Addis Standard Amharic
16.5K subscribers
3.59K photos
84 videos
3 files
2.87K links
አዲስ ስታንዳርድ በጃኬን አሳታሚ ኃ.የተ.የግ.ማ. ባለቤትነት ስር የሚታተም በኢትዮጵያ የሚገኝ ነፃ እና ገለልተኛ ሚዲያ ነው። አዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የአዲስ ስታንዳርድ እንግሊዝኛ ሕትመት አካል ነው።
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
Download Telegram
ዜና: #በኢትዮጵያ የከተማ ወባ በሽታ ስርጭትን ለመቆጣጠር በሶስት ከተሞች ላይ ያተኮረ የምርምር ፕሮጀክት ተጀመረ

#በጅጅጋ#ሰመራና #ሎጊያ ከተሞች አደገኛ የከተማ ወባ በሽታ ስርጭትን ለመቆጣጠር የሚያስችል፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ አዲስ የምርምር ፕሮጀክት ተጀመረ።

የጥናት ፕሮጀክቱ ለሶስት አመታትን እንደሚካሄድ የተጠቆመ ሲሆን ከሰሜን #አሜሪካ ኤምሪ ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር ምርምሩን በዋናነት የሚያካሂዱት፣ የአዲስ አበባ እና ጅጅጋ ዩንቨርስቲዎች መሆናቸው ተገልጿል።

ፕሮጀክቱ ከጌትስ ፋውንዴሽን በተገኘው የሁለት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ይካሄዳል የተባለ ሲሆን በኢትዮጵያ አደገኛ የሆኑ የከተማ ወባ አማጪ ትንኞችን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ቴክኖሎጂና ርካሽ የሆነ ዘዴን ለመጠቀም የሚያስችል መሆኑ የጀርመን ድምጽ ባስደመጠው ዘገባ ጠቁሟል።

ከጣቢያው ጋር ቆይታ ያደረጉት በጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ የዚሁ ፕሮጀክት ተባባሪ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ሰሎሞን ያሬድ እንደተናገሩት ባለው ነባራዊ የቁጥጥር ዘይቤ፣ የትንኝ ዕጭ ቁጥጥር የነበረው፣ የብዙ የሰው ኃይል የሚያስፈልገው እና ወጭውም ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

አክለውም የትንኝ መራቢያ ቦታዎችን ለመለየት ቀልጣፋና ትክክለኛ የሆነ መረጃን መስጠት የሚችል ቴክኖሎጂን ጥቅም ላይ በማዋል ስርጭቱን ለመቆጣጠር መታሰቡን አመልክተዋል።

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የዚህ ፕሮጀክት ሌላኛው ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር አርአያ ገብረሥላሴ በበኩላቸው "ኢኖሬሌስ ስቴፌንሲ" የተሰኘችው የወባ ትንኝ በተለይም በምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል በሚገኙ ከተሞች መስፋፋቷን ገልጸዋል።

https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid0C4BPZCwu5CcwsHMHxhf4CyUWnkNmij9NDQQTrzhpkvJWBEa2QSqNzH4ARp9zvzCEl
በፎቶ፤ በ #ጁቡቲ#ኢትዮጵያ ኢምባሲ በፍቃደኝነት ወደ ኢትዮጵያ መመለስ የሚሹ ዜጎችን እየመዘገበ መሆኑን ገለጸ

የጂቡቲ መንግስት በህገ-ወጥ መንገድ በጂቡቲ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎች ለቀው እንዲወጡ መመሪያ መስጠቱን ተከትሎ በጁቡቲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ በፍቃደኝነት ወደ ኢትዮጵያ መመለስ የሚፈልጉ ዜጎችን እየመዘገበ መሆኑን አስታውቋል።

የሀገሪቱ መንግስት ህጋዊ የመኖሪያ ሰነድ የሌላቸው የውጭ አገር ዜጎች ከመጋቢት 25 እስከ ሚያዚያ 24 2017 ዓ/ም ድረስ በፍቃደኝነት እንዲወጡ፤ ይህን የማይከተሉ ከሆነ በሀይል እንዲወጡ እንደሚደረግ አሳስቧል።

የኢትዮጵያ ኢምባሲ ከጁቡቲ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ባደረገው የከፍተኛ ደረጃ ውይይት ቀነ ገደቡ እንዲራዘም ያቀረበው ጥሪ አለመሳካቱን ገልጿል።
ዜና፡ በአቶ #ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት 'ትግራይ ሊብራል ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ' የሚባል አዲስ ፓርቲ ሊያቋቁም መሆኑ ተገለጸ

በአቶ ጌታቸው የሚመራው #ከህወሓት የተከፈለው ቡድን አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ለማቋቋም በሂደት ላይ መሆኑ ተጠቆመ።

ይህ አዲስ በምዝገባ ሂደት ላይ የሚገኘው የፖለቲካ ፓርቲ በሊብራል ዴሞክራሲ ጽንሰ ሃሳብ የሚከተል መሆኑን እና "ትግራይ ሊብራል ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ" በማለት ለመጠራት መወሰኑን ከአመራሮቹ መካከል አንዱ እንደገለጹለት ቢቢሲ በዘገባው አስታውቋል።

ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁት እኚህ የቀድሞ የህወሓት አመራር "ይህ ስም የፖለቲካ ፓርቲውን ለመመሥረት በእንቅስቃሴ ላይ ባሉ ሰዎች የተመረጠ እንጂ ከምርጫ ቦርድ እውቅና ስላላገኘ ጉባዔ ሲካሄድ ሊቀየር ወይንም ሊሻሻል ይችላል" ብለዋል።

የህወሓት መሰረዝ ስጋት የፈጠረባቸው በአቶ ጌታቸው የሚመራው የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ከሳምንታት በፊት ባወጡት መግለጫ በዶ/ር ደብረፂዮን ለሚመራው ቡድን በጋራ ጉባዔ ለማካሄድ ጥሪ አቅርበው የነበረ ቢሆንም በጎ ምላሽ አለማግኘታቸውን ገልጸዋል።

"የህወሓት ሕጋዊነት ስለሚያበቃ የህወሓት የፖለቲካ ዓላማዎችን ለማሳካት የሚያስችለን አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ለመመሥረት ተገድደናል" ሲሉ ምንጮቼ ገልጸዋል ያለው ቢቢሲ የፓርቲው ሕገ ደንብና ፕሮግራሞቻችን አርቅቀው መጨረሳቸውን ነግረውኛል ብሏል።

ምንጩ አክለውም የደጋፊዎቻቸውን ፊርማ በማሰባሰብ ላይ እንደሚገኙ መናገራቸውን ያመላከተው ዘገባው ምርጫ ቦርድ ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች ገና ስላላሟሉ እስካሁን ድረስ ለቦርዱ በይፋ ያቀረቡት ጥያቄ እንደሌለ መናገራቸውን አስታውቋል።

ፓርቲው ክልላዊ መሆኑን ምንጩ እንደነገሩት የጠቆመው ቢቢሲ ከምርጫ ቦርድ በግንቦት የመጀመሪያ ወር ላይ ቅድመ እውቅና እናገኛለን ብለው እንደሚጠብቁ ገልጸውልኛል ብሏል
ዜና: ማህበሩ #ለአማራ ክልል ዳኞች የተወሰነው የደመወዝ ጭማሪ መዘግየቱ በዳኞች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ እያስነሳ መሆኑን አስታወቀ

የአማራ ክልል #ዳኞች ማህበር በክልሉ ለሚገኙ ዳኞች እና የጉባኤ ተሿሚዎች የተወሰነው የደመወዝና የጥቅማ ጥቅም ጭማሪ ተፈጻሚ ሳይሆን በመዘግየቱ “ከፍተኛ ቅሬታ” ማስነሳቱን አስታወቀ።

“ለክልሉ ዳኞች እና የጉባኤ ተሿሚዎች የተወሰነው የደመወዝ እና የጥቅማ ጥቅም ጭማሪ የዘገየው የፌደራል እና የክልሉ መንግስት በጀቱን ባለመልቀቃቸው ነው ሲል ማህበሩ ሚያዝያ 19 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ባጋራው መረጃ ጠቁሟል።

መረጃው አክሎም “የሚያስፈልገውን በጀት የሚመድበው የክልሉ መንግስት በመሆኑ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዐብይ ጉባዔው ውሳኔ መሰረት የሚያስፈልገውን የበጀት መጠን ጠቅሶ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳደደር፣ ለክልሉ ምክር ቤት እና ለክልሉ ገንዘብ ቢሮ በማሳወቅ እንዲለቀቅለት የቅርብ ክትትል እና ጥረት እያደረገ በመጠበቅ ላይ የሚገኝ መሆኑን አስታውቋል።

በተጨማሪም ሀገር አቀፍ የኑሮ ውድነት ደመወዝ ማሻሻያን አስመልክቶ ደግሞ በጀቱ ከፌደራል መንግስት የሚለቀቅ በመሆኑ በቅርብ በተካሄደው ሀገር አቀፍ የህግ ተርጓሚዎች መድረክ ላይ ውይይት በማድረግ ኮሚቴ ተዋቅሮ ጥያቄው በሁሉም ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤቶች ስም ለፌደራል መንግስቱ ቀርቦ በጀቱ እንዲለቀቅ በጥረት ላይ ያሉ መሆኑን ባገኘሁት መረጃ ለማወቅ ችያለሁ ብሏል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=7653
ዜና፡ #የተባበሩት_አረብ_ኤምሬትስ #ቢትኮይን ኩባንያ በ #ኢትዮጵያ የማይኒንግ አቅሙን በ52 ሜጋ ዋት ኣሳደገ

የተባበሩተ አረብ ኤምሬትስ የቢትኮይን ማይኒንግ ኩባንያ የሆነው ፎኒክስ ግሩፕ፤ በኢትዮጵያ ባለው የማይኒንግ አቅም ላይ 52 ሜጋ ዋት ጭማሪ ማድረጉን አስታውቋል።

ኩባንያው ትናንት ሚያዚያ 21 ቀን 2017 እንዳስታወቀው፤ አዲስ ተግባራዊ ካደረገው ጭማሪ ጋር በኢትዮጵያ የፎኒክስ የቢትኮይን ማይኒንግ አቅም 132 ሜጋ ዋት ደርሷል። የኩባንያው አጠቃላይ አቅም አሁን ከ500 ሜጋ ዋት በላይ መሻገሩ ተገልጿል።

የፎኒክስ ተባባሪ መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሙናፍ አሊ፤ የኩባንያው ስትራቴጂ "የተትረፈረፈ እና ዝቅተኛ ኃይል ወጭ ያላቸውን ዋና ዋና አካባቢዎች ማገኘት ላይ የተመሠረተ ነው" ብለዋል።

"በኢትዮጵያ ያደረግነውን የቅርብ ጊዜ መስፋፋታችን የመሳሰሉ ተነሳሽነቶች ወሳኝ እርምጃዎች ናቸው፣ ዛሬ ከፍተኛ ዋጋ በመፍጠር ብቻ ሳይሆን አቋማችንን በማጠናከር ላይም ይገኛሉ" ሲሉም መናገራቸውን ኮይንቴሌግራፍ ዘግቧል።

ይህ ማስፋፊያ ዜና የተሰማው የ #አቡ_ዳቢው ክሪፕቶማይኒንግ ኩባንያ ፎኒክስ ግሩፕ የ80 ሜጋ ዋት ኃይል ግዥ ስምምነት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር መፈራረሙን ተከትሎ ነው። በወቅቱ ኩባንያው በ2025 ሁለተኛው ሩብ አመት ስራ እንደሚጀምር ገልጿል።

ፎኒክስ ኩባንያ በአቡዳቢ ኢንተርናሽናል ሆልዲንግ ኩባንያ (IHC) የሚደገፍ ሲሆን፣ በመላው #ኤምሬትስ#አሜሪካ እና #ካናዳ ውስጥ የክሪፕቶ ማይኒንግ ስራዎችን ያከናውናል።
ዜና፡ #ኢትዮጵያ#አፍሪካ ሀገራት በ #ኒውክለር ኢንጂነሪግ የመጀመሪያ ዲግሪ እንድትሰጥ ተመረጠች

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ አባል ሀገራት በኒውኩለር ኢንጂነሪግ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም እንድትሰጥ በአለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ (IAEA) መመረጧን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኢትዮጵያ ለሀገር ውስጥና ለአፍሪካ አባል ሀገራት የኒኩለር ሳይንስና ቴክኖሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም እንዲሰጥ ስምምነት ላይ የተደረሰው፤ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ አለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ (IAEA)፣ በ #ቻይና መንግስት የቺንጓ ዩኒቨርሲቲ፣ እንዲሁም የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ባደረጉት የምክክር መድረክ ነው ተብሏል።

ስምምነቱ በኢትዮጵያ የኑክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም በመክፈት በኢንዱስትሪ፣ በጤና፣ በግብርና፣ በአካባቢ ሳይንስ፣ በማዕድን፣ በማኑፋክቸሪንግና በሌሎችም ዘርፎች ላይ አቅም በመፍጠር ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ፤ በኢትዮጵያ የኒኩለር ሳይንስና ቴክኖሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ለአፍሪካ አባል ሀገራት እንዲሰጥ ኢትዮጵያ የተመረጠችው “ዘርፈ ብዙ ድርድሮች ተደርገውና የማስተናገድና አቅሟ ከግምት ውስጥ ገብቶ እንደሆነ” ገልፀዋል፡፡

በኢትዮጵያ የኑኩሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ለመስጠት የሚያስችሉ ላብራቶሪና አስፈላጊ ግብዓቶች በአለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲና በቻይና መንግስት በኩል ድጋፍ እንደሚደረግ መግባባት ላይ ተደርሷል።

https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid0o1mwaQdprukv24GiZXFMEqLXyGz8hbAESJ4CsDcRdCEFQPcTL9bBFJ4sg5maoPwwl
ዜና: መንግሥት ከሠራተኞች ደመወዝ ላይ በተለያዩ ምክንያቶች የሚደረጉ ተጨማሪ ቅነሳዎችን “እንደገና እንዲያጤን” #ኢሠማኮ ጠየቀ

#የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ሀሙስ ሚያዚያ 23 ቀን 2017 ዓ.ም የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ቀንን አስመልክቶ ትናንት ሚያዚያ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ላይ መንግሥት ከሠራተኞች ደመወዝ ላይ የሚደረጉ ተጨማሪ ቅነሳዎችን “እንደገና እንዲያጤን” ጠይቋል።

ኮንፌደሬሽኑ ከሠራተኞች ደመወዝ ላይ በተለያዩ ምክንያቶች የሚደረጉ ተጨማሪ ቅነሳዎችን በዝርዝር ባያስቀምጥም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለአደጋ ስጋት ፈንድ በየወሩ ከደመወዛቸው ላይ እንዲቀነስ ሀሳብ መቅረቡ ይታወሳል።

እነዚህ ቅነሳዎች እየጨመረ የመጣውን የኑሮ ውድነትና ዝቅተኛ ደመወዝን ተከትሎ የሠራተኞችን “የኑሮ ጫና የበለጠ ያባብሳል” ሲል አስጠንቅቋል።

ከእጅ ወደ አፍ የሚኖሩ ሠራተኞች የኑሮ ውድነትን መቋቋም እንደማይችሉ እና በአሁኑ ሰዓት በዝቅተኛ ደመወዝ ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ለመደገፍ እየተቸገሩ ነው ሲል አጽንኦት ሰጥቷል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=7658
ርዕስ አንቀጽ: ፖሊስ በአዲስ ስታንዳርድ ሚዲያ ላይ ያካሄደው ብርበራ #በኢትዮጵያ የመረጃ ደህንነት ጥበቃ ላይ የተቃጣና ወደፊት መደገም የሌለበት ነው!

ተጠያቂ አልባነትን እንቃወማለን! ለዚህም የማስጠንቀቂያ ደወሉንም እናሰማለን!

ሰሞኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ በአዲስ ስታንዳርድ ሚዲያ ቢሮ ላይ ብርበራ በመፈፀም በርካታ የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎችን መውሰዱ በፕሬስ ነጻነት ላይ የተፈጸም አሳዛኝ ተግባር እና የመረጃ ነጻነት ላይ የተፈጸመ ጥቃት ነው።

የቀድሞው የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ፀሐፊ አምባሳደር ቲቦር ናጊ ሁኔታውን ለመግለፅ የተጠቀሙበትን ትክክለኛ አገላለፅ እዚህ ላይ መጠቀም ወሳኝ ሁኖ እናገኘዋለን፣ ይህ ህትመት (አዲስ ስታንዳርድ) “ኃላፊነት የጎደለው ተራ ህትመት ሳይሆን ተጨባጭ የሆነ የጋዜጠኝነት ስራ የሚያከናውን ህትመት ነው”።

ፖሊስ “ሁከት ለመቀስቀስ” ዶክመንተሪ ለመስራት በዝግጅት ላይ ስለመሆናችሁ መረጃ ደርሶኛል የሚል የፈጠራ ምክንያት በማቅረብ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን ማለትም ላፕቶፖችን፣ ሞባይል ስልኮችን፣ ሃርድ ድራይቭንና ፍላሽ ድራይቮችን ከቢሯችን አፋፍሶ ወስዶ ነበር።

ይህ በፖሊስ የቀረበው ምክንያት በሚዲያ ተቋማችን (ጃኬን አሳታሚ) በይፋ ፍጹም ሀሰት መሆኑን የሚገልጽ ማስተባበያ መግለጫ ከመሰጠቱም በላይ በፍርድ ቤት ምንም ዓይነት ክስ መመስረት አለመቻሉ ልብ ሊባልልን ይገባል።

ይልቁንም ይህ የፖሊስ ተግባር ያልተለመደ፣ የመረጃ ነጻነትና ደህንነትን ለመጋፋት እንዲሁም ጥቃት ለማድረስ በማለም የተደረገ ግልጽ ሙከራ ነው።

እነዚህን ጥሰቶች ከወዲሁ መከላከል ካልተቻለ የሚያስከትሉት መዘዝ እና የሚያሳድሩት ጠባሳ ከዚህ የሚዲያ ተቋም ያለፈ እጅግ የላቀ ይሆናል።

https://addisstandard.com/Amharic/?p=7662
#አዲስ_አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ “ከእውቀት እናት የማይጠበቅ ተገቢ ያልሆነ ቅጣት” የፈጸመች መምህርት “ከስራ በማገድ በህግ ጥላ ስር” እንድትውል ማድረጉን ገለፀ

ሚያዝያ 23/2017 ዓ.ም. - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በሰላም በር ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2ኛ ክፍለ ተማሪን “የቤት ስራ አልሰራሽም” በማለት ተገቢ ያልሆነ ቅጣት የፈጸመች መምህርት “ከስራ በማገድ በህግ ጥላ ስር” እንድትውል ማድረጉን ገለፀ፡፡

“ትውልድን ከመቅረፅ፣ የነገ ሀገር ተረካቢ ተተኪ ዜጋን ከመፍጠርና የቀለም እናት ከመሆን ባለፈ ከእናት የማይጠበቅ ፤ ያለንበትን ዘመንና ወቅት የማይዋጅና የማይመጥን መሰል ድርጊት መፈጸም ተገቢ አለመሆኑን” የገለፀው ቢሮው ድርጊቱ እንደተፈጸመ ጥብቅ ክትትል በማድረግ ወዲያዉኑ የማጣራት ስራዎች እንዲሰሩና መምህርቷ በህግ ከለላ ውስጥ እንድትሆን መደረጉን በመግለፅ፤ “ጉዳዩም በህግ አግባብ እንዲታይና ፍትህ እንዲያገኝ በትኩረት እየሰራ ይገኛል” በማለት አክሎ አብራርቷል፡፡

ጉዳቱ የደረሰባት ተማሪንም በሚመለከት “ህክምና አግኝታ በጥሩ የጤንንነት ሁኔታ ላይ የምትገኝ ሲሆን በነገው እለትም ትምህርቷን የምትጀምር ይሆናል” በማለት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ገልጿል፡፡

ትምህርት ቢሮው “መሰል ችግሮች እንዳይፈጸሙና ለሌሎችም ትምህርት እንዲሆን” ይህንን እርምጃ የወሰደ ገልፆ፤ በህግ አግባብ የሚሰጠዉን ውሳኔም ተከታትሎ በቀጣይ የሚያሳውቅ መሆኑን አብራርቷል፡፡
ዜና፡ በደቡብ አፍሪካ 44 #ኢትዮጵያውያን አንድ ቤት ውስጥ ተቆልፎባቸው መገኘታቸውን የሀገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ

በደቡብ አፍሪካ #ጁሃንስበርግ 44 ኢትዮጵያውያን አንድ ቤት ውስጥ ተቆልፎባቸው መገኘታቸውን የሀገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ።

በጁሃንስበርግ በአንድ ቤት ውስጥ ተቆልፎባቸው በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ናቸው የተባሉት 44ቱ ኢትዮጵያውያኑ በህገወጥ አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ወደ ደቡብ አፍሪካ የገቡ ሳይሆኑ አልቀሩም ሲል ፖሊስ ገልጿል።

ትላንት ሚያዚያ 23 ቀን 2017 ሰባት ሰአት ተኩል አከባቢ በአንድ ቤት ግቢ ውስጥ አጠራጣሪ ድምጽ በመሰማቱ ፖሊስ ኦፐሬሽኑን ማካሄዱን የሀገሪቱ ጋዜጣ ኒውስ 24 ተመለከትኩት ያለውን የጆሃንስበርግ ፖሊስ ሪፖርት ዋቢ በማድረግ አስነብቧል።

የከተማዋ ፖሊሶች ወደ ቤቱ ቅጥር ግቡ በመግባት ፍተሻ ሲያደርጉ በሁለት ክፍል ውስጥ 44 ኢትዮጵያውያኑ ተቆልፎባቸው መገኘታቸውን ዘገባው አመላክቷል።

አንዱ ብቻ በተሰባበረ እንግሊዝኝ ከፖሊሶች ጋር ለመነጋገር መሞከሩን የጠቆመው ዘገባው ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ለፖሊስ መግለጹን አስታውቋል።

በግቢው ውስጥ የነበረው ሁኔታ አስከፊ መሆኑን ፖሊስ በሪፖርቱ አመላክቷል ያለው ዘገባው ኢትዮጵያውያኑ በቂ ምግብ እንዳልቀረበላቸው፣ ከተቆለፈባቸው ክፍል እንዳይወጡ መደረጋቸውና የፀሃይ ብርሃን አይተው እንደማያውቁ እንዲሁም ደህና ልብስ እንኳ እንደሌላቸው አስታውቋል።

ባሳለፍነው አመት 2016 ዓ.ም ሐምሌ ወር ላይ የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ “ኢ-ሰብአዊ በሆነ ሁኔታ” ታጋተው የነበሩ ናቸው ያላቸው 90 ኢትዮጵያውያንን አስለቅቂያለሁ ሲል መግለጹን የተመለከተ ዘገባ ማቅረባችን ይታወሳል።
ዜና፡ “#በአፋርና #በኦሮሚያ ክልል ለአፈር ማዳበሪያ ግብአትነት የሚውል 371 ሚሊየን ቶን የፖታሽ እና ፎስፌት የማዕድን ክምችት መኖሩን ባካሄድኩት ጥናት አረጋግጫለሁ” - ኢንስቲትዩቱ

ኢትዮጵየ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት በአፋር እና በኦሮሚያ ክልል አካሄድኩት ባለው ጥናት ለአፈር ማዳበሪያ ግብአትነት የሚውል 371 ሚሊየን ቶን የፖታሽ እና የማዕድን ክምችት መኖሩን አረጋግጫሉ ሲል ገለጸ።

ከዚህ ቀደም በአፋር ክልል በሸከት (አብአላ) ከተማ ዳሎል ላይ ባአካሄድኩት የማዕድን ፍለጋ 191 ሚሊዬን ቶን የፖታሽ ክምችት መኖሩን በጥናት አረጋግጫለሁ ያለው ኢንስቲትዩቱ በኦሮሚያ ክልል በባሌ ዞን መልካ አርባ እና መካና ጎበሌ አካባቢ180 ሚሊዮን ቶን የፎስፌት ማዕድን ክምችት እንዳለ ያካሄድኩት ጥናት አመላክቶኛል ብሏል።

በአሁኑ ወቅት እነዚህ ማዕድናቶች ጋር በተያያዘ በመልካ አርባ እና መካና ጎበሌ አካባቢ ቀጣይነት ያለው ጥናት በስፋት እያካሄድኩ ነው ሲል ጠቁሟል።

የጥናቴ አላማ የግብርና ዘርፉን በማጠናከር ከውጭ በሚገቡ ማዳበሪያዎች ላይ ያለውን ጥገኝነት በመቀነስ ለምግብ ዋስትና እና ለኢኮኖሚ ዕድገት ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ያለመ ነው ሲል ገልጿል።

የሀገር ውስጥ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ የአፈር ማዳበሪያ ላይ ጥናት እያካሄድኩ ነው ሲል ኢትዮጵየ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት ባጋራው መረጃ አስታውቋል።

================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
ዜና፡ በሱዳን በስደተኞች መጠለያ ባጋጠመ የእሳት አደጋ አንዲት ነፍሰጡር #ኢትዮጵያዊት ከሶስት ልጆቿ ጋር ህይወቷ ማለፉ ተገለጸ

#በሱዳን ኡምጉርጉር መጠለያ ካምፕ ውስጥ በተነሳ የእሳት አደጋ አንዲት ነፍሰጡር ኢትዮጵያዊት እናት ከሶስት ልጆቿ ጋር ህይወቷ ማለፉ ተገለጸ።

ህይወቷ ያለፈው ነፍሰጡሯ እናት በትግራይ በተካሄደው ጦርነት ሳቢያ ከቀየዋ ተፈናቅላ ወደ ሱዳን በመሰደደ በመጠላያ ካምፕ ውስጥ የምትኖር መሆኗ ተጠቁሟል።

እስካሁን ኢትዮጵያውያኑ ተጠልለውባቸው በሚገኙ የሱዳን የስደተኞች ካምፕ ውስጥ በእሳት አደጋ ምክንያት የ10 ኢትዮጵያውያን ህይወት ማለፉን ከትግራይ ቴሌቪዢን ያገኘነው ዘገባ ያሳያል።

በፕሪቶርያው ስምምነት ሙሉ በሙሉ አለመተግበሩ ስደተኞቹ ወደ ሀገራቸው መመለስ አለመቻላቸውነ ዘገባው አመላክቷል።

በተያያዘ ዜና በትግራይ ክልል በአብይ አዲ ከተማ በጣለ ከፍተኛ ዝናብ ሳቢያ የተፈጠረ ጎርፍ በከተማዋ በሚገኘው የተፈናቃዮች ካምፕ ውስጥ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል።

በካምፑ በሚገኙ የተፈናቃዮች መኖሪያ ጎርፉ በመግባቱ በጠና ታማሚ እናቶች እና ህፃናት ላይ ጉዳት ማድረሱን የማዕከሉ አስተባባሪዎች መናገራቸውን ከትግራይ ቴሌቪዢን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የጉዳቱ መጠን እና የተጎጂዎችን ብዛት እያጣራን ነው ሲሉ ማዕከላቱ አስተባባሪዎች መግለጻቸውን ዘገባው አመላክቷል።

================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
ዜና፡ የአውሮፓ ህብረት እንዲሁም መቀመጫቸው አዲስ አበባ የሆነ 14 ኤምባሲዎች #በኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉ እንዳሳሰባቸው ገለጹ

ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን ባወጣው ሪፖርት ዘንድሮ ኢትዮጵያ ከ180 ሀገራት ውስጥ 145ኛ ደረጃ ይዛለች፣ ከ100 ነጥብ ያስመዘገበችው 37 አይሞላም

የአለም የፕሬስ ነጻነት ቀን በየአመቱ ሚያዚያ 25 ቀን 2017 ዓ.ም መከበርን አስመልክቶ #የአውሮፓ ህብረት እንዲሁም መቀመጫቸው አዲስ አበባ የሆነ 14 ኤምባሲዎች በጋራ ባወጡት መግለጫ በኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉ እጅግ እንዳሳሰባቸው አስታወቁ።

ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች መብት ቡድነ በበኩሉ የዘንድሮን የ2025 እ.አ.አ የሀገራትን የፕሬስ ነጻነት አስመልክቶ ባወጣው ደረጃ እና ሪፖርት “የኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉን” አስታውቋል፤ ከ100 ነጥብ ውስጥ 36 ነጥብ 92 በማስመዝገብ 180 ሀገራት መካከል 145ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ጠቁሟል።

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል (EHRDC) በበኩሉ ትላንት ሚያዚያ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ “ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመገናኛ ብዙሃን ላይ ጫናዎች እየበረቱ መምጣታቸውን በመግለጽ እጅግ አሳስቦኛል ብሏል።

https://addisstandard.com/Amharic/?p=7671