This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፕሬዚዳንት ዘሌንስኪ የዩክሬይን ኦርቶዶክስ አባቶችን በቤተ ክርስቲያናቸው እንዲህ አስደርጓቸው ነበር። ሌሎች ቪዲዮዎችን ራሳችሁ ጉግል አድርጋችሁ ማየት ትችላላችሁ ። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጦርነት አንፈልግም ፣ ሰላም ነው የምንፈልገው ማለታቸው ለዩክሬይን ሕዝብና ለራሲያ ሕዝብ ትልቅ ዜና ነው::
የአድዋ ድል ሰሞን እንደመሆኑ፣ በጠላቶቻችን ባለመሸነፋችን ካተረፋናቸው ቅርሶቻችን መካከል ስለሆኑት "ስለ ስሞቻችን" ጥቂት ብንጨዋወት ምን ይመስላችኋል? የዛሬ 15 ዓመት ግድም የጻፍኩትን አጠር ብሎ ረዘም ያለ፣ መካከለኛ ርዝመት ያለው ጽሑፍ ልጋብዛችሁ።
"ምኒልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ፣
ኡምቤርቶ ነበር ስምህ ይህን ጊዜ ሐበሻ።" 🤔
(** ዓመታት ያለፉት ጽሑፍ እንደመሆኑ አሁን ያለንበትን ወቅት ያላገናዘቡ ጉዳዮች ቢገኙበት በትዕግሥት እለፉኝ።)
========
የስም ነገር .....
=======
(ከቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ)
አሜሪካ የራሷ የስም አሰጣጥና አጠራር ያላት የምትገርም ሀገር ናት። አሜሪካ ረዥም ስም አትወድም። አሜሪካ ሰዎች ትቀበላለች ይባል እንጂ ስትቀበል የራሷን ስም አውጥታ ነው። በየዘመኑ ወደ አሜሪካ የመጡ ስደተኛ ሕዝቦች በሙሉ የራሳቸውን ማንነት እና ስም አወጣጥ እንደጠበቁ ነገር ግን መጠነኛ ማሻሻያ በማድረግ ስማቸውን አሜሪካዊ አድርገዋል። “አሌክሳንደር የነበረው አሌክስ፣ ክሪስቲያን የነበረው ክሪስ ወይም “አል” ብለው የሚጀምሩ የተለያዩ ስሞችን በማሳጠር “አል” የሚለውን ብቻ በመውሰድ የራሳቸውን ስያሜ ይፈጥራሉ። (Al Gore/ አል ጎርን ያስታውሷል)። ታዲያ ለአዲሱ ስም ዳቦ አትቆርስም፣ አታስቆርስም። ረዝሞና ረዛዝሞ የተቀመጠ ስም እንዲያጥር በፍቅሯ ታስገድዳለች። ይህንን ሁሉ ማሻሻያ የሚያደርጉት በአብዛኛው በስመ ተጸውዖ (መጠሪያ) ስማቸው ላይ እንጂ በቤተሰባቸው ስም ላይ አይደለም።
በምንኖርበት በዚህኛው የምዕራቡ ዓለም የሚጠቀሱ ሦስት ስሞች አሉ። የመጀመሪያው “መጠሪያ ስም” ወይም “ስመ ተጸውዖ” (Personal Name፣ First Name፣ Given name) ነው። መጠሪያ ስም ወይም ስመ ተጸውዖ በየትኛውም ዓለም የተለመደ ነው። ሁለተኛው ደግሞ በእኛ የስያሜ ባህል የማናገኘው “የመካከል ስም” (Middle Name) የሚባለው ሲሆን እርሱን ተከትሎ የሚመጣው ሦስተኛው ደግሞ “የቤተሰብ ስም” (Family Name፣ surname) ነው። እነዚህ ሁለቱ ማለትም “መካከለኛው” እና ሁል ጊዜም የማይለዋወጠው “የቤተሰብ ስም” የሚባለው በእኛ ባህል ባይኖርም በፈረንጆቹ እና ፈረንጅኛውን ባህል በሚከተሉት ዘንድ ግን ይዘወተራሉ። በባህል ደረጃ ሁለቱ ስሞች የሉንም እንበል እንጂ በጽሑፍ ደረጃ፣ በተለይም ወደ ውጪ አገር ስንሄድ ግን፣ ሁለቱንም ስሞች እንዲኖሩን እየሆንን ነው ማለት ይቻላል። የአባታችን ስም “መካከለኛ ስማችን/ Middle Name”፣ የአያታችን ስም ደግም “የቤተሰብ ስም”/(Family Name፣ surname) እየሆነ ነው።
መንግሥት ያወጣልን ስም :)
=======
ለመጀመሪያ ጊዜ ፓስፖርት ሳወጣ አሁን ያለው አዲሱ ፓስፖርት ሥራ ላይ አልዋለም ነበር። የበፊቱ “ባለካኪ ወረቀቱ” ፓስፖርት ነው የነበረኝ። የድሮው ፓስፖርት ስማችንን በኢትዮጵኛው በደፈናው ደርድሮ ሲያበቃ የትውልድ ቀንን የሚያክል ትልቅ ቁም ነገር ማስቀመጫ ቦታ አልነበረውም። በሄድኩባቸው ሀገራት ሁል ጊዜ የሚያስቸግረው ይኸው የትውልድ ቀን አለመኖር ጉዳይ እንደነበር ትዝ ይለኛል። አንድ ቀን አዲሱን ፓስፖርት የመመልከት ዕድል ገጥሞኝ ስገልጠው የድሮውን ችግር ቀርፎት ነገር ግን የስም አሰጣጡ የእንግሊዝኛውን/ የፈረንጆቹን ባህል የተከተለ ሆኖ ተቀምጦ አገኘኹት። ስም ከነአባትን “Given name”፤ የአያት ስምን ደግሞ “surname” ብሎ ጠቅሶታል።
ይኼ መካከል ያለው “Middle Name” እና “የቤተሰብ ስም” የሚባሉት በእኛ ዘንድ ባይታወቁም አዲስ የወጣው ፓስፖርታችን “በውዴታ ግዴታ” ይህንን ስም ሰጥቶናል። እያንዳንዳችን የአያቶቻችን ስሞች “የቤተሰብ ስም” ሆነው ታድለውናል። በተለይም አሜሪካን በመሳሰለው በውጪው ዓለም ለምንኖረውና “የቤተሰብ ስም” የግድ እንዲኖረን “በውድ ለምንገደደው” የፓስፖርቱ ስም አወጣጥ ለውይይት ይጋብዛል።
በእርግጥ የፈለግነውን ስም ብንይዝ አሜሪካ ግድ የሌላት ትመስላለች። ነገር ግን “የቁርጡ ቀን” ሲመጣ ስም በራሱ መወያያ ሆኖ ቁጭ ይላል። በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሰሞን ራሳቸው ሴኔተር ኦባማም ሆኑ ተቃዋሚዎቻቸው፣ ኮሜዲያን እና የሚዲያ ሰዎች አንዱ የመወያያ ርዕሰ-ጉዳይ አድርገው ይዘውት የነበረው የሴኔተር ባራክ (የቤተሰብ) መጠሪያ የሆነው “ኦባማ” የሚለው ኬኒያዊ ስም ነበር። የስም ነገር ፖለቲከኞቹ በእንደዚህ ዓይነቱ አደባባይ ውሎ የሚያነሡት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ሕጻናቱ ደግሞ በየዕለቱ እርስበርሳቸው ሲጫወቱ እና ሲተዋወቁ ስለ ምንነቱ እና ትርጉሙ የሚከራከሩበትም ነው።
የልጆች ስም የወላጅ ፈተና
=========
በተለይም በስደት ዓለም ላለን ከተለያዩ አህጉራት ለተሰበሰብን መጻተኞች ስማችን ቀላል አንድምታ የለውም። የራሴን ገጠመኝ ላንሳ። አንድ ቀን ልጄ ከትምህርት ቤት ሲመለስ ዱብ ዕዳ የሆነ ጥያቄ ይዞ መጣ። “አባባ ስሜ ይቀየር” አለ። ለምን? ማን ልትባል ፈለግህ? እኮ እንዴት?” ብዬ በኢትዮጵያዊ ወኔም፣ በአባትነት ተደፈርኩ ባይነትም፣ በወንድነትም በሉት (ሴቶች እናዳትቀየሙ) ኮምጨጭ ብዬ ጠየቅኹት። ለምን ላልኩት “ስሜን አያውቁትም”፣ ማን ልትባል ትፈልጋለህ ላልኩት “ጄደን፣ ወይም ጆርዳን” ብሎ አጭር መልስ ሰጠኝ።
ከውስጣዊ ስሜቴ ራሴን ቶሎ ገትቼ ማስረዳት ገባኹ። በሆዴ “አዬ አለማወቅህ” እያልኩ የስሙን ትርጉም፣ እኔና እናቱ ለምን እንደዚያ እንዳልነው፣ እንዴት የተከበረ ስም እንደሆነ አብራራሁለት። አበው “እስመ ስሙ ይመርሖ ሀበ ግብሩ፤ ስሙ ወደ ግብሩ [ተግባሩ] ይመራዋል[ና]” ሲሉ ስምና ግብር፤ ስምና ማንነት ያላቸው ተዛምዶ የተሰናሰለ መሆኑን ሲያጠይቁ የተናገሩት መሆኑን በልቤ እያወጣኹ እያወረድኹ በአቅሙ ሊገባው የሚችለውን ነገር ለማስያዝ ሞከርኩ። የገባው መሰለኝ። ዝም ብሎ ተቀብሎኛል። ግን ጥያቄው ለረዥም ጊዜ ከአእምሮዬ አልወጣም።
“ጆርዳን” የሚባለውን ስም አውቀዋለኹ። ታዋቂ ጆርዳኖች አሉ። ግር አልተሰኘኹም። ይኼ “ጄደን/ Jaden/ Jayden” የተባለውን ስም ገና መስማቴ ነበር። እንኳን ትርጉሙን ላውቀው እስከነስምነቱ ያኔ መስማቴ ነው። ቶሎ ወደ ኢንተርኔት ሄጄ ማንነቱን እና ምንነቱን ፍለጋ ጀመርኩ። ባገኘኹት መልስ የበለጠ ተናደድኹ።
ይህ ስም አሜሪካ-ወለድ የሆነ፣ ትርጉሙ በትክክል ይህ ነው ተብሎ ያልተበየነ፣ ነገር ግን ከ1990ዎቹ መጀመሪያ ጀምሮ በመጠሪያነት በጥቅም ላይ መዋል የጀመረ፣ ታዋቂው የፊልም አክተር “ዊል ስሚዝ” ለልጁ ያወጣለት መሆኑ በአብነት የተጠቀሰ ስም መሆኑን “የሕጻናት ስሞች” ዝርዝር እና ትርጉም ውስጥ አገኘዅ። “ጉድ በል እንትን” የተባለው ደረሰ ማለት አይደለም? ገና አምስት ዓመት ለሞላው ልጅ ይህንን መንገሩ ማደናገር እንጂ ማሳወቅ/ መጥቀም ስለማይሆን ለአቅመ-ዕውቀት እስኪደርስ በአዳር ይዤዋለኹ። ዕድሜ ለንስሐ ዘመን ለፍስሐ ቢያድለኝ ያኔ እነግረዋለኹ። ከገባውና ከተስማማ የራሱን ስም ይጠብቃል፣ ለልጁና ለልጅ ልጁ ያስተላልፋል። የስም-ነገር ቀላል አይደለም።
እኛ ኢትዮጵያውያኑ ብቻ ሳንሆን ሌላውም ዓለም ወደ አሜሪካም ሆነ የራሱ ባህል ወዳልሆነ ቦታ ሲሄድ ተመሳሳይ ችግር ላይ መውደቁ አይቀርም። ከጥቂት ዓመታት በፊት የተጻፈውና ቆይቶም ለፊልምነት የበቃው የሕንዳዊ-አሜሪካዊቱ ደራሲ የ“Jhumpa Lahiri” የሕንዳዊ ቤተሰብ ታሪክን የሚያሳየው “ሞክሼ/Namesake” የተሰኘው ድርሰት ጥሩ አብነት ይሆነናል። (ማንበብ ለሚወዱ መጽሐፉን እጠቁማለኹ። ፊልሙም ግሩም ሆኖ ተሠርቷል።)

መስመር የሳተ የስም አወጣጥ 👈👈
=========
በርግጥ እንኳን ባህር ተሻግረን ሰው አገር ሄደን፣ እዚያው አገራችን ውስጥ ተቀምጠንም ቢሆን የስም አወጣጣችን መስመሩ እየተለየ መሔዱን ለመረዳት ብዙም ምርምር አይፈልግም። ወላጆች የልጃቸው ስም አጠር ብሎ፣ ሲጠሩት አፍ ላይ ደስ-ደስ የሚል፣ ዜማ ያለው፣ ሲያሞካሹት የሚጥም፣ ልክ እንደሚበላ ምግብ፣ እንደሚጠጣ መጠጥ እርካታን የሚፈጥር ዓይነት፣ ከተቻለ ብዙ ሰዎች ያላወጡት እና አዲስነት ያለው እንዲሆን ይጥራሉ። ለዚህ ጥሩ መፍትሔ የሆነው እንደየቤተ እምነቱ ወደሚቀበሉት “ቅዱስ መጽሐፍ” ማተኮር ነው።
የጥንት የኢትዮጵያውያንን ስም አወጣጥ ስንመለከት ሃይማኖት ትልቅ ድርሻ እንደነበረው የታሪክን ሀሁ የሚያውቅ ማንም ሰው ሊገነዘበው ይችላል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ በሃይማኖት የመጣላትን ሁሉ በጅምላ አልተጫነችም። የተቀበለችውን ነገር “ኢትዮጵያዊ” (ethiopianize) አድርጋ፣ አገርኛ ጸጋ አላብሳ፣ የራሷን አሻራ ትታ፣ አገራዊውን ባህል መንግላ ሳትጥል አስማምታ ነው። ከእስልምናውም ይሁን ከክርስትናው ዓለም ያገኘችውን በራሷ መሰለቂያ አጥርታ ነው ያሳለፈችው። በዚህም ምክንያት በቤተ እምነቶች ምክንያት አገራዊ ባህል ከሥሩ ተነቅሎ ሳይጠፋ ዘመናትን ተሻግሮ ለእኛ ሊደርስ ችሏል።
ይህ ትውልድም ይህንን የቆየ ኢትዮጵያዊ አሠራር ቢጠቀምበት ባህሉን፣ ማንነቱን እንደጠበቀ ለልጆቹም የሚያስተላልፍ ይሆናል። እንዲያው “ከዚህ መጽሐፍ ነው ያገኘኹት፣ ከዚያ እምነት ነው የወሰድኹት” እያለ የራሱን ባህል፣ ያውም ከእምነቱ ጋር በምንም መልኩ የማይጋጨውን፣ እያጠፋ ቢሄድ በጦር ሜዳ ያላጣውን ነጻነት በሰላሙ ዘመን በባዶ ሜዳ ሊያጣው ይችላል።
ከመጽሐፍ ቅዱስ የወጣ ስም 👈👈
========
አንድ ቀን ብዙ ሕጻናት ከተሰበሰቡበት፣ የአንዲቱ ልጅ ልደት ከሚከበርበት ቦታ ተገኝቼ ነበር። የልጅቱ ስም “ፍራኦል” ነው። ተሰብሳቢዎቹ የስሙን ትርጉም አላወቁም። አጠገቤ ከተቀመጡት ሰዎች መካከል አንደኛዋ ሌላዋን ትጠይቃለች። “ምን ማለት ነው?”። የምትመልሰው ደግሞ “አይ-ዶን’ኖ፤ ከመጽሐፍ ቅዱስ ያገኙት መሰለኝ” ትላለች። አንዳንዱ ሰው ምንጩን የማያውቀው ስም ሲያገኝ “መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለ ሳይሆን አይቀርም” ማለት ጀምሯል ማለት ነው።
ሴት አያቴ “ወ/ሮ ፊሮ/ፍሮ ሮቢ” (ዘመድ፣ ዘመድነሽ፣ ዘመዴ ለማለት ነው) መሆናቸው የዚህኛውንም ስም መነሻ ቶሎ ለመገመት አስችሎኛል። “በእርግጠኝነት ከመጽሐፍ ቅዱስ አይደለም ምንጩ። ኦሮምኛ መሰለኝ” ብዬ የአያቴን ስም በእማኝነት ከነገርኳቸው በኋላ እርግጠኛ ለመሆን የልጅቱ እናት ከጓዳ ስትወጣ ጠብቀው ጠየቋት። “ፍራኦል/ ፊራኦል ማለት ኦሮምኛ እንደሆነ፤ ከዘመድ በላይ” ወይም ማን-እንዳንቺ-ዘመድ ለማለት ፈልገው እንዳወጡት ነገሩን። ጠያቂዎቹም “ደስ አይልም? ውይ ደስ ሲል” ምናምን ተባብለን አጀንዳችን ቀየርን።
አፍ ላይ ቀለል ያለ ስም? 🫣
========
በእርግጠኝነት ግን ለፈረንጅ አፍ ቀለል ያለ ስም ማውጣት የተለመደ ነው። በሥራ ቦታ የሚያጋጥመንን ላንሣ። ሥራ ቦታ ላይ ስማችን ወሳኝ ነው። ግልጽ ነው። በተለይም እኛ አዲስ መጤዎቹ በምንሠራቸው አነስተኛ ሥራዎች ላይ ከደንበኛም፣ ከሌሎች ሠራተኞችም ጋር አብሮ ለመሥራት ነገሩን ቀለል እንዲያደርገው “አጠር ያለ ስም” መኖሩ አስፈላጊ ነው። ረዥም ስም አሜሪካ ይደብራታል። “አጠር አርገው አቦ” ምናምን ማለቷ አይቀርም። ሙሉነህ፣ ሙሉነሽ፣ ሙሉጌታ፣ ወዘተ ዓይነት ስሞቻችን በሙሉ በአጭሩ “ሙለር” ብለን ደረታችን ላይ እንለጥፋቸዋለን። ዓለማየሁ “አል” ወይም አሌክስ ይሆናል። መሐመድ የሚባሉ ሰዎች “ሞ/ Mo” ተብለው ያጥራሉ። አሜሪካ ስገባ የቀጠሩኝ ኢራናዊ ሰውዬ ለረዥም ጊዜ “ሞ” ሲባሉ ስማቸው መሀመድ መሆኑን ያወቅኹት ዘግይቼ ነው። ከዚያ ወዲህ ብዙ “ሞ”ዎች በየሚዲያው አይቻለኹ። አንዳንድ ስሞች ለማጠር ምንም አማራጭ የማይገኝላቸው ሲሆን ለሥራ ቦታ እንደ ቅጽል ስም ዓይነት (ኩኩ፣ ባቢ ወዘተ ዓይነት) ሲጠቀሙ አይቻለኹ። የመዝገብ ስማቸው ግን ከዚያ ፍፁም የተለየነው። አንዳንድ ጊዜ በሥራ ላይ የምናውቃቸው ሰዎች ትክክለኛ ስመ-ተጸውዖ ወይም መጠሪያ ስማቸው ሌላ ጊዜ ከምናውቀው ፍፁም የተለየ ሆኖ እናገኘዋለን።
ወደ ቀደመ ነገራችን ስንመለስ ለፈረንጅ አፍ የቀለለ ስም ማለት ብዙ ጊዜ ባህላችንን ያልተከተለ ይሆናል። እንግዲህ በቀላሉ ኢትዮጵያዊ ስማችንን እየጣልን ይመስላል። ለምን እንደዚህ እንደሚያደርጉ ወላጆች ምክንያት ለማቅረብ ይሞክራሉ። “ልጃችን የተለየ ስም ካወጣንለት ነገ ችግር ሊገጥመው ይችላል” የሚል አንድምታ አላቸው። ማስረጃ ግን የላቸውም። “የራሳቸው ሳይንሳዊ ትንታኔ” ነው። “አማርኛ ብናናግረው ልጃችን ወደፊት እንግሊዝኛ ለማወቅ ይቸገራል” እንደሚለው ዓይነት ምንም ዕውቀትን ያልተመረኮዘ አባባል ማለት ነው።
ባህል እና ታሪክ ያለን ሕዝቦች ነን። ነገር ግን የባህላችንን እና የታሪካችንን ድልብ እና ያለውን ጥቅም በቅጡ መረዳት ስላልቻልን ልክ ታሪክ እንደሌላቸው ሕዝቦች የራሳችንን እየጣልን የሩቁን ለማግኘት መከራችንን እንበላለን። ምናልባት እንደ ሌሎች አፍሪካውያን ወንድሞቻችን የራሳችንን ሀብት ሙሉ በሙሉ ካላጣን ምናልባት የነበረንን አንረዳው ይሆን?
ትርጉም የሌለው ስም 👈👈
======
የሴት አፍሪካ-አሜሪካውያት ስሞች ሁል ጊዜ ይደንቁኛል። እነዚህ ጥቁር አሜሪካውያት ስማቸውን ከነጮቹ ሴቶች በመለየት የራሳቸው የስያሜ ይትበሃል ዘዴ ይከተላሉ። “ኒኪሻ፣ ኒኪታ፣ ናታሻ፣ አይሻ፣ ነኪያ፣ ለታሻ፣ ሳሻ፣ አዚያ ” ወዘተ የሚሉ የምዕራቡን ዓለም ተለምዷዊ ስም አወጣጥ ያልተከተሉ፣ ከሒንዱ እና ከአፍሪካ እንዲሁም ከአረብኛ ስሞች የሚወስዷቸው ብዙ ስሞች አሏቸው። ከቻሉ ሙሉ ስም ከሌላ ቋንቋ ይዋሳሉ። አሊያም ከሁለት ነገር አዳቅለው አንድ ስም ይፈጥራሉ። ትርጉም ኖረው አልኖረው ደንታቸው አይደለም።
እኛም ወደዚያው እያመራን ይሆን ያሰኘኛል። ዛሬ ዛሬ ትርጉማቸውን ወዲያው ሰምቼ የማላውቃቸው ብዙ የኢትዮጵያ ልጆች ስሞች እሰማለኹ። ምናልባት ይህ “ትርጉሙ በቀላሉ የማይገኝ ስም” ማግኘት ራሱ ይሆናል ምስጢሩ። የድሮዎቹ ስሞችማ ከዚህ በኋላ “የጥንት ስሞች ሙዚየም” ውስጥ ካልሆነ በሕያው ሕጻን ስምነት ጥቅም ላይ ሲውሉ አንመለከታቸው ይሆናል።
ከዓመታት በፊት የሰማኹት አንድ ቀልድ ትዝ አለኝ። ሕጻናት መዋያ ውስጥ፣ ከልጆቹ መካከል አንደኛው ልጅ ስሙ “ኢትዮጵያዊ” ነው። እንደ ሌሎቹ ሕጻናት ዓይነት ‘ዘመናዊ ስም’ አይደለም። እናም ሌሎቹ ልጆች ሲቀልዱበት “የትልቅ ሰው ስም፣ የትልቅ ሰው ስም” አሉት ሲባል፣ ሲቀለድ ሰምቻለኹ። አገርኛው ስም እንዲህ “አድልዎ እና መገለል” እየተፈጸመበት በራሱ ጊዜ ከጨዋታው ሜዳ ውጪ ሊሆን ነው ማለት ነው? ታሪክ ሲለወጥ …
የእኛ Middle name 👈👈👈👈
===============
በውጪ ያለነው ሰዎች ይኼ “ሚድል ኔም” የተባለውንም ነገር መጠቀማችን ካልቀረ ትርጉም ባለው መልክ ለማድረግ ብንሞክር ጥሩ ሳይሆን አይቀርም። ለምሳሌ ያህል ክርስቲያኖቹ ኢትዮጵያውያን ልጆቻቸው በባዕድ አገር አድገው ነገር ግን እምነታቸውን የሚያስታውሳቸው አንድ ቋሚ ነገር ለማስቀመጥ የክርስትና ስማቸውን “ሚድል ኔማቸው” ቢያደርጉት ጥሩ ይመስለኛል።

.... (ከላይ የቀጠለ) .....
ለምሳሌ፤ የልጁ ስም አበበ ቢሆን እና የአባቱ ስም ከበደ ዓለማየሁ ቢሆን፤ ልጁን አበበ ከበደ ዓለማየሁ ከማድረግ እና የአባቱን ስም (ከበደን) ሚድል ኔም አድርጎ በአያቱ ከመጥራት የክርስትና ስሙን መካከል በማስገባት አንድ ቋሚ ነገር ማኖር የሚቻል ይመስለኛል። ልጁ ስመ ክርስትናው ወልደ-ኢየሱስ ቢሆን፤ ስሙ ሲጠራ አበበ ወልደ-ኢየሱስ ከበደ፤ ወይም ሲያጥር አበበ ከበደ ይሆናል ማለት ነው። ልጁም ሲያድግ ስመ ክርስትናውን ለማስታወስ ሳይቸገር ሊዘልቅ ይችላል። በአያቱ ከሚጠራ በአባቱ እንዲጠራ ይሆናል። በሌላው እምነት ያለውን ስለማላውቅ ሐሳብ መስጠት ይከብደኛል።
ለማጠቃለል፦ 👈👈👈
=======
ብርሃኑ ብሥራት (መልአከ ብርሃን ቀሲስ) እንዳዘጋጁትና “የመጠሪያ ስሞች መዝገብ” እንደተባለው መጽሐፍ ዓይነት በብዛት በማይገኝበት በእኛ ዓይነቱ ባህል ውስጥ ለልጅ ስም ማውጣቱ ቀላል ስለማይሆን በዘመኑ ታዋቂ ወደሆነው ማድላቱ የግድ ይሆናል። ትክክለኛውን መርጦ ለማውጣት እኮ የሚናገርና የሚያስተምር አገርኛ ምሑር ማግኘቱም እንዲህ ቀላል አይደለም። አለበለዚያ ወላጆች ከፊልሞች፣ ከድራማዎች፣ ከልቦለዶች፣ ከቴሌቪዥን እና ሬዲዮኖች ያገኙትን ስም ቀለብ ማድረጋቸው አይቀርም። ምዕራባውያኑ በዚህ በኩል ለሕዝባቸው ጥሩ ነገር አስቀምጠዋል። የሕጻናት ስሞችን ዝርዝር እና ትርጉም የሚያትቱ መጻሕፍት እና ድረ ገጾች አሏቸው። ወላጅ የሚፈልገውን ስም ትርጉም በየዓይነቱ መርጦ መመልከት ይችላል። የእኛዎቹም ስሞች በመጽሐፍነት ለመጠረዝ፣ በድረ-ገጽነት በዝርዝር ለመቅረብ “ክብር” ቢበቁ ወላጆች ምርጫ እንዲኖረን በር ይከፍትልናል። ቢያንስ ቢያንስ ሳናውቅ ከመሳሳት ያድነናል።
ይቆየን
=====

https://www.youtube.com/live/upDg-KbfNPI?si=F1j18gbfYE7JRLhY
ቤተ ክርስቲያን የመክፈል ፖለቲካ፣ የዩክሬይን እና የኢትዮጵያ ተመሳስሎ
======
በቅርብ ዘመን ባየናቸው ጦርነቶችና የፖለቲካ ምስቅልቅሎች ውስጥ ዋነኛ ተጎጂዎች የሆኑት ክርስቲያኖች ናቸው።
** ከ1917ቱ የሩሲያ አብዮት ጀምሮ አሁን እየቀጠለ እስካለው የዩክሬይን ፋሲያ ጦርነት ድረስ ትልቁን መስዋዕትነት እየተቀበሉ ያሉት ክርስቲያኖች ናቸው።
** አሜሪካ መር በነበረው በኢራቅ ጦርነት ምክንያት ጥንታውያን የኢራቅ ክርስቲያኖች በሚያሳዝን ሁኔታ ከርስታቸውና ከታሪካዊ ሥፍራዎቻቸው ተነቅለዋል።
** በምዕራቦች የሚታገዝ ኃይል ሦሪያን ሲቆጣጠር ቁጥር አንድ ተጎጂዎች ጥንታውያን የሀገሪቱ ክርስቲያኖች ሆነዋል።
** በኢትዮጵያ እየቀጠለ ባለው የጎሳ ፖለቲካ ትልቁ ዒላማ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ናት። እልቂቱና የመከራው ዶፍ በሚዘገንን ሁኔታ የሚዘንበው ክርስቲያኑ ላይ ነው::
** አውሮፓ ክርስቲያናዊ ማንነቱን ሙሉ በሙሉ ካጣበት ደረጃ ከደረሰ ቆይቷል። ይህ ሁሉ ለምን ተፈጸመ? ይህንን ሁሉ ጸረ ክርስትና ተግባር የሚመራው ማን ነው ብሎ የሚጠይቅ አዕምሮ አለን ይሆን?
** ሌላውን ለጊዜው ብናቆየው እንኳን በዩክሬይን እና በኢትዮጲያ ባለው የአብያተ ክርስቲያናት ጥፋት ዙሪያ ተመሳስሏቸው ላይ ትኩረት አድርገን ዝግጅት እናቀርባለን።

Youtube
- YouTube
Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.
ራሳችንን እንጠይቅ፤
እንዴት እና ለምን የነዚህ ምናምንቴዎች ማላገጫ ልንሆን ቻልን?
=====
"አቤቱ፥ ለሕዝብህ ራራ፥ አሕዛብም እንዳይነቅፉአቸው ርስትህን ለማላገጫ አሳልፈህ አትስጥ፤ ከአሕዛብ መካከል፦ አምላካቸው ወዴት ነው? ስለ ምን ይላሉ?" (ትንቢተ ኢዮኤል 2፥17)

የድሮው ጴ*ን*ጤ እና የአሁኑ የብልጽግና ጴ*ን*ጤ
======
(ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ)
፩. መነሻ፦
የዛሬ ስንት ዓመት ደብረ ብርሃን ላይ የሆነ የጴ*ን*ጤ ድርጅት ሕክምና በነጻ ልስጣችሁ ብሎ ሕዝቡን ጠራ። ሕክምና ፍለጋ የሄደውን ሕዝብ በጾም በሬ አርደው ካልበላህ አናክምህም አሉት። ሕዝቡ ለሕክምና ተጠርቶ መከልከሉ ሳያንስ በግድ ጾሙን እንዲሽር በንቀት መጠየቁ አበሳጭቶት የዘረጉትን ድንኳን አፈረሰው ተባለ። በዚህ የተነሣ የተበሳጨ አሁን ታዋቂ ታዋቂ የሚጫወት ገጣሚ ጴንጤ ልጅ "እናንተ ያልሰለጠናችሁ፣ ወንጌል የማይገባችሁ አሕዛብ ደንቆሮዎች" ብሎ በጽሑፌ ሥር ኮሜንት አደረገ።
ይህ ልጅ ገና ግጥም ለመለማመድ ዳዴ ሲል ጀምሮ አውቀዋለሁ። ታዋቂ እንዲሆን ብዙ ኦርቶዶክሶች ልጆች ሲደግፉት እንደነበር አውቃለሁ። ከኔም ጋራ በውስጥ ብዙ እናወራ ነበር። ጴ* ን* ጤ ይሁን አይሁን ትዝ ብሎኝም አያውቅም ነበር። ያቺ የእምነት ጉዳይ ስትመጣ ግን የማላውቀው ሰው ከውስጡ ከነቀንዱ ብቅ ሲል ገረመኝ።
የብልጽግና መንግሥት ባዘጋጀው የስብከት በዓል ላይ ተመርኩዞ በተነሣው ተቃውሞ ብዙ "ታዋቂ" ጴ*ን*ጤ*ዎች ከነቀንዳቸው ብቅ ሲሉ ያንን ገጣሚ ልጅ አስታወሱኝ። እምነታቸውን ለማስፋፋት ከሆነ ሀገርም፣ ባህልም፣ መከባበርም፣ አብሮ መኖርም ገደል ቢገባ ግድ አይሰጣቸውም። ግን ለምን? ለምሳሌ …
ጴጥሮስ መስፍን የኢሳት አሁን ደግሞ የEMS ጋዜጠኛ ነው። ሁሉንም ያከብራል ብለን እንጠብቀው ነበር። አነቃቂ ንግግር የሚናገረው ዮናስ ከበደ የመንግሥት ባለሥልጣንም ነበር። ፈላስፋ ነው ሲባል ሰምቻለሁ። ሚዛናዊ ይሆናል ብለን እንጠብቀው ነበር። ሁለቱም ዛሬ በክርስቲያኑ ላይ ሲሳለቁ ተመልክተናል።
=========
፪. Empowering ጴ*ን*ጤ*ዎች
ጴንጤዎችን empower የማድረግ ዘመቻ ከ10 ዓመታት በላይ የዘለቀ ጉዳይ ነው። እናውቀዋለን። ኋላ አድጎ የመንግሥትን ሥልጣን ሙሉ በሙሉ ወረሰ። ልክ እንደ እንቦጭ አረም ተስፋፋ። በደቡብ ብቻ ሳይሆን በኦሮሚያና በሌሎችም ክልሎች ጴ*ን*ጤ*ነት የሁሉም ነገር መስፈርት ነው። ልክ በውጪው ዓለም እንዳሉ secret ሶሳይቲዎች ኢትዮጵያን በጥርሱ ውስጥ ማስገባት እና መንግሥት መሆን ችሏል።
ይህ empowered የሆነ የጴ*ን*ጤ ሰብሰብ በተቃዋሚነት ደረጃ ባሉ ፓርቲዎች፣ ሚዲያዎች፣ ማኅበራት ውስጥ በደንብ ተስፋፍቷል። ራሱን መደበቅና ማስመሰል እያቃተው ከነቀንዱ ብቅ የሚለው በዚህ ዓይነቱ አጋጣሚ ወቅት ነው።
ጴ*ን*ጤ*ዎች empower በሚደረጉበት ዘመን ከሥራና የትምህርት ዕድል ጀምሮ በሥልጣን እርከን ላይ እንዲፈነጩ ተደርገዋል። ይህንን ዕድል የሚፈልጉ ካሉም እምነታቸውን መቀየርና የዚህ secret society የሚመስል ድርጅት አባል ለመሆን ነፍሳቸውን እንዲሽጡ ይጠየቃሉ። በቤተ ክርስቲያን የምናውቃቸው ብዙ ወንድም እህቶች ነፍሳቸውን ገብረው ይህንኑ ቡድን ተቀላቅለዋል። በሥልጣን ላይ ያሉ አያሌ የትናንት ኦርቶዶክሶች ማተባቸውን የበጠሱ empowered ጴ*ን*ጤ*ዎች መሆናቸውን እናውቃለን።
========
፫. የብልጽግና ጴ*ን*ጤ*ነት ሁሉንም ጴ*ን*ጤ ይወክላል?
ብዙ ጴ*ን*ጤ ወዳጆች፣ ቤተሰቦች አሉን። በዚህ በአዲሱ secret society መሰል ጴ*ን*ጤ*ነት ውስጥ የሌሉ ብዙ በጎ ሕሊና ያላቸው ጴ*ን*ጤ*ዎች እናውቃለን። ስለዚህ የብልጽግና ጴ*ን*ጤ*ነት ሁሉንም ጴ*ን*ጤ ይወክላል ብለን አናምንም። ነገር ግን የብልጽግናን ጴ*ን*ጤ*ነትን መቃወም ሁሉንም ጴ*ን*ጤ መቃወም እየመሰላቸው ስለሚከፉ እነርሱን ላለማስቀየም ብዙ ጥረት ተደርጓል። ነገር ግን የሚቻል አልሆነም። ነገሩ መስመር አለፈ።
** የብልጽግና ጴ*ን*ጤ*ነት ባህል የለውም። የሰው ባህልም አያከብርም። ደፋርና ባለጌ ነው:: አንተ በምታከብረው እና የተቀደሰ ነው ብለህ በምታምነው ነገር ሲያላግጥ ለከት የለውም።
** ለምሳሌ በጥምቀት ሰሞን በታቦታተ ሕጉ ሲቀልዱ ነበር። በሕግ መጠየቅ አለመጠየቅ ሌላ ነገር ነው። መከባበር ሕግ ስላለ ብቻ የሚፈጠር ነገር አልነበረም። ግን የብልጽግና ጴ*ን*ጤ ደንታ የለውም።
** የቤተ ክርስቲያን ንዋየ ቅድስት (ከበሮ ፣ መቋሚያ፣ ጸናጽል ወዘተ) ልክ እንደ ስማቸው "የተቀደሱ ዕቃዎች" ናቸው። ነገር ግን በየመድረኩና በየአዳራሹ ሲቀልዱበት ቅር አይላቸውም። ምክንያቱም የብልጽግና ጴ*ን*ጤ ስለ ተቀደሱ ነገሮች ደንታው አይደለም።
** የብልጽግና ጴ*ን*ጤ በጴ*ን*ጤ*ነት ውስጥ የተደበቀ ሌላ ጴ*ን*ጤ፣ በኑ*ፋ*ቄ ውስጥ የተደበቀ ሌላ ኑ*ፋ*ቄ ነው። ድንጋይ ካብ ውስጥ እንደተደበቀ እባብ ሌላውን የፕሮቴስታንት ማኅበረሰብ ምሽግ አድርጎ ይነድፍሃል። ነደፈኝ ብለህ ስትናገር ሌላው ፕሬቴስታንት ይቀየማል ። መካከላቸው ያለውን እባብ ከመመልከት በመርዙ የተጎዳኸው ሰው ላይ ይነሱብሃል።
፬. ለብልጽግና ጴንጤ ጥፋት “የራስህን ወገን ተጠያቂ ማድረግ ብቻ” ያዋጣል?
======
በሰሞኑ የብልጽግና ጴንጤ መንግሥታዊ እብደት ብዙ ኦርቶዶክሳዊ ወገን “ይህንን ሁሉ ያመጣብን ቤተ ክህነት ነው፣ የራሳችን አባቶች ናቸው” በሚል ቁጣውን ወደራሱ አባቶችና ወደ ራሱ ተቋማት ሲያዞር ተመልክተናል። ለዚህ ሁሉ ውድቀታችን አጭር መልስ ለማግኘት መጣራችን ራሳችንን satisfy ያደርገን ካልሆነ በስተቀር መልሱ በአጭሩ አባቶችን በመውቀስ እና በመጥላት ብቻ እንደማይገኝ ደፍረን መናገር ይኖርብናል። ጳጳሳትን በመሳደብ፣ በመናቅና ጣት በመጠቆም የብልጽግና ጴ*ን*ጤ*ን ማስቆም ቢቻል እንዴት ደስ ባለን። ግን አይደለም።
ነገሩን ሰፋ አድርገን ለማየት ለምን አንፈልግም? ከቤተ መቅደሱ ጀምሮ አገልግሎታችንን እያረከስን ከእግዚአብሔር መራቃችን ለእግዚአብሔር የለሾች አሳልፎ እንደሰጠን ለምን እንዘነጋለን? አዎ “አክሊል ከራሳችን ወድቋል” (ሰቆቃወ ኤርምያስ 5፥16)። ምናምንቴዎች፤ እግዚአብሔርንም የማያውቁ ሰዎች ሰልጥነውብናል (መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 2፥12)። ለዚህ መፍትሔው ግን የራሳችንን ችግር፣ ተቻችለን፣ በራሳችን ለመፍታት መጨከን ነው። “ችግሩ የሌላ፣ መፍትሔው የእኛ” የሚል የግብዝነት መንገድ የትም አላደረሰንም።
አሁንም ቢሆን ሁሉም የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ከልሒቅ እስከ ደቂቅ ከመናናቅና ከመገፋፋት መንገድ ተመልሶ (ቢያንስ በዚህ ጊዜ እንኳን) ለራሱ ሲል ቁጭ ብሎ መፍትሔ ቢፈልግ ይሻለዋል። ሌላው መንገድ እንደማያዋጣ ተፈትኖ ታይቷል።
በዚህ ረገድ፣ ምዕመናንም ራሳቸውን ቢፈትሹ ጥሩ ነው። የእነርሱ ምንም ኃጢአት የሌለ ይመስል ሌላው ላይ ብቻ ጣት በመጠቆም ቤተ ክርስቲያን ላይ የመጣው መዓት አይመለስም።
=======
፭. የብልጽግና ጴ*ን*ጤ*ነት ለእኩልነት ቦታ የለውም
===========
የብልጽግና ጴ*ን*ጤ*ነት ለእኩልነት፣ ለመቻቻል፣ አብሮ በሰላም ስለመኖር ቦታ የለውም፤ ቁርጥህን እወቅ። አሁን ታንኩም፣ ባንኩም በእጁ ነው። ሀገሪቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ በጎሳ፣ በቋንቋ እና በእምነት የተከፋፈለችበት ዘመን ስለሆነ “ተባብሮ ሊቃወመኝ የሚችል ኃይል የለም” ብሎ ገምቷል። ራሳቸው ኦርቶዶክስ የሆኑ ብዙ ወገኖቻችን የዚህ መንግሥታዊ እምነት ደጋፊዎች ናቸው። ይህንን ቡድን መቃወም የእነርሱን ብሔረሰብ መቃወም አድርገው ይመለከታሉ። ስለዚህ “ይህንን ቡድን ከመቃወም ቢያንስ ዝምታን መምረጥ ይበጃል” ብለው ያስባሉ።

በሌላም በኩል ይህንን የጴ*ን*ጤ ቡድን በመቃወም ስም በጅምላ የጭቃ ጅራፍ የሚሰነዝሩ፤ ራሳቸው ጎጠኛና ጎሰኛ መሆናቸው የማይታያቸው ስመ ኦርቶዶክሶች መኖራቸው የብልጽግና ጴ*ን*ጤ*ውን ቡድን በአያሌው ጠቅሞታል። እነርሱ የሚናገሩትን ሌላውን ወገን ለማነሣሣት ይገለገልበታል። እነዚህ አዳዲስ ጎሰኞች ቢመከሩም አይሰሙም። አልሰሙምም።
ስለዚህ ለራሳችን እንወቅበት። ራሳችንን ከዘረኝነት ኑ*ፋ*ቄ እናውጣ። በሃይማኖትህ ላይ የመጣ አደጋ የትኛውንም ቋንቋ ብትናገር፣ የየትኛውም ብሔረሰብ አባል ብትሆን አይመለስልህም። አንደኛውኑ ነፍስህን ሸጠህ ለነርሱ አገልጋይ እስካልሆንህ ድረስ።
በሀገር ቤት ያለው የያዘው ይዞት አንድ አልሆነም እንበል። በውጪ ዓለም ያለው ለራሱ አንድ ሆኖ መቆም ያቃተው ለምን ጣቱን ይጠቁማል? ለምን አንድ አይሆንም? ለምን አይጠናከርም? ለምን በውጪ ያለውን ሕዝብ ምእመን አያነቃም፣ አያደራጅም? የእናቴ መቀነት ጠለፈኝ ምን ይበጀዋል?
፮. ውጊያው ከሥጋና ከደም ጋር ብቻ አይደለም
==============
ችግሩ ከጥንተ ጠላታችን ከዲያብሎስ የመነጨ ነው። “በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱን አሳብ አንስተውም።” (2ኛ ቆሮንቶስ 2፥11)። ይሁን እንጂ ዲያብሎስ እንዴት እንደሚሸነፍ ቤተ ክርስቲያን አስተምራናለች። በቤተ ክርስቲያን ትምህርት እንሂድ።
በዚህ የጾም ወቅት ጾም ጸሎቱ እያቃጠለው ከየተደበቀበት የማስመስል ዋሻ ተገፍትሮ የወጣውን ክፉ መንፈስ ይኸው በዓይናችን እያየነው ነው። እንዲህ የሚያቅበዘብዘው ለምን እንደሆነ ልንረዳ ይገባናል። መጽሐፍ “አጋንንት ያደሩባቸው ሁለት ሰዎች ከመቃብር ወጥተው [ጌታን] ተገናኙት። እነርሱም ሰው በዚያ መንገድ ማለፍ እስኪሳነው ድረስ እጅግ ክፉዎች ነበሩ” ይለናል (ማቴዎስ 8፥28)።
በጾም ወቅት እየጠበቁ እንዲህ ለያዥ ለገናዥ የሚያስቸግሩት፣ በዚህ የጌታ ጾም ወቅት፣ ስለ ጌታ ሕማማት ክብር ከአገልግሎት እረፍት የምንሰጣቸውን ንዋያተ ቅድሳት መጨፈሪያ የሚያደርጉት፤ የጌታን ሕማም እያሰብን ዕልልታ ሁካታ ጭብጨባ ሳይኖር በርጋታ ነገረ መስቀሉን እያሰብን በጥሙና በምንመላለስበት ወቅት ከተማውን የሚያውኩት በምን መንፈስ እንደሆነ ግልጽ ሊሆንልን ይገባል። አስቀድሞ በመጽሐፍ የተነገረን “ሌላ ኢየሱስ፥ ልዩ መንፈስ ወይም ልዩ ወንጌልመሆኑን ልብ እንበል” (2ኛ ቆሮንቶስ 11፥4)። ይህ ደግሞ “ከእግዚአብሔር አይደለም። ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፤ ይህም እንዲመጣ ሰምታችኋል፥ አሁንም እንኳ በዓለም አለ” (1ኛ ዮሐ. 4፥3)።
========
ይቆየን!!!!
እያየን እንጨምራለን።

ቀሲስ ዶ/ር Mebratu Kiros Gebru ጣትዎን ቁርጥማት አይንካብን። ከዚህ ቀደም ያበረከቱልንን መጽሐፍ በየጊዜው እደጋገምኹ የማነብበው ፣ የመጻሕፍት መደርደሪያ ላይ ሳይሆን ጠረጴዛዬ ላይ የሚቀመጥ ማመሳከሪያዬ ነው። ይህኛውን አዲሱንም አግኝቼ እስካነብበው እቸኩላለሁ።
(በነገራችን ላይ በመጽሐፋቸው ዙሪያ ከቀሲስ መብራቱ ጋራ በወቅቱ ያደርግነው ቃለ ምልልስ ከዚህ ይገኛል።
https://www.youtube.com/live/14ZKk-wakFs?si=eLESTiyOPw9YQR0z)
======
ካልእ መጽሐፍ በእንተ ቅዳሴ
==================
(ቀሲስ መብራቱ ኪሮስ (Ph.D.)
በልዑል እግዚአብሔር ቸርነት "ቅዳሴ፡ ወደ ጌታ ደስታ የመግባት ምሥጢር" በሚል ርእስ በቅዳሴአችን ላይ ሁለተኛ መጽሐፍ ጽፌአለሁ፡፡ በያዝነው ዐቢይ ጾም ለንባብ ይበቃል፡፡ መጽሐፉ በዋነኝነት ለማን እንደተጻፈና የተጻፈበትን ምክንያት ለማወቅ ለቅምሻ ያህል ከሥር ያለውን መቅድም ይመልከቱ፡፡
=====
** ምስጋና
አኰቴተ ቊርባን በሚል ርእስ የታተመው መጽሐፌ አራተኛ እትም አንድ ኮፒ ሲደርሳቸው መጽሐፉን በሚገባ አንብበው፣ “ይህ መጽሐፍ ለቤተ ክርስቲያናችን ካህናት በተገቢው መልኩ መዳረስ አለበት” በሚል መንፈሳዊ ቅንዐት (ተነሳሽነት) አምስተኛው እትም (1000 ኮፒዎች) በራሳቸው ወጪ San Diego, California ውስጥ እንዲታተም ላደረጉትና እርሳቸው በሚያገለግሉበት ሀገረ ስብከት ለሚገኙ ካህናት በሙሉ መጽሐፉን በነጻ በማደል እውነተኛና ወንድማዊ ፍቅራቸውን ያሳዩኝን መልአከ ብርሃን ቀሲስ ማንችሎት ገበየሁን (በአትላንታ የደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ) በምን አይነት ቃላት እንደማመሰግን አላውቅም፡፡ መንፈሳዊ ፍቅርን ለደቀ መዛሙርቱ “አዲስ ትእዛዝ” አድርጎ የሰጠ ጌታ (ዮሐ. 13፡ 34-35) ለቀሲስ ማንችሎት ፍቅረ ቢጽን አብዝቶ እንዲያድላቸውና ባለቤታቸውን ከነልጆቻቸው እንዲባርክላቸው ከመመኘት በስተቀር ከዚህ የተሻሉ ቃላት ማግኘት አልቻልኩም፡፡
ከአኰቴተ ቊርባን መጽሐፍ ሳንወጣ፣ የመጽሐፉን አንድ ኮፒ ስሰጠው “ተጨማሪ መጽሐፎችን መጻፍ አለብህ” ከሚል መልእክት ጋር ለዚሁ ሥራ የሚሆን laptop ገዝቶ ያበረከተልኝን፣ የቶሮንቶ መንበረ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ትጉህና ቅን አገልጋይ የሆነውን ቴዎድሮስ መብራቱን አመሰግናለሁ፤ የበጎ ሥጦታዎች ሁሉ ባለቤት የሆነው ልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቡን በሰማያውያንና ምድራውያን በረከቶቹ ይባርክለት ለማለት እወዳለሁ፡፡
በዚህ መጽሐፍ መቅድም በዝርዝር እንደተገለጸው ለዚህ መጽሐፍ መዘጋጀት ምክንያት የሆኑት ሲሳይ ደምሴ (የበገና መምህር) እና ብሌን ታከለ (ዘቶሮንቶ መንበረ ብርሃን) በያሉበት ምስጋናዬ ይድረሳቸው፡፡ በተጨማሪ፣ ብሌን በምእመናን ቦታ ሆና የመጽሐፉን ረቂቅ በደስታ በማንበብና ገንቢ አስተያየቶችን በፍጥነት በመስጠት ታላቅ አስተዋጽኦ አበርክታለች፡፡ “በጎ ስጦታ ሀሉ፣ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው . . . ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ” ተብሎ እንደተጻፈ (ያዕ. 1፡17) ካሰብነው በላይ በመስጠት ሁሌም የሚያስደንቀን አምላካችን የልቧን መሻት ይፈጽምላት፡፡
የአርጋኖን መጻሕፍት መደብር ባለቤት የሆነው አብርሃም (ክፍሎም) ኃይሉ በቅዳሴ ላይ ሁለተኛ መጽሐፍ የመጻፍ እቅድ እንዳለኝ፣ ነገር ግን የኅትመቱ ውጣ ውረድና የሥርጭቱ ጉዳይ ልቤን እንደሚያዝለው ስነግረው፣ “አንተ ጻፍ እንጂ ለኅትመቱና ለሥርጭቱ እኛ አለን” በማለት ብርታትና ጉልበት ስለሆነኝ በጣም አመሰግናለሁ፤ እንደ አብርሃም ያሉ በጎ እና ቅን አገልጋዮችን ያብዛልን፡፡
በመጨረሻም፣ ለቅዳሴ ልዩ ፍቅር ያላት ውዷ ባለቤቴ ሔለን (ወስመ ጥምቀታ “ፍቅርተ ኢየሱስ”) በቅዳሴ ላይ ሁለተኛ መጽሐፍ እንደምጽፍ ካወቀችበት ጊዜ ጀምሮ፣ ለዚህ መጽሐፍ ዝግጅትና ለተለያዩ የአገልግሎት ጉዳዮች በቶሮንቶ መንበረ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ቢሮ ውስጥ ረጅም ሰዓታትን በማሳለፍበት ወቅት የልጆቻችንን (ዮሐና እና ሳሙኤል) የትምህርት ሂደት በትጋት በመከታተልና የቤታችንን ሸክም በመሸከም አገልግሎቴን ትደግፍ ስለነበር ልትመሰገን ይገባታል፡፡ እነዚህን ሁሉ በረከቶች ላበዛልኝ፣ በምሕሩቱ ባለጸጋ ለሆነው ሕያው አምላካችን ክብር፣ ምስጋና፣ አምልኮና ውዳሴ ይሁን፡፡
=========
** ማውጫ
• መታሰቢያ
• ምስጋና
• መቅድም፡ ምክንያተ ጽሒፍ
• መግቢያ፡ በደስታ የተሰበሰቡ አእላፍ ቅዱሳን
** ክፍል ፩፡ ወደ ቅድስናው ምስጋና የመግባት ዝግጅት
† ቡራኬ 1፡ የሰማያዊ ሠርግ ጥሪ
† ቡራኬ 2፡ ግብአተ መንጦላዕት: የዝግጅት ጸሎት
† ቡራኬ 3፡ ቤተ ልሔም
† ቡራኬ 4፡ ሚ መጠን ግርምት ዛቲ ዕለት
† ቡራኬ 5፡ አግብኦተ ግብር
† ቡራኬ 6፡ አሐዱ አብ ቅዱስ . . .
† ቡራኬ 7፡ በእንተ ቅድሳት
** ክፍል ፪፡ የቃሉ ትምህርት
† ቡራኬ 8፡ የሐዋርያት መልእክታት ምንባብ
† ቡራኬ 9፡ ዝ ውእቱ ጊዜ ባርኮት
† ቡራኬ 10፡ ሠለስቱ ቅዳስያት
† ቡራኬ 11፡ ነዋ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያት
† ቡራኬ 12፡ ፃኡ ንኡሰ ክርስቲያን
† ቡራኬ 13፡ ጸሎተ ሃይማኖት
† ቡራኬ 14፡ ተሐፅቦተ እድ እና አምኃ ቅድሳት
** ክፍል ፫፡ አኰቴተ ቊርባን፡ የአማንያን ቅዳሴ
† ቡራኬ 15፡ አልዕሉ አልባቢክሙ
† ቡራኬ 16: ጸሎተ አኰቴት፡ መቅድመ አኰቴተ ቊርባን
† ቡራኬ 17፡ ከዝማሬ ሱራፌል እስከ ጸሎተ ፈትቶ
† ቡራኬ 18፡ ቅድሳት ለቅዱሳን
† ቡራኬ 19: ነአኵቶ ለእግዚአብሔር ቅድሳቶ ነሢአነ
† ቡራኬ 20: አስተናጽሖ
† ቡራኬ 21: እትዉ በሰላም
• ማጠቃለያ
• መፍትሔ ቃላት (የቃላት መፍቻ)
===========
** መቅድም
ምክንያተ ጽሒፍ
አኰቴተ ቊርባን፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ቅዳሴ መሠረት፣ ታሪካዊ እድገት እና ይዘት የተሰኘው መጽሐፌ የመጀመሪያ እትም ለንባብ ከበቃበት ኅዳር 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ስድስተኛው እትም እስከታተመበት ነሐሴ 2016 ዓ.ም. ድረስ በቃልም ሆነ በጽሑፍ የተለያዩ አስተያየቶች ደርሰውኛል፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓተ ቅዳሴ ላይ ሰፊ ጥናቶች ያደረጉ ሊቃውንት መጽሐፉ በተለይ ለካህናት፣ ለዲያቆናትና ለነገረ መለኮት (theology) ምሁራን ያለውን ጠቀሜታ አውስተውና ጠንካራ ጎኖቹን አድንቀው፣ በተሻለ መልኩ ሊቀርቡ ይገባቸዋል ያሏቸውን ነጥቦች ደግሞ በጽሑፍ እንዲደርሰኝ አድርገዋል፡፡ በርካታ ምእመናን አኰቴተ ቊርባን በቅዳሴ ውስጥ ያለውን የአምልኮ ውበት በማሳየት በአማርኛ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰፋ ባለ መልኩ የተዘጋጀ መጽሐፍ በመሆኑ ደስታቸውን የገለጹ ሲሆን፣ በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴያትና በአገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ በየዘመናቱ የታዩትን የሥርዓተ አምልኮ ሂደቶች የሚያትቱት የመጽሐፉ ሁለተኛና ሦስተኛ ምዕራፎቸ ለካህናት ካልሆነ በስተቀር በቂ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት የሌላቸውን ሰዎች ትኩረት እንዳልሳቡ ሳይሸሽጉ ነግረውኛል፡፡ እንዲያውም መጽሐፉ ውስጥ በየገጹ የሚታዩትን የኅዳግ ማስታወሻዎች (footnotes) እንደ ትርፍ ነገር የቆጠራቸውና - ምንም እንኳን ማብራሪያ የሚያስፈልጋቸው የተወሰኑ ቦታዎች ላይ ሲደርስ ማስታወሻዎቹን ለማየት ቢገደድም - እነርሱን በማንበብ ጊዜ እንዳላጠፋ በግልጽ የነገረኝም ምእመን አጋጥሞኛል፡፡

YouTube
የኢትዮጵያ ሥርዓተ ቅዳሴ፡- ይዘቱ፣ አመሠራረቱና ዕድገቱ
ውይይት በአደባባይ ከቀሲስ ዶ/ር መብራቱ ኪሮስ ጋር
መጠነኛ የንባብ ልምድ ያላቸው ሰዎች ዳጎስ ያሉ መጻሕፍትን ለማንበብ የሚያስችል ትዕግሥት እንደሌላቸው ይታወቃል፡፡ ለቅዳሴ ካላቸው ፍቅር የተነሣ ከላይ የተጠቀሰውን መጽሐፍ ገዝተው ለማንበብ የሞከሩና “ቅዳሴ ምንድን ነው?” የሚል ርእስ የሰጠሁትን የመጽሐፉን የመጀመሪያ ምዕራፍና የቅዳሴን ሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ከመጠነኛ ገላጻ ጋር የሚያስቃኘውን አራተኛውን ምዕራፍ ብቻ ያነበቡ ወገኖች እንዳሉም ሰምቻለሁ፡፡ በተለይ ሲሳይ በገና የተባለ የቤተ ክርስቲያናችን አባል መጽሐፉ በቅዳሴ ላይ ጥናት ማድረግ ለሚፈልጉ ሰዎች ያለውን ግብዐት አምኖበት፣ ነገር ግን በይዘቱ ትልቅ በመሆኑ (ከመግቢያውና መቅድሙ ውጪ 367 ገጾች አሉት) የንባብ ልምድ የሌላቸውን ምእመናን ትኩረት መሳብ ስላልቻለ፣ ምእመናን በቅዳሴ ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ የሚያሳይና ቀለል ባለ መልኩ የተጻፈ ሁለተኛ መጽሐፍ እንዳዘጋጅ በfacebook የላከልኝ መልእክት ይህን መጽሐፍ እንድጽፍ ዋነኛ ምክንያት ሆኗል፡፡ ወንድማችን ሲሳይ የጻፈልኝ የfacebook ምክረ ሐሳብ ይህን ይመስላል፡-
ይህ መጽሐፍ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለማያውቁት ለማስረዳት በቀሲስ ዶ/ር መብራቱ ኪሮስ ለዓመታት በታመቀ እውቀት፣ በእምነትና በቁጭት የተጻፈ መጽሐፍ ሆኖ አገኘሁትና በፍቅር አነበብኩት። መጽሐፉ የጥናትና ምርምር መጽሐፍ በመሆኑ የንባቤ ትኩረት ቅዳሴው ላይ ብቻ ነበር፤ ከአቅሜ በላይ የሆኑትን መንፈሳዊና የታሪክ ጭብጦችን ጠልቄ ልመረምር አልሞከርኩም። መጽሐፉ በአብነትም በዘመናዊ ትምህርትም ተምረናል፣ አውቀናል ብለው ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንንና ቅዳሴን ለሚያቃልሉ አላዋቂዎች ትዕቢታቸውን የሚያስተነፍስ ፍቱን መድኃኒት እንደሚሆን አስተውያለሁ። ቅዳሴን በዚህ ልክ ሰማያዊና ዓለም አቀፋዊ አገልግሎቱን፤ አስፈላጊነቱን፣ ጥቅሙን፣ ክብሩን፣ የቅዳሴ ዓላማና ግቡን አስረድቶ የጻፈ መጽሐፍ ከዚህ በፊት አላነበብኩም። ስለ ቅዳሴ ለማወቅ ይኽን መጽሐፍ ሁሉም ሕዝበ ክርስቲያን ሊያነበው የሚገባ መጽሐፍ ሆኖ ሳለ፣ መጠኑ ትልቅ ስለሆነ በቤት ቁጭ ተብሎ እንጂ ለኪዳንም [ሆነ] ለቅዳሴ ሲሄዱ ይዘውት ሊንቀሳቀሱ ባለመቻሉ ቀዳሹም አስቀዳሹም በቀላሉ [ሊጠቀሙበት አልቻሉም]። ስለዚህ “አኰቴተ ቊርባን” መጠኑ ትልቅ ስለሆነ፣ የታተመው እንዳለ ባለው ይዘት ኅትመቱ ቀጥሎ፣ ዘወትር በቅዳሴ የሚሳተፉ ምእመናን በቀላሉ ከጸሎት መጽሐፋቸው ጋር ሊይዙት በሚችሉት መጠን ቀዳሹና አስቀዳሹ ሊያውቁት የሚገባውን ክፍል ስለቅዳሴ ለብቻ አውጥቶ በትንሹ መታተም ቢችል እጅግ በጣም ጥሩ ነው ብዬ ይህን የአደራ መልእክት አስተላልፋለሁ። (ትልቁ የቅዳሴው መጽሐፍ እያለ፤ ለምዕመናን [ለተሰጥዎ] መማሪያ ተብሎ በትንሹ በጸሎት መጽሐፍ መልክ እንደተዘጋጀው ዓይነት ማለት ነው)።
ብሌን ታከለ የቶሮንቶ መንበረ ብርሃን ቅድስት ማርያም ካቴድራል አባል ናት፡፡ የቅዳሴን ጣዕም ከልጅነቷ ጀምሮ የቀመሰችና ባደገችበት የሐዋሳ ገብርኤል ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ታላቅ የአገልግሎት ተሳትፎ የነበራት ልጅ ስለሆነች፣ አኰቴተ ቊርባን እጇ ውስጥ እንደገባ በደስታ አነበበችው፡፡ አቀራረቡን አስመልክቶ ግን ለየት ያለ አስተያየት ሰጠችኝ፡፡ “ቅዳሴን በትረካ መልኩ ያቀረበ መጽሐፍ መስሎኝ ነበር” አለች ብሌን፡፡ ይህን አስተያየት በርካታ ምእመናን ሊጋሩት እንደሚችሉ ተረዳሁ፡፡ ስለዚህ ይህ መጽሐፍ “ፍቅርተ ኢየሱስ” የተባለች፣ በጌታ የተወደደች፣ በደሙ እንደተዋጀች የምታውቅና የቅዳሴን ውበት እንድታይ በቅዱስ ቃሉ ትምህርት ዐይነ ልቡናዋ የበራላት ምእመን፣ ቅዳሴው ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ በጣዕመ ዜማው፣ ከአዲስ ኪዳን መጻሕፍት በሚነበቡ ምንባባት፣ በቅዳሴው ጸሎትና ዑደት ሐሴት እያደረገች የቅዳሴው ተሳታፊ የምትሆንበትን ሂደት በዝርዝር ለማስረዳት ይሞክራል፡፡ ፍቅርተ ኢየሱስ ለቅዳሴ ካላት ፍቅር የተነሣ ዘወትር እሑድና በዐበይት በዓላት የቅዳሴ ተሳታፊ ስለምትሆን፣ ምእመናን ለዲያቆናቱና ለካህናቱ የሚሰጡትን የዜማ መልስ (ተሰጥዎ) በሚገባ ታውቃለች፤ መቅደሱ ላይ ያለውን የጌታ ስቅለት ሥዕል እያየች ዐይነ ልቡናዋን ወደ ቀራንዮ አቅንታ፣ ድምጽዋን ከፍ አድርጋ ታዜማለች፡፡ በሥርዓተ አምልኮው ከሚከናወኑ ድርጊቶች መካከል ምሳሌያዊ ትርጉሙ ያልገባት ነገር ካለ ወይም በአብዛኛው ከሚቀደሱት ቅዳሴያት ለየት ያለ ቅዳሴ (ለምሳሌ ቅዳሴ ሠለስቱ ምእት፣ ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ፣ ቅዳሴ ኤጲፋንዮስ ወዘተ.) ከተቀደሰ፣ የንስሐ አባትዋን ቀሲስ ፍቅረ መለኮትን ትጠይቃለች፡፡ እርሳቸውም መጽሐፈ ቅዳሴውን ይዘው የአማርኛውን ትርጉም እያስነበቡ ጥያቄዎቿን በሙሉ በዕርጋታና በዝርዝር ይመልሱላታል፡፡
ይህ መጽሐፍ ማንኛውም የቤተ ክርስቲያናችን አባል ስለ ቅዳሴ ሊያውቃቸው የሚገባቸውን መሠረታዊ ትምርህቶች ለማቅረብ ሙከራ አድርጓል፡፡ ትምህርተ ቅዳሴው የቀረበበትም መንገድ፣ የቅዳሴውን ሦስት ዋና ዋና ክፍልች በመከተልና ከየክፍሉ በተመረጡ አርእስት ላይ መጠነኛ ሐተታ (ገለጻ) በመስጠት ሲሆን፣ ፍቅርተ ኢየሱስ የተባለች ገጸ-ባሕርይ የቤተ ክርስቲያናችንን ምእመናን እንድትወክል ተደርጓል፡፡ በሦስቱ የቅዳሴ ክፍሎች ሥር የቀረቡ ትምህርቶችን በምዕራፍ ከመከፋፈል ይልቅ፣ “ቡራኬ 1፣ ቡራኬ 2 . . .” የሚል ስያሜን መርጫለሁ፡፡ ባጠቃላይ መጽሐፉ በሦስት ዐበይት ክፍሎችና በሃያ አንድ (21) ቡራኬያት የተከፈል ሲሆን፣ ትምህርታዊ ገላጻ የተሰጠባቸው ሃያ አንዱ ቡራኬያት፣ ሠራዒው ካህን በቅዳሴ ሰዓት የሚያከናውናቸውን ሃያ አንድ የአፍኣ (የውጭ) እና የውስጥ ቡራኬያትን ያስታውሱናል፡፡
በመጽሐፉ ውስጥ ለተጠቀሱ የግእዝ ቃላትና የሥርዓተ አምልኮ ስያሜያት (liturgical terminologies) መፍትሔ ቃላት (glossary) ተዘጋጅቷል፡፡ ምእመናንን ወክላ በዚህ መጽሐፍ የቅዳሴውን ሂደት በተመስጦ፣ አንዳንዴም በዕንባ፣ የምትከታተለው ፍቅርተ ኢየሱስ የቅዳሴ ጸበል ብቻ ጠጥታ ወደ ቤቷ የምትመለስ ሳትሆን፣ ጌታችን ኢየሱስ በቅዱስ ወንጌል “ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው” (ዮሐ. 6፡51) እንዳለ፣ ከኃጢአት በሽታ የምትፈወስበትን ኅብስተ ሕይወትና ጽዋዐ አኰቴት (ሥጋውና ደሙን) የምትቀበል ኦርቶዶክሳዊት ክርስቲያን ናት፡፡ ፍቅርተ ኢየሱስን በምናባቸው እየሳሉ ይህን መጽሐፍ የሚያነብቡ፣ ነገር ግን ከቅዱስ ቊርባን የራቁ ወይም ከተቀበሉ ዓመታትን ያስቆጠሩ የቤተ ክርስቲያናችን አባላት በእውነተኛ ንስሐና በምክረ ካህን ተዘጋጅተው “ጸጋ ሆኖ የተሰጠንን ሥጋውንና ደሙን በእግዚአብሔር ጥበብ” እንደሚቀበሉ ተስፋ አደርጋለሁ - መልካም ንባብ፡፡
=======
ቀሲስ መብራቱ ኪሮስ (PHD) ቶሮንቶ፣ ካናዳ

የሊቢያ ሰማዕቶቻችንን ለምን ዘነጋናቸው? || 10ኛ ዓመት የሰማዕትነታቸው መታሰቢያ
========
በሀገረ ሊቢያ በደማቸው ምስክርነትን ሰጥተው ካለፉ ሰማዕታት እነሆ ድፍን አሥር ዓመት ሞላቸው። ጸጋ በረከታቸው፣ አማላጅነታቸው ከሁላችን ጋራ ይኹን።
=====
** ዛሬ 8pm በዋሺንግተን ዲሲ እነዚህን ሰማዕታት እናስታወሳቸዋለን፣ እነርሱን በተመለከተ መደረግ ይገባው ስለነበረው ጉዳይ እናነሣለን።
https://www.youtube.com/live/fACAU_WO0Yg?si=E9Cer0ButaMvKd5d

++++
አደባባይ ሚዲያን ለማግኘት
👉 በ YouTube
https://www.youtube.com/adebabaymedia
👉 በ Facebook
https://facebook.com/adebabaymedia
👉 በ Telegram
https://t.me/adebabaymedia
👉 በ Twitter
https://twitter.com/adebabaymedia…
++++
አደባባይ ሚዲያን ለማግኘት
👉 በ YouTube
https://www.youtube.com/adebabaymedia
👉 በ Facebook
https://facebook.com/adebabaymedia
👉 በ Telegram
https://t.me/adebabaymedia
👉 በ Twitter
https://twitter.com/adebabaymedia…
ሐሙስ 8pm EST (DC Time)
=====
** ሴቶችን የመድፈር እና ሰዎችን የማገት ፖለቲካ፤ ከወጣቷ ብርቱካን ተመስገን ጉዳይ ባሻገር፤
+++++
ተወያዮች፦
** ጠበቃ ተክለሚካኤል አበበ
** ጋዜጠኛ አያሌው መንበር
** መምህር አቤል ጋሼ እንዲሁም
** ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ
https://www.youtube.com/live/qq4nknPxrcM?si=w4pthpxfn313h8S4
Teklemichael Ab Sahlemariam Ayalew Menber Abel Gashe Ephrem Eshete Ephrem

ሴቶችን የመድፈር እና ሰዎችን የማገት ፖለቲካ || ከወጣቷ ብርቱካን ተመስገን ጉዳይ ባሻገር
++++ አደባባይ ሚዲያን ለማግኘት ..... +++
👉 በ YouTube
https://www.youtube.com/adebabaymedia
👉 በ Facebook
https://facebook.com/adebabaymedia
👉 በ Telegram
https://t.me/adebabaymedia
👉 በ Twitter
https://twitter.com/adebabaymedia
አደባባይ ሚዲያ፦ የሁላችን ስለሆነች ኢትዮዽያ!
👉 በ YouTube
https://www.youtube.com/adebabaymedia
👉 በ Facebook
https://facebook.com/adebabaymedia
👉 በ Telegram
https://t.me/adebabaymedia
👉 በ Twitter
https://twitter.com/adebabaymedia
አደባባይ ሚዲያ፦ የሁላችን ስለሆነች ኢትዮዽያ!