ዜና: #ኮሚሽኑ ከ65 ሺህ 500 በላይ የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ ማህበረሰባቸው መቀላቀላቸውን አስታወቀ
የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ከህዳር 2017 ዓ.ም አንስቶ እስከአሁን ድረስ ከ65 ሺህ 500 በላይ የቀድሞ ተዋጊዎችን በተሃድሶ ሂደት በማሳለፍ ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ ዛሬ ነሐሴ 6 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በሰላም ስምምነት እንዲሁም በመንግስት፣ በሀገር ሽማግሌዎችና በሀይማኖት አባቶች የቀረቡ ጥሪዎችን ተቀብለው ወደ ሰላም የሚመጡ የቀድሞ ተዋጊዎች የሀገሪቱ የሰላምና የልማት ኃይል እንዲሆኑ ለማስቻል እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡
በዚህም ከህዳር 2017 ዓ.ም ወዲህ ከ65 ሺህ 500 በላይ የቀድሞ ተዋጊዎችን የተሃድሶ ሂደት በማሳለፍ ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ማድረጉን ጠቁሟል፡፡
ከእነዚህም ውስጥ 53 ሺህ 319 ያህሉ ከትግራይ ክልል ሲሆኑ፥ በኦሮሚያ ክልል 5 ሺህ 365፣ በአማራ ክልል 5 ሺህ 168 እንዲሁም በአፋር ክልል 1ሺህ 712 መሆናቸው በመግለጫው ተመላክቷል፡፡
ትጥቅ ላወረዱ የቀድሞ ተዋጊዎችም የሳይኮሶሻል ድጋፍና የሲቪክ ስልጠና እንዲያገኙ በማድረግ እንዲሁም፤ ዲጂታል መታወቂያ በመስጠት እና የአጭር ጊዜ መልሶ መቀላቀል ክፍያ በመፈጸም ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ መደረጉ ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም በተሃድሶ ማዕከላት ከፌደራል መንግስትና ከክልሎች ከ1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ድጋፍ መደረጉን ገልጾ፥ የቀድሞ ተዋጊዎች በተለያዩ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በመሳተፍ በዘላቂነት እንዲቋቋሙ እየተደረገ መሆኑን ኮሚሽኑ በመግለጫው አንስቷል፡፡
https://www.facebook.com/100076048904470/posts/774388425106114/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

“#ቲክቶክን በመጠቀም ግጭት ቀስቃሽ መረጃ ሲያሰራጩ የነበሩ አምስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል”: የአዲስ አበባ ፖሊስ
አዲስ አበባ – የአዲስ አበባ ፖሊስ እንደገለጸው ከሆነ አምስት ግለሰቦችን የማህበራዊ ሚዲያ መድረክ የሆነውን ቲክቶክን በመጠቀም የከተማዋን ሰላም ለማደፍረስ እና የጸጥታ ስጋት ለመፍጠር ያለሙ እንቅስቃሴዎችን በማደራጀት ወንጀል ጠርጥሮ በቁጥጥር ስር አውሏል።
“ፖሊስ በክትትል ከደረሰባቸው መረጃዎች በተጨማሪ የህብረተሰቡን ጥቆማ መነሻ በማድረግ በህብረተሰቡ እና በከተማችን ላይ የደህንነት ስጋት ለመፍጠር በማሰብ ቲክቶክን በመጠቀም የተለያዩ መልዕክቶችን ሲያሰራጩ የነበሩ ኪሩቤል መላኩ ፣ አህመድ ሻሂር ፣ ምኺኤል አብይ፣ በረከት ዳንኤል እና አብዩ ደግአረገ የተባሉ አምስት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሏል” በማለት የከተማዋ ፖሊስ አስታውቋል። ብሩክ ተስፋዬ አርአያ የተባለ ተጠርጣሪ እያፈላለገ እንደሆነም ተናግሯል።
ተጨማሪ ለማንበብ
https://www.facebook.com/share/p/19h3douP9W/
______________________
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm

ዜና: ኢዜማ ገዥው ፓርቲ “የራሱን ድክመቶች ችላ ብሏል” ሲል ወቀሰ፤ ተጠያቂነትን እንዲቀበል እና የፕሪቶሪያው ስምምነት አለመፈጸምን እንዲፈታ ጠየቀ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ገዥው ፓርቲ በኢትዮጵያ የፖለቲካ እና የፀጥታ ሁኔታ አስመልክቶ በቅርቡ ያወጣው መግለጫ “የራሱን ድክመቶች ወደ ጎን ችላ ያለበት” እና “ለተጠያቂነት ያለውን ዝቅተኛ ተነሳሽነት ያሳየበት” ነው ሲል ወቀሰ።
የብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት ባሳለፍነው ሳምንት ባወጣው መግለጫ “ታሪካዊ ጠላቶች” እና “የውስጥ ባንዳዎች” ሲል የጠራቸው አካላት ኢትዮጵያን ለማተራመስ አዲስና የተቀናጀ ሙከራ እያደረጉ ነው ሲል ከሷል።
ፖርቲው “ከጥቂት ዓመታት በፊት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የገጠመንን ጦርነት በአሸናፊነት ተወጥተናል” ያለ ሲሆን፤ “ወታደራዊ ድላችንን በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ቋጭተናል። ዳሩ ግን ይፈልጉት የነበረው የተራዘመ ጦርነት በስምምነቱ የተጨናገፈባቸው ጠላቶቻችን ሌሎች ስልቶችን ወደ መሞከር ገብተዋል” ብሏል። እነዚህ ኃይሎች “ከሀገር ውስጥ እና ከውጪ” ሲንቀሳቀሱ ነበር ሲል ገልጿል።
ይህን የገዢው ፓርቲ መግለጫ ተከትሎ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ዛሬ ነሐሴ 6 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የብልጽግና ፓርቲ በትግራይ ክልል የነበረውን ጦርነት ለማስቆም እና የፕሪቶሪያ ስምምነትን በመፈረም ረገድ የኢትዮጵያውያንን “የጋራ አስተዋጽዖ” እና የስምምነት ድንጋጌዎችን በማሟላት ረገድ የታዩ ድክመቶችን ችላ ብሏል ሲል ወቅሷል።
ኢዜማ “ለሁከትና ብጥብጥ ተጠያቂው የውጭ ጠላቶች” ናቸው የሚለውን የገዥው ፓርቲ መግለጫ በመተቸት የመንግስት የአስተዳደር ብልሽቶች እና ግልጸኝነት አለመኖር ውጥረቶች እንዲባባሱ ምቹ ሁኔታ መፍጠራቸውን አመልክቷል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8809

Addis standard
ኢዜማ ገዥው ፓርቲ "የራሱን ድክመት ችላ ብሏል" ሲል ወቀሰ፤ ተጠያቂነትን እንዲቀበል እና የፕሪቶሪያው ስምምነት አለመፈጸምን እንዲፈታ ጠየቀ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6/ 2017 ዓ/ም፡- የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ገዥው ፓርቲ በኢትዮጵያ የፖለቲካ እና የፀጥታ ሁኔታ አስመልክቶ በቅርቡ ያወጣው መግለጫ “የራሱን ድክመት ወደ ጎን ችላ ያለበት” እና “ለተጠያቂነት ያለውን ዝቅተኛ ተነሳሽነት ያሳየበት” ነው ሲል ። የብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት ባሳለፍነው ሳምንት ባወጣው መግለጫ “ታሪካዊ ጠላቶች” እና “የውስጥ ባንዳዎች” ሲል…
ትንታኔ: የኦሮሚያ ማዕድን ልማት ባለሥልጣን የማዕድን ፈቃድ የመስጠት እና የመቆጣጠር ሙሉ ድርሻ እንዲኖረው ይሻል፤ የሆንግ ኮንጉ ሺንግሹ ማዕድን እና በርካታ ኩባንያዎች ‘ፈቃዳቸው ሊሰረዝ' ይችላል
በ #ኦሮሚያ ማዕድን ልማት ባለሥልጣን ሐምሌ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ለፌዴራል የማዕድን ሚኒስቴር ተጽፎ ግልባጩ ለክልሉ ፕሬዝዳንት ቢሮ የተላከና አዲስ ስታንዳድር የተመለከተው ደብዳቤ፣ የማዕድን ፈቃዶችን የመስጠት፣ የመሰረዝ ወይም የማደስ ሥልጣን ለክልሉ መንግስት መሰጠቱን ይገልጻል።
ይህ ውሳኔ የተላለፈው አዲስ ስታንዳርድ ሐምሌ 12/ 2017 ዓ/ም ባሰራጨው ልዩ ዘገባ፤ ሆንግኮንግ ሺንግሹ ማዕድን ኢንተርናሽናል ኢንቨስትመንት ኩባንያ በምዕራብ ወለጋ ዞን ሶስት የማዕድን ፍለጋ ፈቃድ መታደሱን ማጋለጡን ተከትሎ ነው።
ዘገባው ኩባንያው በማዕድን ሚኒስቴር የተሰጠው ፈቃድ ከአንድ ሺህ 170 ካሬ ኪሎ ሜትር በላይ የወርቅ እና ሜታል ቤዝን እንደሚሸኝ እና ፈቃዱ የታደሰው የሚመለከተውን የህግ ማዕቀፍ በመጣስና መደበኛ የክልል ምክክር ሳይደረግበት መሆኑን አጋልጧል።
ሆንግኮንግ ሺንግሹ ማዕድን ኢንተርናሽናል ኢንቨስትመንት ኩባንያን ጨምሮ 15 ኩባንያዎች ፈቃዳቸው ሊሰረዝ መሆኑን አዲስ ስታንዳርድ የተመለከተው ደብዳቤ አስታውቋል። በተመሳሳይ 21 ኩባንያዎች ስራቸውን እያቆሙ ወይም ፈቃዳቸው እንዳይታደስ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።
“በኦሮሚያ የተሰጡ አብዛኛዎቹ የማዕድን ሥራ ፈቃዶች… የተቀመጡ የቁጥጥር ግዴታዎችን አላሟሉም” ሲል ባለስልጣኑ በደብዳቤው ላይ ገልጿል።
ሙሉ ለማንበብ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8814

ትንታኔ: የኦሮሚያ ማዕድን ልማት ባለሥልጣን የማዕድን ፈቃድ የመስጠት እና የመቆጣጠር ሙሉ ድርሻ እንዲኖረው ይሻል፤ የሆንግ ኮንጉ ሺንግሹ ማዕድን እና በርካታ ኩባንያዎች ‘ፈቃዳቸው ሊሰረዝ' ይችላል …
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6/ 2017 ዓ/ም፡- የኦሮሚያ ማዕድን ልማት ባለሥልጣን፤ በክልሉ እያደገ በመጣው ማዕድን ዘርፍ፤ ፈቃድ የመስጠት እና የመቆጣጠር ሙሉ ድርሻ እንዲኖረው ይሻል። በባለስልጣኑ ሐምሌ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ለፌዴራል የማዕድን ሚኒስቴር ተጽፎ ግልባጩ ለክልሉ ፕሬዝዳንት ቢሮ የተላከና አዲስ ስታንዳድር የተመለከተው ደብዳቤ፣ የማዕድን ፈቃዶችን የመስጠት፣ የመሰረዝ ወይም የማደስ ሥልጣን ለክልሉ…
ዜና: #ግብፅ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ ከኢትዮጵያ ጋር ባላት ውዝግብ የውሃ መብቷን እንደማትተው አስታወቀች
የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አል ሲሲ በአባይ ወንዝ ላይ የሚደረጉ ማናቸውንም የተናጠል እርምጃዎችን እንደሚቃወሙ በመግለጽ፣ ግብፅ የውሃ መብቷን ችላ ትላለች ብሎ የሚያስብ ማንኛውም አካል "ተሳስቷል" ሲሉ አስታውቀዋል።
ሲሲ ከዩጋንዳ አቻቸው ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋር በመሆን በካይሮ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ከናይል ገባር ወንዞች የሚገኘው ዓመታዊ የውሃ ፍሰት 1,600 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ሲሆን አብዛኛው በደን፣ ረግረጋማ ቦታዎች፣ በትነት እና የከርሰ ምድር ውሃ አማካኝነት ይጠፋል ብለዋል።
አክለውም “ወደ ናይል የሚደርሰው አነስተኛ መጠን ያለው ውሃ ነው፤ ግብፅና ሱዳን በድምሩ 85 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የሚጠጋ ውሃ ይደርሳቸዋል ይህም ከጠቅላላው 4 በመቶው ብቻ ነው” ብለዋል።
የግብፁ መሪ ሀገራቸው አማራጭ የውሃ ሀብት እንደሌላት እና የምታገኘው የዝናብ መጠንም አነስተኛ መሆኑን ጠቅሰው ለግብፅ ይህንን የውሃ ድርሻ መተው “ሕይወቷን እንደመተው ይቆጠራል” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ግብፅ የናይል ወንዝ ለእህት ሀገራት በግብርና፣ በኤሌክትሪክ ምርት ወይም በአጠቃላይ ልማት ላይ የሚኖረውን ጥቅም እንደምትቀበል የገለጹት አል ሲሲ “ይህ ግን ለግብፅ የሚደርሰውን የውሃ መጠን መቀነስ የለበትም” ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ የናይል ውሃ ጉዳይን ከግብፅ ጋር ያልተገናኙ ዓላማዎችን በሀገሪቱ ላይ ለማራመድ የታሰበ ሰፊ ግፊት የመድረግ ዘመቻ አካል አድርጎ አቅርቦታል።

ዜና፡ ብሔራዊ ባንክ በ2017 #ከትግራይ ክልል 189 ኩንታል፣ #ከአፋር ክልል ደግሞ 225 ኪሎ ግራም ወርቅ መግዛቱ ተገለጸ
#የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት ከትግራይ ክልል 189 ኩንታል ወርቅ፣ ከአፋር ክልል ደግሞ 225 ኪሎ ግራም ወርቅ ግዢ መፈጸሙ ተገለጸ።
የትግራይ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 189 ኩንታል ወርቅ ለብሔራዊ ባንከ በማስገባት ከ250 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የክልሉ ማዕድን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዓለም ሀድጉ አስታውቀዋል።
በተመሳሳይ ከአፋር ክልል ወደ ብሄራዊ ባንክ 225 ኪሎ ግራም ወርቅ መቅረቡን ክልሉ አስታውቋል፤ ወደ ባንኩ የሚገባው የወርቅ መጠን በእጥፍ መጨመሩን የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊአብዱል ኢንድሪስ ገልጸዋል።
በ2016 በጀት ዓመት 96 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ መግባቱን ያስታወሱት ምክትል ኃላፊው በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመትይህ ቁጥር ወደ 225 ኪሎ ግራም ወርቅ ማሳደግ እንደተቻለ መግለጻቸውን ከፕረስ ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2017 በጀት ዓመት ወደ ብሔራዊ ባንክ 4ሺህ 700 ኪሎ ግራም ወርቅ ማስገባቱን የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ ማስታወቁን መዘገባችን ይታወሳል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
#የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት ከትግራይ ክልል 189 ኩንታል ወርቅ፣ ከአፋር ክልል ደግሞ 225 ኪሎ ግራም ወርቅ ግዢ መፈጸሙ ተገለጸ።
የትግራይ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 189 ኩንታል ወርቅ ለብሔራዊ ባንከ በማስገባት ከ250 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የክልሉ ማዕድን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዓለም ሀድጉ አስታውቀዋል።
በተመሳሳይ ከአፋር ክልል ወደ ብሄራዊ ባንክ 225 ኪሎ ግራም ወርቅ መቅረቡን ክልሉ አስታውቋል፤ ወደ ባንኩ የሚገባው የወርቅ መጠን በእጥፍ መጨመሩን የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊአብዱል ኢንድሪስ ገልጸዋል።
በ2016 በጀት ዓመት 96 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ መግባቱን ያስታወሱት ምክትል ኃላፊው በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመትይህ ቁጥር ወደ 225 ኪሎ ግራም ወርቅ ማሳደግ እንደተቻለ መግለጻቸውን ከፕረስ ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2017 በጀት ዓመት ወደ ብሔራዊ ባንክ 4ሺህ 700 ኪሎ ግራም ወርቅ ማስገባቱን የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ ማስታወቁን መዘገባችን ይታወሳል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
በ #ማላዊ እስር ቤት ውስጥ የነበሩ 200 ኢትዮጵያውያን ወደ አገር ቤት ተመለሱ
በማላዊ በተለያዩ እስር ቤቶች ታስረው የነበሩ 210 ኢትዮጵያውያን ዜጎች በመንግስትና በዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋራ ጥረት ወደ አገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ፤ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ከዓለም አቀፍ ፍልሰተኞች ድርጀት እና ዳር ሳላም ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ኢትዮጵያውያኑ ዜጎቹን ከነሐሴ 1- 7 ቀን 2017 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገር ቤት መመለስ ተችሏል ብሏል፡፡
ዜጎቹ ህጋዊ ቪዛ ሳይዙ በህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ ደላሎች በመታለል ከፍተኛ ገንዘብ ጭምር በመክፈል በሞያሌ በኩል ከሀገር በመውጣት የኬንያ እና የታንዛንያ ድንበሮችን በማቋረጥ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሻገር ጥረት እያደረጉ በሚገኙበት ጊዜ በማላዊ ሀገር የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር በመዋል ለረዥም ጊዜ እስርቤት ውስጥ የቆዩ ናቸው ተብሏል፡፡
እንደ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጻ፤ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የማላዊ መንግስት ጋር በመነጋገር እንደዚሁም የትራንስፖርት ወጪኣቸውን ለመሸፈን ከዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት እና ከኢትየጵያ አየር መንገድ ድጋፍ በማገኘት ዜጎችን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረግ ችሏል፡፡
መንግሥት ዜጎች በህገወጥ ደላሎች በመታለል ህጋዊ ቪዛ ሳይዙ ወደ ተለያዩ አገራት በመጓዝ ለተለያዩ ችግሮች እንዳይጋለጡ ራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳስቧል።

ዜና: በአማራ ክልል በሐምሌ ወር ብቻ ከ3ሺህ በላይ ታጣቂዎች "የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ትጥቅ ፈትተዋል" ተባለ
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ባሳለፍነው ሐምሌ ወር ብቻ ከ3ሺህ 100 በላይ ታጣቂዎች "የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ትጥቃቸውን በመፍታት ወደ ህብረተሰቡ መቀላቀላቸውን" የዞኑ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ አስታወቀ።
የዞኑ የሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሃላፊ የሆኑት ይደሰቱ ክፈተው በዞኑ አንዳንድ አካባቢዎች "የጽንፈኛ ቡድኑ" ሲል የገለጿቸው አካላት እንቅስቃሴ እንደነበር አስታውሰው፤ በቅርብ ወራቶች "የተሰለፉበት ዓላማ ስህተት መሆኑ እየገባቸው በርካቶች ትጥቃቸውን አስረክበው ወደ መደበኛ ህይወታቸው እየተመለሱ ነው" ሲሉ ገልጸዋል።
በዚህም በሐምሌ ወር 2017 ዓ.ም 3ሺህ 155 በክልሉ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የቀድሞ ታጣቂዎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለውና ትጥቃቸውን ፈትተው ሕብረተሰቡን መቀላቀላቸውን ተናግረዋል።
አክለውም "የመንግስትና የሕዝብ ተቋማትን በማውደም፣ መንገድ በመዝጋት፣ ህጻናት እንዳይማሩ በማድረግ፣ እናቶች በጤና ተቋም እንዳይወልዱና ሕብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት እንዳያገኝ ለፈጠሩት ችግር በመጸጸት በስራ ለመካስ መዘጋጀታቸውን የቀድሞ ታጣቂዎቹ አረጋግጠዋል" ብለዋል።
በዞኑ ከመርሃ ቤቴ፣ ሚዳ እና ሌሎችም ወረዳዎች በየእለቱ እጃቸውን እየሰጡ ያሉት በርካቶች መሆናቸውን የገለጹት ሃላፊው፤ ሌሎችም ይህንን መልካም እድል እንዲጠቀሙ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
https://www.facebook.com/100076048904470/posts/775110691700554/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

#ኢትዮጵያ #ስዕላዊ_ዘገባ፡ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የ #ደቡብ_ሱዳን ተልዕኮ (UNMISS) ስር የሚገኙ ከ150 በላይ #ኢትዮጵያውያን ሰላም አስከባሪዎች በ #ታምቡራ ከተማ ተሰማርተው እየሰሩ ነው።
ሰላም አስከባሪዎቹ “ባለፉት አምስት አመታት የበርካቶችን ህይወት የቀጠፈ እና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ያፈናቀለው ግጭት የፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ፣ በየጊዜው በሚያደርጉት ጥበቃ፣ እንዲሁም ከ30,000 በላይ ለሚሆኑ ተፈናቃይ ቤተሰቦች በሚሰጡት ጥበቃ እና የሰላም አገልግሎት የህብረተሰቡን እምነት ለመገንባት እየሰሩ ናቸው” ሲል UNMISS በዛሬው እለት ገልጿል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሀምሌ ወር እንዳስታወቀው እ.ኤ.አ. በ2021 በምዕራብ ኢኳቶሪያ ግዛት፣ #ታምቡራ ከተማ በተቀሰቀሰው የጎሳ ግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ የአካባቢው ነዋሪዎች አሁንም በተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ይገኛሉ።
ተጨማሪ ለማንበብ
https://www.facebook.com/share/p/1Aw3UG7rLY/
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
ሰላም አስከባሪዎቹ “ባለፉት አምስት አመታት የበርካቶችን ህይወት የቀጠፈ እና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ያፈናቀለው ግጭት የፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ፣ በየጊዜው በሚያደርጉት ጥበቃ፣ እንዲሁም ከ30,000 በላይ ለሚሆኑ ተፈናቃይ ቤተሰቦች በሚሰጡት ጥበቃ እና የሰላም አገልግሎት የህብረተሰቡን እምነት ለመገንባት እየሰሩ ናቸው” ሲል UNMISS በዛሬው እለት ገልጿል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሀምሌ ወር እንዳስታወቀው እ.ኤ.አ. በ2021 በምዕራብ ኢኳቶሪያ ግዛት፣ #ታምቡራ ከተማ በተቀሰቀሰው የጎሳ ግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ የአካባቢው ነዋሪዎች አሁንም በተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ይገኛሉ።
ተጨማሪ ለማንበብ
https://www.facebook.com/share/p/1Aw3UG7rLY/
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
ዜና: ዓመታዊው የ #አሜሪካ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ሪፖርት በ #ኢትዮጵያ ከህግ ውጭ ግድያዎች፣ ማሰቃየት፣ የጅምላ እስራት መፈጸማቸውን አመላከተ
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ይፋ ባደረገው የ2024 የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሪፖርት፤ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በመካሄድ ላይ ባሉት ግጭቶች በመንግስት እና መንግስታዊ ባልሆኑ አካላት መጠነ ሰፊ የመብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን ገልጿል።
ሪፖርቱ በምዕራብ ትግራይ በአማራ ሚሊሻዎች እና አጋሮቻቸው ፤ “በርካታ የሲቪሎች ግድያ፣ በጅምላ ማፈናቀል፣ የዘር ማጽዳት፣ በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የሚፈጸሙ አስገድዶ መድፈር እና ሌሎች ጥቃቶች፣ ዝርፊያ እና የንብረት ውድመት” መፈጸማቸውን ጠቅሷል።
በተጨማሪም በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች “በሲቪሎች እና በመንግስት ባለስልጣናት ላይ መጠነ ሰፊ ከህግ ውጭ ግድያዎችን” መፈጸማቸውን ገልጿል። ለእነዚህ ድርጊቶች የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እና የአማራ ፋኖ ታጣቂዎችን ተጠያቂ አድርጓል።
በሪፖርቱ መሠረት፣ በአፋር፣ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ጋምቤላ እና ሶማሌ ክልሎች የሚገኙ የሚሊሻ ቡድኖች “በሲቪሎች ላይ ጥቃት እና ግድያ በመፈጸም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን አፈናቅለዋል”። በተጨማሪም “በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች እንዲሁም ትግራይን ጨምሮ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች በግጭት አውድ ውስጥ በርካታ ሰዎች ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መገደላቸውን” ሪፖርቱ ይገልጻል።
ተጨማሪ ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8854

አመታዊው የአሜሪካ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ሪፖርት በኢትዮጵያ ከህግ ውጭ ግድያዎች፣ ማሰቃየትና የጅምላ እስራት መፈጸማቸውን አመላከተ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7/ 2017 ዓ/ም፡- የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የ2024 የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሪፖርትን ይፋ አድርጓል። ሪፖርቱ፤ በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች በመካሄድ ላይ ባሉት ግጭቶች በመንግስት እና መንግስታዊ ባልሆኑ አካላት መጠነ ሰፊ የመብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን በዝርዝር ገልጿል። በአምነስቲ ኢንተርናሽናል፣በሂዩማን ራይትስ ዎች፣ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ…
ዜና: #ደቡብሱዳን ፍልስጤማውያንን በሀገሯ የማስፈር ዕቅድ አላት የሚሉ ዘገባዎችን ውድቅ አደረገች
የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር መንግሥት ፍልስጤማውያንን በሀገሯ ለማስፈር ከእስራኤል ጋር ውይይት እያደረገ ነው በሚል የወጡ ዘገባዎችን አስተባበለ።
ሚኒስቴሩ ዛሬ ረቡዕ ነሐሴ 7 ቀን ባወጣው መግለጫ ዘገባዎቹን “መሰረተ ቢስ” ሲል የገለጻቸው ሲሆን የደቡብ ሱዳን መንግሥትን “ይፋዊ አቋም ወይም ፖሊሲን” እንደማይወክሉ አስታውቋል።
አክሎም የመገናኛ ብዙሃን መረጃዎችን ከማውጣታቸው በፊት “ተገቢውን ትኩረት እንዲያደርጉ” እና ይፋዊ የመንግስት ምንጮችን በማረጋገጥ እንዲዘግቡ አሳስቧል።
ሚኒስቴሩ ማስተባበያውን ያወጣው እስራኤል ፍልስጤማውያንን ከጋዛ የማዛወር ዕቅድን በተመለከተ ከደቡብ ሱዳን ጋር ውይይት እያደረገች ነው የሚሉ ዘገባዎች ባለፉት 24 ሰዓታት በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን መሰራጨታቸውን ተከትሎ ነው።
ዕቅዱ እስራኤል ለ22 ወራት በሃማስ ላይ ካካሄደችው ወታደራዊ ዘመቻ በኋላ በፈራረሰችው ጋዛ የሚኖሩ ነዋሪዎችን በጅምላ ሀገራቸውን ጥለው እንዲሸሹ የምታደርገው ሰፊ ጥረት አካል መሆኑን ዘገባዎች አመላክተዋል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር መንግሥት ፍልስጤማውያንን በሀገሯ ለማስፈር ከእስራኤል ጋር ውይይት እያደረገ ነው በሚል የወጡ ዘገባዎችን አስተባበለ።
ሚኒስቴሩ ዛሬ ረቡዕ ነሐሴ 7 ቀን ባወጣው መግለጫ ዘገባዎቹን “መሰረተ ቢስ” ሲል የገለጻቸው ሲሆን የደቡብ ሱዳን መንግሥትን “ይፋዊ አቋም ወይም ፖሊሲን” እንደማይወክሉ አስታውቋል።
አክሎም የመገናኛ ብዙሃን መረጃዎችን ከማውጣታቸው በፊት “ተገቢውን ትኩረት እንዲያደርጉ” እና ይፋዊ የመንግስት ምንጮችን በማረጋገጥ እንዲዘግቡ አሳስቧል።
ሚኒስቴሩ ማስተባበያውን ያወጣው እስራኤል ፍልስጤማውያንን ከጋዛ የማዛወር ዕቅድን በተመለከተ ከደቡብ ሱዳን ጋር ውይይት እያደረገች ነው የሚሉ ዘገባዎች ባለፉት 24 ሰዓታት በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን መሰራጨታቸውን ተከትሎ ነው።
ዕቅዱ እስራኤል ለ22 ወራት በሃማስ ላይ ካካሄደችው ወታደራዊ ዘመቻ በኋላ በፈራረሰችው ጋዛ የሚኖሩ ነዋሪዎችን በጅምላ ሀገራቸውን ጥለው እንዲሸሹ የምታደርገው ሰፊ ጥረት አካል መሆኑን ዘገባዎች አመላክተዋል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
ዜና: በ #አፋር ክልል 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ዓመት ዕድሜ ያለው የሰው ቅሪተ አካል ተገኘ
በአፋር ክልል "ሌዲ ገራሩ" በተባለው የጥናት ቦታ 2.8 ሚሊዮን ዓመት ዕድሜ ያለው የአዲስ የአውስትራሎፒቴከስ እና የሆሞ ዝርያዎች ቅሪተ አካላት ተገኘ።
የአሪዞና ስቴት ዩኒቨርስቲ የሳይንቲስቶች እና የተመራማሪዎች ቡድን 13 ጥርሶችን በማግኘት በሰው ልጅ ዝግመተ ለውጥ ሂደት ያልተጠናውን ጊዜ ለመረዳት የሚረዱ መረጃዎች መሰብሰባቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ጥርሶቹ የተገኙት ከዚህ በፊት የሰው ልጅ ቅሪተ አካል በተገኘበት አከባቢ ሲሆን የቅሪተ አካል አጥንቶቹ ሙሉ ስላልሆኑ በእነዚህ 13 ጥርሶች የተወከሉት የአውስትራሎፒቲከስ እና የሆሞ ዝርያዎች ስያሜ ገና እንዳልተሰጣቸው ተገልጿል።
በኔቫዳ ዩኒቨርሲቲ የፓሊዮአንትሮፖሎጂስት እና ረቡዕ ዕለት በኔቸር ዕትም ላይ የወጣው የምርምር ስራ መሪ የሆኑት ብራያን ቪልሞር “ይህ የሰው ልጅ የዝግመተ ለውጥ ታሪክ ቀስ በቀስ እየተለዋወጠ የመጣ የአንድ ዝርያ ታሪክ ብቻ አለመሆኑን ያረጋግጣል” ብለዋል።
ቪልሞር አክለውም “ይልቁንም የሰው ልጅ የዝግመተ ለውጥ ሂደት ልክ እንደሌሎች ህይወት ያላቸው ነገሮች ነው፤ በተለያዩ ጊዜያት ብዙ ዝርያዎች ያሉት እና አብዛኛዎቹም በተመሳሳይ ጊዜ ይኖሩ ነበር” ብለዋል።

ዜና፡ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በ #ትግራይ ያደረገውን ውይይት “ትርጉም የለሽ” ሲሉ የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አጣጣሉ
የ #ኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል ከጊዜያዊ አስተዳደሩ አመራሮች፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሲቪክ ማኅበራት እና ከትግራይ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ አባላት ጋር ምክክር ለማድረግ የሚያስችል "ውጤታማ" ውይይት ማድረጉን አስታውቋል።
ይሁን እንጂ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውጤታማ ውይይቶች እንዳልተካሄዱ በመግለጽ የኮሚሽኑን መግለጫ አጣጥለዋል። እንዲሁም ባልተፈቱ የፖለቲካ ጥያቄዎች ምክንያት በምክክር ሂደቱ ላይ ከፍተኛ ጥርጣሬ እንዳላቸው ገልጸዋል።
የትግራይ ነጻነት ፓርቲ እና የሳልሳይ ወያነ ትግራይ አመራሮች ከፓርቲዎቹ ጋር "ትርጉም ያለው ውይይት እንዳልተደረገ" ገልፀው፤ ጊዜያዊ አስተዳደሩ በሂደቱ ላይ ትግራይን መወከል እይችልም ሲሉ ተቃውመዋል።
የትግራይ ነጻነት ፓርቲ ሊቀመንበር ደጀን መዝገበ፤ “የትግራይ ሕዝብ አሁንም ያልተፈቱ ወሳኝ የፖለቲካ ጉዳዮች አለበት። የሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ ሙሉ በሙሉ እስኪመለስ ድረስ ምክክሩ ሊቀጥል አይችልም። የትኛውም እንዲህ ያለ ሂደትም መከናወን ያለበት፤ የትግራይን ሕዝብ በሚወክልና ለሕዝቡ የሚናገር መንግሥት ነው” ሲሉ ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል።
ሙሉውን ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8862

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ያደረገውን ውይይት “ትርጉም የለሽ” ሲሉ የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አጣጣሉ - Addis standard
መቀለ፣ ነሐሴ 8/ 2017 ዓ/ም፦ የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል ከጊዜያዊ አስተዳደሩ አመራሮች፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሲቪክ ማኅበራት እና ከትግራይ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ አባላት ጋር ምክክር ለማድረግ የሚያስችል “ውጤታማ” ውይይት ማድረጉን አስታውቋል። ይሁን እንጂ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውጤታማ ውይይቶች እንዳልተካሄዱ በመግለጽ የኮሚሽኑን መግለጫ አጣጥለዋል። እንዲሁም…
ዜና፡ የፓርላማ አባሉ በአማራ ክልል ትጥቅ ፈቱ የተባሉ ታጣቂዎች ቁጥር ላይ ባለስልጣናት የሰጡት መረጃ የተለያየ መሆኑን በመጠቆም ተቹ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን "የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ትጥቃቸውን የፈቱ ታጣቂዎችን" አስመልክቶ በሁለት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በአንድ ቀን ውስጥ የወጡ የቁጥር መረጃዎች በእጅጉ የሚቃረኑ መሆናቸውን በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ በመጠቆም ትችት ሰነዘሩ።
በ #አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሃላፊ የሆኑት ይደሰቱ ባሳለፍነው ሐምሌ ወር ብቻ “ከ3ሺህ 100 በላይ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን በመፍታት ወደ ህብረተሰቡ መቀላቀላቸውን" ሲገልጹ የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኤልያስ አበበ በበኩላቸው “ከ1,300 በላይ ታጣቂዎች” ትጥቅ ፈተዋል በለዋል።
የፓርላማ አባሉ ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) በሁለቱ የስራ ሃላፊዎች የተገለጹትን መረጃዎች አሃዛዊ ልዩነት በመጥቀስ "ከአዲስ አበባ የመርካቶ ነጋዴ" ጋር አነጻጽረውታል።
"አቶ ይደሰቱ እና አቶ ኤልያስ በአንድ ዞን ውስጥ የካቢኔ አባላት ናቸው" ያሉት የፓርላማ አባሉ "የሚጠሩት ቁጥር ግን ልክ መርካቶ በቫት እና ያለ ቫት ዋጋ እንደሚጠራው ነጋዴ ይመስላል። የአቶ ይደሰቱ በቫት፣ የአቶ ኤልያስ ያለቫት ነው?" ብለዋል።
አክለውም "እንደዚህ ያሉ እርስ በርሳቸው የሚቃረኑ ቁጥሮችን በሠላሳ ደቂቃ ልዩነት ውስጥ መጥቀስ አጠያያቂ ነው" ብለዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8876

የፓርላማ አባሉ በአማራ ክልል ትጥቅ ፈቱ የተባሉ ታጣቂዎች ቁጥር ላይ ባለስልጣናት የሰጡት መረጃ የተለያየ መሆኑን በመጠቆም ትችት ሰነዘሩ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8/2017 ዓ/ም፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን “የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ትጥቃቸውን የፈቱ ታጣቂዎችን” አስመልክቶ በሁለት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በአንድ ቀን ውስጥ የወጡ የቁጥር መረጃዎች በእጅጉ የሚቃረኑ መሆናቸውን በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ በመጠቆም ትችት ሰነዘሩ። በአማራ ክልል…
#ጁባላንድ የ #ሶማሊያ ፌዴራል መንግሥትን በጌዶ ግጭት በማስነሳት ከሰሰች
ጁባላንድ አስተዳደር በምዕራብ ጌዶ ክልል በምትገኘው በባልድሀዎ ወረዳ በቅርቡ ለተፈጠረው ግጭት የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት እና የጸጥታ ባለሥልጣናት ተጠያቂ ናቸው ሲል ከሰሰ። ግጭቱ የበርካታ የጁባላንድ ወታደሮችን እና መኮንኖችን ሕይወት ቀጥፏል ብሏል።
የጁባላንድ የመረጃ ሚኒስቴር ባወጣው ትናንት ረቡዕ ባወጣው መግለጫ፣ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼክ ሞሃሙድን እና የጌዶ የጸጥታ ሃላፊ የሆኑትን አብዲራሺድ ጃናንን ሁከትን በማስፋፋትና ክልሉን በማተራመስ ወንጅሏል።
በተጨማሪም ጁባላንድ የፌዴራል መንግሥቱ የክልሉን አስተዳደር ለማዳከም ወይም ለማፍረስ የተነደፈ ዕቅድ እንዳለው መግለጹን ጋሮዌ ኦንላይን ዘግቧል።
መግለጫው፤ “የጁባላንድ መንግሥት፤ የጁባላንድን አስተዳደር እና የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሥርዓትን ለማፍረስ የሚደረጉ ሙከራዎችን ለመቃወም ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት ያረጋግጣል” ብሏል።
አስተዳደሩ ይህን መግለጫ ያወጣው፤ የጁባላንድ ኃይሎችን ከባልድሀዎ ከተማ እና ከአካባቢው ያስወጣ ጥቃት በቅርቡ በመንግሥት ወታደራዊ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ነው። የፌዴራል ባለሥልጣናት በጌዶ የሚገኙ ቀሪ የጁባላንድ ወታደሮች የክልሉን ሰላም ለማስመለስ ለሶማሊያ ብሔራዊ ጦር ኃይሎች እጃቸውን እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።