'
•••✿❒ ነብዩሏህ ሉጥ ዐለይሂ ሰላም ❒✿•••

#ክፍል 1

★ የሉጥ ሕዝቦች ነብያቸውን በምድር ላይም ብልሹነትን አነገሱ፥ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፦

وَلُوطًا إِذْ قَالَلِقَوْمِهِۦٓ أَتَأْتُونَ ٱلْفَـٰحِشَةَ وَأَنتُمْ تُبْصِرُونَ ﴿٥٤﴾ أَئِنَّكُمْ لَتَأْتُونَ ٱلرِّجَالَ شَهْوَةًۭ مِّن دُونِ ٱلنِّسَآءِ ۚ بَلْأَنتُمْ قَوْمٌۭ تَجْهَلُونَ ﴿٥٥﴾
“ሉጥንም ለሕዞቦቹ ባለ ጊዜ (አስተውስ) እናንተ የምታዩ ስትኾኑ ጸያፍን ነገር ትሠራላችሁን።

እናንተ ከሴቶች አልፋችሁ ወንዶችን ለመከጀደል ትመጣላችሁን በውነቱ እናንተ የምትሳሳቱ ሕዝቦች ናችሁ። (አን-ነምል፥ 54-55)

እነዚህ ሕዝቦች በምሥራቃዊ ዮርዳኖስ ይኖሩ ነበር።

ይህ ቦታ በሙት ባህር አቅራቢያ ይገኛል። በአካባቢው አምስት መንደሮች ነበሩ። እነሱም;- “ሰዱም፣ ዑመራ” “አደመህ” “ሱወይም” “ባሊ’ዕ” ናቸው።ሉጥ (ዐ.ሰ) በዋናው መንደር ሰዱም ይኖሩ ነበር። መጥፎና ርካሽ ተግባራትን ትፈፅም የነበረችውም መንደር እሷ ነች።

የሰዱም ነዋሪዎች እርኩሶችና መጥፎ ከመሥራት የማይፈሩ ነበሩ። አስፀያፊ ተግባራቸውን በግልጽ የሚፈጽሙበት መሰብሰቢያ ቦታ ነበራቸው። መንገደኛን ይዘርፋሉ። ከሌላ አካባቢ ነጋዴዎች ከመጡ ተሰብስበው ዕቃቸውን ይቀማሉ።

የሉጥ ሕዝቦች ነፍሳቸውንም በእጅጉ የሚበድሉ እጅግ ቆሻሾች ነበር።ካቆሻሻነታቸው የተነሳ በፆታ ግንኙነት ከሴት ይልቅ ወንድ ከወንድ ጋር መገናኘት ይመርጡ ነበር።

እነዚህ ሰዎች መጥፎ ተግባራቸው ወሰን ያለፈ ስለሆነ ይህ አስፀያፊ ተግባር ወደ ሌሎችም አካባቢዎች እንዳይዛመት እነሱን በማስተካከል ወይም በማጥፋት ይህን መጥፎ ተግባራቸውን ማስወገድ የግድ ነበር። ምክንያቱም ሲባል ነው።

#የሉጥ_ጥሪ

★ ሉጥ (ዐ.ሰ) ሕዝቦቻቸው የሚሠሩትን አስፀያፊ ነገር ሲያዩ የወገኖቻቸው በዚህ ሁኔታ መገኘት አሳሰባቸው።

ሥነ-ምግባራቸው እንዲስተካከል በማሰብም ምክር መለገስ ጀመሩ። የሉጥ ጥሪ ሥነ-ምግባራቸው በጅጉ ለተበላሹና ቀልባቸው ለደረቀ ሰዎች የሚደረግ በመልካም ተግባር ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል ነበር።

እነዚህ ሰዎች ምንም ሐያእ /ሐፍረት/ የሌላቸውና አስጸያፊ ወንጀልን በጠራራ ፀሐይ የሚፈፅሙ ነበሩ።

ከዚህም በላይ ሴት በማግባት አላህ የፈቀደላቸውን ግንኙነት መፈጸም ትተው ከወንዶች ጋር በመገናኘት ማንም አድርጎት የማያውቀውን አስጸያፊ ተግባር ይፈፅሙ ነበር።

ስለዚህም አላህ (ሱ.ወ) ሉጥ (ዐ.ሰ) ወደ እነዚህ ሕዝቦች ሄደው ከቆሻሻ ተግባራቸው እንዲፀዱ ጥሪ እንዲያደርጉላቸው ላካቸው።

ሉጥ (ዐ.ሰ) የነበዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) የወንድም ልጅ ሲሆኑ በኢራቅ ባቢል ነበር የተወለዱት።

ነቢዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ወደ ተውሂድ ጥሪ ሲያደርጉ አምነው ከሳቸው ጋር ወደ ሻም አካባቢ ስደት በመሄድ በምሥራቅ ዮርዳኖስ በሚገኘው ሱዲም ሸለቆ አካባቢ ሰፈሩ።በአካባቢው ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት የምትፈጽስም ሰዱም የምትባል መንደር ነበረች።

አላህ (ሱ.ወ) ነቢዩላህ ሉጥን ወደ ሰዶምና አካባቢዋ ሕዝቦች፣ አላህን ብቻ እንዲያመልኩና ከመጥፎ ተግባራቸው እንዲርቁ ለማስተማር ና

ወንድ ለወንድ ግንኙነት መፈጸማቸውን ትተው አላህ የፈቀደላቸውን ሴቶቻቸውን በማግባት ግንኙነት እንዲፈፅሙ እንዲያዟቸው አላህ ሉጥን ላካቸው።ይህ ዓይነቱ ወንጀል ከሰዶም ሕዝቦች በፊት ማንም ያልሠራው አስጸያፊ ወንጀል ነበር

إِذْ قَالَ لَهُمْ أَخُوهُمْلُوطٌ أَلَا تَتَّقُونَ ﴿١٦١﴾ إِنِّى لَكُمْ رَسُولٌ أَمِينٌۭ ﴿١٦٢﴾ فَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ﴿١٦٣﴾

“አትጠነቀቁምን? እኔ ለናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝ። አላህንም ፍሩ። ታዘዙኝም” (አሽ-ሹዐራእ፥ 161-163)

አሏቸው። እንዲሁም ሉጥ እያዘኑላቸው ለዘብ ባለ ቃል!

وَمَآ أَسْـَٔلُكُمْ عَلَيْهِ مِنْ أَجْرٍ ۖ إِنْ أَجْرِىَ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّ ٱلْعَـٰلَمِينَ﴿١٦٤﴾

“በርሱም ላይ ምንም ዋጋ አልለምናችሁም። ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጅ በሌላ አይደለም።” (አሽ-ሹዐራእ፥ 164) በማለት አስገነዘቧቸው።
በዚህ ቃላቸው ውስጥ ሉጥ (ዐ.ሰ) ከነሱ ዓለማዊ ጥቅም እንደማይሹና ብቸኛው ፍላጐታቸው የነሱ መስተካከልና አላህን ብቻ ማምለካቸው እንደሆነ አስረዷቸው።

በመቀጠልም ሉጥ (ዐ.ሰ) ወደነዚህ ሰዎች አስፀያፊ ተግባር በመዞር የሚከተለውን ተናገሯቸው።

وَلُوطًا إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِۦٓ أَتَأْتُونَ ٱلْفَـٰحِشَةَوَأَنتُمْ تُبْصِرُونَ ﴿٥٤﴾ أَئِنَّكُمْ لَتَأْتُونَ ٱلرِّجَالَ شَهْوَةًۭ مِّن دُونِ ٱلنِّسَآءِ ۚ بَلْأَنتُمْ قَوْمٌۭ تَجْهَلُونَ ﴿٥٥﴾ ۞

“ሉጥንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስተውስ) እናንተ የሚታዩ ስትኾኑ ጸያፍን ነገር ትሠራላችሁን። እናንተ ከሴቶች ወንዶችን ለመከጀል ትመጣላችሁን በውነት እናንተ የምትሳሳቱ ሕዝቦች ናችሁ። (አን-ነምል፥ 54-55)

የሰዶም ሰዎች አስፀያፊ ተግባራቸውን በግልጽና በስብሰባ ቦታዎች ሁሉ ሳይቀር መፈጸማቸው ሉጥን በጣም አሳዘነ።
ሉጥ (ዐ.ሰ) ከዚህ አስፀያፊ ተግባር ቢከለክሏቸውም «አንተ ሴቶችን አስተናግድ ወንዶችን ተውልን።»በማለት አስፀያፊ መልስ ሰጧቸው።

ይህ ሁሉ ቢሆንም ነቢዩላህ ሉጥ (ዐ.ሰ) ተስፋ ባለመቁረጥ የተለያዩ ማስረጃዎችን በመጥቀስ ጥሪያቸ እውነት መሆኑን ሊያሳምኗቸው ሞከሩ።

ነገር ግን ድካማቸው በከንቱ ነበር። ቀናት ወራትን ወራት ዓመታትን እየተኩ ዘመኑ ሄደ። ሉጥም ዳዕዋቸውን ቀጠሉ። ነገር ግን ከቤተሰባቸው ውጭ አንድም ሰው አላመነላቸውም ነበር። ከቤተሰባቸውም ውስጥ ሚስታቸው አላመነችም ነበር።

ከከሓዲያን ጐን ተሰለፈች። ይህም ሁኔታ ሉጥ (ዐ.ሰ) ከቤታቸው ውጭ ከሓዲያንን፣ በቤት ውስጥ ደግሞ ከሓዲት ሚስታቸውን መታገል አስገደዷቸው።ስለሆነም በጣም ድካም ይሰማቸው ነበር። ቢሆኑም ግን ትዕግስት እያደረጉ ያለ መሰላቸት ወደ አላህ ጥሪ ማድረጋቸውን ቀጠሉ።

ሕዝባቸው ግን ማመናቸው ቀርቶ በዳዕዋቸው በማላገጥ “ከእውነተኞቹ እንደ ሆንክ የአላህን ቅጣት አምጣብን።
” (አል-ዐንከቡት፥ 29)

ሉጥ (ዐ.ሰ) ሕዝባቸው ቢቀልዱባቸውም ታግሰውና ችለው አሁንም ማስተማራቸውን ቀጠሉ። ከሓዲያኑ የሰዶም ሕዝቦች ሉጥ ላይ ማፌዛቸውንና ማስቸገራቸውን አጠናክረው ቀጠሉ።

ሉጥ (ዐ.ሰ) በአላህ (ሱ.ወ) እንደሚጠበቁ በመዘንጋት የሰዶም ሕዝቦች ሊያጠቋቸው ሞከሩ። ሉጥንና ቤተሰባቸውን በመናቅም።

وَمَا كَانَ جَوَابَ قَوْمِهِۦٓ إِلَّآ أَن قَالُوٓا۟ أَخْرِجُوهُممِّن قَرْيَتِكُمْ ۖ إِنَّهُمْ أُنَاسٌۭ يَتَطَهَّرُونَ ﴿٨٢﴾
“ሉጥንና ተከታዮቹን ከከተማችሁ አውጧቸው። አሉ። እነሱ፡ የሚጥራሩ ሰዎች ናቸውና።” (አል-አዕራፍ፥ 82)

አሉ።የሰዶም ሕዝቦች ቆሻሾች ስለነበሩ ነቢያቸው ሉጥ «ከመጥፎ ነገር ተመለሱ። በተመሳሳይ ፆታ መካከል ግብረ ሥጋ ግንኙነት አትፈጽሙ።»

ብለው ሲመክሯቸው በሉጥና ተከታዮቻቸው ንፁህነት በመቀለድ “እነሱ ንፁሃን ናቸው” ሲሉ አሾፉባቸው።

★ ሉጥ (ዐ.ሰ) ሕዝባቸው ቢቀልዱባቸውም ታግሰውና ችለው አሁንም ማስተማራቸውን ቀጠሉ።


ክፍል 2 ይቀጥላል....

#share
@alahu_akber1