኑህን ያመኑበትን ሁሉ መርከቧ ላይ እንዲጭን እና ከእያንዳንዱ እንስሳት እና የዱር አራዊት አንድ ወንድ አንድ ሴት በመርከቧ እንዲጭን አዘዘ።የምዕመናኑ ቁጥር 80 ብቻ ነበር።

ለኑህም ዐ ሰ ሁለት ሚስቶች ነበሩት አንደኛዋ ሙስሊም ስትሆን ሁለተኛዋ አመፀኛ ካፊር ናት።እሱም ሙስሊሟን መርከብ ላይ ጫናት።

መርከቧ ውስጥ ሁሉም ቦታውን ከያዘ በኋላ ፀሀይ ብርሀኗን ተነጠቀች ምድር በአስፈሪ ፅልመት ተዋጠች።

ሰማይም ዶፍ ዝናብን ማንቧቧት ጀመረ...በከርሰ ምድርም ታምቆ የነበረው ውሀ ምድሪቱን እየሰነጠቀ ለጉድ መፍለቅ ጀመረ።

ከሰማይ የወረደው ውሀ እና ከምድር የወጣው ውሀ ሲገናኝ ምድር ከአቅሟ በላይ መጥለቅለቅ ጀመረች።ያን ግዜ መርከቧ ቀስ እያለች መንሳፈፍ ጀመረች።

ክፍል 2 ይቀጥላል....

#share
@alahu_akber1
'
•••✿ ❒ የነብዩሏህ ኑህ ዐለይሂ ሰላም ❒✿•••

#ክፍል 2

ከሰማይ የወረደው ውሀ እና ከምድር የወጣው ውሀ ሲገናኝ ምድር ከአቅሟ በላይ መጥለቅለቅ ጀመረች።ያን ግዜ መርከቧ ቀስ እያለች መንሳፈፍ ጀመረች።

ውሀው በየሰዐቱ እየጨመረ ነው አጋጣሚ ኑህ ዐ ሰ ሁኔታውን ለማጣራት ወደ ምድር ሲመለከቱ የአብራካቸው ክፋይ የሆነው ልጃቸው አንዴ ሲወድቅ አንዴ ሲነሳ ውሀው ሲያንከራትተው ተመለከቱት።

እንዲህም ሲሉ ተጣሩ፦"ልጄ ና ከኛ ጋር ተሳፈር ከካሀዲያን ህዝብም አትሁን"

ልጁ ግን በትዕቢት የተሞላ ነው'ና፦"ከውሀው ይጠብቀኝ ዘንድ ወደ ተራራ እወጣለሁ" ብሎ መለሰላቸው።

እሳቸውም፦" ዛሬ ከአላህ ትዕዛዝ ምንም ጠባቂ የለም (እርሱ) ያዘነለት ካልሆነ በቀር" ብለው ንግግራቸውን ሳይጨርሱ እንደ ትልቅ ተራራ ያለ ማዕበል መጣና ልጁን ጠራርጎ ወሰደው።

ኑህም ልጄ እያሉ ወደ አላህ ሲጮሁ አላህም፦" ኑሕ ሆይ! እርሱ ከቤተሰብህ አይደለም፤ እርሱ መልካም ያልሆነ ሥራ ነው፤ በርሱ ዕውቀት የሌለህንም ነገር አትጠይቀኝ፤ እኔ ከሚሳሳቱት ሰዎች እንዳትሆን እገስጽሀለሁ" አለው።ወዲያውኑ ኑህ ተፀፀተና ተመለሰ፡፡አለም ጌታዬ ሆይ በሱ እውቀት የለለኝን ነገር የምጠይቅህ ከመሆን ኤኔ በንተ አጠበቃለሁ ዓለ፡፡ ለኔም በትመረኝ እና በታዝነልኝ ከከሳረመዎች እሆናለሁ ዓለ፡፡

ውሀውም ምድርን ለ40 ቀናት ያህል ካጥለቀለቀ በኋላ ምንም አይነት ነፍስ ያለው ነገር ከምድረ ገፅ ጠፋ።

እብኑ አባስ በወሩት ሀዲስ ኑህ እና ተከታዬቹ በመርከቧዎ ውስጥ ለ6ወራት ቆይተዋል፡፡ በቡዙ ዘገባወች እንደተጠቀሰው ኑህ እና አማኞቹ ከመርከቢቱ የወረዱት በአሹራ እለት ነው፡፡በሙሀረም በ10ኛው ቀን ማለት ነው፡፡በቡዙ ዘገባወች እንደተጠቀሰው ነቢያችን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ይህነን አሏህ ሙሳን ዐ ሰ ከመስመጥ ያደነበትን አና ኑህን አለይሂሰላም ከመጥለቅለቅ ያደነበትን ያአሹራ እለት በፆም አክበረዋል፡፡

መጥለቅለቁ በአሏህ ሲበሀነሁ ወተዓላ በወረደ ትዕዛዝ ተጠናቀቀ፡፡

ያን ግዜ አላህም ምድርን፦"ምድር ሆይ! ውሃሽን ዋጪ፡፡ ሰማይም ሆይ (ዝናብሽን) ያዢ፡፡" ብሎ ምድርን ከመጥለቅለቅ አስቆመ።ቅጣቱም ተጠናቀቀ፤

ምድር ትንሽ ጠፈፍ ማለት ስትጀመር ኑህን እና ተከታዮቹን የተሸከመችው መርከብ በሰላም ጁዲይ በተባለ ተራራ ላይ አረፈች።

ከዚያነም፡አሏህ ሱ ወ እንዲህ ዓለው ኑህ ሆይ ከኛ በሆነ ሰላም በንተ ለይ እና አንተምጋ ባሉት ህዝቦች፣ ትውልድ ላይ በሆኑ በረከቶችን የተጎናጠፉክ ሁነህ ውረድ፡፡

ከነሱ ዘሮች የሆኑ ህዝቦችም በቅርቢቱ አለም በርግጥ እናስመቻችዋለን።ከዝህ ብሇላ መልሰው ወደ ክህደት ለሚገቡ ደግሞ ከዚያም ከኛ የሆነ አሳማሚ ቅጣት ይነካችዋል ተባለ፡፡

ኑህ በመርከቢቷዋ በቆየበት ቆይታ ውሃው ቶሎ እንዲሰርግ ይፈልግ ነበር፣ በዚሂም ግዜ እርግበን አዲስ ነገር ታመላክተው ዘንድ ይልካት ነበር፣

ምነም ነገር ሰትይዝ ተመለስ ነበር፡፡

ከእለታት አንድ ቀን የዘይቱን ቅረጫፉ አመጣቺለት፣ በዚህም ወሃው የሰረገና አተክልቶች መብቀል እንደጀመረ አወቀ፡፡

እንደገና መልሶ ሲልካት በግሮቿዋ ላይ የጭቃ ቅሬት የዛ ተመለሰች፡፡ ፉቺው በመሬት ላይ አረፈች ማለት ነው፡፡

የበዚህም መጥለቅለቁ እንዳበቃ አወቀ፡፡

ይህ እኛ ዘንድ በታረክ መዛግብት ውስጥ ይገኛል፡፡ከዚህ ተነስተው ነው ሌሎች የሰላም እርግብ የሚሉት፡፡
በግሮቻ የምታዝለውም የዘይቱን ቀንዘል ያነን የሚጦቅም ነው፡፡

ኑህ ዐ ሰ ከአደም ልጆች መካከል እነዚያ ከሱጋ የቀሩት ብቻ እንጂ ሌሎች የሌሉ ሲሆን ወረድ፡፡በምደር ላይ የሉ ሰወች ሁሉ አለቀዋል፡፡በረግጥ መደር እንዳዐሁኑ ግዜ የሰው ልጆች አልተሰረጬባትም፡፡
በተወሰነች ስፉራ በአረብ ደሴት ፣ በፊሊስጢን፣ና በዙሯዋ ብቻ ነበር የሰው ልጆች ሰፈረውባት የነበረው እነኝህ ክልል ብቻ ነበሩ፡፡የተቀሩ ምድሮች የሰው ልጆች፡አልነበሩባትም፡፡ግን የተጥለቀለቀቺው ምደር ሁላ ነበር፡፡

ከዚያን አሏህ ከኑህ ዐ ሰ ጋ የነበረትን ህዝቦች በሙሉ መሀን አደረጋቸው፡፡ መውለድ የማይቺሉ፤ ለኑህ ና ለባለቤቱ በስተቀር ለሌሎች ልጅ ሊወለድ አልቻለም፡፡ከመደር ላይ ከዘለቀው ከኑህ ዝሪያ በስተቀር ሌላ አልቀረም ፡፡

ከዚህም የተነሳ ኑህ ዐ ሰ ሁለተኛው አደም በመባል ይጠራል፡፡ሁለተኛ የሰው ልጅች አባት በመባል ተሰይሞል፡፡

በመጨረሻም አላህ ኑህን ዐ ሰ፦"ኑህ ሆይ! እኔ ፍጥረታትን የፈጠርኩት እንዲገዙኝ ነው።እኔ ያዘዝኳቸውንም እንዲታዘዙኝ ነው።ነገር ግን አመፁኝ፤ከኔ ሌላ የሆነንም አካል ጌታ አድርገው ያዙ። ያን ግዜ ቁጣዬም እነሱ ላይ ተፈፃሚ ሆነ በውሀም አጥለቀለቅኳቸው" ብሎ ወህይ አወረደለት።

አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ የ ኑህን (ዐ ሰ) ህዝብ በውሀ ካጥለቀለቀ በኋላ በምድር ላይ ከ ኑህ(ዐ ሰ) ጋር አብረው ከዳኑት ምዕመናን ውጭ ምንም አይነት የሰው ልጅ አልቀረም ነበር።ኑህ ከወሃው መጥለቅለቅ ቡሇላ 350ዓመት ኖረ፡፡

አሏህ ሱበሃነሁ ወተዓላ እንደጠቀሰው፤ለ350አመታት አሏህን ተገዢና አመስጋኝ ሆኖ ነው የኖረው፡፡

እብኑ ማጀህ በዘገቡት ሀዲስ፣ ነቢዩ (ሰዐወ) የኑህን ፆምን ሲገልፁ ኑህ ዐ ሰ ከኢድ ቀናት ውጭ ያሉትን የዓመቱ ቀናትን ሁሉ የፆሙ ነበር በለዋል፡፡በኢድ ለት ያፈጥራል እንጂ በተቀሩት ቀናት ሁሉ በፆም ላይ ነው፡፡ ኑህ ዐ ሰ የሆን ዓመት ከቆየ ቡሇላ ሞቴ፡፡

ስለሱ ከተዘገቡ ዘገባወች አመዛኙ መካ እንደተቀበረ የሚናገረው ነው፡፡በዐንዳድ ዘገባዎች ደግሞ ሉብናን ሊባኖስ ሀገር በሚገኘው ከርከር በቃ በተባለ ስፉራ የተቀበረ መሆኑን ተነግሯል፡፡ይህም ዘገባ ሚዛን ያለው ነው፡፡ኑህ አለይሂሰላም 3ልጆች ነበሩት ፣ ሳም ፣ሃም ና ያፌስ!!

በሳም ልጆች ውስጥ፦ነጭ ነት ና ትነሽ ጡቁረነት ነበረበት፡፡ ወደ ጠይምነተም የሚያመዝን መልክም አለ፣ነጭነትም ቀይነትም ነበረበት፡፡

በሀም ልጆች ዉስጥ ደግሞ፦ጡቅረት የሚሃይል ሲሆን፣ ጢቂትነጭነት ይገኝበታል፡፡አብዛኛቸው ግን ጡቅረት አለበት፤
የያፌስልጆች ደግሞ፦ነጭነት ና ቀይነት የለባቸው ናቸው፡፡አረቦች እና ኢስሪዒላዊያን የሳም ዝሪያወች ናቸው፡፡

አፍሪካዊያን ደግሞ፦ የሃም ዝሪያ ናቸው፡፡ቱርኮች ፣ምስረቅ ኢሲያወች ና አውሮፓዊያኖች ደግሞ የያፌስ ዝሪያወች ናቸው፡፡

•••✿ ❒ ተ_ፈ_ፀ_መ ❒✿•••

በቀጣይ #ነብዩሏህ ሁድ(ዐ.ሰ) ታሪክ እንጀምራለን 🥰
#share
@alahu_akber1
'
•••✿❒ ነብዩሏህ ሁድ ዐለይሂ ሰላም ❒✿•••

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኑህ ዐ ሰ እና በዘመኑ የነበሩት ሰዎች ከሞቱ በኋላ አንዱ አንዱን ሲተካ ምድር ዳግም በሰዎች ትሞላ ጀመር።

ያ ዘመን ካለፈ በኋላ የነበሩ ህዝቦችም ማንም አምልኮ ከምያውቀው በላይ ጣኦትን ማምለክ ተያያዙት።የህዝቡ መለያ ስማቸውም (ዓድ) ይባላል።

በመጀመርያ የዓድን ህዝቦች ላስተዋውቃችሁ...

የዓድ ህዝቦች በዐረቢያ ምድር በየመን ግዛት አህቃፍ በሚባል አካባቢ ኢረም በተባለች ከተማ የሚኖሩ በጣም ትላልቅ ቁመና ያላቸው ህዝቦች ሲሆኑ፤አላህ ስፍር ቁጥር የሌለውን የፀጋ አይነት ያትረፈረፈባቸው ህዝቦች ናቸው።

ከፀጋዎቻቸውም የሚኖሩበት ምድር በጣም ለቡቃያ አመቺ እና ለም አፈር ያለበት አካባቢ ነው።

ሰውነታቸውም በጣም ግዙፎች እና ረጃጅሞችም ነበሩ።

ከሰውነታቸው መግዘፍ የተነሳ አንድን የቴምር ዘንባባ በሁለት ጣታቸው ይነቅሉ ነበር።(የተምር ዛፎች ምን ያህል ግዙፍ እንደሆኑ ዐረብ ሀገር ያላችሁ ውዶች ታውቁታላችሁ)

ነገር ግን አላህ ለዋለላቸው እንዲህ አይነት ኒዕማ ምላሻቸው ምስጋና ሳይሆን ድንበር ያለፈ አመፅ እና መኩራራት ነበር።

የኑህ ህዝቦች ያደርጉት የነበረውን የጣኦት አምልኮ አሟሙቀው ጀመሩት።ያም አላንስ ብሏቸው ምድርን በተለያዩ የወንጀል አይነቶች ይሞሏትም ጀመር።

ነገር ግን ለቅጣት የማይቸኩለው አላህ በእዝነት አዘል ጥበቡ ከመጥፎ ከልክሎ ወደ መልካም የሚመራቸውን (ሁድ) የተባለውን መልዕክተኛ ከመሀከላቸው ላከላቸው።

ሁድ ዐ ሰ መልካም፣ቁጥብ፣የተረጋጉ እና አንደበተ ርቱዕ እና ዐረብኛ ቋንቋን ለመጀመርያ ግዜ የተናገሩ ሰው ናቸው።አላህም እሳቸውን ወደ ህዝባቸው በመሄድ የጌታቸውን ተልዕኮ እንዲያደርሱ አዘዛቸው።

ሁድ'ም ዐ ሰ የጌታቸውን ትዕዛዝ በመቀበል ወደ ዝባቸው ሄደው፦"እኔ ከጌታችሁ የተላክሁ ነብይ ስሆን፤በዚህ አለምም አላህ የሚባል ጌታ አላ።ከሱ ሌላ አምላክ የለም እነዚህ ከተለያዩ ድንጋይ እና እንጨት ጠርባችሁ ምታመልኳቸው ጣኦታት መጥቀምም መጉዳትም የማይችሉ ደካማ ሲሆኑ ከናንተ ጥበቃን ይሻሉ እንጂ እራሳቸውንም አይጠብቁም።

እኔን የታዘዘኝ ከሞት በኋላ ጀነት ይገባል እኔንም ያስተባበለኝ ጀሀነም መቀመጫው ስትሆን መቀመጫነቷስ ምንኛ ከፋ።" ብለው ማስጠንቀቅ ጀመሩ።

እነሱም ነቢያቸው በሚናገረው ግራ በመጋባት፦"እንዴት ነው አማልክቶቻችንን ትተን አንድን ፈጣሪ ብቻ ምንገዛው!!! ይህ ሰውዬ ምን አይነት ቂልነት ነው ይዞብን የመጣው" ይሉ ነበር።

ሁድ ዐ ሰ ህዝቦቹ የሚያሳዩት የመልስ ምት ለቅፅበት እንኳን ተስፋ አላስቆረጣቸውም ነበር። ይልቁኑ፦"እኔ ከናንተ ዘንድ የፈጣሪያችሁን ጥሪ ለማድረስ ከመሀከላችሁ የተመረጥኩ ስሆን፤የተላክሁበትንም ተልዕኮ ያለመሰላቸት በተደጋጋሚ ወደ እናንተ አደርሳለሁ።

እስቲ ፀሀይን እና ጨረቃን ተመልከቱ...ማን ነው የሚያፈራርቃቸው!!!

ማን ነው'ስ የፈጠራቸው!!!

ምድርንና ሰማይንም ተመልከቱ ማን ነው ምድርን አንጥፎ ሰማይን ያለ መሶሶ ያንጣለለው!!!

ተዉ ህዝቦቼ ጌታችሁን አምልኩት።ተጠንቀቁ እናንተ ከሞታችሁ በኋላ ትቀሰቀሱ'ና በሰራችሁት ትተሳሰባላችሁ።መልካም የሰራ ለነፍሱ ነው መጥፎ የሰራም ከከሳሪዎችም ይሆናል" እያሉ ይጠሯቸው ነበር።

ይህን የነቢያቸውን ጥሪ በሰሙ ግዜ፦"ይህን ሰው ከአማልክቶቻችን አንዱ በመጥፎ ተመልክቶታል(አብዷል)" በማለትም ይተቹት ጀመር።

አንዳንዴም፦"ይሄ ሂሳብ፣ጀነት፣ጀሀነም፣መቀስቀስ....ምናምን ምትለው ምን ማለት ነው?" እያሉም ይከራከሩታል።

የዓድ ህዝቦችም በምድር ላይ ያለ አግባብ ኮሩ፡፡ «ከእኛ ይበልጥ በኀይል ብርቱ ማን ነው?» አሉም፡፡ ያ የፈጠራቸው አላህ እርሱ በኀይል ከእነርሱ ይበልጥ የበረታ መኾኑን አያዩምን? በተዓምራታችንም ይክዱ ነበሩ። (ሱረቱል ፉሲለት)

ሁድ ዐ ሰ የህዝቡ ሁኔታ ተስፋ ሲያስቆርጠው፦"እናንተ ከምትሰሩት ሁሉ እኔ ነፃ መሆኔን ምስካሪ ሁኑ" እያለ የሱን ጥሪ ባለመቀበላቸው በዱንያ የሚወርድባቸውንም ቅጣት ያበስራቸውም ጀመር።

እነሱም፦"ምንድነው ዝም ብለህ ቅጣት ቅጣት...እያልክ ምታስፈራራን!!! እንደውም እስቲ ቅጣት ምትለውን አምጣው" እያሉ ሲያሾፉ

ሁድም ዐ ሰ፦"ይህ የማስጠንቅቃችሁ ቅጣት በናንተ ላይ ተፈፃሚ ይሆናል። አትጠራጠሩ" አሏቸው። በመጨረሻም ሁድ ዐ ሰ በህዝባቸው ላይ ዱዓ ማድረግ ጀመሩ።

ከዚያም አላህ የቅጣቱን አርጩሜ በህዝቡ ላይ ሊያወርድ መጀመርያ ለረጅም አመታት ዝናብ በማቋረጥ ምድሪቱን አድርቆ እንስሳቶቻቸውን አጠፋባቸው።

ሁድም ዐ ሰ፦"ከዚህ ሁሉ እንግልት ሊያድናችሁ እሚችለው በጌታችሁ ማመን ብቻ ነው" አላቸው።

እነሱም፦"በረሀብ እና በጥማት እንሞታታለን እንጂ ከጣኦቶቻችን ሌላ ማንንም አንለምንም" በማለት ጣኦታት ዘንድ እየሄዱ ኡኡኡ... ይሉ ጀመር።

ጣኦቶቻቸው ዘንድ ሄደው እሪ ብለው ሲወጡ ሰማይን በደመና ተሞልቶ አገኙት።በጣምም ተደሰቱ አማልክቱ ፀሎቶቻቸውንም እንደሰሙ አመኑ ጥሩ ዝናብ ሊዘንብልን ነው በማለትም ተመፃደቁ።

ያን ግዜ ሁድ ዐ ሰ፦"ይህ እኮ አምጣልን ያላችሁት የቅጣት ደመና ነው እንጂ እናንተ እንደምትሉት ዝናብ አይደለም" አላቸው።

ከዚያም ከፍተኛ ጉልበት የለው ንፋስ ከተማቸውን ያናውጥላቸው ጀመር።ቀስ በቀስ ንፋሱ አስፈሪ ድምፅን እየቀላቀለ በክፍተኛ ጩሀት ህዝቡን ወደ ሰማይ ማፈናጠር ጀመረ።

በዚህ ሁኔታ ለ 7 ሌሊቶች እና ለ 8 ቀናት

ያህል ንፋሱ ዘለቀ። በነዚያ የቅጣት ቀናት ሰውም እንስሳትም ምንም አይነት ፍጥረት አልቀረም ነበር።በሁድ ዐ ሰ ያመኑት ምዕመናን ሲቀሩ ሁሉም የመቅሰፍቱ ሰለባ ሆኑ.....

አሏህ ሱበሃነሁ ወተዓላ ነቢዩሏህ ሁድን ዐ ሰ እና ከሱጋ ያመኑት አዳነቸው፡፡

•••✿ ❒ ተ_ፈ_ፀ_መ ❒✿•••

በቀጣይ #ነብዩሏህ ሉጥ(ዐ.ሰ) ታሪክ እንጀምራለን 🥰
#share
@alahu_akber1
'
•••✿❒ ነብዩሏህ ሉጥ ዐለይሂ ሰላም ❒✿•••

#ክፍል 1

★ የሉጥ ሕዝቦች ነብያቸውን በምድር ላይም ብልሹነትን አነገሱ፥ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፦

وَلُوطًا إِذْ قَالَلِقَوْمِهِۦٓ أَتَأْتُونَ ٱلْفَـٰحِشَةَ وَأَنتُمْ تُبْصِرُونَ ﴿٥٤﴾ أَئِنَّكُمْ لَتَأْتُونَ ٱلرِّجَالَ شَهْوَةًۭ مِّن دُونِ ٱلنِّسَآءِ ۚ بَلْأَنتُمْ قَوْمٌۭ تَجْهَلُونَ ﴿٥٥﴾
“ሉጥንም ለሕዞቦቹ ባለ ጊዜ (አስተውስ) እናንተ የምታዩ ስትኾኑ ጸያፍን ነገር ትሠራላችሁን።

እናንተ ከሴቶች አልፋችሁ ወንዶችን ለመከጀደል ትመጣላችሁን በውነቱ እናንተ የምትሳሳቱ ሕዝቦች ናችሁ። (አን-ነምል፥ 54-55)

እነዚህ ሕዝቦች በምሥራቃዊ ዮርዳኖስ ይኖሩ ነበር።

ይህ ቦታ በሙት ባህር አቅራቢያ ይገኛል። በአካባቢው አምስት መንደሮች ነበሩ። እነሱም;- “ሰዱም፣ ዑመራ” “አደመህ” “ሱወይም” “ባሊ’ዕ” ናቸው።ሉጥ (ዐ.ሰ) በዋናው መንደር ሰዱም ይኖሩ ነበር። መጥፎና ርካሽ ተግባራትን ትፈፅም የነበረችውም መንደር እሷ ነች።

የሰዱም ነዋሪዎች እርኩሶችና መጥፎ ከመሥራት የማይፈሩ ነበሩ። አስፀያፊ ተግባራቸውን በግልጽ የሚፈጽሙበት መሰብሰቢያ ቦታ ነበራቸው። መንገደኛን ይዘርፋሉ። ከሌላ አካባቢ ነጋዴዎች ከመጡ ተሰብስበው ዕቃቸውን ይቀማሉ።

የሉጥ ሕዝቦች ነፍሳቸውንም በእጅጉ የሚበድሉ እጅግ ቆሻሾች ነበር።ካቆሻሻነታቸው የተነሳ በፆታ ግንኙነት ከሴት ይልቅ ወንድ ከወንድ ጋር መገናኘት ይመርጡ ነበር።

እነዚህ ሰዎች መጥፎ ተግባራቸው ወሰን ያለፈ ስለሆነ ይህ አስፀያፊ ተግባር ወደ ሌሎችም አካባቢዎች እንዳይዛመት እነሱን በማስተካከል ወይም በማጥፋት ይህን መጥፎ ተግባራቸውን ማስወገድ የግድ ነበር። ምክንያቱም ሲባል ነው።

#የሉጥ_ጥሪ

★ ሉጥ (ዐ.ሰ) ሕዝቦቻቸው የሚሠሩትን አስፀያፊ ነገር ሲያዩ የወገኖቻቸው በዚህ ሁኔታ መገኘት አሳሰባቸው።

ሥነ-ምግባራቸው እንዲስተካከል በማሰብም ምክር መለገስ ጀመሩ። የሉጥ ጥሪ ሥነ-ምግባራቸው በጅጉ ለተበላሹና ቀልባቸው ለደረቀ ሰዎች የሚደረግ በመልካም ተግባር ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል ነበር።

እነዚህ ሰዎች ምንም ሐያእ /ሐፍረት/ የሌላቸውና አስጸያፊ ወንጀልን በጠራራ ፀሐይ የሚፈፅሙ ነበሩ።

ከዚህም በላይ ሴት በማግባት አላህ የፈቀደላቸውን ግንኙነት መፈጸም ትተው ከወንዶች ጋር በመገናኘት ማንም አድርጎት የማያውቀውን አስጸያፊ ተግባር ይፈፅሙ ነበር።

ስለዚህም አላህ (ሱ.ወ) ሉጥ (ዐ.ሰ) ወደ እነዚህ ሕዝቦች ሄደው ከቆሻሻ ተግባራቸው እንዲፀዱ ጥሪ እንዲያደርጉላቸው ላካቸው።

ሉጥ (ዐ.ሰ) የነበዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) የወንድም ልጅ ሲሆኑ በኢራቅ ባቢል ነበር የተወለዱት።

ነቢዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ወደ ተውሂድ ጥሪ ሲያደርጉ አምነው ከሳቸው ጋር ወደ ሻም አካባቢ ስደት በመሄድ በምሥራቅ ዮርዳኖስ በሚገኘው ሱዲም ሸለቆ አካባቢ ሰፈሩ።በአካባቢው ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት የምትፈጽስም ሰዱም የምትባል መንደር ነበረች።

አላህ (ሱ.ወ) ነቢዩላህ ሉጥን ወደ ሰዶምና አካባቢዋ ሕዝቦች፣ አላህን ብቻ እንዲያመልኩና ከመጥፎ ተግባራቸው እንዲርቁ ለማስተማር ና

ወንድ ለወንድ ግንኙነት መፈጸማቸውን ትተው አላህ የፈቀደላቸውን ሴቶቻቸውን በማግባት ግንኙነት እንዲፈፅሙ እንዲያዟቸው አላህ ሉጥን ላካቸው።ይህ ዓይነቱ ወንጀል ከሰዶም ሕዝቦች በፊት ማንም ያልሠራው አስጸያፊ ወንጀል ነበር

إِذْ قَالَ لَهُمْ أَخُوهُمْلُوطٌ أَلَا تَتَّقُونَ ﴿١٦١﴾ إِنِّى لَكُمْ رَسُولٌ أَمِينٌۭ ﴿١٦٢﴾ فَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ﴿١٦٣﴾

“አትጠነቀቁምን? እኔ ለናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝ። አላህንም ፍሩ። ታዘዙኝም” (አሽ-ሹዐራእ፥ 161-163)

አሏቸው። እንዲሁም ሉጥ እያዘኑላቸው ለዘብ ባለ ቃል!

وَمَآ أَسْـَٔلُكُمْ عَلَيْهِ مِنْ أَجْرٍ ۖ إِنْ أَجْرِىَ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّ ٱلْعَـٰلَمِينَ﴿١٦٤﴾

“በርሱም ላይ ምንም ዋጋ አልለምናችሁም። ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጅ በሌላ አይደለም።” (አሽ-ሹዐራእ፥ 164) በማለት አስገነዘቧቸው።
በዚህ ቃላቸው ውስጥ ሉጥ (ዐ.ሰ) ከነሱ ዓለማዊ ጥቅም እንደማይሹና ብቸኛው ፍላጐታቸው የነሱ መስተካከልና አላህን ብቻ ማምለካቸው እንደሆነ አስረዷቸው።

በመቀጠልም ሉጥ (ዐ.ሰ) ወደነዚህ ሰዎች አስፀያፊ ተግባር በመዞር የሚከተለውን ተናገሯቸው።

وَلُوطًا إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِۦٓ أَتَأْتُونَ ٱلْفَـٰحِشَةَوَأَنتُمْ تُبْصِرُونَ ﴿٥٤﴾ أَئِنَّكُمْ لَتَأْتُونَ ٱلرِّجَالَ شَهْوَةًۭ مِّن دُونِ ٱلنِّسَآءِ ۚ بَلْأَنتُمْ قَوْمٌۭ تَجْهَلُونَ ﴿٥٥﴾ ۞

“ሉጥንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስተውስ) እናንተ የሚታዩ ስትኾኑ ጸያፍን ነገር ትሠራላችሁን። እናንተ ከሴቶች ወንዶችን ለመከጀል ትመጣላችሁን በውነት እናንተ የምትሳሳቱ ሕዝቦች ናችሁ። (አን-ነምል፥ 54-55)

የሰዶም ሰዎች አስፀያፊ ተግባራቸውን በግልጽና በስብሰባ ቦታዎች ሁሉ ሳይቀር መፈጸማቸው ሉጥን በጣም አሳዘነ።
ሉጥ (ዐ.ሰ) ከዚህ አስፀያፊ ተግባር ቢከለክሏቸውም «አንተ ሴቶችን አስተናግድ ወንዶችን ተውልን።»በማለት አስፀያፊ መልስ ሰጧቸው።

ይህ ሁሉ ቢሆንም ነቢዩላህ ሉጥ (ዐ.ሰ) ተስፋ ባለመቁረጥ የተለያዩ ማስረጃዎችን በመጥቀስ ጥሪያቸ እውነት መሆኑን ሊያሳምኗቸው ሞከሩ።

ነገር ግን ድካማቸው በከንቱ ነበር። ቀናት ወራትን ወራት ዓመታትን እየተኩ ዘመኑ ሄደ። ሉጥም ዳዕዋቸውን ቀጠሉ። ነገር ግን ከቤተሰባቸው ውጭ አንድም ሰው አላመነላቸውም ነበር። ከቤተሰባቸውም ውስጥ ሚስታቸው አላመነችም ነበር።

ከከሓዲያን ጐን ተሰለፈች። ይህም ሁኔታ ሉጥ (ዐ.ሰ) ከቤታቸው ውጭ ከሓዲያንን፣ በቤት ውስጥ ደግሞ ከሓዲት ሚስታቸውን መታገል አስገደዷቸው።ስለሆነም በጣም ድካም ይሰማቸው ነበር። ቢሆኑም ግን ትዕግስት እያደረጉ ያለ መሰላቸት ወደ አላህ ጥሪ ማድረጋቸውን ቀጠሉ።

ሕዝባቸው ግን ማመናቸው ቀርቶ በዳዕዋቸው በማላገጥ “ከእውነተኞቹ እንደ ሆንክ የአላህን ቅጣት አምጣብን።
” (አል-ዐንከቡት፥ 29)

ሉጥ (ዐ.ሰ) ሕዝባቸው ቢቀልዱባቸውም ታግሰውና ችለው አሁንም ማስተማራቸውን ቀጠሉ። ከሓዲያኑ የሰዶም ሕዝቦች ሉጥ ላይ ማፌዛቸውንና ማስቸገራቸውን አጠናክረው ቀጠሉ።

ሉጥ (ዐ.ሰ) በአላህ (ሱ.ወ) እንደሚጠበቁ በመዘንጋት የሰዶም ሕዝቦች ሊያጠቋቸው ሞከሩ። ሉጥንና ቤተሰባቸውን በመናቅም።

وَمَا كَانَ جَوَابَ قَوْمِهِۦٓ إِلَّآ أَن قَالُوٓا۟ أَخْرِجُوهُممِّن قَرْيَتِكُمْ ۖ إِنَّهُمْ أُنَاسٌۭ يَتَطَهَّرُونَ ﴿٨٢﴾
“ሉጥንና ተከታዮቹን ከከተማችሁ አውጧቸው። አሉ። እነሱ፡ የሚጥራሩ ሰዎች ናቸውና።” (አል-አዕራፍ፥ 82)

አሉ።የሰዶም ሕዝቦች ቆሻሾች ስለነበሩ ነቢያቸው ሉጥ «ከመጥፎ ነገር ተመለሱ። በተመሳሳይ ፆታ መካከል ግብረ ሥጋ ግንኙነት አትፈጽሙ።»

ብለው ሲመክሯቸው በሉጥና ተከታዮቻቸው ንፁህነት በመቀለድ “እነሱ ንፁሃን ናቸው” ሲሉ አሾፉባቸው።

★ ሉጥ (ዐ.ሰ) ሕዝባቸው ቢቀልዱባቸውም ታግሰውና ችለው አሁንም ማስተማራቸውን ቀጠሉ።


ክፍል 2 ይቀጥላል....

#share
@alahu_akber1
ማንም ወደ ከተማዋ እንዳይዞር ማስጠንቀቂያ ስለተሰጠ ማንም አልዞረም ነበር።የሉጥ ሚስት ግን ወደኋላ በመዞር፦"ወይኔ ወገኔ,,,,!!!" በማለት ጮኸች።
ትልቅ የድንጋይ ፍንጣሪ መጣና እራሷን ለሁለት ከፈለላትና የመቅሰፍቱ ሰለባ ሆነች።

አላህም ይህን ዘግናኝ ክስተት ሲተርክ እንዲህ ይላል፦
"ትዕዛዛችንም በመጣ ግዜ (የከተማይቱን) ላይዋን ከታች አደረግን(ገለባበጥናት) ተከታታይም የሆነ የሸክላ ድንጋይ በርሷ ላይ አዘነብን" (ሱረቱል ሁድ)

እንዴት አድርጎ እንደገለባበጣቻው ታውቃላችሁ...!!!
መጀመሪያ ጂብሪል ክንፉን በከተማይቱ መሬት ውስጥ ዘቅዝቆ አስገባው።
ከዚያም ከተማይቱን ከነ ህንፃዎቿ ነቅሎ ወደ ሰማይ ከፍ ካደረገ በኋላ ገለበጠው'ና መልሶ ወደ ምድር ተከለው።

ሉጥ ከነ ተከታዮቹ ብዙ ርቀት ከተጓዘ በኋላ ሱዒር የተባለ አከባቢ በመስፈር ይህ ነው ተብሎ በታሪክ መዛግብት እድሜው ባይሰፍርም እዛው ሱዒር ላይ ህይወቱ አልፏል። (ዐለይሂ ሰላቱ ወሰላም)

•••✿ ❒ ተ_ፈ_ፀ_መ ❒✿•••

በቀጣይ #ነብዩሏህ ሷሊህ(ዐ.ሰ) ታሪክ እንጀምራለን 🥰
#share
@alahu_akber1
ሁለተኛው ቀን ደርሶ በነጋታው ሰዉ ሲነቃ ሁሉም ፊቱ ደም መስሏል።በድንጋጤ የሞቱትም ብዙ ነበሩ።ያን ቀን በትካዜ እና በፍራቻ ካሳለፉ በኋላ የማይደርስ የለም'ና ሶስተኛዋ ቀን መጣች።

ፊቶቻቸውን ጥቁረት ወረረው፣ተስፋም ቆረጡ ሁሉም በመሰባሰብ ከፈናቸውን ለብሰው ሽቶ ተቀብተው ሞታቸውን መጠባበቅ ጀመሩ።
ልክ ፀሀይ ጀንበሯን ተሻግራ ብቅ ማለት ስትጀመር ከወደ ሰማይ በኩል እንደመብረቅ ያለ፣ ከፍተኛ ድምፅ ያለው ነገር መጣ።ምድርም በሀል መንቀጥቀጥ ጀመረች...ጂብሪልም በከፍተኛ ድምፁ ጮኸባቸው።ያን ግዜ ልቦቻቸው ከደረታቸው መበጣጠስ ጀመረ።አይኖቻቸውን ወደ ሰማይ ያፈጣሉ...

መቅሰፍቱ ከየት በኩል እንኳን እንደመጣ ማወቅ እየተሳናቸው ነፍሶቻቸው ወደ ሰውነታቸው ዳግም ላትመለስ ተነጠለቻቸው።
የከተማይቱ ህዝብ ሁሉም በያሉበት በድን ሁነው ሲሞቱ አንዲት ሴት ብቻ ቀረች ስሟም ከልባ ቢንት ሰለቅ ይባላል።

ለሳሊህ ዐ ሰ ከፍተኛ ጥላቻ ሲኖታት የክህደትን ዘውድ ከራሷ አኑራለች። ይህን ስትመለከት እግሬ አውጭኝ ብላ ከሀገሩ ሸሸች። ብዙ ከተጓዘችም በኋላ አንድ የዐረብ ነገድ የሚኖሩበትን መንደር ደረሰችና የሆነውን ሁሉ ነገረቻቸው።
በመጨረሻም ውሀ እንዲያጠጧት ጠይቃ ልክ ውሀውን ስትቀምሰው ነፍሷ የሙታንን መንደር ተቀላቀለች።
ሳሊህ ዐለይሂሰላም ወደ ሌላ ቦታ ተሰደደ ሷሊህ እና ከሱጋ ያመኑት ሰወች ወደ ተከበረቺው ወደ ተባረከቺው ፊለስጢን ሀገር ተሰደደ፡፡
ከዚያንም በረምላ ከተማ መኖር ጀመረ፡፡ ቆይቶም ሷሊህ ዐለይሂሰለም በ58 አመታቸው በዛው በረምላ ከተማ የዚህችን አለም ጣጣ አጠናቅቀው ነፍሳቸውን ለጌታቸው አስረከቡ።

በነገራችን ላይ ረሱላችን (ሰዐወ) አንድ ቀን ለተቡክ ዘመቻ ባልደረቦቻቸውን ይዘው በመሄድ ላይ ሳሉ የሳሊህ ህዝቦች የጠፉበትን ከተማ ደረሱ። ማንም አይኖርበትም..የተወሰኑ ሶሃቦች በሷሊህ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ምንጮች ውስጥ ሊቀዱ ሄዱ፣ የተወሰኑት፣ ደግሞ መገልገያ እቃወችን አመጡ፥

የአሏህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መገልገያ መሰረያወቹ እንዲሰበሩ እና የተቀዳም ውሃ እንዲደፋ አዘዙ፡፡ከዚያ ውሃ የተሰረው ምግብ ሁሉ እንድደፋ አዘዙ፦ከዚያም ነቢያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፦

"ይህችን ከተማ ስትገቡ እያለቀሳችሁ ፣መልቀስ እንኳዋ ባትችሉ ለማልቀስ የዳዳቹህ ሁናቹህ እንጂ ዝም ብላችሁ እንዳትገቡ።
እኔ በነሱ የወረደው በላእ እናንተን እንዲያገኝብኝ አልፈልግም" አሏቸው።ፊዳከ አቢ ወ ኡም ወነፍሲ ወደሚ ወዒርዲ ያ ረሱሉላህ

በዚያ አከባቢም ያሉ ነገሮችን ሁሉ ለባልደረቦቻቸው አሳይዋቸው።ግመሏም የወጣችበትን እና የተገደለችበትንም ቦታ ወስደው አሳይዋቸው።

•••✿ ❒ ተ_ፈ_ፀ_መ ❒✿•••

በቀጣይ #ነብዩሏህ_ኢብራሂም(ዐ.ሰ) ታሪክ እንጀምራለን 🥰
#share
@alahu_akber1
•••✿ ❒ የነብዩሏህ ኢብራሂም ዐ,ሰ ታሪክ ❒✿•••


#ክፍል 1

#ኢብራሂም #(ኡሉል-ዐዝም)ከተባሉት ከአምስቱ ከበርት ነቢያቶች አንዱ ናቸው።
    
ኢብራሂም ከጣኦት አምላኪያን ቤተሰቦች ነው የተወለዱት።አንዱ ድንጋይ ጠርቦ ያመልካል፣ከፊሉ ፀሀይን እና ኮከብን ያመልካል፣ሌላው ደሞ ንጉሶች ያመልካል።
በዚህ የድንቁርና ዘመን ኢብራሂም ገና በልጅነታቸው ነበር የሰዉ ጅልነት ሚያስገርማቸው።ከምንም በላይ እሚገርመው የኢ ብየ አባት ነበር
ለከተማይቱ ህዝብ የተለያዩ ጣኦታትን እየሰራ የሚሸጥላቸው።
በዚህም የተነሳ የነኢብራሂም ቤተሰብ እጅጉን የተከበሩ ነበሩ።

በዚህች ድንቁርና በተጠናወታት ባቢሎን በምትባል ከተማ ኢብራሂም
ከጣኦታት ሁሉ ታቅበው አደጉ።አሁን አሁን ኢብራሂም በጣም ማሰላሰል ጀምረዋል።
ኢብራሂም ብቻውን ቁጭ ብሎ፦"እንዴት አባቴ ከእንጨት እና ከድንጋይ
እየጠረበ የሚሽጠውን ግኡዝ ነገር ሰዉ ያመልከዋል !!!
ሰዉ ጤና የለውም እንዴ !!!
አይ... ! አይ... ! ነገሩ እንኳን እንዲህ አይሆንም። በእርግጠኝነት ጌታ ማለት
ፍጥረታትን ይፈጥራል እንጂ ፍጥረታት እሱን አይፈጥሩትም። 

እሺ እነዚህ አማልክት ምንም አይጠቅሙም አይጎዱም ካልኩ ታዲያ ፈጣሪ
የታለ !!! እራሱስ ማን ነው?" በማለት ያሰላስላል
ከእለታት አንድ ቀን ኢብራሂም ዐ ሰ እንደተለምዶዋቸው ቢቻቸውን ቁጭ
ብለው ስለ ፈጣሪ ማንነት እና ምንነት እያሰላሰሉ ስለ ድንገት አይናቸው
ጨለማ ውስጥ በሚምዘገዘግ ኮከብ ላይ አረፈ
ኢብራሂምም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው፦"ይሄው ጌታዬን አገኘሁ። አዎ ጌታዬ
በሰው እጅ አይፈጠርም እንደ ጣኦታትም ወድቆ አይሰበርም" አሉ።
      
  በጣም ተደሰተ ከደስታው ብዛት ለዚያ ኮኮብ ሌሊቱን ሙሉ
ሲሰግድ አደረ።በዚያ ሌሊት ትክክለኛውን ጌታ እንዳገኘ ለህዝቡ ሁሉ
ተናገረ።ሌሊቱን ሲሰግድ ካነጋ በኋላ ድንግት ጠዋት ላይ ቀና ሲል ያ ጌታ
የመሰለው ኮከብ በብርሀን ተሸፈኖ ጠለቀ።
አሀ...አሁን ማታውን ሙሉ ሲሰግድ ያሳለፈው ለትክክለኛ ጌታ እንዳልሆነ
ተገነዘበ።ከዚያም፦"እኔ ጠላቂዎችን አልወድም" አለ።
ኢብራሂም አሁንም ግን ተስፋ አልቆረጠም።ጌታውን ፍለጋ ዳግም አጠናክሮ
ቀጥሏል።በሁለተኛውም ቀን ኢብራሂም በማታ ብቻውን ቁጭ ብሎ ስለ ጌታው
እያሰላሰለ ሳለ ወደ ላይ ቀና ሲል የሰማዩን ፅልመት በብርሀኑ የገፈፈ ውብ
ጨረቃ ተመለከተ።
አሁን ትንሽ ከመጀመርያው ረጋ አለ'ና፦"ትክክለኛ ጌታዬማ ይህ ነው እንዴት ግን
እስካሁን አላየሁትም!!!" ሲል ከራሱ አወራ።
የዛሬዋን ግን እንደትናንቱ እየሰገደ አላደረም ትንሽ ቆይቶ ተኛ።ጠዋት ላይ
ጌታዬን ልየው ብሎ ሲያንጋጥጥ ጨረቃው ተሰውሯል።
ኢብራሂምም እጅጉን አዘነ እዛው ባለበት ሆኖም፦"ጌታዬ ቀጥተኛውን መንገድ
እራሱ ካልመራኝ ከተሳሳቾች እሆናለሁ" አለ።

     
ተስፋ ቆርጦ በባይተዋርነት ውጭ ላይ ቁጭ ብሎ ሳለ ፀሀይን
ተመለከተ።በጣም ግዙፍ ናት፣ከጨረቃ እና ከኮከብ ስትነፃፀር በጣም ጎልታ
ታየችው።
ኢብራሂምም
፦"ጌታዬን አገኘሁ ይህ ትክክለኛው ጌታዬ ነው በዛ ላይ ከሁሉም
ይገዝፋል" ብሎ ቀኑን በደስታ አሳለፈ።
በመጨረሻም ፀሀይ ወደ ጀምበሯ ስትቃረብ ዘውታሪ አለመሆኗን ተረዳ።ጌታ
ሁሌም ያልለ መሆኑን ተገነዘበ እንዲህም አለ፦"ወገኖቼ ሆይ !! እናንተ
ከምታጋሩት ነገር እኔ ነፃ ነኝ"
አሁን ኢብራሂም ሁሉ ነገር እየተገለፀለት መጥቷል..ጨረቃም፣ፀሀይም
፣ኮከብም አንድ አስተናባሪ ጌታ እንዳላቸው እና እነሱም ጌታ እንዳልሆኑ ተረዳ።
ያ ጌታ ደሞ በአይን ሊታይ እንደማይችልም ተገንዝቦ በዛ የፍጥረተ አለሙ ጌታ
በሆነው አላህ አመነበት።

    
አሁን ኢብራሂም ከድንቁርና ወጥቷል...ቀጣይ እቅዱ ህዝቡን ከድንቁርና
ለማውጣት ቢሆንም ቅድሚያ ለአባቱ መስጠት እንዳለበት ተገንዝቧል።
አባቱ ዘንድም ሄደ'ና፦"አባቴ ሆይ! ለምንድነው እነዚህን የማይጠቅሙ
አማልክትን ጌታ አድርገህ የምትገዛው?
እስቲ አባቴ ተመልከት እነኚህ አማልክት... ምንም አያዩም አይሰሙም እንዴት
በነዚህ ታምናለህ።
አባቴ ሆይ!! ፈጣሪያችን አላህ ነው። ልናየው አይቻለንም እሱን ብቻ ነው
ልንገዛ የሚገባን።ይህም ብቻ ነው ቀጥተኛው መንገድ" በማለት አባቱን ጥሪ
አደረገለት።
ያን ግዜ አባቱ ቁጣው ገነፈለ..."ይህ ብላቴና እንዴት እድሜ ልኬን
ካመለክኩት ጣኦት ተው ይለኛል" ብሎ በጣም ተናደደ።

    
ኢብራሂምም፦"አባቴ ! ላንተም ለወገኖችህም ሸይጣን ነው ይህንን መንገድ
አስውቦ ሚያሳያችሁ። በምትፈፅሙት ሺርክ ከዝወተራችሁ መመለሻችሁ ወደ
እሳት ይሆናል" እያለ በመለማመጥ ወደ አላህ ይጠራቸው ጀመር።
ከዚያም አባትየው በጣም በመቆጣት ካሁን በኋላ ግን
ሊመታው፣ሊገድለው፣በድንጋይም ሊወግረው እንደሚችል አስጠንቅቆ
ኢብራሂምን ከቤት አባረረው።

     
ኢብራሂም አባትየውን መምከር ምንም ጥቅም እንደሌለው በተረዳ
ግዜ፦………
"ሰላም ሆንልኝ።ጌታዬንም ላንተ ምህረት እንዲያደርግልህ እለምነዋለሁ
እርሱ ለኔ በጣም ርኅሩኅ ነው'ና" ብሎት ቤቱን ትቶ ተሰናበተው።
በቃ አሁን የዳዕዋው ጥሪ ከቤት ወጣ ለመላው ህዝብ ይሰራጭም
ጀመር።
ኢብራሂምም ከአላህ ሌላ ምንም አምላክ እንደሌለ እና ሌላ

አማልክትም ምንም እንደማይፈይዱ በየሄደበት ማውራት ጀመረ።

ይህ የኢብራሂም ጉዳይ ቀስ በቀስ የከተማዋ ወሬ ሆነ።በዘመኑ ሀገሪቷን ይመራ ለነበረው እና ከአማልክቱ አንዱ አካል ለሆነውም ኑምሩድ ይህ ወሬ ደረሰው።
ኢብራሂምንም እንዲያቀርቡለት ወታደሮቹን አዘዘ።
ኢብራሂምም ከንጉሱ ፊት ቆመ። በሀገሪቱም ሆነ በመላ አለም የሚመለኩ

አማልክት ሁላ እንደማይጠቅሙ እና እንደማይጎዱ በድፍረት አስረዳው።አላህ

ህያው የሚያደርግ እና የሚገድል ጌታ መሆኑንም አክሎ ነገረው።

ንጉሱም፦"እኔ መግደልም ህያው ማድረግም እችላለሁ" አለው።

ኢብራሂምም፦"እንዴት?" አለው።
ያን ግዜ ንጉሱ ሁለት የሞት ፍርድ የተፈረደባቸውን እስረኞች እንዲቀርቡ
ካደረገ በኋላ አንዱን በመግደል አንዱን በመተው፦"ይኸው እገድላለሁም ህያውም አደርጋለሁ" ብሎ ተመፃደቀበት።

ኢብራሂምም፦"አላህ ፀሀይን ከምስራቅ አስወጥቶ በምዕራብ ያስገባታል።እስቲ አንተ ጌታ ከሆንክ ከ ምዕራብ እስወጣት"ሲለው ንጉሱም
በሀፍረት አንገት ደፋ። ነምሩድ ስለተባለው ንጉስ ወደፊት እናያለን ኢንሻ አላህ የኢብራሂምን ጥሪ ለማሰናከል ሲሞክር አላህ እሱንም ወታደሮቹንም በትንኝ አጠፋቸው።ከእለታት አንድ ቀን የሀገሪቱ ህዝብ ለአመታዊ በአል በጠዋት ወደ መሰብሰቢያ ቦታ መትመም ጀመሩ። ኢብራሂምም በዚህ አጋጣሚ አንድ ምርጥ ሀሳብ መጣላቸው'ና ለመፈፀምም ወሰኑ።

ክፍል 2 ይቀጥላል....

#share
@alahu_akber1
'
•••✿ ❒ የነብዩሏህ ኢብራሂም ዐ,ሰ ታሪክ ❒✿•••

#ክፍል 2

ከዚያም ህዝቡ ሙሉ ለሙሉ መሰብሰቢያው ቦታ ሲሆድ እሱን ለምን እንደማይሄድ ሲጠይቁት፦"አሞኛል" ይል ነበር።

በመጨረሸም ሰዉ ሁሉ ከተማይቷን ለቅቆ ወደመሰብሰቢያው ሄደ'ና ኢብራሂም ብቻውን በከተማይቱ ቀረ።

አሁን ልበ ሙሉው ኢብራሂም ሀሳቡን ሊያሳካ ጉዞ ወደ ቤተ አምልኮ ጀምሯል...ልክ ጣኦታቱ ያሉበትን በር ሲከፍተው ቤተ አምልኮው ከተለያዩ እንጨቶች እና ድንጋዮች በተሰሩ ጣኦታት ተሞልቷል።

ኢብራሂም ምንም አልፈራም ዘልቆ ወደ ውስጥ ገባ።ከዚያም በጣኦታቱ አጠገብ በቁርባን መልኩ የተደረደረውን የምግብ መዐት ተመለከተ'ና
ጠኦቶቹን፦"አትበሉም እንዴ!!!" አላቸው እየፎገረ... አሁንም በመሀከላቸው ትንሽ ተዟዟረና፦……………
"ምንድነው...!!

!መልሱልኛ ማውራትም አትችሉም እንዴ!!" አላቸው።

ምንም ሚመልሱት ነገር የለም። በእጁ በያዘው ፋስ እያንዳንዱን የድንጋይ እና የእንጨት ቅርፃ ቅርፅ ብትንትኑን አውጥቶ አንድ ትልቁን ጣኦት ብቻ ተወው'ና ሌሎች ጣኦታትን የቆረጠበትን ፋስ በትልቀኛው ላይ አሸክሞ ሰዉ ከተሰበሰበበት ሳይመጣ ኢብራሂም ቤተ አምልኮውን ትቶ ወጣ።
ህዝቡ ገና ከተማ ከመግባቱ አማልክቱ ጋር ሊሳለም ሲገባ ሁሉም አይናቸውን ማመን እስኪያቅታቸው ድረስ ያዩት ነገር አስደነገጣቸው።

ህዝቡ ባጠቃላይ ክፉኛ ተቆጣ...ይህን ተግባር የተገበረውንም ሰው አይቀጡ ቅጣትንም ለመቅጣት መዛት ጀመሩ።
ግን ነገሩን በጥልቀት ሲመረምሩት ከኢብራሂም ሌላ ማንም እንዲህ ሊያደርግ እንደማይችል በመገመት ኢብራሂምን ለፍርድ ለማቅረብ ፍለጋ ተጀመረ..... ብዙም ሳይፈልጉት ነበር ኢብራሂምን አግኝተው ለፍርድ ያቆሙት።

ዳኛውም፦"ይህን አሳፋሪ ተግባር በአማልክቱ የፈፀምከው አንተ ነህ እንዴ?"

ኢብራሂም፦"አረ እኔ አይደለሁም ይሄ ትልቀኛው ነው እሱም ጠይቁት እንጂ...በዛ ላይ ፋስ ተሸክሟል እራሱ ነው የፈጃቸው። ከፈለጋችሁ ጠይቁት"አላቸው።

ህዝቡ፦"እንዴት መናግር እና መስማት የማይችልን ጣኦት ጠይቁት ትላለህ!!!"

ኢብራሂም፦"አያችሁ መናገር እና መስማትን የማይችሉ ጣኦታትን ነው እያመለካችሁ ያላችሁት።ግን ትንሽ አታስተነትኑም!!!"

ኢብራሂም እችን ሲናገር ሁሉም ጥፋት ላይ መሆኑን ተረድቶ ቀዘቀዘ።
ነገር ግን ሸይጣን አስውቦ ገለፀላቸውና ወደ ጥመታቸው በመመለስ ኢብራሂምን ለሰራው ቅጣት ይሆን ዘንድ በእሳት ለማቃጠል ትዕዛዝ አስተላለፉ።

አሁን ኢብራሂምን ለማቃጠል ማገዶ ለቀማ ተጀምሯል...እያንዳንዱ ነገድ በርካታ ማገዶ እንጨቶችን ሰብስቦ መከመርም ጀምሯል።

በመጨረሻም ኢብራሂምን ለማቃጠል የተከመረው የእንጨት ብዛት ትልቅ ተራራን አከለ።

ከተለያዩ አጎራባች ሀገራት የኢብራሂምን አስከፊ እና ዘግናኝ ቅጣት ለመመልከት ወደ ባቢሎን ከተማ ሰዉ መጥቷል።

እሳቱ መቀጣጠል ሲጀምር የእሳቱ ነበልባል በሰማይ በራሪ አዕዋፋትን እየጠበሰ ይጥላቸው ነበር።እንግዲ በዚህ ውስጥ አሁን ኢብራሂም ሊገባ ነው።

እሳቱ በጣም ከተፋፋመ በኋላ አይደለም ኢብራሂምን ለማስገባት ይቅርና ራቅ ብሎ እንኳን ወደ እሳቱ ድንጋይ ለመወርወር ነበልባሉ አይሰጥም ነበር።

ይህን ግዜ ሸይጣን በሰው ተመስሎ መጣ'ና አንድ መፍትሄ ሹክ አላቸው።እሱም መስፈንጥር በመጠቀም ኢብራሂምን ወደ እሳቱ ማስፈንጠር እንዳለባቸው ነገራቸው።
ከዚያም ያ የተባለው መስፈንጥር ተዘጋጀ'ና ኢብራሂምን ወደ እሳቱ ለመወርወር ማስፈንጠሪያው ላይ አስቀመጡት።

ልክ ኢብራሂም እዛ ላይ ቁጭ ብሎ ሳለ ጂብሪል መጣ'ና፦"ምትፈልገው ነገር ካለ እኔ ልርዳህ...ከፈለግክም እሳቱን ላጥፋልህ" አለው።

ኢብራሂምም፦"አይ ዛሬ እርዳታን ከአላህ ብቻ ነው ምፈልገው" ብለው መለሱለት።

በመስፈንጥሩ ኢብራሂም ወደ እሳት ሲወረወር እዛ የተሰበሰበው ህዝብ ሁላ፦'እሳት ትገባላችሁ እያለ ይዝትብን የነበረው ሰውዬ ቀድሞ እራሱ ገባ አይደል!!" እያለ ማላገጥ ጀመረ።

ነገር ግን በአላህ ልዕልና እና በሁሉ ነገር ቻይነቱ እሳትን፦"አንች እሳት ሆይ!!! ኢብራሂም ላይ ቀዝቃዛ እና ሰላም ሁኚለት" በማለት ትዕዛዙን አስተላለፈ።

ከረጅም ርቀት በማስፈንጠሪያ ወደ እሳቱ የተወረወረው ኢብራሂምም ልክ እሳቱ ውስጥ ሲገባ ከላይ እሳት ሆኖ የታየው ውስጡን እንደ ጀነት ሆኖ አገኘው።
እሳቱ ተፋፍሟል ህዝቡ በደስታ እራሱን አያውቅም።በመጨረሻም እብራሂም ሞቷል ብለው ሁሉም ተበታተኑ እሱቱ ግን ይባስ እየተፋፋመ ነው።

የኢብራሂም እናት ቁጭ ብላ የልጇን መጨረሻ በመጠባበቅ ላይ ሳለች ድንገት ከነበልባሉ ውስጥ ልጇን ኢብራሂምም ተመለከተች።

ድምፅዋን ከፍ አድርጋ፦"ኢብራሂም....እኔ ወደንተ ልመጣ እፈልጋለሁ ጌታህን ለምንልኝ'ና አንድ ግዜ ልምጣ" አለችው።

ኢብራሂምም መንገድ እየጠቆማት፦"ነይ በዚህች በኩል" አላት።
እሷም እየፈራች ትንሿን መንገድ ይዛ ወደ ልጇ ገሰገሰች።መሀል ከደረሰች በኋላም እሳቱ ሲንቀለቀል ስታይ፦"ኢብራሂም ፈርቻለሁ"አለችው። (ወይ እናት!!!)

ኢብራሂምም፦"እናቴ እሳቱ እኮ አያቃጥልም ዝም ብለሽ ነይ" ሲላት እሳቱ መሀል ደረሰች'ና ያብራኳን ክፋይ በእቅፏ አስገባችው።

በሁለት እጆቿ አቅፋው እየሳመችው ፊቱን ትጠራርግ'ና ዳግም ወደ እቅፏ ታስገባዋለች።ለተወሰኑ ሰዐታት አብራው ካሳለፈች በኋላ ኢብራሂምም ወደ ህዝቧ እንድትመለስ ያዝዛትና ለመመለስ ስትሞክር እሳቱን ይበልጥ ተፋፍሞ አገኘችው።

ወደ ልጇ ዞራም፦"ልጄ በጌታህ ይሁንብህ ጌታህን ለምንልኝ'ና አሳልፈኝ"አለችው።ኢብራሁምም ዱዓ አደረገና እናቱን እንድትሻገር አደረገ።እናትየውም ልክ የእሳቱን መውጫ ጫፍ ላይ ስትደርስ፦"ልጄ ሰላም ሁን" ብላው ወጣች።

በነጋታው የከተማይቱ ነዋሪ እሳቱ ጋር መጥተው ሲያጣሩ እሳቱ እንደነበር ነው ምንም አልቀነሰም።በዚህ ሁኔታ ኢብራሂም ለ40 ቀናት እሳት ውስጥ አሳለፉ።

በመጨረሻም እሳቱ ሲጠፋ ህዝቡ ግር ብሎ መጣ።በዚህ አጋጣሚ ነበር ኢብራሂም ከመጀመሪያ ውበቱ 70 እጥፍ ጨምሮ ከእሳቱ ሲወጣ የተሰበሰበው ሰው ሁሉ ሸይጣን መስሎት ኡኡኡ....ያለው።
ኢብራሂም ሲከተላቸው እነሱ ሲሸሹ ሩቅ ከተጓዙ በኋላ አላህ እሱን አድኖት እነሱን አጠፋቸው።የኢብራሂም በእሳት 40 ቀን ቆይቶ በሰላም የመውጣቱ ነገር በተለያዩ ሀገራት ለአመታት የሰው ልጆች መነጋገሪያ ሆኖ ከረመ።

ኢብራሂም ምንም እንኳን የዳዕዋ ጥሪያቸውን አጠናክረው ቢቀጥሉም ሳራ እና ሉጥ ከተባሉ ሁለት ሰዎች በላይ ተከያይ ሊያፈሩ አልቻሉም ነበር።

ኢብራሂምም ሚስቱ ሳራን እና ሉጥን ይዞ ወደ ሌላ ሀገር ለመሰደድ ወሰነ።ከባቢሎን ምድር ብዙ ተጉዘው ፊለስጢን ደረሱ።

በዚያ ዘመን ፊለስጢንን የሚያስተዳድረው የግብፅ ንጉስ ነበርና ሳራ የምትባል በጣም ቆንጅዬ ሴት በግዛቱ ውስጥ እንደምትገኝ በወሬ ደርሶት ወታደሮቹ እሷንም አብሯት ያለውንም ሰው እንዲያቀርቡለት አዘዘ።

ሁለቱም በወታደሮች ተከበው ወደ ቤተ መንግስት በመሄድ ላይ ሳሉ አንድ ነገር ተመካከሩ።ኢብራሂም ባሏ ነኝ ብሎ ከተናገር ስለሚገድሉት ወንድሟ ነኝ ሊል ወሰኑ። ሌላው የአላህ ስራ ነው ብለው ኢብራሂምን ወደ እንግዳ ማረፊያ አስገብተው ሳራን ለንጉሱ አሳልፈው ሰጡ።

ኢብራሂምም ምኗ ነህ ተብሎ ሲጠየቅ ወንድሟ ብሎ በመመለሱ ከሞት ተርፏል።አሁን የሳራ እንግልት ከወደ ውስጥ በኩል ጀምሯል....ንጉሱ ሊተናኮላት ሲሞክርም፦"ጌታዬ እኔ ባንተ ያመንኩ ስሆን ከመጥፎ ነገር ሁሉ ባንተ እጠበቃለሁ።

ክፍል 3 ይቀጥላል..

#share
@alahu_akber1
•••✿ ❒ የነብዩሏህ ኢብራሂም ዐ,ሰ ታሪክ ❒✿•••

#ክፍል 3

አሁን የሳራ እንግልት ከወደ ውስጥ በኩል ጀምሯል....ንጉሱ ሊተናኮላት ሲሞክርም፦"ጌታዬ እኔ ባንተ ያመንኩ ስሆን ከመጥፎ ነገር ሁሉ ባንተ እጠበቃለሁ። ይህንንም ንጉስ እኔ ላይ ስልጣን አትስጠው" እያለች አላህን ተማፀነችው።

ንጉሱም እጁን ወደ ሳራ ሲዘረጋ እዛው በዘረጋበት እጁ ደርቆ ቀረ።ያን ግዜ ንጉሱ በከፍተኛ ሁኔታ መጮህ ሲጀምር ሳራም ይህ ንጉስ ከሞተ ወታደሮቹ እሷንም እንዷይገድላት ሰግታ አላህን ለመነችው።

አላህም የንጉሱን እጅ ሲለቅለት ንጉሱ ከመጀመሪያው ፀያፍ ተግባር አልተማረም ነበር።ዳግም እጁን ወደ ሳራ ላከ....ሳራም እንደመጀመሪያው ጌታዋን ተማፀነች።የንጉሱ እጅም በቦታው ደረቀ። ያን ግዜ ንጉሱ በከፍተኛ ሁኔታ መጮህ ሲጀምር አሁንም ሳራም ይህ ንጉስ ከሞተ ወታደሮቹ እሷንም እንዳይገድላት ሰግታ አላህን ለመነችው።

አላህም የንጉሱን እጅ ሲለቅለት ንጉሱ ከመጀመሪያው ውዳቂ ተግባር አልተማረም ነበር።ዳግም እጁን ወደ ሳራ ላከ....ይህን ግዜ አላህ የንጉሱን መላ ሰውነት ፓራላይዝድ አደረገው።ንጉሱም ዳግም ላይተናኮላት ቃል ገብቶላት አላህም ለቀቀው።

ንጉሱም አገልጋዮቹን ጠርቶ፦"ሰው ናት ብላችሁ ሸይጣን ታመጡልኛላችሁ እንዴ!!! በሉ አንድ አገልጋይ ስጧት'ና ከዚህ አስወጡልኝ" አላቸው።

አሁን እነኢብራሂም ሁለት ሆነው የገቧትን ከተማ ከአገልጋይቱ ሶስት ሆነው ወጡ። በነገራችን ላይ ሳራ ምንም እንኳን ቆንጂት ብትሆንም መውለድ ማትችል(መሀን) ነበረች።

ኢብራሂምም እድሜውን ዳዕዋ ላይ ብቻ በማሳለፍ እድሜውን ፈጅቶ ሸምገልገል ብሏል።ሳራ አንድ ቀን ኢብራሂምን፦"አንተ እድሜህ ገፍቷል እኔም እንደምታየው መውለድ አልቻልኩም።ስለዚህ ይህችን አገልጋያችንን አግባት'ና ልጅ ውለድ" አለችው።

ኢብራሂምም፦"ተይ ተይ...ሳራ እኔ እሷን ባገባ ትንሽ ቅናት ቢጤ ሊያገኝሽ ይችላል።በተለይ ደሞ ልጅ ስንወልድ...እኔ ደሞ አንችን ምንም እንዲከፋሽ አልፈልግም" ብሎ መለሰ

ጁምሁሮች እዛ በመካ ሸለቆ ሰፈሩና ሃጀር የመኖሪያ ሁኔታ እንደዚህ ሆነ፡፡

ዘምዘምን ለእነዛ ሰወች እያከራየች በምታገኘው መተዳደር ጀመረች፡፡

እስማኢል በጁሩሁም ጎሳወች መሀከል አደገ፤ ከነሱም የነጠቀ አረበኛ ቋንቋ ተማረ፡

እንደውም ከሁለቸውም የበለጠ አንደበሩትዕ እስኪሆን ደረሰ፡፡እስሚኢለም ቆይቶ ከጁሩሁም ጎሳ የሆነችን ሴት ነው የገባው፡፡

አልዐዕአረቡ ሙስተዕሪባ ወደ አረብነት የተለወጡ በመባል የተሰየሙት የአረብ ትውልዶች ከኢስማኢል ትውልዶች ነቸው፡፡
ነቢዩ ሙሀመድ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከነዚህ ዚረያች መሃከል ነቸው፡፡ይህ የሆነው አሏህ ሱበሃነሁ ወተዓላ የአብራሂምን ዐለይሂሰላም ጥረ (ዱዓ) በመቀበሉ ነበር፡፡

እብራሂም አለይሂሰለም በተጎዘና ሃጀር ከጠገቡ በተመለሰች ግዜ በቁረዐን የተጠቀሰውን ዱዓ ዐደረገ።

ያጥሪ መልስ አገኜ ፦ ጌታችን ሆይ በተከበረው ቤትህ፡አጠገብ አዝመራ በሌለው ሸለቆ ውስጥ ከዝሪያወቼ አስፉረያለሁ አለ፡፡
የተከበረው ቤት በዘን ሰዐት ነበር እንዴ? እብራሂም ሃጀረን እዛ በስቀመጠበት ግዜ የተገነባ ቤት ነበረዴ ?

አልነበረም ከዚያ በፊት ተገንብቶ የነበረ ነው ወይነስ ቦታው ብቻ ነበር የሚታወቀው፤ በዘመህ ዙሪያ ሁለት ዘገባወች አሉ፣

እንዴኛው ቦታው ብቻ ነው የሚታወቀው ሌሌኛው ደግሞ ከዚያ በፊት የአደም alehesalam ልጅ ሺስ ገብቶት ነበረና ከግዜ ረዝመት እና ቆይታ ቡሇላ ነው የፈራረሰው የሚል ነው ሁለተኛው፡፡

አለህ ሱበሃነሁ ወተዓላ የተባረከ ሲሆን ሰወች የመልኩበት ዘንድ የሰወች መጀመሪያ የተቀመጠላቸው ቤት በመካ የለው ነው ሰለሚል ሺስ ገንብቶት መሰረቱ ነበር የሚለውን ዘገባ ጠንካራ ነው፡፡

እብሪሂሚም ከጥሎ ዱዓውን ጌታዬ ሆይ ሶላትነም እንዲያቋቅሙ ከሰወች ወደ እነርሱ የሚያዘነብሉ ልቦችን አድረግ ሊያመሰግኑህም ዘንድ ከፈራፈሬወችም መግባቸው ብለው ዱዓ አደረጉ።
በተግባረም ተለውጦ የጁሩሁም ጎሳወች ሃጀር አከባቢ ሰፈሩ። ቀናት አመታት አልፎ እስማኢል በጁሩሁም ውስጥ ወጣት ሆነ።

ከረጅም ግዜ በኋላም ኢብራሂም ልጁን ኢስማዒልን እና ሚስቱን ሀጀርን ከምን እንደደረሱ ለማጣራት ያስቀመጣቸው ቦታ ሲመጣ ቦታውን ሊያውቅ አልቻለም።
ምክንያቱም ያኔ ሲመጣ አከባቢው ምንም አይነት ነፍስ ያለው ነገር የማይኖርበት ምድረ በዳ ነበር።
አሁን ግን ቤቶች ተገንብተዋል...የብዙ ተጓዥ ነጋዴዎችም ማረፊያ ከተማ ሆኗል።

ይህን ሲያይ መንገድ ተሳስቼ ይሁን እያለ ያሰላስል ጀመር።በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለ የአከባቢውን ሰው ሀጀር ስለምትባል ሴት ሲጠይቁት ከነ ቤቷ ጠቆሙት።

ኢብራሂምም ቤቷ ሲሄድ በጥሩ ሁኔታ ላይ ከልጇ ጋር ተመለከታት...እንባ ተናነቀው...ሁለቱንም ለረጅም ሰዐት አቀፏቸው ያለቅስም ጀመር።
ከዚያ በዚህ ሁኔታ ከተገናኙ በኋላ ኢብራሂም ወደ መጣበት ተመለሰ።
ምንም እንኳን የልጁ ኢስማዒል እና የሚስቱ ፍቅር እንደ አዲስ በውስጡ ማንሰራራት ቢጀምርም በመሀከላቸው ካለው ርቀት አንፃር በፈለገ ሰዐት እየመጣ ሊዘይራቸው ምቹ አልነበረም'ና ሁሌ በአመት አመት ሊያያቸው መምጣት ጀምሯል።

ኢብራሂም ዐለይሂሰለም ሰላም፡በዐማት አንድ ግዜ ከሃጅር ጋ በመካ የለውን እስማኢልን ይጠይቅ ነበር፤ አንድ ታላቅ ክስተት እስከመጣበት ግዜ ደረስ በዚህ ሁኔታ ላይ ዘወተረ፡፡

ኢብራሂም አለይሂሰላም መካን በጎበኘበት በአንደኛው ጉብኝት አስማኢል ሊጎበኝ በመጣበት፡በመካ ተኝቶ ሳለ በእንቅለፉ ውስጥ ህልም(ራኢይ ተየው)

"ኢብራሂም ሆይ! አላህ ልጅን ኢስማዒልን እንድታርደው አዞሀል" የሚል ድምፅ ሰማ'ና ደንግጦ ተነሳ።

ከዚያም፦"ጌታዬ ኢስማዒልን እንዳርደው ምትፈልግ እንደሆን ታዛዥህ ነኝ" ብሎ ተመልሶ ተኛ።

አሁንም እንቅልፍ ትንሽ ሸለብ እንዳደረገው፦"ኢብራሂም ሆይ! አላህ ልጅህ ኢስማዒልን እንድታርደው አዞሀል" የሚል ድምፅ በህልሙ ተሰማው።
አሁንም ደንግጦ ተነሳ'ና ረክዐተይን ሰግዶ አላህ ትዕዛዙን ግልፅ እንዲያደርግለት ዱዓ አድርጎ ተመልሶ ተኛ።

አሁንም ልክ እንደተኛ ለሶተኛ ግዜ፦" ኢብራሂም ሆይ! አላህ ልጅህ ኢስማዒልን እንድታርደው አዞሀል" የሚል ድምፅ ሲሰማ ኢብራሂም የነቢያት ህልም ውሸት እንደል ሆነ ስለሚያቅ ቅዠት የማታዝል እና ሸይጣነም ተመስሎ እነደማይቀርበበት በረግጥ ያውቅ ነበር እናም የጌታው ትዕዛዝ ምንም እንኳን ለህሊና ሚከብድ ቢሆንም ኢብራሂም ሊፈፅም ወሰነ።
ኢስማዒልን ብቻውን ሊያናግረው ወጣ አድርጎ፦"ልጄ አንተን እንዳርድህ ጌታዬ በህልሜ አዞኛል ምን ትላለህ!?" አለው።

ኢስማዒል፦"ዞር በል ከዚህ. ስንት አመት ጥለኸኝ የትም የትም ብዬ ካደግኩ በኋላ አባትህ ነኝ ብለህ ስትመጣ መቀበሌ አንሶህ ልረድህ ትለኛለህ እንዴ!!!" አላለውም ነበር።
ነገር ግን በእናቱ መልካም ተርቢያ ያደግው የመልካም ስነምግባር ባለቤት የሆነው ኢስማዒል፦"አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ፈፅም አሏህ ካለ እኔንም ከተጋሾች ሆኜ ታገኘኛለህ" ነበር መልሱ።አሁን ኢብራሂም ልጁን ሊያርድ ዝግጅቱን ጀምሯል።

ኢስማዒለም አበቴ ሆይ ልታርደኝ ከፈለክ ግንባሬን መሬት ላይ ድፋው የሂን ያልኩበት ምክኒያት ፊቴን አይተሄው ረህራሄ እንዳይዝህ ብዬ ነው አለው፡፡ ተመልከት ጭንቀቱን ሊያቀልለትና ነገረን ሊያገራለት ሲፈልግ ነው፡፡

ክፍል 4 ይቀጥላል..

#share
@alahu_akber1
•••✿ ❒ የነብዩሏህ ኢብራሂም ዐ,ሰ ታሪክ ❒✿•••

#ክፍል 4

ከዚያ አባት ኢብረሂም በሆዱ አስተኝቶ ፊቱን ወደ መሬት በመድፋት የጌታውን ትዕዛዝ ተፈፃሚ ሊያደርግ ቢለዋውን በልጁ ኢስማዒል አንገት ላይ ሲያሳርፍ ከዚያም ቢለዋውን በንገቱ ለይ ማንቀሳቀስ ጀመረ ፣ ገዘገዘው ገዘገዘው ግን ቢለዋ መቁረጥ አልቻለችም ኢብራሂም እሳት ማቀጠል እንዳልቻለቺው ሁሉ ቢለዋም እስማኢለን መቁረጥ አልቻለችም።

በአሏህ ፉቃድ ቢሆን እንጂ ቢለዋ የመቁረጥ ችሎታ የላትም፡፡ እሳትም በአሏህ ፈቃድ ቢሆን እንጂ የማቃጠል ችሎታ የላትም፡፡

በጊዜው አሏህ ሱ ወ እንዲህ ያለውን ችሎታ ነጥቋወት ነበረ ኢብረሂም ዐ ሰ ቢለዎውን ጫን እያለ የገዘገዝ ጀመረ እስማኢለም ደግሞ አባቴ ጫን በል የለዋል ጫን ብሎ ይገዘግዛል፥

ግን ቢለዋ አልቻለችም አልቆረጥ አለች አሏህ ሱ ወ ይሂነን ቲረት አስመልክቶ ሲናገር ሁለቱም ተዛዙን በተቀበሉና በግንባሩ ግን ላይ በጣለው ግዜ የሆነው ሆነ ይላል።

አስለማ ይላል እጅ ሰጡ ትዛዙን ለመፈፀም ሆኑ። ፈተናው አዚህ ቦታ ላይ ተጠናቀቀ።

ከላይ በኩል፦"ኢብራሂም ሆይ !!! ህልሙን እውን አድርገሀል እኛም እንደዚህ መልካም ሰሪዎችን እንመነዳለን" የሚል ድምፅ መጣ።

ኢብራሂምም ቀና ሲል ከሰማይ አንድ መልዐክ ለኢስማዒል ቤዛ ይሆን ዘንድ፡ከጀነት የሆነን በግ ይዞ መጣ'ና፦"ኢስማዒልን ፈትተህ ይሄን እረድ" አለው።

ከዚያም ኢብራሂም ደስታው ወደር አጣ...እየተቻኮለ የልጁን...የአብራኩን ክፋይ እጆች መፍታት ጀመረ።

ከዚያም ከሰማይ የመጣለትን በግ አረደው።ያን ቀን በማስመልከት ነው እንግዲህ በየዐረፋ በአሉ የእርድ ስነስርዐት ሙስሊሞች የምንፈፅመው።

የእስሃቅን ብስራት በተመለከተ፣ በስራቱ የተፈጠመው እብራሂም ዐ ሰ በመካ ልጁን የመሰዋት ፈተና ከለፈና ወደ ፊሊስጢን መደር ከተመለሰ ብሇላ ነው፡፡

አሏህ ሱ ወ እሱን እና በለቤቱን ሰራን ማክበር ፈለገ ፤ በዚያን ግዜ የእብራሂም ዐ ሰ እድሜ 120 ነበር፤ የሳረ እድሜ ደግሞ 90 አመት ነበር።

እነርሱን ሊያበስራቸው 3 መላዕከን ከሰማይ አወረደ፦ ጂብሪል ፣ ሚካኢል ና መለከል ሞት ነቸ የወረዱት።

አመጣጠቸውም አሏህ ሱ ወ የሉጥ ህዝቦችን እንዲያጠፉ አዙያቸው ነበር።

ወደዚያ እየሄዱ ሳለ እግር መንገዳቸውን ወደ እብራሂም ዐ ሰ እና ወደ ባለቤቱ ሳረ ወረዱ ሲወርዱ የሰው ልጅን መልክ የዘው ነበር የወረዱት።

እብራሂ ዐለይሂሰላም እንግጆችን ይወድ ሰለነበር፣እንግዶቹ ወደሱ ሲመጡ ተመለከተ ሰላም አሉት እናም እሱም በመገረም ሰላም አለቸው፡፡

ለምን ተገረመ ? እነዚህ ሰወች በአከባቢው የሚታወቁ ሰወች አልነበሩም ፣ የመንገጀኛ ምለክትም አልነበረቸውም፤ የሚታወቅ የጉዞ መለያ ፤ መጓጓዣ አንሰሳም አልነበራቸውም፡፡
ወደ ቤት አስገባቸው ና ወሬ ሳያበዛ ጥጃን አረደላቸው የተጠበሰ የጥጃ ስጋ አቀረበላቸው። አቦ ወላሂ ይመቸው እንግዳን በወሬ ከማድረቅ በፊት ምግብ ሲቀርብ ነው ሙድ ያለው...ጥጃ ማረደም አያስፈልገም ነበር ግን የእብራሂም ቸረነት እስከዚህ ነበር ፡፡

ቸረነት የነቢያት ና የመልክተኞች መለያ ነት፡፡

ኢብራሂም ምግቡን ካቀረበ በኋላ እጃቸውን ቢያይ ቢያይ ምንም ወደ ምግቡ አይዘረጉም።
ይህን ግዜ ኢብራሂም በልቡ ፍራቻ አደረ።

ሊዘርፉኝ የመጡ ሌቦች ናቸው!!!?

ወይስ ሊገድሉኝ..!!?

ወይስ ሚስቴን ሊተናኩሉ ነው..!!? እያለ ይጨነቅ ጀመር።

አላተዕ ኩሉን(አትበሉም እንዴ ሲላቸው) አዎ ስጦታን አነቀበለም ገዝተን ካልሆነበቀር አንበላም አሉት የባላል፣ ዋጋዉን ክፈሉና ብሉ አለቸው፡፡

መላእክትም ዋጋው ስንት ነው ብለው ሲጠየቁት፣

ዋጋው መብላት ከመጀመራቹህ በፊት ብስሚላህ ማለታቹህ እና ስታጠናቅቁ ደግሞ አልሀምዱሊላህ መለታቹህ ነው አላቸው።
በዚህም ግዜ ከሊሉረህማን የአረህማን ወዳጅ ብሎ ላንተ ስያሜ መሰጠቱ ተገቢነው አሉት።
ኢብራሂምም፦"ምን ፈልጋችሁ ነው እነ ማን ናችሁ?" ብሎ ጠየቃቸው።

ወጣቶቹም፦ አትፉራ "እኛ ከሰማይ የመጣን መላዕክቶች ስንሆን ላንተ ልጅ እንደምትወልድ ልናበስርህ እና የሉጥን ህዝቦች ልናጠፋ ነው የመጣነው" አሉት!

ይሁን ሁሉ ንግግራቸውን ስትሰማ የነበረችው ሳራ ቁማ ነበር እና ከት ብላ ሳቀችም። ለምን ነበር የሳቀቺው? ገና በልጅ ዜና ሰትበሰር በፊት ነበር።

ኡለማ እንደተናገሩት የሰቀችበት ምክኒያት የሉጥ ህዝቦች እንደሚያጠፉ በመስማቱዋ ነው ብለዋል።ያም እነሱ ምደረን በጥፋት መድረስ በመሆነቸው ሳቢያ ነው። እንደ ሚጠፉ ስሰማ ነው የሳቄቸው ብለዋል።

ኢብራሂም ሚያላግጡበት መስሎት በመገረም፦"ይህ እንዴት ይሆናል? እኔ እኮ የጃጀው ሽማግሌ ነኝ" አላቸው።

እነሱም፦"ይህ የጌታህ ትዕዛዝ ነው እሱ ባሻው ነገር ላይ ቻይ ነው" ብለው መለሱለት።

መላዕቱም ወደ ሳራ ዞሩ'ና፦"አንችም ኢስሀቅ የተባለን ነቢይ ትወልጃለሽ" አሏት።

ሳራም በጣም በመገረም አፏን ይዛ፦"ይህ ግን እንዴት ይታሰባል ኢብራሂም እኮ የጃጀ ሽማግሌ ሲሆን እኔም መሀን ነኝ" ስትላቸው።

መላዕክቱም ምንም እንኳን ሳራ መሀን ብትሆን እና ኢብራሂምም ሽማግሌ ቢሆንም አላህ ልጅ በቅርቡ እንደሚሰጣቻው እና ያ ልጅም ወደፊት ነቢይ እንደሚሆንም አክለው አረጋገጡላቸው።

እና መላዕክቱም ጉዞ ወደ ሰዶማውያን ጀመሩ።(በነገራችን ላይ ሉጥ ከኢብራሂም ከተለያየ በኋላ ሰዶም ወደተባለ ሀገር በመሄድ ዳዕዋ ማድረግ ጀምሯል።ይህን ደሞ ነገ ምንዳስሰው ይሆናል።
ብዙም ሳይቆይ ወደመካ በተጎዘበት ግዜ ዳግም ሌላ ትዕዛዝ ከጌታው በኩል መጣለት፦"ከልጅህ ጋር በመሆን ልጅህ በሚገኝባት ከተማ እኔ ምመለክበትን ቤት(ካዕባ) ስራ" የሚል ነበር ትዕዛዙ።
ኢብራሂምም ለጌታው ታዛዥ በመሆን ልጁን ሲያማክረው ልጁም መርሀባ ይለውና ማቴርያል አሰባስበው ግንባታ ጀመሩ።

ኢብራሂም እላይ ሲክብ ኢስማዒል ደሞ ከታች ድንጋይ ያቀብለው ነበር።

በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ፦"ጌታችን ሆይ! የምንሰራውን ተቀበለን አንተ ሰሚም አዋቂም ነህ" በማለት ዱዓ ያደርጉ ነበር።

አሁን የታዘዙትን ቤት ሰርተው አጠናቀዋል ኢብራሂምም ከቤቱ ጎን በመቆም፦" ጌታዬ ሆይ! ይህንን አገር (መካን) ጸጥተኛ አድርገው፡፡
እኔንም ልጆቼንም ጣዖታትን ከመገዛት አርቀን።
ለእዚያ ከሽምግልና በኋላ ኢስማዒልን ኢስሐቅንም ለእኔ ለሰጠኝ አላህ ምሰጋና ይገባው፡፡

ጌታዬ ልመናን በእርግጥ ሰሚ ነውና...ጌታዬ ሆይ! ሰላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ፡፡ ከዘሮቼም (አድርግ)፡፡ ጌታችን ሆይ! ጸሎቴንም ተቀበለኝ።

ጌታችን ሆይ! ለእኔም ለወላጆቼም ለምእመናንም ሁሉ ምርመራ በሚደረግበት ቀን ማር" በማለት ዱዐ አደረገ።
በግን ባታው ላይ እያሉ ወደ መዐዘኑ ሲደርሱ እበራሂም ዐለይሂሰላም የህ መዐዘን ከሌለ የተለየ እንዲሆነና የተቀረው ግንባታ ከርሱ እንዲቀጥል ፈለገ ከዚያም እስማኢልን ከዛ መዐዘን የሚገጥም ደንጋይ እንዲፈለግ አዘዘው፡፡
እስማኢለም አባቴ ሆይ ደክሞኛል አለው ተነስ አለው ምንም እንኳ የደከመ ቢሆነም አባቱ በዘዘው ግዜ ቆመና ድንጋይ ሊፈለግ ጀመረ ፈለገ ፣ ፈለገ፣ ፈለገ ግን ለዚያ መዐዘን የሚሆን ዲንጋይ ሊገኝ አልቻለም።

ተመለሰ ከዚያን አንደ እጅግ ነጭ የሆነ ድንጋይ በመዐዘኑ ላይ ተቀምጦ አየ፣ እብራሂም ዐለይሂሰላም ግንባተውን እያገባደደ ተመለከተ፣

ክፍል 5 ይቀጥላል..

#share
@alahu_akber1
•••✿ ❒ የነብዩሏህ ኢብራሂም ዐ,ሰ ታሪክ ❒✿•••

#ክፍል 5

አባቴ ሆይ ይህንን ድንጋይ ምን ነው ይዞልህ የመጣው ሲል ጠየቀው ፣ ያ መተረሰት የመይፈለገው እንዲሁም የማይደክመው አካል ጅብሪል ነው ያመጣልኝ አለው። እናም አል ሀጀሩል አስወድ ከጀነት ነው።

ይህን ትልቅ ቤትም ገንብተው ካጠናቀቁ በኋላ አላህም ኢብራሂምን፦"ሰዎች ከየሀገሩ በመምጣት ቤቴን ይጎብኙ ዘንድ ተጣራ" አለው።

ኢብራሂምም፦"ጌታዬ እኔ ደካማ ባሪያህ ነኝ ድምፄ እኮ አይደርስም"አለው።

አላህም፦"አንተ ተጣራ ማድረስ የኔ ስራ ነው" አለው።

ኢብራሂምም ትልቅ ተራራ ላይ በመውጣት ተጣራ።ያን ግዜ ከየሀገሩ ያሉ ህዝቦች ጥሪውን በመቀበል መካ መጥተው ሞሉ። ኢብራሂምም የሀጅን ስነስርዐት ለሁሉም አስተማራቸው።

ከዚያ በኋላ የኢብራሂም ሚስት ሳራ በከንዐን ምድር ሀብሩን በምትባል ቦታ በ127 አመቷ ዱንያን ተሰናበተች።
ከዚያ በኋላ ኢብራሂም ለሳራ ልጅ ኢስሀቅ ሪፍቃ ቢንት በቱኢል የተባለችን እንስት አጭቶለት አጋባው።
ኢብራሂም እደሚያቸው 175 ሲሆን ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

እስማኢል ና እስሃቅቀበሯቸው። ኢብራሂም የተቀበሩት #በሀብሩንነው።የቺ አከባቢ በሁን ሰዐት ከሊል በመባል ትተወቃለች።

አይሁዶች ና እንግሊዛዊያን ሄብሮን በማለት ይጠሯታል።እብራሂም ዐ ሰ የነቢያት አባት ነቸው።

ከኢብራሂም ዐ ሰ ብሇላ ከሰቸው ዘር ካልሆነ በስተቀር አንደም ነቢይ አልተላከም።

•••✿ ❒ ተ_ፈ_ፀ_መ ❒✿•••

በቀጣይ #የነብዩሏህ_ኢስሃቅ_ና_የያእቁብ(ዐ.ሰ) ታሪክ እንጀምራለን 🥰
#share
@alahu_akber1
'
•••✿ ❒ የነቢዩሏህ_እስሃቅ_ና_የአቆብ_ዐለይሂሰላም_ታረክ ❒ ✿•••

#ክፍል 1

ለኢስሀቅ አባቱ ኢብራሂም (ዐሰ) በህይወት ሳለ በ40 አመቱ ነበር ረፍቃ ቢንት በትዋዪል ከተባለች እንስት ትዳር ያስያዘው።

ምንም እንኳን ረፍቃ መውለድ የማትችል መሃን ብትሆንም በባለቤቷ ያላሰለሰ ዱዓ ሁለት መንታ ልጆችን ለመታደል በቅታለች።

አንደኛው፦ዒስ ሲሆን

ሁለተኛው፦ያዕቁብ (ዐሰ) ይባላል።

ዒስ የሮም ህዝቦች ቅድመ አያት ሲሆን፤ ያዕቁብ ደሞ የእስራኢላውያን ቅድመ አያት ነው። የሁለቱም አባት ሁለቱንም ልጆቹን በጣም ቢወዳቸውም ከያዕቁብ ይልቅ ለዒሱ ግን ለየት ያለ ቦታ ነበረው።

እናታቸው ረፍቃ ግን ያዕቁብ ታናሽ ስለሆነ ይበልጥ እሱን ነበር የምትወደው።

ኢስሀቅ ከእርጅና የተነሳ አይናቸው ማየት ካቆመ ትንሽ ሰንበትበት ብሏል።

ከእለታት አንድ ቀን ኢስሀቅ (ዐሰ) ስጋ ያምራቸውና የሚወዱትን ልጃቸውን ዒስን አደን አድኖ ስጋ እንዲያመጣለቸው እናም ከባድ ዱዓም እንደሚያደርጉለት ነግረውት እሱም ለአደን ሄደ።

ይህን በድብቅ ስትሰማ የነበረችውም የልጆቹ እናት ረፍቃ ለያዕቁብ ነግራው ከፍየሎቹ ወፍራሙን ሙኩት እንዲያርድ ካደረገች በኋላ የወንድሙን ዒስን ልብስ አልብሳው እራሱን(ዒስን) አስመስላ የሰራውን ስጋ ለአባቱ እንዲያቀርብ አደረገች።

ያዕቁብም ያዘጋጀውን ምግብ ይዞ አባቱ ዘንድ ሲያቀርብ

አባቱ፦"ማን ነህ አንተ?" አሉት።

ያዕቁብም፦"ልጅዎት ነኝ"አለ።

አባቱም(ኢስሀቅ)፦"ድምፅህ የያዕቁብ ነው፤ልብስህ ግን የዒስ ነው" በማለት የቀረበላቸውን ምግብ በሉት።

ምግቡን በልተው እንደጠገቡም ምግቡን ላቀረበው አላህ ክብሩን ከፍ እንዲያደግለት፣ የበላይ ዘርም እንዲያደርገው፣ልጆቹንም ሪዝቁንም አላህ እንዲያበረክትለት ዱዓ አደረጉ።

ልክ ዱዓውን እንዳጠናቀቁ ያዕቁብ አሚን ብሎ የአባቱን ክፍል ለቆ ወጣ።ያዕቁብም ሲወጣ ዒስ በታዘዘው መልኩ ያደነውን ስጋ ጠባብሶ ለአባቶ አመጣ'ና አቀረበ። አባቱ ግን ቅድሙኑ ጠግበዋል።

ዒስ ምግቡን ሲያቀርብላቸው፦"ልጄ ይህ ምንድነው?" አሉት።

ዒስ'ም፦"አምጣልኝ ያሉት ስጋ ነዋ" አላቸው።

አባትየውም፦"አሁን አምጥተህልኝ በልቼ ዱዓ አላደረግኩልም እንዴ!!!"ሲሉት ወንድሙ ያዕቁብ እንደቀደመው እና ዱዓውንም ሸውዶ እንደተቀበለ በመረዳት ሀይለኛ እልህ ያዘው።

ዒስ አባታቸው ኢስሀቅ ከሞተ ያዕቁብን እንደሚገድለውም ይዝትበት ጀመር።ያን ግዜ አባት ለልጃቸው ዒስ ማስተዛዘኛ ይሆም ዘንድ፦"አላህ ዝርያዎችህን ጠንካሮች ያድርጋቸው፣ፍራፍሬዎችን እና ሪዝቆቹንም አላህ ሰፋ አድርጎ ይስጥህ" በማለት ዱዓ አደረጉለት።

ነገር ግን እናት ልጇ ያዕቁብ ላይ ሚዛተው ዛቻ እረፍት ነስቷት ስለነበር የዒስ ቁጣ እስኪበርድለት ድረስ ያዕቁብን ሀራን በሚባል አካባቢ ወደሚገኘው ወንድሟ (ላባን) ላከችው።

ያዕቁብም ስንቁን ይዞ ወደ አጎቱ ላባን እየተጓዘ ሳለ መንገድ ላይ መሸበት እና አንድ ድንጋይ ተንተርሶ ፏ ያለ እንቅልፍ ተኛ።

እዛው በተኛበትም በህልሙ ወደ ሰማይ መወጣጫ ይመለከታል።በዚያ መወጣጫ መላዕክት ይወጣሉ...ይወርዳሉ።በዚያ መሀከል አላህም፦"እኔ አንተን እባርክሀለሁ።ዝሪያዎችህንም አበዛልሀለሁ...ምድርንም ላንተ እና ለዝርያዎችህ አደርጋታለሁ" አለው። በህልሙ ማለት ነው....

ልክ ይሄን እንዳየ ከእንቅልፉ ነቃ። ባየው ነገርም በጣሙን ተደሰተ'ና፦"ጌታዬ አሁን ከምሄድበት በሰላም ከመለስከኝ እዚህ ቦታ ላይ ላንተ አምልኮ እሚሆን ቤት እገነባለሁ።ከሚኖረኝም ሀብት አንድ አስረኛውን ባንተ መንገድ አውላለሁ" በማለት እዛ ቦታ ላይ የሆነ ምልክት አድርጎ ስለት ገብቶ ጎዞውን ቀጠለ።

ብዙ ተጉዞ የሀራንን ምድር ደረሰ'ና ከአጎቱም ተገናኘ።ለአጎቱ ሁለት ሴት ልጆች ነበሩት አንዷ (ለያ) ስትባል ታናሿ ደሞ (ራሂል) ትባላለች።

ምነው ለያ ራሂል...ስል የዩሱፍ ፊልም ትዝ አላችሁ ሀ....!!! ቆይ ዩሱፍንም ደርሰነዋል ትንሽ ነው የቀረን።

ትንሸኛዋ ራሂል ቆንጅዬ ነገር ስትሆም ትልቋ ግን እስከዚህም ነገር ነበረ።ከዚያም ያዕቁብ ትንሸኛዋ ራሂል በልቡ መግባቷን ሲያውቅ አጎቱን ላባንን እንዲድረው ጠየቀው።

አጎቱም፦"7 አመት በጎችን ካገድክልኝ እድርሀለሁ" በማለት ቃል ገባለት'ና ያዕቁብም ቆንጂዬዋን ራሂልን ለማግኘት ለ7 ተከታታይ አመታት እረኛ ሆኖ አሳለፈ።

የማይደርስ የለም'ና ሰባቱ አመት ተጠናቅቆ የቀጠሮው ቀን ብቅ አለ።ላባንም ድል ያለ ድግስ ደግሶ ዘመድ አዝማድ ከጠራ በኋላ ኒክህ እስሮ ሙሽሪትንም ለያዕቁብ አስረከበው።

በማግስቱ ጠዋት ላይ ጨለማው በብርሀን መገፈፍ ሲጀምር ያዕቁብ ሙሽሪትን ተመለከታት።

ነገር ግን 7 አመት ለሷ ብሎ በግ የጠበቀላት ራሂል ሳትሆን ብዙም ማታምረዋ ለያ ሆና አገኛት።

ያዕቁብ በጣም ተናደደ....

ያዕቁብ ሙሽሪትን ተመለከታት ነገር ግን 7 አመት ለሷ ብሎ በግ የጠበቀላት ራሂል ሳትሆን ብዙም ማታምረዋ ለያ ሆና አገኛት።

ያዕቁብ በጣም ተናደደ በጠዋት አጎቱ ጋ በመሄድ፦"አንተ ቃል ኪዳንን አፍርሰሀል።እኔ የተዋዋልኩት ልጅህን ራሂልን ሀኖ ሳለ እንዴት ለያን ትሞሽርልኛለህ" በማለት ወቀሰው።

የያዕቁብ አጎትም ላባን ብልጣ ብልጥ ነገር ነበር'ና፦"ይህማ በኛ ባህል ነውር ነው...እንዴት ታላቅ እያለች ታናሽ ትዳራለች!!! በል ራሂልን ምትፈልግ እንደሆን ለ7 አመት በጎችን አግድልኝ" አለው።

ያዕቁብም ራሂልን በጣም ወዷት ስለነበር 7 አመታትን ለመጠበቅ ተገደደ።የማይደርስ የለም'ና ይህም ቀን ደረሰ።ያዕቁብም ለ14 አመት የጠበቃትን ራሂልን በእጁ አስገባት።

(በነገራችን ላይ ሁለት እህትማማቾችን በአንድ ግዜ ማግባት በነሱ ህግ/ሸሪዓ ክልክል አልነበረም።ከዚያ በኋላ ነው ተውራት ሲወርድ ይህ ህግ የተሻረው።)

ከዚያ ያዕቁብ ሁለት እህትማማቾችን አግብቶ ሳለ አጎቱ ላባን ለሁለት ለልጆቹ ሁለት አገልጋዮችን በስጦታ መልኩ ጀባ አላቸው።

ለያ ለምትባለዋ፦ዘልፋ የምትባል አገልጋይ ሲሰጣት

ራሂል ለምትባለዋም፦በልሃ የምትባል አገልጋይ ሰጣት።

አላህም ለያ የምትባለዋን(ፉንጋዋን) 4 ወንድ ልጆችን በመስጠት ካሳት።ልጆቿም

1፦ረውቢል

2፦ሸምዑን

3፦ላዊ

4፦የሁዳ...ናቸው።
ትንሿ ረሂል ምንም እንኳም ቆንጅዬ ብትሆንም ልጅ መውለድ ግን አትችልም።

በታላቅ እህቷ መውለድ በጣም ቅናት ይይዛት'ና እራሷ ዘንድ የምትገኘውን በልሀ የተባለችውን አገልጋይ ለገዛ ባለቤቷ ዳረችው'ና አገልጋይዋም ከያዕቁብ

5፦ዳን

6፦ኒፍታሊ...የተባሉ ልጆችን ወለደች።
ያን ግዜ ለያ ከእህቷ ረሂል እልህ ተያያዘች'ና እሷም ዘልፋ የምትባል አገልጋይዋን ለያዕቁብ ዳረችለት'ና ያዕቁብም ከዘልፋ

7፦ጃድ

8፦ዐሺር...የተባሉ ልጆችን ወለደችለት። ኧረ የሌላ ይደላል ያዕቁብ ዐ ሰ በመሀል ተመቻቸው እኮ...ሱብሀን አላህ የአላህ ተርቲብ

ከዚያም ለያ(ታላቋ) አምስተኛ አረገዘች'ና

9፦ያሳካር...የተባለ ልጅ ወልዳ ብዙም ሳትቆይ

10፦ዛብሎን... የተባለ ልጅ ደገመች።
አሁንም አላረፈችም

11፦ዲና... የምትባል ሴት ልጅ ለያዕቁብ አሳቀፈችው።ያ ማለት ለያ ከያዕቁብ 7 ልጆችን ወለደች ማለት ነው።

ይህን ስታይ መቋቋም ያቃታት ራሂል አላህን ልጅ እንዲሰጣት መማፀን ጀመረች።

አላህም በሩን ያንኳኳውን በከንቱ ማይመልስ ጌታ ነው'ና ዱዓዋን ተቀብሎ

12፦ዩሱፍ (ዐሰ) የሚባል ውብ እና ገራሚ የሆነ ልጅ ጀባ አላት።
ይህ ሁሉ የሚሆነው በአጎቱ ሀገር በሀራን ምድር ላይ ነው።

ክፍል 2 ይቀጥላል...

#share
@alahu_akber1
•••✿ ❒ የነቢዩሏህ_እስሃቅ_ና_የአቆብ_ዐለይሂሰላም_ታረክ ❒ ✿•••

#ክፍል 2

አሁን ያዕቁብ የትውልድ ሀገሩን ፊለስጢንን ለቅቆ የሀራንን ምድር ከረገጠ 20 አመታትን አስቆጥሯል።

ያዕቁብም አጎቱ ዘንድ በመሄድ፦"አጎቴ አሁን ፍቀድልኝ'ና ሚስት ልጆቼን ሰብስቤ ቤተሰቦቼ ጋር ልሂድ" ይለዋል።

አጎቱ ላባንም፦"ያዕቁብ እኔ ባንተ ሰበብ ብዙ ንብረቴ በረካ ሆኖልኛል።ስለዚህ የፈለግከውን ያህል ንብረት ጠይቀኝ" አለው።

ላባን በጣም ለቁጥር ሚያዳግት የእንስሳት መዐት ስለነበረው

ያዕቁብም፦"በዚህ አመት የሚወለዱትን ሁሉ ባጎች ስጠኝ።

ከተቀረው እንስሳቶችህ መልካቸው ጥቁር በነጭ የሚወልዱትንም ስጠኝ።

ነጭ ዳማዎችን እና ቀይ ዳማዎችንም ስጠኝ" አለው።

አጎቱ ላባንም፦"እሺ" አለው።

ያዕቁብም ይህን ሀላፊነት ልጆቹ እንዲወጡ አዘዘ።

በመጀመርያ ያዕቁብ እርጉዝ የሆኑ እንስሳቶችን ከሌሎቹ እንስሳት የሶስት ቀን መንገድ ያህል ርቀት አራራቃቸው።

ነጭ ዳማዎችን እና ቀይ ዳማዎችን እንደዚያው አራራቃቸው።ይህን ካደረገ በኋላ እርጉዞቹም ወለዱ ያዕቁብም ድርሻውን ለይቶ በአላህ ትዕዛዝ ለጉዞ ተዘጋጀ።

አሁን ያዕቁብ የብዙ ሺህ በጎች...እንስሳቶች...እና የብዙ አገልጋዮች ባለቤት ሆኗል።

ወደ ፊለስጢን ጉዞ ሲዝጀምሩ ራሂል የተባለችዋ የያዕቁብ ሚስት የአባቷን ጣኦት ደብቃ ይዛ ወጣች።

ያዕቁብ ልጆቹን፣ሚስቶቹን፣አገልጋዮቹን፣እንስሳቶቹን...ሁሉ ሰብስቦ በረሀውን እያቋረጠ ብዙ ተጎዞ የሀራንን ምድር ካጋመሰ በኋላ አጎቱ ላባን እና የሀራን ከተማ ነዋሪዎች ተከትለውት ደረሱበት።

ልክ እንዳገኙት አጎቱ ላባን በወቀሳ መልኩ፦"ያዕቁብ ለምን ሳትነግረኝ ትተህ ትሄዳለህ!!!

ምነው በደስታ ተሰነባብተን ከአከባቢው ህዝብ ጋር ጨፍረን ብንሸኛቹስ" በማለት አንድ ጣኦት ይዘው እንደመጡም አክሎ ጠየቀው።

ያዕቁብ ዐ ሰ ምንም አይነት ከጣኦት ጋር ግንኙነት ባይኖረውም ለአጎቱ ሲል የሚስቶቹን እቃ ሀሉ ፈተሸለት ምንም አላገኘም።

ራሂል ግን ጣኦቱን ይዛው ስለነበር ለፍተሻ ፍቃደኛ አልሆነችም ነበር አሞኛል አልነሳም አለች።

ያን ግዜ ያ ጣኦት ምናልባት ጀልዓድ በተባለ ዳገት ላይ ይኖራል በሚል ግምት ላባን ልጆቹን እና የእህቱን ልጅ ያዕቁብን ተሰናብቷቸው ተመለሰ።

ያዕቁብ የትውልድ ሀገሩን ሊገባ ጥቂት ሲቀራው መላዕክት እየወረዱ እንኳን ደህና መጣህ እያሉት ያልፉ ነበር።

አሁን ያዕቁብ ሳዒር የምትባል ቦታ ላይ ደርሷል ግን ሀገሩ ሊገባ የወንድሙን በቀል ፈርቷል።

እዛው ሆኖ እንደማለማመጥ አይነት ነገር ፅፎ ደብዳቤ ለወንድሙ ላከለት።

በነጋታው ሌላ የዛቻ ደብዳቤ የያዘች ወረቀት ዒስ(የያዕቁብ ወንድም) 400 እግረኛ ጦር አሰልፎ እየመጣ መሆኑን የሚያስረዳ መልዕክት ከወደ ፊለስጢን በኩል ለያዕቁብ መጣችለት።

ያዕቁብም ፈራ...አላህንም ከወንድሙ ተንኮል እንዲታደገው ተማፀነ...ለአላህም ስለት ገባ።

ያዕቁብም ፈራ...አላህንም ከወንድሙ ተንኮል እንዲታደገው ተማፀነ...ለአላህም ስለት ገባ።

ከዚያም ወንድሙን ሊያስደስት በርከት ያለ ስጦታም አዘጋጀለት...

200 ሴት ፍየሎችን እና 20 ወንድ ፍየሎች

200 ሴት በጎችን እና 20 ወንድ በጎች

30 (ኮርማ)በሬዎችን እና 40 ላሞች

20 ሴት ግመሎችን እና 10 ወንድ ግመሎች

እና አራቱንም የስጦታ አይነቶችን ለያይቶ ሊልክ በአራት ቡድን የተደራጀ አገልጋዮችን አዘጋጀ እና ቀድሞ አንዱን ቡድን ለከ።

የመጀመርያው ቡድን ስጦታን ይዞ ሄዶ ትንሽ ራቅ ሲል ሁለተኛውን ይልካል ሁለተኛውም ትንሽ ራቅ ሲል ሶስተኛውን ይልካል....

እንዲ እንዲ እያለ አራቱንም የስጦታ አይነት ከነ አገልጋዮቻቸው ጨምሮ፦"ማንም የማን ነው ብሎ ከጠየቃችሁ ከያዕቁብ ለዒስ የተላከ ስጦታ ነው በሉ" ብሎ ላካቸው።

ይህንንም ሊያደርግ የቻለው ወንድሙ ዒስ ስጦታዎች በተከታታይ ሲመጡለት ደስታው የላቀ ይሆናል በሚል ነው።

ከዚያም የመጀመሪያውን ስጦታ የያዘው የአገልጋልይ ቡድን ዒስ እና ወታደሮቹ ያሉበትን ቦታ ሲደርሱ

ዒስ፦"ይህ የማን ነው?" ብሎ ጠየቀ።

አገልጋዮቹም፦" ከያዕቁብ ለዒስ የተላከ ስጦታ ነው" አሉት።

እሱን ተቀበላቸውና ሁሉም የስጦታ ነጂ ቡድኖች ስጦታዎቻቸውን ተራ በተራ እየነዱ አስረከቡት።

ያዕቁብም ሚስቶቹን ልጆቹን እና የተቀሩ አገልጋዮቹን አስከትሎ በሌሊት ወደ ወንድሙ ጉዞ ጀመረ።

(በነገራችን ላይ በዚህች የሌሊት ጉዞ ነበር ክርስቲያን ወገኖች ያዕቁብ እና እግዚአብሄር ተደባድበው ያዕቁብ አሸነፈው የሚሉት።)

ሌሊቱን ተጉዞ ፀሀይ ጀንበሯን አምልጣ መውጣት ስትጀምር ለ20 አመታት ያህል የተለያዩ ወንድማሞች አይን ለአይን ተገጣጠሙ።

ዒስ 400 ጦረኛዎችን አሰልፏል።ያዕቁብም ወንድሙን ሲያየው 7 ግዜ አጎበደደለት(ይህ በዘመናቸው ሀራም አልነበረም የዘመናቸውም ሰላምታ ነበር።

በቀጣይ ክፍላችን ለዩሱፍ ሲሰግዱ እንዳስሳለን"

ዒስ ዱዓውን ከአባቱ የዘረፈውን ወንድሙን ሲያይ ሄዶ ተጠምጥሞበት ወንድሙን እየሳመ ያለቅስ ጀመር።በዚህ አጋጣሚ ከአጠገቡ ያሉትን ሴቶችን

ልጆችን እና አገልጋዮችን ሲመለከት፦"ይሄም ሁሉ ኬት አምጥተህ ነው?" አለው።

ያዕቁብም፦"እነዚህ አላህ የሰጠኝ ስጦታዎቼ ናቸው" አለው።

ይህን ግዜ የያዕቁብ ልጆች እና ሚስቶች ተራ በተራ እየመጡ ዒስን ከዘየሩ በኋላ ያዕቁብ በአገልጋዮቹ አማካኝነት ለዒስ የላከውን ስጦታ ዒስ መቀበል እንቢ አለ።

ያዕቁብም ለምኖት እንዲቀበል አደረገው'ና አብረው በረሀውን እያቆራረጡ አባታቸው ወደሚገኝበት የፊለስጢን ምድር መትመም ጀመሩ።

በዚህ ጉዞ ላይም ሳሉ ያኔ....ያዕቁብ አጎቱ ጋ ሲሄድ ተኝቶ ህልም ያየበትን ቦታ ደረሱና እዛ ቦታ ያዕቁብ በ200 በግ ያንን ቦታ ከአንድ ገበሬ ገዛው'ና

አንድ ትልቅ የአምልኮ ቦታ ሰራ(ቁድስ) ከዚያ በኋላ ነው በሱለይማን ዘመን ሱለይማን ያደሰው።

በዚህ ጉዞ ላይም ሳሉ ነበር አንድ ደስታ እና ትልቅ ሀዘን በያዕቁብ ቤተሰብ የተከሰተው።

ነፍሰ ጡር የነበረችው ትንሿ ራሂል ምጥ አስቸገራት...ብዙ ከተጨነቀች በኋላ ቢንያሚን የተባለ ልጅ ተገላግላ ለራሷም ዱንያን ተገላገለቻት።


ያዕቁብም ባለቤቱን መንገድ ላይ ቀብሮ ሀዘኑን ታቅፎ ወደ አባቱ ጉዞ ቀጠለ።

ከአባቱም ተገናኝቶ በከንዓን ምድር ሀብሩን በምትባል(ኢብራሂም ይኖር በነበረበት) አካባቢ መኖር ጀመረ።

ኢስሀቅም እርጅና ተጫጭኖትም ስለነበር ጌታው የፃፈለትን 180 አመት ካጠናቀቀ በኋላ ነፍሱን ለጌታው አስረከበ።

የነበቢዩሏህ የኢስሃቅ ዐለይሂሰላም ታረክ አዚህ ላይ ተፈፀመ።

የነቢዩሏህ የአቆብ ዐለይሂሰላም ታሪክ የቀረውን የነቢዩሏህ ዩሱፍ ታረክ ውስጥ እናየወለንን!!


•••✿ ❒ ተ_ፈ_ፀ_መ ❒✿•••

በቀጣይ #ነብዩሏህ_የአቆብ_ና_ዩሱፍ(ዐ.ሰ) ታሪክ እንጀምራለን 🥰
#share
@alahu_akber1
'
•••✿ ❒ ነብዩሏህ_የአቆብ_ና_ዩሱፍ_ዐለይሂ_ሰላም_ታርክ ❒✿••

#ክፍል 1

ያዕቁብ ልጆቹን ሚስቶቹን እና አገልጋዮቹን ይዞ ከንዓን ምድር ላይ ኑሯቸውን ጀምረዋል።

ያዕቁብ ልጆቹን ሁሉ እላፊ በመውደዱ የሚታወቅ አባት ቢሆንም ለየቲሞቹ ለዩሱፍ እና ለቢንያሚን ያለው ቦታ ልዩ ነበር።

ከእለታት አንድ ቀን ዩሱፍ በሌሊት ተነስቶ ለአባባቱ ያየውን ድንቅ ህልም እንዲህ ሲል ይነግረዋል፦" አባቴ ሆይ! እኔ ዐስራ አንድ ከዋክብትን ፀሐይንና ጨረቃንም (በሕልሜ) አየሁ፡፡ ለእኔ ሰጋጆች ሆነው አየኋቸው"

አባትየውም፦"ልጄ ሆይ! ሕልምህን ለወንድሞችህ አታውራ፡፡ ላንተ ተንኮልን ይሰሩብሃልና።

ሰይጣን ለሰው ግልጽ ጠላት ነውና..... እንደዚሁም (እንዳየኸው) ጌታህ ይመርጥሃል፡፥

ከንግግሮችም ፍች ያስተምርሃል፡፡ ጸጋውንም ከአሁን በፊት በሁለቱ አባቶችህ በኢብራሂምና በኢስሐቅ ላይ እንዳሟላት በአንተ ላይና በያዕቆብ ዘሮችም ላይ ይሞላታል፡፡

ጌታህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና" ብሎ አብስሮት ህልሙንም ለማንም እንዳይናገር አስጠነቀቀው።

አባትየው ያዕቁብ የዩሱፍን ህልም ከሰሙ በኋላ ለዩስፍ ያላቸው ፍቅር ወደ አክብሮት እና ለሱ ወደ መተናነስ ያደላም ጀመር።

ይህ ግን ለዩሱፍ ለአባቱ ልጆች የእግር እሳት ሆኖባቸው ቅናት እረፍት ነስቷቸዋል።

ከእለታት አንድ ቀን የዩሱፍ የአባት ልጆች በዩሱፍ እና በአባቱ መካከል ያለውን ፍቅር እንዴት በአጭሩ ማኮላሸት እንዳለባቸው ሊመካከሩ አንድ ቦታ ተሰበሰቡ።

ብዙ ሀሳቦችን አንስተው በመጨረሻም ዩሱፍን በአንድ ውሀው ጨዋማ በሆነ ስምጥ ጉድጓድ ውስጥ ሊጨምሩት ወሰኑ።

ማታ ላይ አባታቸው ዘንድ በመሄድም፦" አባታችን ሆይ! በዩሱፍ ላይ ለምን አታምነንም እኛም ለእርሱ በእርግጥ አዛኞች ነን።

ነገ ከእኛ ጋር ላከውና ይደሰት፤ ይጫወትም፡፡

እኛም ለእርሱ ጠባቂዎች ነን" በማለት ዩሱፍ ከነሱ ጋር እንዲሄድ አባታቸው ያዕቁብን ተማፀኑት።

ያዕቁብም፦" እኔ እርሱን (ዩሱፍን) ይዛችሁ መሄዳችሁ በእርግጥ ያሳዝነኛል፡፡
እናንተም ከእርሱ ዘንጊዎች ስትሆኑ ተኩላ ይበላዋል ብዬ እፈራለሁ" በማለት መለሰላቸው።

ከዚህም ከዚያም ብለው አባታቸውን ካሳመኑት በኋላ የልባቸውን ሊፈፅሙ ዩሱፍን ወዳጅ መስለው አቅፈው ወሰዱት።

ያሰቡበትም ጉድጓድ ውስጥም እየለመናቸው እጅ እግሩን አሳስረው ቀሚሱን አውልቀው ወረወሩት።

ማታ ሲሆንም የሁዳ ባመጣው ሀሳብ መሰረት ያወለቁትን የዩሱፍን ቀሚስ አንድ ፍየል አርደው ቀሚሱን በፍየሏ ደም ለወሱት።

በመጨረሻም ምሽቱ ሲደምቅ እንስሳቶቹን እየነዱ መንደር ከደረሱ በኋላ የዩሱፍን በደም የተለወሰ ቀሚስ ይዘው እዬዬዬ....በማለት እያለቀሱ ሰፈሩን ቀወጡት።

ይህን ሲያይ ያዕቁብ እግሩ ተብረከረከ ተንኮለኛ ልጆቹ በውዱ ልጁ ሴራቸውን ተግባር ላይ እንዳዋሉ ተረዳ።

እሱም፦"ልጄ ምን ሆነ" ሲላቸው...

እነሱም፦" አባታችን ሆይ! እኛ (ለሩጫና ለውርወራ) ልንሽቀዳደም ሄድን፡፡ ዩሱፍንም ዕቃችን ዘንድ ተውነው፡፡ ወዲያውም ተኩላ በላው፡፡

አንተም እውነተኞች ብንሆንም የምታምነን አይደለህም" አሉት (እነዚህ ቀልበ ደረቆች)

አባታቸውም፦" አይደለም፤ ነፍሶቻችሁ (ውሸት) ነገርን ለእናንተ ሸለሙላችሁ፡፡

ስለዚህ መልካም ትዕግስት (ማድረግ አለብኝ) በምትሉትም ነገር ላይ መታገዣው አላህ ብቻ ነው" ብሎ ጉዳዩ ለአላህ የወው።

ዩሱፍም እዚያ ጉድጓድ ውስጥ ሳለ ወደ ግብፅ የሚሄድ ቅፍለት(ተጓዥ ነጋዴዎች) በዚያ ጉድጓድ ሲያልፉ ውሀ ለመቅዳት ባልዲያቸውን ወደ ውስጥ ወርውረው ውሀ ለማውጣት ወደ ላይ ሲጎትቱ ቆንጅዬ ልጅ ባልዲው ላይ ተንጠልጥሎ ወጣ።

በዚህ ሁኔታ ላይ ውሀውን ሚቀዳው ሰውዬ ልጅ አገኘሁ እያለ ሲጮኽ የዩሱፍ ወንድሞች ሰምተው መጡ'ና፦

"ከኛ ያመለጠ ባሪያ ነው ከፈለጋችሁ ግዙን እንጂ በነፃ አትወስዱም" በማለት ወንድማቸውን በርካሽ ዋጋ ለነጋዴዎቹ ሸጡላቸው።

ነጋዴዎቹ ደግሞ ሸቀጣቸውን ከሚገዙባት ግብፅ ከተማ ሲደርሱ ለግብፅ አስተዳዳሪ በርካሽ ዋጋ ሸጡለት።

የሀገሪቱ አስተዳዳሪም ዩሱፍን ለሚስቱ በስጦታ ምልኩ አበርክቶላት ልጅ ስለሌላት እንድ ልጇ አድርጋ እንድታየውም ነገራት።

ሚስቱም እጅጉን ተደሰተች የልጁ ውበትም ከልጅነቱ ጋር አጓጊነቱም ማረካት።

ግዚያት ነጎዱ ቀን ሌሊትን ክረምት በጋን እየተተካኩ ብዙ አመታት ተቆጠሩ።

ዩሱፍም ወጣትነቱ እና የአዕምሮ ብስለቱ ይልቅ ውበቱን ጨምሮበታል።

የአስተዳዳሪው ሚስት ይህን ስታይ ሁኔታዋ እየተቀያየረ መምጣት ጀመረ።

ከእለታት አንድ ቀንም ለዝሙት እራሷን አዘጋጅታ ክፍሏ አስጠራችው'ና በሩን ዘጋጋች።ከዚያም፦"ተዘጋጅቼልሀለሁ ናልኝ" ስትለው

ዩሱፍም፦" በአላህ እጠበቃለሁ እርሱ (የገዛኝ) ጌታዬ ኑሮዬን ያሳመረልኝ ነውና፤ (አልከዳውም)፡፡ እነሆ! በደለኞች አይድኑም" አላት።

በዚህ አጋጣሚ ዩሱፍ በሩን ከፍቶ ሲወጣ የሴትየዋ ባል፣የከተማይቷ አስተዳዳሪ፣የራሱ አለቃ....በር ላይ ተገጣጠሙ።

ሚስቱ ዩሱፍን ተከትላም ስትወጣ ባሏን በር ላይ አገኘችው።ለትንሽ ሰዐት በሶስቱም መሀከል ዝምታ ሰፈነ።በመቀጠልም ምን እየተከሰተ እንደነበር አስተዳዳሪው ሲጠይቃቸው

ሚስትየው ቀደም ብላ፦" በባለቤትህ መጥፎን ያሰበ ሰው ቅጣቱ መታሰር ወይም አሳማሚ ስቃይ እንጂ ሌላ አይደለም" አለች።

ዩሱፍም ንግግሯ ውሸት እንደሆነ አስተባበለ በዚህ መሀልም አንድ በወራት ቤት ያለ የዙለይካ የዘመዷ ህፃን ልጅ ሊዳኛቸው አላህ በመሀል አስገባው።

ህፀኑም፦" ቀሚሱ ከበስተፊት ተቀድዶ እንደሆነ (እሷ)እውነት ተናገረች፡፡ እርሱም ከውሸታሞቹ ነው

ቀሚሱም ከበስተኋላ ተቀድዶ እንደሆነ እሷ ዋሸች፡፡እርሱም ከእውነተኞቹ ነው"በማለት ፍርዱን ሰጠ።

አስተዳዳሪውም በመገረም ቀሚሱን ሲመለከት የተቀደደው ከኋላ ነው።ወደ ሚስቱ ዞር በማለት፦

"እርሱ (የተናገርሺው) ከተንኮላችሁ ነው (ሴቶች) ተንኮላችሁ በእርግጥ ብርቱ ነውና" ብሎ ወቀሳት።

ለዩሱፍም ወሬውን እንዳያሰራጭ ነገረው።

ነገር ግን በጥቂት ቀናት ውስጥ ወሬው በከተማይቱ እጅጉን ተሰራጨ።(ወይ dire tube የለ...ወይ ethiopian dj የለ...)ግን ብቻ ወሬው ከአጥናፍ እስካጥናፍ ተሰራጨ።

ይንህ የወሬውን መሰራጨት ዙለይካ ስትሰማ አንድ ሴራ ጠነሰሰች'ና አንድ ትልቅ ዝግጅት በማዘጋጀት የከተማውን የመሳፍንት እና የከበርቴ ሚስቶችን ባጠቃላይ ጠራች።

ከዚያም በዝግጅቱ ሁሉም ሴት መገኘቱን ስታረጋግጥ ፍራፍሬ እና ቢለዋ በመስጠት እሷ መብላት ጀምሩ ሳትል ማንም እንዳይበላ አዘዘቻቸው።

በዚህ መሀል አሁን መብላት ትችላላችሁ ብላ ሴቶቹ የያዙትን ፍራፍሬ መቆራረጥ ሲጀምሩ፦"ዩሱፍ ና ግባ" በማለት ድምጿን ከፍ አድርጋ ጠራችው።

ዩሱፍም ያማረ ልብስ አስለብሳው ነበር'ና ልክ የሌሊት ጨረቃ መስሎ ወደ ውስጥ ሲገባ ሴቱ ሁሉ አይናቸው በሱ ፈዘዘ'ና ፍራፍሬውን ረስተው እጆቻቸውን በያዙት ቢለዋ በመሸረካከት፦" አላህም ጥራት ይገባው፡፡ ይህ ሰው አይደለም፡፡ ይህ ያማረ መልአክ እንጅ ሌላ አይደለም" ማለት ጀመሩ።

እሷም፦"ታዲያ ይህ ያ በርሱ (ፍቅር) የዘለፋችሁኝ ነው፡፡ በእርግጥም ከነፍሱ አባበልኩት፡፡ እምቢ አለም፡፡ የማዘውንም ነገር ባይሠራ በእርግጥ ይታሰራል፡፡ ከወራዶቹም ይሆናል" አለቻቸው።

ዩሱፍም፦"ጌታዬ ሆይ! ወደርሱ ከሚጠሩኝ ነገር (ከዝሙት) ይልቅ መታሰር ለእኔ የተወደደ ነው፡፡

ክፍል 2 ይቀጥላል...

#share
@alahu_akber1
•••✿ ❒ ነብዩሏህ_የአቆብ_ና_ዩሱፍ_ዐለይሂ_ሰላም_ታርክ ❒✿••

#ክፍል 2

ተንኮላቸውንም ከእኔ ላይ ባትመልስልኝ ወደነሱ እዘነበላለሁ፡፡ ከስህተተኞቹም እሆናለሁ" ሲል አላህን ተማፀነው።

የከተማይቱ አስተዳዳሪም በሚስቱ ሰበብ የጠፋውን ስሙን ለማደስ ሲል ዩሱፍን እስር ቤት ለመጣል ወሰነ።

ዩሱፍም እስር ቤት በገባ ግዜ እሱን በፊትም የሚያውቁት ሁለት እስረኞች(አንዱ የንጉስ የምግብ ሰራተኛ ሲሆን አንዱ ደሞ የንጉስ ጠጅ ጠማቂ ነው።)

ለዩሱፍም እንዲህ ሲል አንደኛው ጠየቀው፦" እኔ በህልሜ የወይን ጠጅን ስጠምቅ አየሁ" ሁለተኛውም፡-"እኔ በራሴ ላይ ዳቦ ተሸክሜ ከእሱ በራሪ (አሞራ) ስትበላ አየሁ፡፡

ፍቹን ንገረን፡፡ እኛ ከአሳማሪዎች ሆነህ እናይሃለን'ና" በማለት ጠየቀው።

ዩሱፍም እችን አጋጣሚ በመጠቀም እስር ቤት ውስጥ ላሉ እስረኞች ዳዕዋ ለማድረግ አሰበ'ና፦"ማንኛውም የሚመጣላችሁ ምግብ ለናንተ ከመምጣቱ በፊት ፍቹን የምነግራችሁ ቢሆን እንጂ አይመጣላችሁም፡፡

ይኸ ጌታዬ ካሳወቀኝ ነገር ነው፤ እኔ በአላህ የማያምኑን እነርሱም መጨረሻይቱን ዓለም እነርሱ ከሓዲዎች የሆኑትን ሕዝቦች ሃይማኖት ትቻለሁ።
የአባቶቼን የኢብራሂምንና፣ የኢስሐቅን፣ የያዕቆብንም ሃይማኖት ተከትያለሁ፤ ለኛ በአላህ ምንንም ማጋራት አይገባንም፤ ያ (አለማጋራት) በኛ ላይና በሰዎቹ ላይ የአላህ ችሮታ ነው፤ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያመሰግኑም።

የእስር ቤት ጓደኞቼ ሆይ! የተለያዩ አምላኮች ከብርና ከወርቅ ከእንጨት የተሠሩ...? ይሻላሉን ወይንስ አሸናፊው አንዱ አላህ? ከርሱ ሌላ እናንተና አባቶቻችሁ (አማልክት ብላችሁ) የጠራችኋቸውን ስሞች እንጅ አትግገዙም፤ አላህ በርሷ ምንም አስረጅ አላወረደም ፍርዱ የአላህ እንጅ የሌላ አይደለም እርሱን እንጅ ሌላን እንዳትግገዙ አዟል፤ ይህ ትክክለኛው ሃይማኖት ነው፤ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም" በማለት ወደ አላህ ከጠራቸው በኋላ

የሁለቱንም ህልም እንዲህ ሲል ፈታላቸው፦"የእስር ቤት ጓደኞቼ አንደኛችሁ ለ ንጉሱ ጠጁን በመጥመቅ ወደ ቀድሞ ስራው ሲመለስ

ሁለተኛችሁ ደግሞ ስቅላት ተፈርዶበት ከተሰቀለ በኋላም ጭንቅላቱን አዕዋፍ ይበሉታል። ይህ የህልማችሁ ፍቺ ጥርጥር የለውም ተፋፃሚ ነው።"

ይህን ካላቸው በኋላ ዩሱፍ ዐ ሰ ህልማቸውን በፈታው መልኩ አንደኛው ተወስዶ ሲሰቀል አንደኛውም ወደ መጀመርያ ስራው ተመልሶ ለንጉሱ ጠጅ እንዲጠምቅለት ተወሰነ።

ለንጉሱ ጠጅ እንዲጠምቅለት የተወሰነለት ሊወጣ ሲል ዩሱፍ አስቆመው'ና፦"ንጉሱ ዘንድ ስትሄድ አንድ ንፁህ ሰው ያለ ወንጀሉ በአስተዳዳሪው አማካኝነት ታስሯል ብለህ በደሌን ንገርልኝ" አለው።

እሱም እሽ ብሎ ከወጣ በኋላ ንጉሱ ዘንድ ወደ ስራ ገበታው ሲቀላቀል ዩሱፍን ከነአካቴው ረሳው።በዚህ ሁኔታ ላይ ዩሱፍ ለረጅም አመታት ያለጥፋቱ እስር ቤት ከረመ።

ከእለታት አንድ ቀን የሀገሪቱ ንጉሱ(በነገራችን ላይ ንጉስ እና አስተዳዳሪ ስል እንዳይመሳሰልባችሁ እሺ...! አስተዳዳሪው ዩሱፍን የገዛው ሲሆን ንጉሱ ደሞ ገና ዩሱፍን አያውቀውም።

የአስተዳዳሪው የበላይ ነው) እናላችሁ ይህ ንጉስ በደረቅ ሌሊት ህልም አየው ብሎ ተነስቶ ቤተ መንግስቱ በአንድ እግር አቆመው።

በአስቸኳይ የኮከብ አዋቂዎችን እና ካህናትን በዚያ ሌሊት እንዲሰበሰቡ አደረገ።ከዚያ ህልሙንም እንዲህ ሲል ተረከላቸው፦" እኔ ሰባትን የሰቡ ላሞች ሰባት ከሲታዎች ሲበሉዋቸው፣ ሰባትንም ለምለም ዘለላዎች ሌሎችንም ደረቆችን (ሲጠመጠሙባቸው በሕልሜ) አያለሁ፤ እናንተ ታላላቅ ሰዎች ሆይ! ሕልምን የምትፈቱ እንደሆናችሁ ሕልሜን ፍቱልኝ "

ካህናቱ እና ጠንቋይዎቹ የንጉሱን ህልም ሊፈቱ እጅጉን ተቸገሩ። ቢያወጡ ቢያወርዱ በቃ ምንም ሊያውቁት አልቻሉም'ና፦"ንጉስ ሆይ! የዚህን ህልም ፍቺ ልናውቅ ስላልቻልን ይህ ህልም ቅዠት ነው" አሉት።

ያን ግዜ ጠጅ ጠማቂው ያ የድሮ የእስር ቤቱን ህልም ፈቺ ጓደኛውን ዩሱፍን አስታወሰ።

ከመሀከል ብድግ በማለትም፦"እኔ የህልሙን ፍቺ ይዤ እመጣለሁ ግን የእስር ቤት ፍቃድ አውጡልኝ" ሲል ለንጉሱ ተናገረ።

ንጉስም አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግለት በማዘዝ ጠጅ ጠማቂውም ዩሱፍ ወደሚገኝበት እስር ቤት ብቅ አለ።

ዩሱፍንም ስለረሳው ይቅርታ በመጠየቅ ንጉሱ ያየውን ህልም ተረከለት'ና ፍቺውን ጠየቀው።ዩሱፍም፦" ሰባትን የተከታተሉ ዓመታት

ትዘራላችሁ፤ ያጨዳችሁትንም ሁሉ ከምትበሉት ጥቂት በስተቀር በዘለላው ውስጥ ተዉት።
ከዚያም ከነዚያ በኋላ፣ ካከማቻችሁት ጥቂት ሲቀር፣ ለነሱ ያከማቻችሁትን ሁሉ የሚበሉ ሰባት

የችግሮች ዓመታት ይመጣሉ።

ከዚያም ከነዚያ በኋላ ሰዎቹ በርሱ የሚዘነቡበት፣

በርሱም (ወይንን) የሚጨምቁበት የጥጋብ ዓመት ይመጣል" በማለት ህልሙን ብቻ ሳይሆን መፍትሄውንም ጭምር ዘረዘረለት።

ጠጅ ጠማቂውም የህልሙን ፍቺ ይዞ በደስታ ወደ ቤተ መንግስት ይገሰግስ ጀመር ልክ እንደደረሰም ለንጉሱ ፍቺውን ከነ መፍትሄው ሲተርክለት ንጉሱ ዩሱፍን አሁኑኑ አምጡልኝ አለ።

ዩሱፍንም ከእስር ቤት አውጥቶ የሚያመጣ ሰው ተመድቦ እስር ቤት ሲደርስ ዩሱፍ፦" ወደ ንጉሱ ተመለስ፤ የነዚያንም እጆቻቸውን የቆረጡትን ሴቶች ሁኔታ ጠይቀው፤ ጌታዬ ተንኮላቸውን አዋቂ ነውና" በማለት ይህ ጉዳይ ሳይጣራ ለመውጣት ፍቃደኛ እንዳልሆነ ለንጉሱ ለከ።

ይህን ግዜ ንጉሱም በዚያ ቀን ያን ዝግጅት ተካፍለው የነበሩ የመሳፍንት፣የከበርቴ እና የአስተዳዳሪውንም ሚስት አንድ ላይ እንዲ ቀርቡ ካደረገ በኋላ፦" ዩሱፍን ከነፍሱ ባባበላችሁት ጊዜ፣ነገራችሁ(ምክንያታችሁ) ምንድነው?" ብሎ ሲጠይቃቸው...

ሴቶቹም በአንድ አፍ፦"ለአላህ ጥራትይገባው፤ በርሱ ላይ ምንም መጥፎን ነገርአላወቅንም" አሉት።

ያን ግዜ ከመሀል የአስተዳዳሪው ሚስት ቀበል አድርጋ፦" አሁን እውነቱ ተገለጸ፤ እኔ ነኝ ከነፍሱ ያባበልኩት፤ እርሱም

ከውነተኞቹ ነው" በማለት በህዝብ ፊት የዩሱፍን ንፁህነት መሰከረች።

ንጉስ ይህን በሰማ ግዜ እውነተኛውን ዩሱፍን ለማየት እጅጉን ጉጉት አደረበት።

ነፃነትህን አስመስክረሀል ና ብሎ ጠርቶት የግል አማካሪው ከማድረግም ባሻገር የሀገሪቱን ጉዳይ ሙሉ በሙሉ ፈላጭ ቆራጭ አደረገው።

አሁን ዩሱፍ ህዝቡ ዘንድ ልዩ ቦታ አለው።አብዝሀኛውም የሀገሪቱ ነዋሪ የዩሱፍን ጥሪ ተቀብሏል...እንዲህ እንዲህ እያሉ 7 አመታት ካሳለፉ በኋላ የድርቁ ዘመን ከች አለ።

ድርቁን ተከትሎ ከተለያዩ ሀገራት በድርቅ የተመቱ እህል ሸማቾች ወደ ግብፅ ምድርም ይተሙ ጀመር።

በዚያ መሀል በከንዓን ይኖሩ የነበሩ የዩሱፍ ቤተሰቦችም የድርቁ ሰለባ ነበሩ'ና 10 ወንድሞቹ እህል ፍለጋ የግብፅን ምድር ረግጠው በማያውቁት የወንድማቸው መጋዘን ለእህል ተሰለፉ።

በግዜው ከመንግስት መጋዘን ሁሉም እህል ሲሸምት ስሙን እና የመጣበትን ሀገር እያስመዘገበ ነበር የሚሸምተው።

እነዚህም ወንድሞቹ ስማቸውን እስመዝግበው እህላቸውን ከመረከባቸው በፊት ዩሱፍ የከንዓን ሰዎች መጥተዋል የሚል ወሬ ሰምቶ ሊያጣራ ሲሄድ ወንድሞቹን ተመለከታቸው።

ምንም እንኳን እሱ ቢያውቃቸውም እነሱ ግን በፍፁም ሊያውቁት አልቻሉም።ግን ዝም ብለው በግምት፦" ይህ ፊት አዲስ አልሆነብኝም ይባባላሉ" እርስ በርስ....

ዩሱፍም ከተለያዩ ሀገራት ከመጡ ቁጥር ስፍር ከሌለው ሰልፈኛ መሀል ለ40 አመት የተለያያቸውን ወንድሞቹን የሰሩበትን ተንኮል ወደ ጎን አድርጎ በናፍቆት ተሸንፎ ስለማንነቱ ምንም ሳይነግራቸው ወደሚኖርበት ቤተ መንግስት ይዟቸው ሄድ።

ክፍል 3 ይቀጥላል...

#share
@alahu_akber1
•••✿ ❒ ነብዩሏህ_የአቆብ_ና_ዩሱፍ_ዐለይሂ_ሰላም_ታርክ ❒✿••

#ክፍል 3

ይህችን ሌሊትም እሱ ጋር አሳልፈው በነጋታው እንደሚሄዱ ካሳመናቸው በኋላ በጥሩ መስተንግዶ እራት አብልቷቸው ያዕቁብ ስለተባለው ነቢይ መጠየቅ ጀመረ።በህይወት እንዳለ እና ዩሱፍ በተባለው ልጁ ሀዘን ምክንያት በጣሙን እንደተጎዳ ነገሩት።

ዩሱፍ ይህን ሁሉ ሲሰማ ሆድ እየባሰው ከእንባው ጋር ትንቅንቅ ቢገጥምም ይህን ሀዘኑን ግን ለወንድሞቹ ግልፅ ሊያደርግ አልፈለገም።ያውቁኛል ብሎ ሰግቶ.....

በነጋታው ዩሱፍ አገልጋዮቹን ጠርቶ፦"ለእህሉ የከፈሉትን ገንዘብ በየከረጢታቸው ውስጥ ደብቁትና ሳያውቁ ስጧቸው" ብሎ አዘዘ።

ዩሱፍ ባዘዘውም መልኩ የከፈሉት ገንዘብ ተመልሶ በየከረጢታቸው ተጨመረላቸው።

በመጨረሻም ሲሸኛቻው፦"በሚቀጥለው ዙር ስትመጡ ከንዓን ትታችሁት የመጣችሁትን ትንሹን ወንድማችሁን ይዛችሁ ኑ። እሱን ካላመጣችሁት ግን ምንም አይነት እህል አንሰፍርላችሁም" ብሎ ሸኛቸው። እነሱም እንደሚሞክሩ ቃል ገብተውለትጉዞ ወደ ከንዓን ጀመሩ።

ረጅም ተጉዘው ከንዓንም ሲደርሱም በግብፅ ከተማ የገጠማቸውን ሁሉ ለአባታቸው ያዕቁብ ተረኩለት'ና በቀጣይ ዙር ግን ታናሽ ወንድማቸውን ቢንያሚንን ካላመጡ ምንም አይነት ስፍር እንደማይሰፈርላቸው ነገሩት።

አባታቸው ያዕቁብ ግን ልጆቹ ከዚህ በፊት በልጁ ዩሱፍ የፈፀሙትን በማስታወስ ዳግም ልጁን ቢንያሚንን ለነሱ አምኖ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆነም ነበር።

ይሁን እንጂ ያዕቁብ ምንም እንኳን ውድ ልጁን ቢንያሚንን ከአጠገቡ ማራቅ ቢከብደውም ከፊትለፊቱ የተደቀነው ድርቅ እና ቸነፈር ቢንያሚንን ወደ ግብፅ ለመላክ አስገድዶታል።

ከመላኩ በፊትም ያዕቁብ ልጆቹን ሰብስቦ፦"ካልተከበባችሁ በስተቀር እርሱን(ቢንያሚንን) በእርግጥ

የምታመጡልኝ ለመሆናችሁ ከአላህ የሆነን ቃል ኪዳን መተማመኛ እስከምትሰጡኝ ድረስ ከናንተ ጋር ፈፅሞ አልልከውም" አላቸው።

መተማመኛቸውንም ቃል ኪዳን በሰጡት ጊዜ ፦"አላህ በምንለው ሁሉ ላይ ምስክር ነው" አላቸው።

በገቡት ቃል ኪዳን መሰረትም ቢንያሚንን ከአባታቸው እቅፍ አውጥተው ከከንዓን ምድር ነዋሪዎች ጋር ጉዞ ወደ ግብፅ ከመጀመራቸው በፊትያዕቁብ ልጆቹን ነጥሎ፦" ልጆቼ ሆይ! ባንድ በር አትግቡ፤ ግን በተለያየ በሮች ግቡ፤ ከአላህም (ፍርድ) በምንም አልጠቅማችሁም፤ (አልመልስላችሁም)፤ ፍርዱ የአላህ እንጅ የሌላ አይደለም፤ በርሱ ላይ ተመካሁ፤ ተመኪዎችም ሁሉ በርሱ ብቻ ይመኩ" ብሎ መከራቸው።

በከንዓን እና በግብፅ መሀከል ያሉትን በረሃማ እና አሸዋማ መንገዶችን ካቋረጡ በኋላ የዩሱፍን ታናሽ ወንድም ይዘው ቤተ መንግስት ገቡ።

ዩሱፍም ከመጀመርያው በተሻለ መልኩ ካስተናገዳቸው በኋላ ታናሽ ወንድሙን ለግል አውጥቶ፦"እነሆ እኔ ወንድምህ ነኝ ይሠሩት በነበሩትም ሁሉ አትቆጭ" ብሎት ነገ እሱን ግብፅ ሊያስቀረው የንጉስ ዋንጫ በሱ ከረጡት እንደሚሸጉጥበትም ጨምሮ ነግሮት ለአዳር ወንድሞቹ ጋ አቀላቀለው።

ጠዋትም ለጉዞ በተዘጋጁ ግዜ ዩሱፍ እቃዎቻቸውን አስጭኖላቸው ሸኛቸው።ብዙም ሳይርቁም ዩሱፍ እና ወታደሮቹ ከአንድ ኮረብታ ላይ ሆነው፦" እናንተ ባለ ግመሎች ሆይ! እናንተ በርግጥ ሌቦች ናችሁ" በማለት ተጣሯቸው።

እነሱም ዞረው፦" ምንድነው የጠፋችሁ?" አሉ።

ዩሱፍም፦" ፦ የንጉሡ መስፈሪያ ጠፍቶናል፤ እርሱንም ላመጣ ሰው የግመል ጭነት ሽልማት አለው፤ እኔም በርሱ ተያዥ ነኝ" አላቸው።

እነሱም፦" በአላህ እንምላለን በምድር ላይ ለማጥፋት እንዳልመጣን በእርግጥ ዐውቃችኋል፤ ሌቦችም አልነበርንም" አሉት።

ዩሱፍም፦" ውሸታሞች ብትሆኑ ቅጣቱ ምንድነው?" አላቸው።

እነሱም፦"ቅጣቱ (በያዕቆብ ሕግ) ዕቃው በጓዙ ውስጥ የተገኘበት ሰው (ራሱን አገልጋይ አድርጎ መወሰድ) ነው፤ እርሱም ቅጣቱ ነው። እንደዚሁ በደለኞችን እንቀጣለን" ብለው መለሱለት።

(ፍተሻውን) ከወንድሙም ዕቃ በፊት በዕቃዎቻቸው ጀመረ፤ ከዚያም (ዋንጫይቱን) ከወንድሙ ዕቃ ውስጥ አወጣት።ሁሉም ደነገጡ ሚሉት ጠፋባቸው በዚህ አጋጣሚ እራሳቸውን ለማዳን፦"እሱ ቢሰርቅ ምንም አይደንቅም አንድ ታላቅ ወንድሙም እንዲህ ይሰርቅ ነበር" አሉ።

ዩሱፍም በውስጡ፦"እናንተ ሥራችሁ የከፋ ነው፤ አላህም የምትሉትን ሁሉ ዐዋቂ ነው" አለ።

ከዚያም እነሱ ራሳቸው በተስማሙት መሰረት እቃውን የሰረቀውን ቢንያሚንን ዩሱፍ እና ወታደሮቹ ይዘውት ሊሄዱ ሲሉ፦"አንተ የተከበርከው ሆይ! ፦ ለርሱ(ለቢንያሚን) በእርግጥ ትልቅ

ሽማግሌ አባት አለው፤ ስለዚህ በርሱ ፋንታ አንደኛችንን ያዝ፤( ይህን ከፈፀምክ) እኛ ከመልካም ሠሪዎች ሆነህ እናይሃለንና" አሉት።

ዩሱፍም፦"ዕቃችንን እርሱ ዘንድ ካገኘነው ሰው ሌላን ሰው ከመያዝ በአላህ እንጠበቃለን፤ እኛ ያን ከፈፀምን በእርግጥ በዳዮች ነን" አለ። ዩሱፍንም ለምነው ለምነው ተስፋ ሲቆርጡ ወደ ጎን ነጠል ብለው መመካከር ጀመሩ።

በመሀልም ታላቅ ወንድማቸው፦" አባታችሁ በናንተ ላይ ከአላህ የሆነን መታመኛ ቃል ኪዳን በእርግጥ የያዘባችሁ መሆኑን ከዚህም በፊት በዩሱፍ ላይ ግፍ የሠራችሁትን አታውቁምን? ስለዚህ አባቴ ለኔ እስከሚፈቅድልኝ ወይም አላህ ለኔ እስከሚፈርድልኝ ድረስ የግብፅን ምድር አልለይም፤ እርሱ ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነው።

ወደ አባታችሁ፣ ተመለሱ፤ እንዲህ በሉትም፦ አባታችን ሆይ! ልጅህ ሰረቀ ባወቅነውም ነገር እንጂ አልመሰከርንም፤ ሩቁንም ነገር (ምስጢሩን) ዐዋቂዎች አልነበርንም፤ ያችንም በውስጧ የነበርንባትን ከተማ ያችንም በውስጧ የመጣነውን ባለ ግመል ጓድ ጠይቅ፤ እኛም በእርግጥ እውነተኞች ነን በሉ" ብሏቸው እነሱን ትቶ ወደ ከተማይቱ ገባ።

እነሱም ምንም አማራጭ አልነበራቸውምና የጫኑትን እህል ጭነው ወደ ከንዓን ተጓዙ።ልክ ከንዓን ሲደርሱ አባታቸው መንገድ ላይ እየጠበቃቸው ነበር።

ሁሉንም ሰላም ብሎ የልጁ ቢንያሚንን መምጣት በጉጉት ሲጠብቅ ቢንየሚን የውሀ ሽታ ሆነበት።ልጄስ ብሎ ሲጠይቃቸውም የሆነውን ሁሉ ነገሩት።

ይህን ግዜ አባታቸው በተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ሆኖ፦"አይደለም ነፍሶቻችሁ አንዳች ነገርን

ለናንተ ሸለሙላችሁ፤ (ሠራችሁትም) መልካምም ትዕግሥት (ማድረግ) አለብኝ፤ እነርሱን፣ (ሦስቱንም ልጆቼን) የተሰበሰቡ ሆነው አላህ ሊያመጣልኝ ይከጀላል፤ እነሆ እርሱ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና"

አላቸው።
ያዕቁብም ከአጠጋባቸው ዘወር ብሎ፦" በዩሱፍ ላይ ዋ ሐዘኔ!" እያለ የድሮውን ዩሱፍን በማስታወስ ይንሰቀሰቅ ጀመር።

እነርሱም ፦ "በአላህ እንምላለን፤ ለጥፋት የቀረብክ እስከምትሆን ወይም ከጠ ፊዎቹ እስከምትሆን ድረስ፣ ዩሱፍን ከማውሳትአትወገድም" አሉ።

ያዕቁብም፦"ጭንቀቴንና ሐዘኔን የማስማው፣ ወደ አላህ ብቻ ነው፤ ከአላህም በኩል የማታውቁትን ነገር ዐውቃለሁ" አላቸው።

ቀን ቀንን እየተካ ቀስ በቀስ ልጆቹ ከግብፅ ይዘው የመጡት ቀለብ አለቀ።ቤተሰቡም አደጋ ላይ ወደቀ። ይህን ግዜ ያዕቁብ ልጆቹን ሰብስቦ፦

"ልጆቼ ሆይ! ሂዱ፤ ስለ ዩሱፍና ስለ ወንድሙም ፊንጭ ሰብስቡ፤ ከአላህም እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፤

እነሆ ከአላህ እዝነት ከሐዲዎች ሕዝቦች እንጂ፣ ተስፋ አይቆርጥም" አላቸው።



እነሱም አባታቸው ባላቸው መልኩ ዩሱፍን እና ወንድሞቹን ፍለጋ ወደ ግብፅ ምድር ለሶስተኛ ግዜ ብቅ አሉ። ዩሱፍ ዘንድም በመግባት፦

" አንተ የተከበርከው ሆይ!

እኛንም ቤተ ሰቦቻችንንም ጉዳት ደረሰብን፤ ርካሽ ሸቀጥም ይዘን መጥተናል፤ ስፍርንም ለኛ ሙላልን፤ በኛም ላይ መጽውት አላህ መጽዋቾችን

ይመነዳልና" እያሉ ሲማፀኑት...

ክፍል 4 ይቀጥላል...

#share
@alahu_akber1