Addis Standard Amharic
17.7K subscribers
4.03K photos
101 videos
3 files
3.24K links
አዲስ ስታንዳርድ በጃኬን አሳታሚ ኃ.የተ.የግ.ማ. ባለቤትነት ስር የሚታተም በኢትዮጵያ የሚገኝ ነፃ እና ገለልተኛ ሚዲያ ነው። አዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የአዲስ ስታንዳርድ እንግሊዝኛ ሕትመት አካል ነው።
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአገር ውስጥ ሚዲያዎች #ኢትዮጵያ ላይ የሚነዙ “የተፈበረኩ የሀሰት ትርክቶችን” እንዲመክቱ ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) አሳሰቡ

"ኢትዮጵያ በርካታ ሜጋ ፕሮጀክቶችን እያከናወነች ትገኛለች፣ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ሊጠናቀቀ ጥቂት ቃናት ቀርተውታል፣ የቀይ ባህር ጉዞአችንም ከግማሽ መንገድ በላይ ተራምዷል" ያሉት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)፤ በዚህም በተለያየ መልኩ "የኢትዮጵያ መዳከም የሚፈልጉ ታሪካዊ ጠላቶች፣ የውስጥ ባንዳዎች እና ሌሎች ኃይሎች ከፍተኛ የሆነ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ከፍተውብናል" ብለዋል።

በዚህም የኢትዮጵያ ሚዲያዎች በዲጂታል መድረክ ተሳስረው የኢትዮጵያን ገጽታ በማጉላት “የሚቃጣባትን ጥቃት፣ የሚነዛባትን የተፈበረኩ የሀሰት ትርክቶችን” እንዲመክቱ አሳስበዋል።

ይመልከቱ
ዜና: የ #አሜሪካ ሴናተር ቴድ ክሩዝ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለ #ሶማሊላንድ እውቅና እንዲሰጡ ያቀረቡትን ጥሪ የሶማሊላንድ ባለስልጣናት እና ታዋቂ ግለሰቦች አደነቁ

የሶማሊላንድ ባለስልጣናት እና ታዋቂ ግለሰቦች የአሜሪካ ሴናተር ቴድ ክሩዝ ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለሶማሊላንድ እንደ እውቅና እንዲሰጡ ያቀረቡትን ጥሪ በደስታ ተቀብለዋል። ጥሪውም ለብዙ አስርት አመታት ሲታገሉለት ለነበረው እውቅና ትልቅ ድጋፍ እንደሆነ ገልጸዋል።

የሴኔቱ የአፍሪካ እና ግሎባል ጤና ፖሊሲ ንዑስ ኮሚቴ ሊቀመንበር የሆኑት ሴናተር ቴድ ክሩዝ ለፕሬዝዳንት ትራምፕ በጻፉት ደብዳቤ፣ ሶማሊላንድን “ለአሜሪካ ወሳኝ የደህንነት እና የዲፕሎማሲ አጋር” በማለት ያሞካሹ ሲሆን፣ “እውቅና እንዲሰጣትም” አሳስበዋል።

በደብዳቤያቸው፣ ሶማሊላንድ በቀይ ባህር ዳርቻ ላይ ያላትን ስትራቴጂያዊ አቀማመጥ፣ ጠንካራ የጦር ሃይል እና ለፀረ-ሽብርተኝነትና ፀረ-ወንበዴ ዘመቻዎች ያበረከተችውን አስተዋጽኦ ጠቅሰዋል። በተጨማሪም “ከቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ እና ከመሳሰሉ ተቀናቃኞች ከፍተኛ ጫና ቢደርስባትም” ሶማሊላንድ “ከአሜሪካ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ለመፍጠር ቁርጠኛ መሆኗን” ገልጸዋል።

የሴናተር ክሩዝ ደብዳቤ የቀረበው የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን መሀመድ አብዲላሂ ኢሮ ወደ አሜሪካ ሊያደርጉት ባቀዱት ጉዞ ዋዜማ ላይ ነው። በዚህ ሳምንት፣ ሚኒስትሩ አብዲራህማን ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደገለጹት፣ ፕሬዝዳንቱ ወደ አሜሪካ በቅርብ ቀናት ውስጥ ይፋዊ ጉዞ ያደርጋሉ።

ተጨማሪ ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8884
ዜና፡ በ #አማራ ክልል መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ተፈናቃዮች በ #ኦሮሚያ ክልል ላላቸው መሬት ግብር ካልከፈሉ “ይወረሳል" መባላቸውን ተናገሩ

ተፈናቃዮቹ "ዱቄት እየለመንን እየኖርን ግብር መክፈል እንዴት እንችላለን?" ሲሉ ጠይቀዋል


ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ እና ከምዕራብ ሸዋ ዞን ዳኖ ወረዳ ተፈናቅለው በአማራ ክልል ጃራ እና ቻይና መጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮች "ተገደን ጥለነው ለመጣነው መሬት” “ግብር ካልከፈላችሁ ይወረሳል" ተባልን ሲሉ ቅሬታቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።

ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ዳኖ ወረዳ ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን ከተማ በሚገኘው ቻይና ካምፕ ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃይ፤ ከቀበሌ ኃላፊዎች ተደውሎላቸው የመሬት ግብር የማይከፍሉ ከሆነ “ንብረታቸው እንደሚወረስባቸው እና ወደ መሬት አስተዳደር እንደሚገባ” እንደተነገራቸው ገልጸዋል።

ከምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ተፈናቅለው በጃራ መጠለያ ተጠልለው የሚገኙ ሌላ ተፈናቃይ፤ ምንም እንኳ ኪረሙ በሚኖር የአጎታቸው ልጅ በኩል የመሬት ግብሩ ቢከፈልላቸውም "አሁን ላይ መሬታቸውን ሌላ ሰው ነው እያረሰ መሆኑን" ተናግረዋል።

የኪረሙ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አለባቸው ዋይሳ ለአዲስ ስታንዳርድ በሰጡት መላሽ፤ "መሬት ይወረሳል አልተባለም" ሲሉ አስተባብለዋል። አክለውም "የግብር ክፍያው ከቀዬአቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ተጠልለው ለሚገኙ ሰዎች አልተጠየቀም እንደዛ የሚል አመራር ካለ እናጣራለን" ብለዋል።

ሙሉውን ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8888
ዜና፡ #የኢትዮጵያ ሶሻል-ዴሞክራቲክ ፓርቲ ዶ/ር ራሔል ባፌን ሊቀመንበሩ አድርጎ መረጠ

- አራት የፓርቲው የስራ አስፈጻሚዎችን ከሃላፊነት ተነስተው በአባልነት እንዲቀጥሉ ውሳኔ አሳልፏል

የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) ማዕከላዊ ምክር ቤት ከነሐሴ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ዶ/ር ራሔል ባፌን ሊቀመንበሩ አድርጎ መምረጡን የፓርቲው ማዕከላዊ ምክር ቤት ትላንት ነሃሴ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

መግለጫው በተጨማሪም አራት የሥራ አስፈጻሚ አባላቱን ከሥራ ኃላፊነት ማንሳቱን ጠቁሟል፤ በአባልነት እንዲቀጥሉ በአብላጫ ድምፅ መወሰኑን ገልጿል።

ከፓርቲዉ ፕሮግራምና ርዕዮተ- ዓለም ጋር ከሚመሳሰሉ የፖለቲካ ፓራቲዎች ጋር በጣምራ ወይም በቅንጅት ወይም በግንባር ለመደራጀት ፈቃደኛ መሆኑን በመግለጽ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ጥሪ አቅርቧል።

ከታጣቂዎች ጋር የተኩስ ማቆም ስምምነት/የተናጠል እንደአስፈላጊነቱ ስለሚመቻችበት መንገድ መንግሥት ቅድሚያ ሰጥቶ እንዲንቀሳቀስ ሲልም ጠይቋል።

https://addisstandard.com/Amharic/?p=8896
ዜና፡ የ #ኦሮሞ_ነፃነት_ሠራዊት የአሜሪካን የሰብዓዊ መብቶች ሪፖርት ተቀበለ፤ ተፈፅመዋል በተባሉ ወንጀሎች ላይ ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ጠየቀ

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት( ኦነሠ) በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ላይ የወጣውን የ2024 የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሪፖርት በመቀበል በሪፖርቱ የተገለጹ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ ዓለም አቀፍ አካል እንዲመረመሩ ጥሪ አቀረበ። በተጨማሪም አሜሪካ ለኢትዮጵያ መንግስት የምትሰጠውን ድጋፍ እንድታጤነውም አሳስቧል።

ኦነሠ ነሐሴ 7 ቀን 2017 በወጣው መግለጫ፤ ሪፖርቱ “ባለፉት ሰባት ዓመታት ሕዝባችን የኖረውን እውነት፣ ስርዓታዊ ሽብር፣ በመንግስት የተቀናጀ ጭካኔ እና ስር የሰደደ አለመከሰስን ዳግም አረጋግጧል” ብሏል።

ኦነሠ በሪፖርቱ በተወሰነ ቦታ ብቻ መጠራቱን በተመለከተም፤ እንደ ሮይተርስና ዋሽንግተን ፖስት ያሉ ገለልተኛና ተዓማኒ የሆኑ የሚዲያ ተቋማት ያደረጓቸው ምርመራዎች፤ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ፈፀመው ተብለው ከተገለጹ ወንጀሎች መካከል አብዛኛዎቹ የተፈጸሙት በመንግስት ኃይሎች ወይም በመንግስት ድጋፍ በሚሰጣቸው ቡድኖች መሆኑን አረጋግጠዋል ብሏል።

አክሎም በተከሰሰበት ወንጀሎች ላይ መርመራ እንዲደረግ ከገለልተኛ አካላት ጋር ለመተባበር ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል።

ተጨማሪ ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8900
ዜና: አገልግሎቱ በአዲስ አበባ ከኃይል መቆራረጥ ጋራ በተያያዘ ከ25 ሺህ በላይ ችግሮች ተለይተዋል አለ

በአዲስ አበባ ከተማ ከኃይል መቆራረጥ ችግር ጋራ በተያያዘ ከ25 ሺህ በላይ ችግሮች ተለይተው 54 በመቶ የሚሆኑት መቀረፋቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።

የአገልግሎቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመት በአጠቃላይ 63.12 ቢሊዮን ብር ገቢ መገኘቱን ዛሬ በሰጡት መግለጫ ጠቅሰው፤ ገቢው ከ2016 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ48 ነጥብ 6 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል። ገቢው ከኃይል ሽያጭ፣ ከምሰሶ ሊዝ፣ከማማከር አገልግሎት፣ ከማያገለግሉ ንብረቶች ሽያጭ የተገኘ መሆኑም ተመላክቷል።

ታሪፍ ጭማሪን በተመለከተ "ታሪፉ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የማህበረሰብ ክፍል ያማከለ አይደለም" በሚል ከመገናኛ ብዙሃን ለተነሳላቸው ጥያቄ ሲመልሱም "በአለም ላይ እጅግ ዝቅተኛ ታሪፍ ያለው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፤ የተደረገው ጭማሪም መጠነኛ ነው" ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8903
ዜና: #ኮሚሽኑ የሲኖትራክ ተሸከርካሪ የጥራት ጉድለት ሳይሻሻል ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ መታገዱን አስታወቀ

የጉምሩክ ኮሚሽን የሲኖትራክ ተሽከርካሪ ያለበትን የጥራት እና የቴክኒክ ችግር እስኪያሻሽል ድረስ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ ማገዱን አስታውቋል።

የጥራት ጉድለቱ በየጊዜው የሰው ሕይወት ብሎም ንብረት እንዲጠፋ ምክንያት በመሆኑ፤ አምራች ድርጅቱ ማሻሻያ እስከሚያደርግ ድረስ ተሸከርካሪው ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ መከልከሉ ተገልጿል።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የሲኖትራክ ተሽከርካሪዎች ላይ ባለው የጥራት እና የቴክኒክ ጉድለት ምክንያት በሰው ሕይወት ላይ በየጊዜው አደጋ እያደረሰ መሆኑን በመጥቀስ ለጉምሩክ ኮሚሽን ተሽከርካሪዎቹ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ በላከው ደብዳቤ ገልጿል።

አዲስ ስታንዳርድ የተመለከተው ደብዳቤ ተሽከርካሪውን የሚያመርተው ኩባንያ በምርቶቹ ላይ ማስተካከያ እስከሚያደርግ ድረስ ከግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ክልከላው ተግባራዊ መደረጉን ይገልጻል።

ይሁን እንጂ የሚንስቴር መስሪያ ቤቱን ፊርማ እና ማህተም በማስመሰል የሲኖትራክ ማስገቢያ ፍቃድ በማሰራት ለማስገባት የሚሞክሩ ሰዎች መኖራቸውን ጠቅሶ ከተጠቀሰው ዕለት ጀምሮ ምንም ዓይነት የማስገቢያ ፈቃድ አለመሰጠቱን ጠቁሟል።

================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
የምስራቅ አፍሪካ በአፍሪካ ልማት ባንክ የገንዘብ ድጋፍ ከሚደረግላቸው ፕሮጀክቶች በግዥ ማጭበርበር እና ሌሎች ማዕቀብ የሚጣሉባቸው ተግባራት ቀዳሚ ነው ተባለ

በቅርቡ ይፋ የሆነ አንድ ጥናት እንደሚያመለክተው፣ በአፍሪካ ልማት ባንክ (AfDB) የገንዘብ ድጋፍ በሚደረግላቸው ፕሮጀክቶች ውስጥ የምስራቅ አፍሪካ ለግዥ ማጭበርበር እና ሌሎች ማዕቀብ የሚጣሉባቸው ተግባራት ማዕከል ሆኗል።

በአፍሪካ ልማት ባንክ የኢንተግሪቲ እና ፀረ-ሙስና ፅህፈት ቤት (PIAC) ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት፣ እ.አ.አ. በ2024 በአጠቃላይ 59 ቅሬታዎች ቀርበዋል።

ቅሬታዎቹ እንደ ማጭበርበር፣ ሙስና፣ ሽርክና (collusion) እና ማስገደድ (coercion) ከመሳሰሉ ማዕቀብ የሚጣሉባቸው ተግባራት ጋር የተያያዙ ናቸው።

ከሁሉም ክልሎች በላቀ ደረጃ፣ የምስራቅ አፍሪካ ከጠቅላላው ክሶች 33 በመቶውን ወይም 19 የሚሆኑ ጉዳዮችን የያዘ ሲሆን፣ ቀጥሎም ምዕራብ አፍሪካ በ29 በመቶ ይከተላል። ሌሎች ክልሎች፣ ማለትም ሰሜን፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ አፍሪካ፣ ከምዕራብ አፍሪካ አሃዝ ከግማሽ በታች አስተዋፅዖ አድርገዋል።

ዘገባው “ይህ አዝማሚያ ባለፉት ዓመታት በተከታታይ የተከሰተ ነው” ብሏል።

ተጨማሪ ለማንበብ
https://www.facebook.com/share/p/1ACVjHRKue/?mibextid=wwXIfr

================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
‘ስምምነት እስኪፈጠር ድረስ ስምምነት የለም’: የ #ትራምፕ እና #ፑቲን ንግግር #ሩሲያ#ዩክሬን ላይ የከፈተችውን ጦርነት ለማስቆም ውጤት አላስገኘም

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና በሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን መካከል የተደረገው የመሪዎች ስብሰባ፣ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችውን ጦርነት በዘለቄታም ሆነ ለአፍታ ለማቆም የሚያስችል ስምምነት ላይ አለመደረሱን ተዘገበ።

ሆኖም እንደ ሮይተርስ ዘገባ፣ ሁለቱም መሪዎች ወደየአገራቸው ከመመለሳቸው በፊት ንግግሩ ፍሬያማ እንደነበር ገልጸዋል።

አርብ ዕለት በአላስካ ውስጥ በተደረገው የሶስት ሰዓታት ስብሰባ ማብቂያ ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት አጭር መግለጫ፣ ሁለቱ መሪዎች በግልፅ ባላብራሩት ጉዳዮች ላይ መሻሻል ማሳየታቸውን ተናግረዋል። ይሁንና ምንም አይነት ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል፥ ለጋዜጠኞች ጥያቄም ምላሽ አልሰጡም።

በተለምዶ ብዙ ንግግር የሚያደርጉት ትራምፕ በጋዜጠኞች የተሰነዘሩለትን ጥያቄዎች ሳይመልሱ እንዳለፉም ዘገባው ጨምሮ ገልጿል።

ሆኖም ግን ትራምፕ “ሰላምን ፍለጋ” በሚል ጽሁፍ ፊት ለፊት ቆመው፣ “አንዳንድ መሻሻሎች አሳይተናል” ብለዋል። አክለውም “ስምምነት እስከሚፈጠር ድረስ ስምምነት የለም” ሲሉ ተናግረዋል።

ውይይቱ በአውሮፓ በ80 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ የሞት አደጋን ያስከተለውን የዩክሬን ጦርነት ማስቆም ትራምፕ ከስብሰባው በፊት ካስቀመጧቸው ግቦች አንዱ ቢሆንም፣ ወዲያውኑ ውጤት ያስገኘ አይመስልም።

ይሁን እንጂ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሩሲያ እ.አ.አ. ከ2022 ጀምሮ በዩክሬን ላይ ሙሉ ወረራ ከፈጸመች በኋላ በምዕራባውያን መሪዎች ተገልለው የቆዩ በመሆናቸው፣ ከአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጋር ፊት ለፊት መገናኘታቸው ብቻ እንደ ድል ተቆጥሯል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለ5 ቀን የሚቆይ አውደ ርዕይ ማዘጋጀቱን አስታወቀ

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ "ሚድሮክ ለሀገር!" በሚል መሪ ቃል ከነሐሴ 26 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ለ5 ቀን የሚቆይ አውደ ርዕይ በሚሊኒየም አዳራሽ ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ኮርፖቴት የኮሚኒኬሽን እና ፕሮሞሽን ዳይሬክተር አቶ ሁናቸው ታዬ በጋዜጣዊ መግለጫው፤ አቶ ሁናቸው በአወደ ርዕዩ 45 ኪባንያዎች ምርትና አገልግሎታቸውን ይዘው እንደሚሳተፉ ገልጸዋል።

ድርጅቱ በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች “በማህበረሰቡ ጥበቃ ያለ ምንም እንከን” ምርቶቹን እያመረተ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ለዚህም ዋነኛው ምክንያት ከሚያገኘው አጠቃላይ ገቢ 10 በመቶ የሚሆነው ትርፍ ለማህበረሰብ አገልግሎት የሚውል መሆኑ ነው ብለዋል።

https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid02zVubcehQmruw7VZKJ2Hh6QwFjwzU8AG5HgHDcstFc4bS26ySPpscMWgLUY8u8HiQl
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በመዲናዋ ያሉ ዛፎች ስታንዳርዳቸውን ጠብቀው ባለመተከላቸው አብዛኞቹ መቆረጣቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው ገለጹ።

ከተማ ውጥ ያሉ ዛፎት ከኤክትሪክ ፖሎች ሶስት ሜትር መራቅ እንዳለባቸው የገለጹት ስራ አስፈጻሚው፤ ይህን ስታንዳርድ ባለመጠበቃቸው አገልግሎቱ ላይ ችግር መፍጠራቸውን ገልጸዋል።

በዚህም ምክንያት አብዛኞቹ ዛፎች መቆረጣቸውን አመላክተዋል። ሙሉውን ይመልከቱ!
ዜና: የ #ሪፖርተር ጋዜጣ ባልደረባ የሆነው ጋዜጠኛ ዮናስ አማረ "ባልታወቁና ጭምብል ባደረጉ ሰዎች" መወሰዱ ተገለጸ

የሪፖርተር ጋዜጣ ባልደረባ የሆነው ጋዜጠኛ ዮናስ አማረ "ባልታወቁና ጭምብል ባደረጉ ሰዎች" ከሚኖርበት ከሸገር ከተማ ኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒዬም ረቡዕ ነሐሴ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት ላይ መወሰዱን የአከባቢው የጥበቃ ሰራተኞች ነገሩኝ ብሎ ሪፖርተር ጋዜጣ አስታውቋል።

ጋዜጠኛ ዮናስ አማረ ላለፉት አራት ቀናት ማለትም ከነሐሴ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ባለመግባቱ በእጅ ስልኩ ላይ ቢደወልለትም ሆነ ከቤተሰቦቹ ለማጣራት ቢሞከርም ማግኘት አለመቻሉም ተጠቁሟል።

ጋዜጠኛውን እነማን እንደወሰዱትና የት እንደተወሰደ እስከ አሁን ድረስ ማወቅ አልተቻለም ተብሏል።

================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
ዜና፡ ንግድ ባንክ በሁለት ሳምንታት ውስጥ ብቻ ከአንድ ሺ በላይ ለሚሆኑ ደንበኞቹ 541 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የውጪ ምንዛሪ ክፍያ ፈጽሚያለሁ አለ

#የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሁለት ሳምንታት ውስጥ ብቻ አንድ ሺ 140 ለሚሆኑ ደንበኞቹ 541 ነጥብ 4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የውጪ ምንዛሪ ክፍያ ፈጽሚያለሁ ሲል ገለጸ።

ከሐምሌ 22 እስከ ነሃሴ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ባሉት ቀናት በአጠቃላይ ለባንኩ አንድ ሺ 140 ደንበኞች 541 ነጥብ 4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተመጣጣኝ የውጭ ምንዛሪ ፈቅጃለሁ ሲል በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጾቹ ባጋራው መረጃ አስታውቋል።

በአንድ ቀን ብቻ ማለትም ነሐሴ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ለባንኩ የቀረቡ የውጭ ምንዛሪ የደንበኞች ማመልከቻዎችን ሁሉንም ማጽደቁን የጠቆመው ባንኩ በዚህም የ420 ነጥብ 4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን የተለያዩ የውጭ ምንዛሪ ዓይነቶች ለተለያዩ ፍላጎቶች መፍቀዱን አመላክቷል።

ባንኩ ከሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለገቢ ንግድና ለአገልግሎት ክፍያዎች በአጠቃላይ ከአንድ ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ክፍያ መፈጸሙንም አስታውቋል።

ይህም የተሰጠው የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ ከነዳጅ፣ ማዳበሪያ እና ሌሎች የአገልግሎት ክፍያዎች ጋር በተያያዘ በየቀኑ ከሚሰጠው መደበኛ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በተጨማሪ የተሰጠ መሆኑን ጠቁሟል።

================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
ዜና: ከመስከረም ወር ጀምሮ ለሰራተኛው የደመወዝ ጭማሪ ሊያደርግ መሆኑን መንግስት አስታወቀ፤ የድግሪ ተመራቂ መነሻ ደመወዝ 11 ሺህ 500 ብር ይሆናል ተብሏል

መንግስት ከመስከረም ወር 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ሊያደርግ መሆኑን የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ፤ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂ መነሻ ደመወዝ ከ6 ሺህ 940 ብር ወደ 11 ሺህ 500 ብር እንደሚሻሻል ጠቁሟል።

ኮሚሽኑ ዛሬ ነሐሴ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፤ መንግሥት የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሀገር ዐቅም የሚፈቅደውን እርምጃ እየወሰደ ይገኛል ብሏል፡፡

የደመወዝ ማስተካከያው ከ160 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት እንደሚጠይቅ ያስታወቀው የኮሚሽኑ መግለጫ፤ ይሄም ለደመወዝ የሚወጣውን ጠቅላላ ዓመታዊ የመንግሥት ወጪ 56ዐ ቢሊዮን ብር እንደሚያደርሰው ተገልጿል።

https://addisstandard.com/Amharic/?p=8908
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በዲጂታል ንግድ ላይ የተሰማሩ አካላት ወደ ግብር ስርዓት ሊገቡ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ጉዳዮች ትምህርት ዳይሬክተር ብርሃኑ ሲሳይ ተናገሩ

ዳይሬክተር እንደ ዩቱዩብና ቲክቶክ ያሉ የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም ገቢ የሚያገኙ ሰዎችም ወደ ታስክ ስርዓት ይገባሉ ብለዋል።
ዜና፡ ጋዜጠኛ አብዱልሰመድ መሐመድ እና ዮናስ አማረ ያሉበትን ሁኔታ መንግስት በግልፅ እንዲያሳውቅ #ኢዜማ እና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር ጠየቁ

#ኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር፤ ጋዜጠኛ አብዱልሰመድ መሐመድ እና ጋዜጠኛ ዮናስ አማረ “ከሕግ አግባብ ውጪ መሰወራቸውን” በመግለጽ ያሉበትን ሁኔታ መንግስት በግልፅ እንዲያሳውቅ በተናጥል ባወጡት መግለጫ ጠየቁ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበርም በበኩሉ ትናንት ባወጣው መግለጫ "ጋዜጠኞቹ በወንጀል ተጠርጥረው ቢሆን እንኳን በሕግ አግባብ ተይዘው በ48 ሰዓት ፍርድ ቤት መቅረብ ሲገባቸው፣ ያሉበት አለመታወቁ በእጅገ ያሳስበናል" ብሏል።

ኢዜማ በበኩሉ፤ "በመንግሥት በኩልም በተደጋጋሚ ያለአግባብ ያሠርኩት ጋዜጠኛም ሆነ ዜጋ የለም የሚል ምላሽ ሲሰጥም ተመልክተናል" ሲል ጠቅሶ፣ “መንግሥት ድርጊቱን እየፈፀመ እየደበቀው ወይም ከመንግሥት እውቅና ውጪ በሌሎች የተደራጁ አካላት እየተፈፀመ መሆኑን የሚያሳይ ነው” ብሏል።

ተጨማሪ ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8911
ዜና፡ ታጣቂዎች በ #ጫንጮ በፈጸሙት ጥቃት የሦስት የ #ኦሮሚያ ኀብረት ሥራ ባንክ ሠራተኞች እና 11 የፀጥታ ኃይሎች መገደላቸው ተገለፀ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን #ሱሉልታ ወረዳ "ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቀ" ታጣቂዎች ባለፈው ሳምንት አርብ ነሐሴ 9 ቀን በተፈጸመ ጥቃት ሦስት የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ሠራተኞች እና 11 የፀጥታ ኃይሎች መገደላቸውን የባንኩ የገበያ እና ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ቶሌራ ሹላ ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል።

የባንኩ ሠራተኞች በዕለቱ ከሙሎ ቅርንጫፍ ወደ #አዲስ_አበባ በመኪና ገንዘብ በማጓጓዝ ላይ እያሉ ጠዋት በአራት ሰአት አካባቢ ጫንጮ ከተማ አካባቢ ሲደርሱ ጥቃቱ እንደተፈጸመባቸው አቶ ቶሌራ ገልጸዋል። ከጥቃቱ የተረፉ አራት ሰዎች የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኙም አስታውቀዋል።

ታጣቂዎቹ ከሰው ህይወት መቀጠፍ በስተቀር ወደ አዲስ አበባ እየተጓጓዘ በነበረው ገንዘብ ላይ የፈጸሙት “የዘረፋ ድርጊት አለመኖሩን” ኃላፊው አክለው ተናግረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8921
ዜና፡ በምዕራብ #ትግራይ ወደ ቀያቸው በተመለሱ ተፈናቃዮች ላይ የመንግስት ወታደሮች ተሳታፊ የሆኑበት ግድያ እና አፈና እየተበራከተ ይገኛል ሰል ህወሓት አስታወቀ

ወደ ቀያቸው በተመለሱ የምዕራብ ትግራይ ጸለምት ወረዳ ተፈናቃዮች ላይ “#የኢትዮጵያ መንግስት ሰራዊት ተሳታፊ የሆነበት ግድያ እና እገታ እየተበራከተ ነው” ሲል ህወሓት ከሰሰ።

በምርጫ ቦርድ ምንም አይነት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እንዳያደርግ እግድ የተላለፈበት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ነሃሴ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው ሳምንታዊ መግለጫው፤ "የኢትዮጵያ መንግስት ከለላ እሰጣችኋለሁ ብሎ እንዲመለሱ ባደረጋቸው የጸለምት ነዋሪዎችን ሊከላከልላቸው አልቻለም" ሲል ተችቷል፤ “ከሌሎች ታጣቂዎች ሊከላከልላቸው ይቅር እና እራሱ ተሳታፊ ሆኗል” ሲል ገልጿል።

“በኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች ባሳለፍነው ሳምንት በማይጸብሪ የተፈጸመው ግድያ የቅርብ ማሳያ ነው” ሲል በመግለጫው አመላክቷል።

https://addisstandard.com/Amharic/?p=8916
ዜና: መንግስት የደመወዝ ማሻሻያ እንደሚያደርግ ማስታወቁን ተከትሎ በሸቀጦች ዋጋ ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እወስዳለሁ ሲል ሚኒስቴሩ አስጠነቀቀ

መንግስት የሠራተኛውን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል ከመስከረም 2018 ዓ.ም ጀምሮ የደሞዝ ማሻሻያ ለማድረግ ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በሸቀጦች ዋጋ ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እወስዳለሁ ሲል የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) መንግስት የሠራተኛውን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል ከመስከረም 2018 ዓ.ም ጀምሮ የደሞዝ ማሻሻያ ለማድረግ ያስተላለፈው ውሳኔ የሠራተኛውን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሚያግዝ መሆኑን ጠቅሰው፤ “በአፍቅሮተ-ነዋይ የታወሩ ነጋዴዎች” ለሠራተኛው ኑሮ ማሻሻያ የሚደረገውን የደሞዝ ጭማሪ ምክንያት በማድረግ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት መሯሯጣቸው ከዚህ ቀደም ከነበረው ልምድ ተስተውሏል ብለዋል።

ሚንስትሩ ይህን ያስታወቁት የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን መንግስት ከመስከረም ወር 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ሊያደርግ መሆኑን ዛሬ ነሐሴ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ማስታወቁን ተከትሎ ነው።

https://addisstandard.com/Amharic/?p=8928
ዜና: “መንግስት የሠራተኞችን ደመወዝ በማሻሻል ያሳየውን ቁርጠኝነት የግል ድርጅቶችም ሊከተሉት ይገባል”_ ካሳሁን ፎሎ

መንግስት የሠራተኞችን ደመወዝ በማሻሻል ያሳየውን ቁርጠኝነት የግል ድርጅቶችም ሊከተሉት ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ አስገነዘቡ።

የደመወዝ ማሻሻያው የመንግስት ሰራተኛውን የኑሮ ጫና ለማቃለል አይነተኛ ሚና ይኖረዋል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ መንግስት የኑሮ ውድነቱ ቀጥተኛ ተጎጂ የሆኑ የመንግስት ሰራተኞችን የኢኮኖሚ ሁኔታ በማጤን የሠጠው ምላሽ ይደነቃል ሲሉ ተናግረዋል።

ማሻሻያው በአነስተኛ ደመወዝ እየሰሩ ያሉ ተቀጣሪዎችን የኑሮ ጫና ለማቃለል አይነተኛ ሚና ይኖረዋል ሲሉ ገልጸው መንግስት የሠራተኞችን ደመወዝ በማሻሻል ያሳየውን ቁርጠኝነት የግል ድርጅቶችም ሊከተሉት ይገባል ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8933