ዜና፡ #የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በአማራ ክልል የተቋሙ ሰራተኛ ታገቶ ከተወሰደ በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደሉን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር #በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን በስራ ላይ የነበረ የተቋሙ ሰራተኛ አቶ ሆነልኝ ፋንታሁን ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች ታግቶ ከተወሰደ በኋላ በተፈጸመበት ድብደባ እና ኢ-ሰብዓዊ ኣያያዝ ምክንያት ነሐሴ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ህይወቱ ማለፉን አስታወቀ።
ማህበሩ ትላንት ነሃሴ 12 ቀን 2017 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ባወጣው መግለጫ አቶ ሆነልኝ ፋንታሁን ነሐሴ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ከደባርቅ ከተማ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ጨነቅ አካባቢ በሰብአዊ አገልግሎት ላይ ተሰማርቶ ባለበት ሁኔታ ነበር የታገተው ብሏል።
ማህበሩ በአከባቢው በተቋሙ የሰብአዊ ድጋፍ ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ዶ/ር ተፈራ አሰፋና አቶ አደላደላው ይግዛው የተባሉ ሌሎች ሁለት ሰራተኞቹ ከዚህ አሳዛኝ ክስተት መትረፋቸውን ጠቁሟል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8936

Addis standard
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በአማራ ክልል የተቋሙ ሰራተኛ ታገቶ ከተወሰደ በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደሉን አስታወቀ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 13/ 2017 ዓ/ም፦ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን በስራ ላይ የነበረ የተቋሙ ሰራተኛ አቶ ሆነልኝ ፋንታሁን ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች ታግቶ ከተወሰደ በኋላ በተፈጸመበት ድብደባ እና ኢ-ሰብዓዊ ኣያያዝ ምክንያት ነሐሴ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ህይወቱ ማለፉን አስታወቀ። ማህበሩ ትላንት ነሃሴ 12 ቀን 2017 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ባወጣው መግለጫ አቶ…
ዜና፡ በ #ፀለምቲ ወረዳ በተከሰተ ድርቅ ወደ 50,000 የሚጠጉ ሰዎች ለረሃብ አደጋ መጋለጣቸውና ከ9,000 በላይ እንስሳት መሞታቸው ተገለፀ
በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ፀለምቲ ወረዳ በተከሰተው ከባድ ድርቅ ምክንያት ወደ 50,000 የሚጠጉ ሰዎች ለረሃብ እና ለመፈናቀል መጋለጣቸውንና ከ9,000 በላይ የሚሆኑ የቤት እንስሳት መሞታቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት ገለጹ።
የላዕለይ ፀለምቲ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ነጋ አዱኛ፤ “9,367 አባወራዎች ወይም 49,799 ሰዎች አደጋ ላይ ናቸው። አንዳንድ ሰዎች ምግብ ፍለጋ አካባቢውን ለቀው መውጣት ጀምረዋል። እስካሁን 807 ከብቶች፣ 8,351 በጎችና ፍየሎች፣ 108 አህዮች እና ሁለት ግመሎች በረሃብ ሞተዋል። ገበሬዎች የቀሩትን እንስሳቶቻቸውን ለመታደግ ከአካባብው በመልቀቅ ላይ ናቸው።” ሲሉ ለክልሉ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።
የትግራይ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ቢሮ ኃላፊ አቶ ገብረሕይወት ገብረእግዚአብሔር የድርቁን ያደረሰውን ጉዳት ለአዲስ ስታንዳርድ አረጋግጠዋል፤ ነገር ግን አሃዞችን ከመስጠት ተቆጥበዋል። “በድርቁ ላይ ክልል አቀፍ ጥናት እያደረግን ነው። ገና አልተጠናቀቀም” ብለዋል
ተጨማሪ ያንብብ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8943

በፀለምቲ ወረዳ በተከሰተ ድርቅ ወደ 50,000 የሚጠጉ ሰዎች ለረሃብ አደጋ መጋለጣቸውና ከ9,000 በላይ እንስሳት መሞታቸው ተገለፀ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13/ 2017 ዓ/ም፦ በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ፀለምቲ ወረዳ በተከሰተው ከባድ ድርቅ ምክንያት ወደ 50,000 የሚጠጉ ሰዎች ለረሃብ እና ለመፈናቀል መጋለጣቸውንና ከ9,000 በላይ የሚሆኑ የቤት እንስሳት መሞታቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት ገለጹ። የላዕለይ ፀለምቲ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ነጋ አዱኛ፤ “9,367 አባወራዎች ወይም 49,799 ሰዎች አደጋ ላይ ናቸው። አንዳንድ ሰዎች…
ዜና: በበጀት አመቱ ኢትዮጵያ 4 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ መቻሏን #ኮሚሽኑ አስታወቀ
በ2017 በጀት አመት ኢትዮጵያ 4 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ ችላለች ሲል የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ዛሬ ነሐሴ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የኢንቨስትመንት ሂደቶችን ለማቀላጠፍ እና የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል በተደረጉ ጥረቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት የሚያደርጉ ባለሀብቶችን እምነት በ20 በመቶ ማሳደግ ተችሏል ሲል ገልጿል።
በበጀት ዓመቱ በኢንቨስትመንት ፈቃድ አሰጣጥ ጠንካራ አፈጻጸም መመዝገቡን ጠቅሶ በአጠቃላይ ለ525 አዳዲስ ኢንቨስትመንቶች እና 19 የማስፋፊያ ፈቃዶች ተሰጥተዋል ብሏል።
ቅድሚያ በሚሰጣቸው እንደ ማኑፋክቸሪንግ፣ የወጪ እና ገቢ ንግድ፣ አይሲቲ እንዲሁም ግብርና ባሉ ዘርፎች የአዳዲስ ኢንቨስትመንት ፈቃዶች 308 ለሚሆኑ ለውጭ ባለሃብቶች፣ 109 ለጣምራ ኢንቨስትመንት እና ከ98 በላይ ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች መሰጠቱን ያስታወቀው ኮሚሽኑ ይህም በተቋሙ ታሪክ ትልቁ ቁጥር መሆኑን አመልክቷል።
በተጨማሪም በ2017 በጀት አመት ኢትዮጵያ 4 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ መቻሏ የተገለጸ ሲሆን ይህም ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የ2.2 በመቶ እድገት አሳይቷል ተብሏል።
https://www.facebook.com/share/1FCRPEJd6N/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

ዜና፡ የተጨማሪ እሴት #ታክስ ምጣኔ 15 በመቶ ሆኖ እንዲቀጥል መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ
የገንዘብ ሚኒስቴር በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ማሻሻያ መሰረት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔ 15 በመቶ ሆኖ እንዲቀጥል ተወስኗል ሲል ገለጸ።
#የኢትዮጵያ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔ ከሰሃራ በታች ከሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት አንጻር ዝቅተኛ ነው ሲል የአለም ባንክ ግሩፕ አባል የሆነው አለምአቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ያደረገውን ጥናት ዋቢ በማድረግ መዘገባችን የታወሳል።
ነባሩ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ከምጣኔ ውጭ ሌሎች ማሻሻያዎችን በማካተት ከ3 አስርት ዓመታት በኋላ ተሻሽሎ በ2017 በጀት አመት ስራ ላይ መዋሉን ሚኒስቴሩ ጠቁሟል።
የታክስ ገቢ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ከነበረው ከ12 በመቶ በላይ ድርሻ በየዓመቱ በተከታታይ እየቀነሰ ከ7 በመቶ በታች መድረሱን ጠቅሶ፣ ከዚህ ጠቅላላ ቅናሽ 44 በመቶው የተጨማሪ እሴት ታክስ ድርሻ እንደሆነ አመላክቷል፡፡
የተጨማሪ እሴት ታክስ ህጉን አሁን ካለው የኢኮኖሚ ሁኔታ የቀጣይ ዓመታት ለውጦች ጋር እንዲጣጣም በማድረግ በመካከለኛ ዘመን የገቢ ስትራቴጂው መሰረት ተሻሽሎ በ2017 በጀት ዓመት ስራ ላይ እንዲውል ተደርጓል ብሏል፡፡
በማሻሻያው መሰረት በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ማሻሻያ መሰረት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔ 15 በመቶ ሆኖ እንዲቀጥል መወሰኑን ሚኒስቴሩ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው መረጃ ጠቁሟል’
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ መንግስት አመራር ተሰጥቷል _ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን
የደመወዝ ጭማሪ ተደረገ ሲባል ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል ሲሉ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) አስጠነቀቁ።
ኮሚሽነር መኩሪያ እርምጃው ለሌም ጊዜ ማስተማሪያ እንዲሆን በመንግስት በኩል አመራር ተሰጥቷል ብለዋል።

ወደ #ሶማሊያ ሲጓዝ በ #ፑንትላንድ ሀይሎች ተይዞ የነበረውና የተለቀቀው የጦር መሳሪያ የጫነ መርከብ አቅጣጫውን ወደ #ጅቡቲ ቀይሮ መጓዙ ተነገረ
“ሲ ወርልድ” የተሰኘው መርከብ በቅርቡ የጦር መሳሪያ ጭኖ ከቱርክ፥ ኢዝሚር ግዛት ወደ ሶማሊያ ሲጓዝ፥ በሶማሊያ ሰሜናዊ ግዛት በፑንትላንድ ሀይሎች ተይዞ ከተለቀቀ በኋላ፥ አቅጣጫውን በመቀየር ወደ ጅቡቲ መጓዙን ከስፍራው የወጡ ዘገባዎች አመላከቱ። የመጀመሪያ መድረሻው ሞቃዲሾ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን በአቅራቢያው ወደምትገኘው ጅቡቲ አቅጣጫውን ቀይሯል።
የጭነት መርከቡ በፑንትላንድ የባህር ኃይል ፖሊስ (PMPF) ተይዞ መክረሙ ከሰሞኑ ሲዘገብ ቆይቷል። መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ መርከቡ የጦር መሳሪያ እገዳ ከጥቂት አመታት በፊት የተነሳላት የሶማሊያን ዋና ከተማ ሞቃዲሾ አቅጣጫ አድርጎ እየተጓዘ ነበር።
በወቅቱ የወጡ ተጨማሪ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት፣ የጦር መሳሪያው በሶማሊያ “TURKSOM” በመባል በሚታወቀው ወታደራዊ ካምፕ የሚውል ነው። “TURKSOM” የሶማሊያና ቱርክ ጥምር ወታደራዊ ማሰልጠኛ በአል-ሻባብ ላይ በሚደረገው ውጊያ ለሚሰለጠኑት የ “ጎርጎር” ወታደሮች ማሰልጠኛ ስፍራ እንደሆነ ይታወቃል።
ተጨማሪ ለማንበብ:
https://www.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid0WaKmqFSFqq58F7EAH4nYDBCKGL1bfUs19ZR8iYnyySZsmrW13eTWMgER7LnthGoVl
===============
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg

#ኢትዮጵያ- #ሩሲያ: የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ ማርሽ ባንድ በሩሲያ ዓመታዊ የስፓስካያ ታወር ፌስቲቫል ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊሳተፍ ነው
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ ማርሽ ባንድ በሩሲያ በሚካሄደው ዓመታዊው የስፓስካያ ታወር ወታደራዊ የሙዚቃ ፌስቲቫል ላይ ለመሳተፍ ትናንት ሰኞ ነሐሴ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ሞስኮ አቅንቷል።
የሙዚቃ ፌስቲቫሉ በአለም ላይ ከሚገኙ ምርጥ ሶስት ወታደራዊ ፌስቲቫሎች አንዱ ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ ከሩሲያ እና ከተለያዩ የአለም ክፍሎች የተውጣጡ ወታደራዊ ባንዶች እና የሙዚቃ ቡድኖች በአንድ ላይ በመሰባሰብ ከነሐሴ 17 እስከ ነሐሴ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ሰፊ ወታደራዊ ሙዚቃ ያቀርባሉ ተብሏል።
የመከላከያ ሰራዊት የስነልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደኪዳን “የመከላከያ ሰራዊት ባንድ ራሺያ ባቀረበችው ግብዣ መሰረት በዚህ ፌስቲቫል ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊሳተፍ ነው” ያሉ ሲሆን 50 አባላት ያሉት ቡድን ወደ ሞስኮ ለማቅናት ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያ ተሳትፎ “በሁለቱ ወዳጅ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር እና ወታደራዊ ልምድን ለመለዋወጥ የሚያመች ይሆናል” ያሉት ሜጀር ጄኔራሉ አክለውም ፌስቲቫሉ መከላከያ ሰራዊት ለዝግጅቱ ከተጋበዙ ሌሎች የአፍሪካ ባንዶች ጋር ልምድ ለመጋራት “ጠቃሚ መድረክ” እንደሚሆን ገልጸዋል።
አያይዘውም የመከላከያ ሠራዊት ባንድ አዳዲስና የራሱን ስራዎች ለማቅረብ ለሁለት ወራት ያህል ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን አንስተዋል።
ልዑካን ቡድኑ ለሁለት ሳምንታት በሩሲያ እንደሚቆይ ጠቅሰው ተሳትፎው “ለቡድኑ ብቻ ሳይሆን ለመላው ሀገር መከላከያ ሰራዊትም የገጽታ ግንባታ ነው” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

አለርት ሆስፒታል የሕፃናት ዓይን ህክምና ማዕከል ሥራ አስጀመረ
አለርት ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህፃናት ዓይን ህክምና ማዕከል ስራ አስጀምሯል።
ማዕከሉ በህፃናት ላይ የሚደርስ ዓይነ ስውርነትን በመከላከል ረገድ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው ተብሎለታል።
በማዕከሉ የምርቃት መርሃግብር ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፤ በሕፃናት ላይ የሚደርስ ዓይነ ስውርነትና የዓይን ጤና ህመም ከህፃናቱ ባለፈ ወላጅ ላይ፣ ማኅበረሰቡ እና ሀገር ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድር መሆኑን አንስተዋል።
ማዕከሉም የተሞላ የዓይን ህክምና በመስጠት የመማር፣ ማንበብ፣ መጫወት በአጠቃላይ ለህፃናቱ ከእይታ ባለፈ የወደፊት ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን ገልፀዋል።
40 በመቶ የሚሆነው የሀገሪቱ የህዝብ ቁጥር ህፃናት መሆናቸውን ገልፀው፤ ዛሬ ላይ በህፃናት ላይ የሚሰራ ስራ ለነገ ሀገር እድገትና ብልፅግና የማይተካ ሚና ያለው መሆኑን አስታውቀዋል።
ማዕከሉም በህፃናት ላይ የሚደርስ የዓይነ ስውርነትና የዓይን ህመምን በመከላከል ረገድ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው ብለዋል።
የአለርት ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ ዶክተር ሽመልስ ገዛህኝ በበኩላቸው፤ ሆስፒታሉ የተሟላ ግብአትና ብቁ ባለሙያዋችን በመጠቀም ጥራቱን የጠበቀ የህፃናት የዓይን ህክምና በመስጠት በህፃናት ላይ የሚደርስ የዓይን ጤና እክልንና ብርሀንን በመመለስ የወደፊት ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን ገልፀዋል።
(ኢፕድ)

ዜና፡ #በመቀለ ከተማ ግማሽ ሚሊየን የሚሆን ሀሰተኛ ባለ ሁለት መቶ ብር የገንዘብ ኖት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ
#በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ ግማሽ ሚሊየን ባለሁለት መቶ ብር ሀሰተኛ (ፎርጅድ) የገንዘብ ኖት ወደ ህብረተሰቡ ከመበተኑ በፊት በቁጥጥር ስር መዋሉን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ።
ተጠርጣሪው ባለሁለት መቶ ብር ኖቱን ከአዲስ አበባ ነው የተላከልኝ ማለቱን ያስታወቀው የክልሉ ፖሊስ ለአንድ ባለ ሁለት መቶ ብር ኖት በ80 ብር ለመሸጥ በህቡእ ተስማምቶ መምጣቱን አመላክቷል።
የክልሉ ፖሊስ ባደረገው ክትትል ተጠርጣሪው ከነ ሙሉ ኢግዚቢቱ ተደብቆበት ከነበረው ቦታ በቁጥጥር ስር እንዲውል መደረጉን ጠቁሟል።
በክልሉ በደማቅ ሁኔታ የሚከበሩ በዓላትን ተከትሎ የሚኖረውን የገበያ ፍሰት እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም ህብረተሰቡን ለማጭበርበር የተደረገ የወንጀል ተግባር ነው ሲል የክልሉ ፖሊስ አስታውቋል።
ህብረተሰቡ በቀጣይ ቀናት የሚካሄዱ እና በክልሉ በድምቀት የሚከበሩ በአላትን ተንተርሶ የሚያካሂደውን ግብይት በጥንቃቄ እንዲያከናውን የክልሉ ፖሊስ አሳስቧል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
#በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ ግማሽ ሚሊየን ባለሁለት መቶ ብር ሀሰተኛ (ፎርጅድ) የገንዘብ ኖት ወደ ህብረተሰቡ ከመበተኑ በፊት በቁጥጥር ስር መዋሉን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ።
ተጠርጣሪው ባለሁለት መቶ ብር ኖቱን ከአዲስ አበባ ነው የተላከልኝ ማለቱን ያስታወቀው የክልሉ ፖሊስ ለአንድ ባለ ሁለት መቶ ብር ኖት በ80 ብር ለመሸጥ በህቡእ ተስማምቶ መምጣቱን አመላክቷል።
የክልሉ ፖሊስ ባደረገው ክትትል ተጠርጣሪው ከነ ሙሉ ኢግዚቢቱ ተደብቆበት ከነበረው ቦታ በቁጥጥር ስር እንዲውል መደረጉን ጠቁሟል።
በክልሉ በደማቅ ሁኔታ የሚከበሩ በዓላትን ተከትሎ የሚኖረውን የገበያ ፍሰት እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም ህብረተሰቡን ለማጭበርበር የተደረገ የወንጀል ተግባር ነው ሲል የክልሉ ፖሊስ አስታውቋል።
ህብረተሰቡ በቀጣይ ቀናት የሚካሄዱ እና በክልሉ በድምቀት የሚከበሩ በአላትን ተንተርሶ የሚያካሂደውን ግብይት በጥንቃቄ እንዲያከናውን የክልሉ ፖሊስ አሳስቧል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
ዜና፡ በ #ደቡብ_ትግራይ የፀጥታ ኃላፊን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገ ሙከራ በተነሳ ግጭት እና ተቃውሞ አምስት ሰዎች ቆሰሉ
በደቡብ ትግራይ መኮኒ ከተማ የወረዳ ፀጥታ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊን በቁጥጥር ስር ለማዋል የፀጥታ ኃይሎች ሙከራ ማድረጋቸውን ተከትሎ በተቀሰቀሰ የቃውሞ ቢያንስ አምስት ሲቪል ሰዎች መቁሰላቸውን የከተማዋ ባለስልጣናት ተነገሩ።
የመኮኒ ከተማ ከንቲባ አቶ መሰለ አሸብር ለ"አዲስ ስታንዳርድ" እንደተናገሩት፣ ክስተቱ የተፈጠረው በትናንትናው ዕለት የፀጥታ ኃይሎች የወረዳው የፀጥታ ቢሮ ምክትል ሃላፊ የሆኑትን ኮሎኔል ሃለፎም መሃሪን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲሞክሩ ነው። "ከመኮኒ ከተማ ሊወስዷቸው ሲሞክሩ ህዝቡ ተሰበሰበ። ከጠዋቱ 5 ሰአት አካባቢ ነበር ተኩስ የተጀመረው" ሲሉ አቶ መሰለ ተናግረዋል።
አክለውም፤ ከተጎዱት ሰዎች መካከል አንዱ አንገቱ ላይ ሌላኛው ደግሞ እግሩ ላይ የተመቱት፤ በኋላ ላይ ወደ መቐለ አይደር ሆስፒታል ተልከዋል፤ የተቀሩት ሶስቱ ደግሞ በመኮኒ ሆስፒታል ህክምና ተደርጎላቸዋል ሲሉ አስረድተዋል።
የመኮኒ ሆስፒታል ሃኪም የሆኑት ዶ/ር ዳንኤል ብርሄ፤ አምስት ሰዎች ላይ ጉዳት መረሱን ለ"አዲስ ስታንዳርድ" አረጋግጠዋል። "አምስት ሰዎች ሆስፒታላችን ገብተዋል። ሁለቱ ከባድ ሁኔታ ላይ ስለነበሩ ወደ መቐለ ተልከዋል። ሌሎቹ ትንሽ ጉዳት ነው የደረሰባቸው ስለዚህ እዚሁ ሆስፒታል ህክምና አግኝተዋል" ብለዋል።
ተጨማሪ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8952

በደቡብ ትግራይ የፀጥታ ኃላፊን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገ ሙከራ በተነሳ ግጭት እና ተቃውሞ አምስት ሰዎች ቆሰሉ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14/ 2017 ዓ/ም፦ በደቡብ ትግራይ መኮኒ ከተማ የወረዳ ፀጥታ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊን በቁጥጥር ስር ለማዋል የፀጥታ ኃይሎች ሙከራ ማድረጋቸውን ተከትሎ በተቀሰቀሰ የቃውሞ ቢያንስ አምስት ሲቪል ሰዎች መቁሰላቸውን የከተማዋ ባለስልጣናት ተነገሩ። የመኮኒ ከተማ ከንቲባ አቶ መሰለ አሸብር ለ”አዲስ ስታንዳርድ” እንደተናገሩት፣ ክስተቱ የተፈጠረው በትናንትናው ዕለት የፀጥታ ኃይሎች የወረዳው…
ዜና፡ በ #ኬንያ የ #ኢትዮጵያ ኤምባሲ አወዛጋቢን የሶማሌ ክልል አዲስ መዋቅር በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ላይ ይቅርታ ጠየቀ
በኬንያ ዋና ከተማ #ናይሮቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሶማሌ ክልል የተቋቋመውን አዲስ የአስተዳደር መዋቅር አስመልክቶ ይፋዊ ገጹ ላይ አውጥቶ በሰረዘው መግለጫ ላይ ይቅርታ በመጠየቅ እና ማብራሪያ ሰጠ። መግለጫው በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ላይ መካከል ውዝግብ አስነስቷል።
ኤምባሲው በመጀመሪያ ባወጣው መግለጫ የጉራ-ዳሞሌ ዞን እና ሃገር ሞቆር ወረዳ መቋቋምን ለማክበር በናይሮቢ ዝግጅት መደረጉን ገልጾ ነበር። በዝግጅቱ አምባሳደር ደመቀ መዋቅሩ የማብቃት እና የአካታች አስተዳደር ምልክት ነው ማለታቸውን መግለጫው ጠቅሷል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እየተካሄደ ላለው የፖለቲካ ማሻሻያ ማሳያ እንደሆነ ገልጸዋል።
ይሁን እንጂ ኤምባሲው በኋላ ላይ ባወጣው የማስተካከያ መግለጫ የመጀመሪያው መልዕክት “ትክክለኛ ያልሆኑ መረጃዎች” እንደያዙ ገልጿል። የሶማሌ ክልል ለጉራ ማህበረሰብ አዲስ ዞን ቢመድብም ይፋዊ ስም እንዳልተሰጠው አስታውቋል።
ሙሉውን ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8956

በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አወዛጋቢን የሶማሌ ክልል አዲስ አደረጃጀት በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ላይ ይቅርታ ጠየቀ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14/ 2017 ዓ/ም፦ በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሶማሌ ክልል የተቋቋመውን አዲስ የአስተዳደር መዋቅር አስመልክቶ ይፋዊ ገጹ ላይ አውጥቶ በሰረዘው መግለጫ ላይ ይቅርታ በመጠየቅ እና ማብራሪያ ሰጠ። መግለጫው በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ላይ መካከል ውዝግብ አስነስቷል። ኤምባሲው በመጀመሪያ ባወጣው መግለጫ የጉራ-ዳሞሌ ዞን እና የሃገር ሞቆር ወረዳ መቋቋምን…
ዜና: የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አባሉ ዮሐንስ ተሰማ አምስት ዓመት ከ10 ወር ጽኑ እስራት ተፈረደባቸው፣ ፓርቲያቸው በበኩሉ ውሳኔውን “ፖለቲካዊ” ብሎታል
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሕገ መንግሥት ማሻሻያ ላይ አቤቱታ ካቀረቡ በኋላ በቁጥጥር ስር የዋሉት በክልሉ ምክር ቤት የተቃዋሚው ቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦዴፓ) ተመራጭ አቶ ዮሐንስ ተሰማ፤ የአምስት ዓመት ከ10 ወር ጽኑ እስራት እና የ15 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንደተፈረደባቸው አንድ የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አመራር ለአዲስ ስታንዳርድ አረጋገጡ።
የአሶሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአቶ ዮሐንስ ላይ የቅጣት ውሳኔውን ያስተላለፈው ከአምስት ዓመት በፊት ተቋርጦ በነበረው “ከሊዝ አዋጅ የከተማ መሬት አስፋፍቶ በመያዝ” ክስ መሆኑን እኚህ አመራር ገልጸዋል።
ቀደም ሲል በ2011 ዓ.ም በፖለቲካ ምክንያት እሳቸውን ጨምሮ [አቶ ዮሐንስን] ተይዘን ነበረ ያሉት አመራሩ በ2012 ዓ.ም ክሱ ተቋርጦ እንደነበረ አስታውሰዋል።
ይሁን እንጂ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሕገ መንግሥት ማሻሻያ ላይ አቤቱታ ካቀረቡ በኋላ “በሽብር እና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን በማፍረስ” በሚል በክልሉ የምክር ቤት አባልነታቸው የነበራቸው ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ በቁጥጥር ውስጥ መዋላቸውን አንስተዋል።
“ፖሊስም ሆነ አቃቤ ህግ በዚህ ክስ [በሽብር] መረጃ በማጣታቸው የተነሳ ከዚህ ቀደም ተከሰውበት እና ተቋርጦ የነበረውን ከሊዝ አዋጁ ጋር ተያይዞ የቀረበባቸውን ክስ እንዲቀጥል ተደርጓል” የሚሉት አመራሩ ፍርድ ቤት ሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ጥፋተኛ ተብለው በትናንትናው ዕለት የመጨረሻ ውሳኔ እንደተሰጠበት አመልክተዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ:
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8966

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አባሉ ዮሐንስ ተሰማ አምስት ዓመት ከ10 ወር ጽኑ እስራት ተፈረደባቸው፣ ፓርቲያቸው በበኩሉ ውሳኔውን "ፖለቲካዊ" ብሎታል - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 14/ 2017 ዓ/ም፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሕገ መንግሥት ማሻሻያ ላይ አቤቱታ ካቀረቡ በኋላ በቁጥጥር ስር የዋሉት በክልሉ ምክር ቤት የተቃዋሚው ቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦዴፓ) ተመራጭ አቶ ዮሐንስ ተሰማ፤ የአምስት ዓመት ከ10 ወር ጽኑ እስራት እና የ15 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንደተፈረደባቸው አንድ የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አመራር ለአዲስ ስታንዳርድ አረጋገጡ። የአሶሳ ከተማ…
ዜና: #ኢንስቲትዩቱ በሚቀጥሉት 11 ቀናት ቅጽበታዊ ጎርፍ የሚያስከትል ከባድ ዝናብ ይኖራል ሲል አስጠነቀቀ
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በሚቀጥሉት 11 ቀናት በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ቅጽበታዊ ጎርፍ መከሰት አስተዋጽኦ የሚያርግ ከባድ ዝናብ ይኖራል ሲል አስጠነቀቀ።
በመደበኛ ሁኔታ በነሐሴ ወር የመጨረሻው 11 ቀናት ዝናብ ሰጪ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በበለጠ ሁኔታ እየተጠናከሩ የሚሄዱበት ጊዜ መሆኑን ኢንስቲትዩቱ አመልክቷል፡፡
በተጨማሪም አልፎ አልፎ ባሉት ቀናት በፀሐይ ኃይል ታግዘው ከሚጠናከሩ የደመና ክምችቶች ጋር ተያይዞ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ለወንዞች ሙላትና ለቅጽበታዊ ጎርፍ መከሰት አስተዋጽኦ የሚያርግ በረዶ የቀላቀለ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ እንደሚኖር ጠቁሟል፡፡
በዚህም በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን እና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር የአሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ ብሏል፡፡
በተጨማሪም በሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ኢፕድ ዘግቧል፡፡
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በሚቀጥሉት 11 ቀናት በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ቅጽበታዊ ጎርፍ መከሰት አስተዋጽኦ የሚያርግ ከባድ ዝናብ ይኖራል ሲል አስጠነቀቀ።
በመደበኛ ሁኔታ በነሐሴ ወር የመጨረሻው 11 ቀናት ዝናብ ሰጪ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በበለጠ ሁኔታ እየተጠናከሩ የሚሄዱበት ጊዜ መሆኑን ኢንስቲትዩቱ አመልክቷል፡፡
በተጨማሪም አልፎ አልፎ ባሉት ቀናት በፀሐይ ኃይል ታግዘው ከሚጠናከሩ የደመና ክምችቶች ጋር ተያይዞ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ለወንዞች ሙላትና ለቅጽበታዊ ጎርፍ መከሰት አስተዋጽኦ የሚያርግ በረዶ የቀላቀለ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ እንደሚኖር ጠቁሟል፡፡
በዚህም በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን እና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር የአሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ ብሏል፡፡
በተጨማሪም በሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ኢፕድ ዘግቧል፡፡
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
ዜና፡ እግድ ላይ የነበሩ ሶስት ከፍተኛ የትግራይ ወታደራዊ አዛዦች ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገለጸ
#በትግራይ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች እግድ ተጥሎባቸው የነበሩ ሶስት ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦችን ከክልሉ ግዜያዊ አስተዳደር ጋር "በማቀራረብ እንዲስማሙና በጋራ እንዲሰሩ የሚያደርግ ምቹ ሁኔታ ፈጥሪያለሁ" ሲል የትግራይ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ፎረም አስታወቀ።
የትግራይ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች እግድ ከተጣለባቸው መካከል ነበሩ የተባሉት ጄኔራል ጉኡሽ ገብሬ፣ ጀነራል ከበደ ፍቃዱ እና ኮሎኔል ገ/ዮሐንስ ዮሃንስ (የአባተ ልጅ) የተባሉ ወታደራዊ ሃላፊዎች ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ጋር እንዲስማሙና እንዲግባቡ በማድረግ አለመግባባቱ እንዲፈታ አድርጊያለሁ ሲል ፎረሙ በመግለጫው አስታውቋል፤ “በመካከላቸው ያለውን ልዩነት በመለየት እንዲወያዩ እና በጋራ መስራት የሚያስችላቸው መድረክ እንዲፈጠር አስችያለሁ” ብሏል።
ፎረሙ ነሃሴ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ “በትግራይ ክልል ያጋጠመውን ሁሉን አቀፍ ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እየሰራሁ ነው” ሲል አስታውቋል። በተለይም ደግሞ “የክልሉን ህዝብ ስጋት ውስጥ ያስገባውን የጸጥታ እና ውስጣዊ የፖለቲካ ችግር በሰላማዊና በውይይት እንዲፈታ ለማድረግ በትጋት እየሰራሁ ነው” ብሏል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8969

ዜና፡ እግድ ላይ የነበሩ ሶስት ከፍተኛ የትግራይ ወታደራዊ አዛዦች ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገለጸ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 15/ 2017 ዓ/ም፦ በትግራይ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች እግድ ተጥሎባቸው የነበሩ ሶስት ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦችን ከክልሉ ግዜያዊ አስተዳደር ጋር “በማቀራረብ እንዲስማሙና በጋራ እንዲሰሩ የሚያደርግ ምቹ ሁኔታ ፈጥሪያለሁ” ሲል የትግራይ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ፎረም አስታወቀ። የትግራይ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ተሰብስበው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራውን ጊዜያዊ…
ዜና፡ #ኢትዮጵያ በ2017 በጀት አመት 7 ነጥብ 17 ቢሊየን ዶላር ከሬሚታንስ አግኝታለች፣ በተያዘው በጀት አመት 8 ቢሊየን ለማግኘት እየሰራች ነው ተባለ
ኢትዮጵያ በ2017 ዓ.ም በጀት አመት ዳያስፖራው በሕጋዊ መንገድ ወደ ሀገር ቤት ከላከው ገንዘብ (ሬሚታንስ) ሰባት ነጥብ 17 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር አግኝታለች፣ በ2018 ዓ.ም በጀት አመት ስምንት ቢሊየን ዶላር ለማግኘት እየተሰራ ነው ሲሉ የዲያስፖራ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዋና ዳይሬክተሩ አምባሳደር ፍጹም አረጋ አስታወቁ።
መንግስት የበጀት አመቱን እቅድ ለማሳካት ያሰበው ዳያስፖራው በሕጋዊ መንገድ ወደ ሀገር ቤት ገንዘብ ለመላክ የሚያስችሉ የተለያዩ መንገዶችን በማሻሻል እና ኢኮኖሚያዊ ዲፕሎማሲን በማጠናከር እንደሆነ አምባሳደሩ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍፁም አረጋ ይህንን ያስታወቁት ከንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት እና በመካከለኛው ምስራቅ ከሚገኙ ዲፕሎማቶች ጋር በበይነ መረብ ባደረጉት ውይይት መሆኑን ከፕሬስ ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
መንግስት የገንዘብ ዝውውሩን ለመጨመር እና የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ በኢኮኖሚያዊ ዲፕሎማሲ ላይ ትኩረት ማድረጉን አምባሳደሩ አብራርተዋል ብሏል።
በ2017 ዓ.ም የበጀት አመት 7 ነጥብ 17 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዲያስፖራው በሕጋዊ መንገድ ወደ ሀገር ቤት ከላከው ገንዘብ የውጭ ምንዛሪ መሰብሰብ ቢቻልም፣ ከዚህ የበለጠ አቅም እንዳለው አምባሳደር ፍፁም አረጋ በውይይቱ ወቅት ማብራራታቸውም ተጠቁሟል።
አክለውም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ጋር በመተባበር ለዲያስፖራው ማበረታቻ ፓኬጆችን እና የተሻሻሉ አገልግሎቶችን በቅርቡ እንደሚያሳውቅ ይጠበቃል ማለታቸውን ዘገባው አስታውቋል።