Adebabay Media
4.44K subscribers
1.47K photos
53 videos
37 files
1.47K links
በወገንተኝነት፣ በጊዜአዊ ጥቅም እና አጋርነት ብቻ የሚደረግ ወደ አንድ ወገን ያጋደለ ጋዜጠኝነት ጥቅም እንደሌለው በመረዳት ዕውቀትና መረጃ ላይ የተመረኮዘ፣ ነባራዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበ፣ ሀገርንና ወገንን በመጥቀም ላይ የተመሠረተ ሁሉን አቀፍ ባለ ብዙ ቋንቋዎች ሚዲያ፤ ቤተሰባችን ስለሆኑ እናመሰግናለን። በFacebook/YouTube (@adebabaymedia) ይመልከቱን። www.adebabay.com
Download Telegram
"በዓሎቻችን ≠ አደጋ"??????
==============
(ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ)
የዚህን ዓለም የጨለማ አሠራር እና በዓለም ላይ የሚደረጉትን የሥነ ልቡና ጦርነቶች ለማይገነዘብ እነዚህ ዜናዎች ተራ ዜናዎች ናቸው። ነገር ግን ደመራው ጥምቀቱ በመጣ ቁጥር ለብዙ ዓመታት ሲሠራብን የነበረውን ተንኮልና የአዕምሮ አጠባ ለሚገነዘብ የዜናዎቹ ዓላማ ግልጽ ነው። ይህም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በዓላትን ከ "አደጋ" ጋራ አስተካክሎና አመሳስሎ በሰው ሕሊና የመቅረጽ ዘመቻ (PsyOp) ነው።

የትኛው የቤተ ክርስቲያናችን በዓል ነው ለሀገርና ለሕዝብ አደጋ ሆኖ የሚያውቀው? ላለፉት ሺህ ዓመታት በዓሏን በሰላም ስታከብር የኖረችን ቤተ ክርስቲያን ዛሬ የመጣ ትውልድ ነው የሚያስተምራት?

የሚዲያ ተቋሞቻችን ይህንን ተንኮል መገንዘብ አለባቸው። ዜና የሚዘገበው በቆሙለት ዓላማ አንጻር እንጂ በተቃዋሚ ቡድን አንጻር አይደለም።

በዓሎቻችን መንፈሳዊ በዓላት እንጂ አደጋዎች አይደሉም።
ካህን በወንጀል ከተገኘ ክህነቱ ምን ይሆናል?
======
(ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ)
አንድ ካህን በተከሰሰበት ወንጀል "ወንጀለኛ" (በዚህ ሀገር አነጋገር Convicted felon) ሆኖ ከተገኘ ሥልጣነ ክህነቱ ምን ይኾናል?
======
ማስታወሻ፦ ቀሲስ በላይ በተከሰሱበት የባንክ የማጭበርበር ክስ ወንጀለኛ መሆናቸውን ፍርድ ቤት የወሰነ ሲሆን ፍርዱ ግን ለሌላ ጊዜ ተቀጥሯል።

"የፌደራሉ ፍርድ ቤት፣ ከአፍሪካ ኅብረት የባንክ ሂሳብ 6 ሚሊየን 50 ሺሕ ዶላር በሐሰተኛ ሰነድ ለማውጣት ሞክረዋል ተብለው በተከሰሱት ቀሲስ በላይ መኮንንና ግብረ አበሮቻቸው በእያሱ እንዳለ፣ በረከት ሙላቱ፣ ዓለምገና ሳሙኤል እና የኒሞና ንግድ ስራ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሥራ አስኪያጅ በኾኑት አበራ መርጋ ላይ የጥፋተኛነት ውሳኔ መስጠቱን ፋና ሜዲያ ዘግቧል። ሦስቱ የችሎቱ ዳኞች በሙሉ ድምጽ ቀሲስ በላይ ጥፋተኛ ናቸው በማለት የወሰኑ ሲኾን፣ በእያሱና በረከት ጥፋተኛነት ላይ ግን አንድ ዳኛ በውሳኔ እንደተለዩ ዘገባው ጠቅሷል። ዓለምገና እና አበራ ፖሊስ ፍርድ ቤት ሊያቀርባቸው ባለመቻሉ፣ ክሳቸው ቀደም ሲል ተቋርጧል። ችሎቱ በሦስቱ ጥፋተኞች ላይ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ለጥር 22 ቀጥሯል ተብሏል።"
[ዋዜማ ሬዲዮ]
======
ጊዜ ያልፋል። በእግዚአብሔር እና በቤተ ክርስቲያን ላይ የድፍረት ቃል መናገር። ጊዜ ሰጠኝ ብሎ አምላክን የሚያሳዝን ተግባር መፈጸም፤ ካህን ከሆኑ በኋላ ኢሬቻን በመሰለ የሌላ እምነት (ዋቄፈና) ሥርዓተ አምልኮ ላይ መገኘት፣ ለሌሎች የዋኅ ምእመናን መሰናከል መሆን ምንም ጥቅም የለውም።
======
"አትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና" (ወደ ገላትያ ሰዎች 6፥7)
የተወደዳችሁ ምእመናን ወምእመናት፤
ቅዳሜ ገሐድ ስለሆነ ጾም ነው:: እንዳይረሣ!!!!
==========
ጥምቀት ረቡዕ/ዐርብ ባይውልም ዋዜማው (ጾመ ገሃድ) ይጾማል።
=======

ጾመ ገሃድ/ጋድ
------
ገሃድ ማለት ለውጥ ወይም ልዋጭ ማለት ነው። በርግጥ የቃሉ ፍቺ ከዘይቤው ጋር አይገናኝም። ይህ ማለት “ገሃድ” የሚለውን ቃል ቀጥተኛ ትርጉም ከተመለከትን “ግልጥ” ማለት ነውና። ለምሳሌ በግልጽ ለማለት በገሃድ እንላለን። የቃሉን ፍቺ በዚህ ገትተን ወደ ጾምነቱ ስንመለስ ቤተ ክርስቲያናችን ከሏት አጽዋማት አንዱ “ጾመ ገሃድ” መሆኑን እናገኛለን።
-----
የገሃድ ጾም የሚጾመው በጥምቀት ዋዜማ ብቻ ነው። አንዳንድ ሰዎች ግን ባለማወቅ የልደትን ዋዜማም “ገሃድ” ብለው ይጾማሉ። ነገር ግን የልደት (ገና) ዋዜማ መጀመሪያውኑ በጾመ ነቢያት ውስጥ ያለ በመሆኑ ድርብ ጾም የለምና ለብቻው አይጾምም።
-----

በተለምዶ ግን ጾመ ነቢያትን ሳይጾሙ ቆይተው ዋዜማዋን ብቻ የሚጾሙ አሉ። ጾመ ገሃድ ግን የጥምቀት ዋዜማ ብቻ መሆኑን መረዳት ይገባናል።
-----
ጥምቀት ረቡዕና ዐርብ በሚውሉበት ጊዜ ቀድመው ያሉት ማክሰኞና ሐሙስ የፍስክ ቀንነታቸው ወደ ጾምነት ተለውጦ ይጾማሉ። በነሱ ለውጥ ጥምቀት የሚውልባቸው የጾም ቀናት (ረቡዕና ዐርብ) የፍስክ ቀን ሆነው ይከበራሉና።
------
ገሃድ የረቡዕና ዐርብ ለውጥ ነው ብለናል። ነገር ግን ጥምቀት በሌላም ቀን ቢውል የጥምቀት ዋዜማ ይጾማል። በዓለ ጥምቀት እሑድ ቢውል ቅዳሜ ጥሉላት አይበላም።
-----
ጥምቀት ሰኞ ቢውል እሑድ ጥሉላት አይበላም። እንደሌሎች የአጽማዋት ቀናት እህልና ውሃ ግን አይጾሙም። አንዳንድ ሰዎች ግን ጥምቀት ሰኞ ሲውል ከቅዳሜና እሑድ አዋጥተው በመጾም ቅዳሜና እሑድ ጥሉላት አይበላባቸውም ይላሉ።
——
ነገር ግን “ገሃድ” አንድ ስለሆነ (ስንክሳር ጥር 10 “ሰላም ለዕለት ዋሕድ ዘስሙ ገሃድ” እንዲል) ጥምቀት ሰኞ ሲውል ቅዳሜን መጾም አጉል የገባ ልማድ ነው።
------

(ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ገጽ 130።)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከዚህ በኋላ በተፈጥሮና በእግዚአብሔር ፍጥረት ላይ የተጀመረው አመጽ አደብ ሊገዛ ይችል ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ዛሬ በዓለ ሲመታቸውን የፈጸሙት አዲሱ ባለ2ኛ ዙር ፕሬዚዳንት አቶ ትራምፕ፤ "የምናውቀው ሁለት ጾታ ብቻ ነው፤ ወንድ እና ሴት ብቻ!" ብለዋል። እግዚአብሔር ይህቺን መጠጊያ የሆችንን፣ ልጆቻችንን ያፈራንባትን ሀገር፣ ሀገረ አሜሪካን 🇺🇸 በሰላም፣ በጤና ይጠብቅልን።
(ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ)
ከኒውዮርክ ሀገረ ስብከት የተላከልን የፕሮግራም ማስታወቂያ
========
አቡነ ጴጥሮስ ይጣራሉ!!!!
====
Topic: Responding to the Social Crisis in Ethiopia
Time: Jan 20, 2025 08:00 PM Eastern Time (US and Canada)

Join Zoom Meeting
https://us06web.zoom.us/j/81190505414?pwd=LqNkFJkT5hN6ALqV5YmbmkBh5UQQpf.1

---

One tap mobile

+16465588656,,81190505414#,,,,*665105# US (New York)
+16469313860,,81190505414#,,,,*665105# US

---

Dial by your location
• +1 646 558 8656 US (New York)
• +1 646 931 3860 US
• +1 309 205 3325 US
• +1 312 626 6799 US (Chicago)
• +1 301 715 8592 US (Washington DC)
• +1 305 224 1968 US
• +1 386 347 5053 US
• +1 507 473 4847 US
• +1 564 217 2000 US
• +1 669 444 9171 US
• +1 689 278 1000 US
• +1 719 359 4580 US
• +1 720 707 2699 US (Denver)
• +1 253 205 0468 US
• +1 253 215 8782 US (Tacoma)
• +1 346 248 7799 US (Houston)
• +1 360 209 5623 US
=====
Meeting ID: 811 9050 5414
Passcode: 665105
የፕሬዚዳንት ትራምኘ ንግግር ትርጉም (በአማርኛ)
======
(ተርጓሚ መምህር አቤል ጋሼ)
47ኛ ትላንት የአሜሪካ ው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ቃለ መሐላ ሲፈጽሙ የተናገሩት ንግግር በጣም የሚገርም ነበር። በመጪው 4 ዓመታት በዚህ በአሜሪካም በአለም ዙሪያም: ብዙ ለውጥ የምናይ መሆኑን የሚጠቁም ኃይለኛ ንግግር ነው፡ ፡ በዚህ ፕሬዚዳንት ዘመን የሚሆኑትን ነገሮች ላጤነ የሚከተሉት የፖለቲካ የማኅበራዊ የሚሊታሪና የኢኮኖሚ ክንውኖች ን መሰረታዊ ለውጥ የሚጠይቁ ይሆናሉ : :
ያስደሰተኝ አንድ ሐረግ :- ከዚህ በኋላ የአሜሪካ መንግሥት ፖሊሲ የምናውቀው ሁለት ፆታ ነው፡ ፡ ወንድ ና ሴት ::

ስለ ሁሉም ነገር ይኸ ንግግር በአማርኛ ተተርጉሞ ይዘቱ ለሁሉም ይደርስ ዘንድ ... እነሆ :

የትርጉም ስህተትና ማስተካከል ካለው በቅድሚያ ይቅርታ እየጠየቅን የማሻሻያ አስተያየት ያዳብረናል ... እርማት ካለ ይላኩልን ...እናሻሽለዋለን ::

https://drive.google.com/file/d/1b0ehpISH5SiYlWLOXM-0Oo-4wmDO91nR/view?usp=drivesdk
የኘ/ት ትራምፕ ንግግርና ፖሊሲ ማንን ያስደስታል? ማንን ያስደነግጣል?
=====
አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዓለ ሲመታቸውን ፈጽመዋል፣ በዚያው ቀን 200 የሚሆኑ ፕሬዚዳንታዊ እግዶችንና መመሪያዎችን አስተላልፈዋል። በዕለቱ ያደረጉት ንግግርም በጣም የተለየ እና አነጋጋሪ ሆኗል። የመንግሥት ሠራተኞችን፣ የጥገኝነት ጥያቄ ያቀረቡ ወገኖችን ወዘተ በተመለከተ የይዟቸው አቋሞች አያሌ ወገኖቻችንን አስጨንቋል። በነዚህ ጉዳዮች ዙሪያ የፕሬዚደንቱን ንግግር ወደ አማርኛ የተጎመው ባልደረባችን አቤል ጋሼ እና ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ ዝግጅታቸውን ያቀርባሉ። (** ዛሬ 8 pm በዲሲ ሰዓት)

======
https://www.youtube.com/live/J6BvAG5PpLI?si=HuL_Wel0r-k0upBb
ለልጅ "አዶናይ" የሚል ስም ማውጣት ተገቢ ነው?
=====
(ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ)
"አዶናይ" የሚለው ከዕብራይስጡ "አዶን" የሚል ቃል የወጣ ሲሆን አዶን ማለት "ጌታ" ማለት መሆኑን ሊቁ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመዝገበ ቃላቸው ነግረውናል። "አዶኒ" ሲሆን ጌታዬ (እግዚእየ)፤ አዶኒም ሲሆን ደግሞ "ጌቶቼ" (አጋዕዝትየ) ማለት ይሆናል።

** "ከመ ዝ ይቤ አዶናይ እግዚአብሔር" (ትንቢተ ሕዝቅኤል 2፥4) ተብሎ ለአምላክ ሲቀጠል የአምላክ ስም ይሆንና ምሥጢሩ ምሥጢረ ሥላሴ ነውና፣ አንድነትን መደብ አድርጎ ሦስትነትን ያሳያል። ዘይቤውም "ጌቶቼ እግዚአብሔር እንዲህ አለ" ያሰኛል። ይቤ (አለ) የሚለው አንድነቱን፣ እግዚአብሔር የሚለው ባሕርየ መለኮቱን፤ አዶናይ የሚለው ደግሞ አካላቱን (በአካል ሦስት/ ብዙ መሆኑን) ያመለክታል። ይህም ሊታወቅ ኢሳይያስ የሱራፌልን ምሥጋና ሦስት ጊዜ ቅዱስ ከተናገረ በኋላ "ወሰማዕኩ ቃሎ ለአዶናይ እንዘ ይብል መነ እፌኑ ወመነ የሐውር ለነ ኀበ ዝ ሕዝብ። ወእቤ ናሁ አነ ፈንወኒ" ይላል። (ኢሳይያስ 6፥ 1)
** (አዶናይ የሚለውን የኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ተመልከት።)
=====
** አይሁድ "ያህዌ" የሚለውን የእግዚአብሔር ስም በሙሉ አፋቸው አይጠሩም። መጽሐፋቸው "ያህዌ" ሲል እነርሱ ግን "አዶናይ" ብለው ያነብባሉ። ታላቅ አክብሮት።
======
** በዚህ የአምላክ ስም የሚጠሩ ብዙ ሰዎች ገጥመውኛል። ትልቅም ትንሽም። ይህ ተገቢ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ?

** እስቲ እንማማርበት።
ጥር 18፤ ዝርወተ አጽሙ ለቅዱስ ጊዮርጊስ
========
እንኳን ለልዳው ፀሐይ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ በዓል አደረሰን፤ አደረሳችሁ!!!
++++
(መ/ር ጌታቸው በቀለ እንደጻፉት)
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሰዓታት በተባለው መንፈሳዊ ድርሰቱ “ፀሐይ ዘልዳ፣ ኮከብ ዘልዳ፣ ዘልዳ ንጉሥ ነዓ ጊዮርጊስ- የልዳው ፀሐይ፤ የልዳው ኮከብ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆይ ና” በማለት ታላቅ ምስጋና ያቀረበለት ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ በዘመነ ሰማዕታት ስለ እግዚአብሔር በመመስከሩ፣ በማስተማሩ፣ አምልኮተ ጣዖትን በማጥፋቱ ከንጉሡ ዱድያኖስና ሰባ ነገሥት እጅግ አሰቃቂ ዘግናኝ የሆኑ ፀዋትወ መከራዎች ተቀብሏል፡፡ ነገሥታቱ ሰማዕቱን ገደልነው ብለው ሥጋውንና አጥንቱን ፈጭተው ዐመድ አድርገው ከረጅም ተራራ ላይ ቢበትኑትም፤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን ወደ ሥጋው መልሷት ዳግም አሥነሣው፡፡ ይህ የሆነው ጥር 18 ቀን ነው፡፡ ይህንንም ቀን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን “ዝርወተ ዐጽሙ” ስትል ሰማዕቱን አዘክራ ትውላለች፡፡ ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡
“መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌም፣ በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ” በማለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያት በተናገረው ቃል መሠረት በሃይማኖት ምክንያት መከራ እየተቀበለና ስለ ክርስቶስ እየመሰከረ በግፍ የተገደለ ሰው ሰማዕት ተብሎ ይጠራል፡፡ ቃሉ ከግእዝ ወደ አማርኛ ሲተረጎም ሰማዕት ማለት ምስክር ማለት ነው፡፡ ይህ የቅድስናና የክብር ስም የሚገኘውም እንዲሁ በከንቱ ሳይሆን ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ከብዙ ተጋድሎና ፈተና በኋላ ነው፡፡ /ሐዋ ሥራ. ፩፥፰፤ ፳፪÷፳፮/፡፡ ከእነዚህ ሰማዕታት አንዱ በየዓመቱ የሰባት ዓመት ተጋድሎውና የዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል በስሙ በታነጹ አብያተ ክርስቲያት ሁሉ በታላቅ ክብር የሚከበርለት የልዳው ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ግምባር ቀደም ሆኖ የሚጠቀስ ነው፡፡
“የልዳው ፀሐይ፣ የልዳው የምሥራቅ ኮከብ”
======== ቅዱስ ጊዮርጊስ ወላጅ አባቱ አንጣስዮስ (ዘሮንቶስ) የሚባል ሲሆን እናቱ ደግሞ ቴዎብስታ በመባል ትታወቃለች፡፡ የአባቱ አገር በዚያን ጊዜው አጠራር “ቀጰዶቅያ” የሚባል ሲሆን የእናቱ አገር ደግሞ ልዳ ተብሎ ይጠራል፡፡ ይህ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሰባት ዓመት ተጋድሎውን ፈጽሞ ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ በተለየና ዘለዓለማዊ ዕረፍትን ባረፈ ጊዜ ሥጋው ያረፈው በዚሁ በልዳ በተሠራች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው፡፡ ስለዚህም ቅዱስ ጊዮርጊስ “የልዳው ፀሐይ፣ የልዳው የምሥራቅ ኮከብ” እየተባለ ይጠራል፡፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሰዓታት በተባለው መንፈሳዊ ድርሰቱ “ፀሐይ ዘልዳ፣ ኮከብ ዘልዳ፣ ዘልዳ ንጉሥ ነዓ ጊዮርጊስ” በማለት የዘመረለትና ታላቅ ምስጋናም ያቀረበለት ይህንኑ መነሻ በማድረግ ነው፡፡ ትርጉሙም “የልዳው ፀሐይ፤ የልዳው ኮከብ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆይ ና” ማለት ነው፡፡
ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ የተወደለበት ዘመን ዘመነ ሰማዕታት ሲሆን ያ ዘመን ብዙ ክርስቲያኖች በመከራ የተፈተኑበትና ስለክርስትና ሃይማኖት ብዙ ዋጋ እየከፈሉ ሕይወታቸውን ለሞት የሰጡበት ዘመን ነበር፡፡ በዚያም ዘመን ያንን አገር የሚመራውና የሚያስተዳድረው “ዱድያኖስ” የሚባል ከሐዲና ጣዖት አምላኪ የሆነ ንጉሥ ነበር፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ አባት ዞሮንቶስ በዱድያኖስ ቤተ መንግሥት ታላቅ ሹመት ተሰጥቶት ሲያገለግል ከቆየ በኋላ ከዚህ ዓለም በሞት ስተለየና በዚያን ዘመንም አባት ሲሞት ልጁ በሥራው የመተካት መብት ስለነበረው የሃያ ዓመት ዕድሜ የነበረው ወጣቱ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስም በአባቱ ሹመት ተተክቶ ለመሥራት ወደ ንጉሡ በሔደ ጊዜ ንጉሥ ዱድያኖስ በቤተ መንግሥቱ ጣዖት አቁሞ ለጣዖት ሲሰግድና ሕዝቡንም ሁሉ እያስገደደ ለጣዖት እንዲሰግዱና ጣዖት እንዲያመልኩ ሲያደርግ በማግኘቱ ይህንን እኩይ ተግባር በመቃወም ገና በሃያ ዓመት ዕድሜው የሰማዕትነት ተጋድሎውን ጀመረ፡፡
የሰማዕቱ ተጋድሎ
=======
በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነትና በእግዚአብሔር ላይ ባለው የፀና እምነት መሠረትም የዚህ ዓለም ተድላና ደስታ ከንቱ መሆኑን በመገንዘብ ያለውን ሀብት ሁሉ ለድኆችና ለምስኪኖች በመስጠት ሹመቱንና ሽልማቱን በጠቅላላ የዚህን ዓለም ክብር ሁሉ በመናቅ ከንጉሡ ከዱድያኖስና ሰባ ነገሥት በመባል ከሚታወቁት ኃያላን ጋር ተጋድሎውን ቀጠለ፡፡ የዚህ ዓለም ከንቱ ነገር ሁሉ በእሱ ዘንድ ፈጽሞ የተናቀና የተጠላ ከመሆኑ የተነሣ ለሥጋዊ ሕይወቱም ሳይሳሳና ሳይፈራ በንጉሡ ፊት ቆሞ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምን እውነተኛ ክርስቲያን መሆኑን እየገለጠና እየተናገረ ስለእውነተኛው አምላክ መመስከርና ማስተማርያ ይገኛል። (ይቀጥላል) ....
ንጉሡና የእሱ ተከታዮች የሚሰግዱለት ጣዖትም ምንም ምን ማድረግ የማይችል ደካማ ፍጡር መሆኑን በሚገባ ከአስረዳ በኋላ ሰማይና ምድርን፣ የሚታየውንና የማይታየውን ሁሉ የፈጠረውን እውነተኛውን አምላክ እንዲያመልኩና ለእሱም እንዲሰግዱ እያስተማረ የንጉሡን ሚስት ንግሥቲቱን ሳይቀር ሕዝቡን ሁሉ በማሳመን የሰማዕትነት ተግባሩን ቀጠለ፡፡ ከሐዲውና ጣዖት አምላኪው ዱድያኖስ በአምልኮ ጣዖት የፀና፣ እውነተኛውን አምላክ እግዚአብሔርንም የካደ ከመሆኑ የተነሣ እሱ ቃሉን ሰምቶ በእውነተኛው አምላክ ማመን ሲገባው በተቃራኒው ቅዱስ ጊዮርጊስ እሱ ለሚያመልከው ጣዖት ቢሰግድና በእሱም ጣዖት ቢያመልክ ከአባቱ የበለጠ ሹመትና ክብር እንደሚሰጠውና ከእሱም ቀጥሎ ባለው የመንግሥት ሥልጣን ላይ እንደሚያስቀምጠው ደጋግሞ ቃል በመግባት ያባብለው እንደነበር ስለቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋድሎ በተጻፈው መጽሐፈ ገድል በሰፊው ተጽፎ ይገኛሉ፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን የእግዚአብሔርን እውነተኛ አምላክነት፣ ከሀላፊነቱንና ኃያልነቱን በሚገባ ያወቀ ከመሆኑም በላይ የዚህን ዓለም ከንቱነት ከልብ የተረዳ ስለሆነ የንጉሡ የዱድያኖስ ቃል አለታለለውም፣ ጊዜያዊ ሹመትና ሽልማትም አልማረከውም፡፡ እንዲያውም ሰባት ዓመት ሙሉ ተጋድሎውን በመቀጠል እጅግ አሰቃቂና ዘግናኝ የሆኑ ፀዋትወ መከራዎችን በመቀበል የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ምስከር ሆኖአል፡፡ ብዙ አስደናቂ ተአምራትንም በማድረግ ብዙ አሕዛብን በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያምኑ አድርጓል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስም በዱድያኖስና በሰባ ነገሥታት ፊት በቆመ ጊዜ በዚያም የተቀመጡባቸው የዕንጨት ወንበሮች ነበሩ፡፡ ቅዱሱንም እሊህን የተቀመጥንባቸውን ወንበሮች እንዲበቅሉ እንዲአብቡና እንዲአፈሩ ታደርጋቸው ዘንድ ከአንተ እንሻለን አሉት፡፡ በዚያን ጊዜ ጸለየ፤ እንዳሉትም አደረጋቸው፤ ይህንንም ድንቅ ሥራ አይተው በርካቶች በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ፡፡ ከሃዲው ንጉሥ ዱድያኖስ ግንድ አምጥተው ቅዱስ ጊዮርጊስን በግንዱ ላይ እንዲቸነክሩት አዘዘ፤ በላዩም ላይ ሰም አፍስሰው እሳት እንዲያነዱበት አደረገ፡፡ ከዚያም ቅዱሱን ወስደው በጐድጓዳ ብረት ምጣድ ውስጥ አበሰሉት፡፡ አቃጥለው፣ አሳርረው ሥጋውንና አጥንቱን ፈጩት፤ አንጀቱ ሁሉ ወጥቶ ከምድር ላይ እስኪዘረገፍ ድረስ አሰቃዩት፡፡ በዚህም ነፍሱ ከሥጋው ተለየች፡፡ የሰማዕቱን ሥጋ አቃጥለው ፈጩት አመዱንም በቀፎ አድርገው ይድራስ ወደሚባል ተራራ ላይ በተኑት “ደብረ ይድራስ” ማለት ምድረ በዳ የሆነ ቦታ ነው፡፡ ጌታችንም የሰማዕቱን ነፍሱን ወደ ሥጋው መልሷት ደግሞ አስነሣው፡፡ ወደ ነገሥታቱም ተመልሶ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰበከ፡፡ በርካታ አሕዛብም ይህንን ታላቅ ተአምራት አይተው አምነዋል፡፡ በኋላም በሰማዕትነት አልፈዋል፡፡ ይህ የሆነው ጥር ፲፰ ቀን ነው ይህንንም ቀን “ዝርዎተ አጽሙ” ስትል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰማዕቱን አዘክራ ትውላለች፡፡ በስሙ በታነጹለት አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ ታቦተ ሕጉ ውጥቶ በደማቅ ሥነ ሥርዐት ተከብሮ ይውላል፡፡

የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ አማላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን፡፡ አሜን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
======
ዋቤ መጻሕፍት፡-
✍️ መጽሐፍ ቅዱስ
✍️ ገድለ ቅዱስ ጊዮርጊስ
✍️ መጽሐፈ ሰዓታት
✍️ መጽሐፈ ስንክሳር
"የቤተ ክርስቲያንን መብትና ጥቅም ለማስከበር እና የሕግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በጥብቅ እየተሠራ ነው"
========
ጥንታዊት፣ ታሪካዊትና ዓለም አቀፋዊት የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎቷን ለማስፋፋት በምታደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ሁሉ የሌሎችን መብትና ጥቅም ባለመንካት በትዕግሥትና በማስተዋል የምትጓዝ፣ አገራዊ ኃላፊነት የሚሰማት፣ ሰላምን አብዝታ የምትሰብክ መንፈሳዊት ተቋም መሆኗ ይታወቃል።

ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓተ አምልኮዋን ለማስፋፋት በተጓዘችባቸው አያሌ ዓመታት አገራችን ኢትዮጵያ የራሷ ፊደላትና የራሷ የቀን አቆጣጠር ባለቤት እንድትሆን ያስቻለች፣ በሊቃውንቷ የመጠቀ እውቀት አማካኝነት የሥነ ጥበብ፣ የሥነ ሥዕል፣ የዕጽዋትና የጠፈር ምርምርና ጥናቶችን በማከናወን ተጨባጭ ውጤቶችን ለዓለም ያበረከተች ጥንታዊት ተቋም ስለመሆኗም አያሌ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል።

ይሁን እንጂ ይህች ለአገረ መንግስት መመስረትና መጽናት፣ ለእውቀት መስፋፋት፣ ለአብሮነት መጎልበት፣ ትውልድን በሥነ ምግባር ቀርጻ ፍቅርና አንድነትን በተግባር የሰበከች እናት ቤተ ክርስቲያን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ አካላት መብትና ጥቅሟን የሚነኩ፣ በአስተምህሮዎቿ፣ በዕምነቷ፣ በንዋያተ ቅድሳቷ ላይ መሠረታቸውን ያደረጉና ትዕግስቷን የሚፈታተኑ ክብርና ሉአላዊነቷን የሚዳፈሩ እኩይ የትንኮሳ ተግባራት እየተፈጸመባት ይገኛል።

ስለሆነም በተደጋጋሚ እየተፈጸሙባት የሚገኙትን እነዚህን እኩይ ተግባራት ከዚህ በላይ በዝምታና በትዕግስት ማለፍ መንፈሳዊ ተልዕኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ የሚያደርጋት ከመሆኑም በላይ መብቷን በእጅጉ የሚጋፋ፣ ጥንታዊያን አባቶች ለሥርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ ሲጠቀሙባቸው የነበሩና በትውልድ ቅብብሎሽ አሁን ያለው ትውልድ የተረከባቸው ንዋያተ ቅድሳቷን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ከመፈጠሩም በላይ በሥርዓተ አምልኮዋ ላይ በማላገጥ በምዕመናን ዘንድ ቁጣ እንዲቀሰቀስ የሚያደርጉ በርካታ ተግባራት እየተፈጸሙ በመምጣታቸው ምክንያት እነዚህ እኩይና ጸብ አጫሪ ተግባራት ሕጋዊ እልባት እንዲያገኙ ማድረግ የግድ የሚልበት ደረጃ ላይ ደርሳለች።

ስለሆነም ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ ማጥናት፣ መከታተልና ሕግን መሠረት ያደረገ መፍትሔ እንዲያገኙ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘችው ወቅታዊ ሁኔታውን በዝርዝር በማጥናት ተቋማዊ እልባት የሚያገኝበትን መንገድ የሚያጠና ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ እንዲገባ ያደረገች ሲሆን የቤተ ክርስቲያናችን የሕግ አገልግሎት መምሪያም በሕግ አግባብ ተጠያቂነትን በማረጋገጥ ፍትሕ ማግኘት የሚቻልበትን ሁኔታ ለመፍጠር አስፈላጊውን መረጃ በማሰባሰብና በማደራጀት ክስ መመስረት የሚያስችለውን ሁኔታ በማመቻቸት ወደ ተግባር ለመለወጥ በዝግጅት ላይ ይገኛል።

ከዚህ ጎን ለጎንም ከፍ ሲል እንደተገለጸው በጠቅላይ ቤተ ክህነት ከሚገኙ መምሪያዎች መካከል ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን መምሪያዎች በማካተት የተቋቋመው ኮሚቴም ዝርዝር ጥናቶችን በሚገባ በማጥናትና ችግሮቹን ለይቶ ከመፍትሔ ሀሳብ ጋር በአጭር ጊዜ ውስጥ በማቅረብ በቤተ ክርስቲያኒቱ ማዕከላዊ አስተዳደር አማካኝነት ተቋማዊ አቋም የሚወሰድበትና በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ የማያዳግም መፍትሔ የሚሰጥበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የሚያስችል ሥራ በመሥራት ላይ መሆኑን እየገለጸች በሁለቱም ዘርፎች የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተ በተከታታይ ለሕዝበ ክርስቲያኑ እንዲገለጽ የምታደርግ መሆኑን ከወዲሁ እያስታወቀች በጉዳዩ ዙሪያ ሙያዊ ድጋፍ ለመስጠት ፈቃደኛ የሆኑ ምዕመናንና ምዕመናት በተቋቋመው ኮሚቴ አማካኝነት የሚደረግላቸውን ጥሪ ተቀብለው ለቤተ ክርስቲያናችን መብት መከበር የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ እናት ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታቀርባለች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
ጥር ፲፯ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
=====

++++ አደባባይ ሚዲያን ለማግኘት ..... +++
👉 በ YouTube
https://www.youtube.com/adebabaymedia
👉 በቲክቶክ
https://adebabaymedia
👉 በ Facebook
https://facebook.com/adebabaymedia
👉 በ Telegram
https://t.me/adebabaymedia
👉 በ Twitter
https://twitter.com/adebabaymedia

አደባባይ ሚዲያ፦ የሁላችን ስለሆነች ኢትዮዽያ!!!
የቅ/ፓትርያርኩ የሰላም ጥሪ ከምን ደረሰ?
=======
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የስደትና የመከራ ጊዜ ላይ መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ይህም ሆኖ በችግሩ መካከልም ቢሆን ተስፋ ሰጪ የሆኑ ምልክቶችን ፈንጠቅ ማድረጉ አልቀረም። በሀገሪቱ ያለው ጦርነት እልባት እንዲያገኝ ቅዱስ ፓትርያርኩ ያደርጉትን ጥሪ ብዙዎች በበጎ ጎኑ ተመልክተውታል። አምርረው የተቹትም አሉ። ይሁን እንጂ ጥሪው የተላለፈላቸው ወገኖች ግን የዝኆን ጆሮ ይስጠን ብለው ዝም ማለትን መርጠዋል። ለምን?

በሌላም በኩል በቤተ ክርስቲያናችን ላይ በይፋ እና በአደባባይ የሚፈጸመው ክቡረ ነክ የፕ*ሮ*ቴ*ስታንት ቤተ እምነት አማኞች ተግባር እንደቀጠለ ነው። ይህም በግላቸው ብቻ የሚያደርጉት ሳይሆኑ በመሪዎቻቸው እና በሰባኪዎችቸው ደረጃም ያለ ነው፡፡ በተወሰነ ደረጃ በጥምቀት ሰሞን በታቦታት ላይ ያላገጡ ሰዎች መያዛቸውን አይተናል። ነገር ግን ሁሉም ሕግ ፊት ይቀርባሉ ወይ? ቅጣትስ ያገኛሉ ወይ? የሚለው ገና መልስ አላገኘም። የፕ*ሮ*ቴ*ስታንት መሪዎች ይህንን ዕብደት እንዴት ማስቆም አቃታቸው የሚለውም ጥያቄያችን ነው። የዛሬ ዝግጅታችን በዚህ ላይ ያተኮረ ይሆናል።

ዛሬ ረቡዕ በዲሲ ሰዓት 8 PM ላይ ።
======
https://www.youtube.com/live/hP3LatAGYcQ?si=CElzzXD3ptKVcGR7
የረቡዕ ዝግጅት (8pm DC Time)
======
የቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ፣ ነገረ መለኮትና ሥርዓተ አምልኮ በእንግሊዝኛ
የቀሲስ ዶ/ር አምሳሉ ተፈራ መጽሐፍ ሲዳሰስ
+++
ስለ ሃይማኖታችን በእንግሊዝኛ ጥንቅቅ ብለው የተጻፉ መጻሕፍት በብዛትና በጥራት ባለመኖራቸው ምክንያት በውጪው ዓለም የተወለደ ልጆቻችን ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ለማወቅ ብዙ ይቸገራሉ። ይህንን ችግር ከሚቀርፉ መጻሕፍት መካከል ደግሞ ቅዳሜ በዋሽንግተን ዲሲ ደብረ ምሕረት ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አዳራሽ የሚመረቀው የቀሲስ ዶ/ር አምሳሉ ተፈራ መጽሐፍ አንዱ ነው:: የዛሬ ዝግጅታችን በዚህ መጽሐፍ ዙሪያ ከደራሲው ጋራ ውይይት የምናደርግበት ነው::

https://www.youtube.com/live/2fUCM9hrKJQ?si=cFaBdmOPgXcySR59
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተላለፈ የምህላ ሱባኤ
======
የብፁዕ_አቡነ_ጴጥሮስ_የነነዌ_መልእክት.pdf
545.1 KB
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ፣ የቅ/ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ጾመ ነነዌን አስመልክተው ባስተላለፉት መልእክት ""የዛሬዋ ነነዌ ኢትዮጵያ መሪዎች ልብ ገዝተው ወይም ራሳቸው ማቅ እስከለብሱና እስኪመለሱ ወይም ደንዳና ልባቸው ጎርፍ ሆኖ እንደ ፈርዖንና እንደ ሔሮድስ እንዲሁም ዲዮቅልጥያኖስ ይዟቸው እስኪሔድ ድረስ ተጋድሏችን ይቀጥላል። ተጋድሏችን ከሥጋና ከደም ጋር አይደለም።" ብለዋል።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"እመቤቴ የአምላክ እናት" የሚለው መዝሙር (በልሳነ ኮንሲቲ)
=====
የኮንሶ ብሔረሰብ ድንግል ማርያምን በቋንቋው ሲያመሰግናት።
==========
"ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ይሉኛል" የተባለው ይፈጸም ዘንድ ግድ ነው።
======
(ምንጭ:- ከKune Demelash kassaye -Arba Minch የፌስቡክ ገጽ የተገኘ)