Addis Standard Amharic
17.6K subscribers
4.02K photos
101 videos
3 files
3.24K links
አዲስ ስታንዳርድ በጃኬን አሳታሚ ኃ.የተ.የግ.ማ. ባለቤትነት ስር የሚታተም በኢትዮጵያ የሚገኝ ነፃ እና ገለልተኛ ሚዲያ ነው። አዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የአዲስ ስታንዳርድ እንግሊዝኛ ሕትመት አካል ነው።
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
Download Telegram
ፕሬዝዳንት ትራምፕ የ #ሶማሊላንድን የእውቅና ጥያቄ እንደሚያውቁና ውይይት መኖሩንም ገለጹ

ከአዘርባጃን እና ከአርሜኒያ መሪዎች ጋር ትላንት ምሽት በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፣ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሶማሊላንድን ዓለም አቀፍ ዕውቅና የማግኘት የረጅም ጊዜ ጥያቄን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።

ስለ ሶማሊላንድ ጥያቄ ተጠይቀው ሲመልሱ፣ ትራምፕ "ጥሩ ጥያቄ ነው፣ አሁን እየተመለከትነው ነው" ብለዋል፣ ይህም ዩናይትድ ስቴትስ ጉዳዩን በንቃት እያጤነችው መሆኑን ያመለክታል ሲል ሆርን ትሪቢውን ዘግቧል።

ሶማሊላንድ እ.አ.አ ከ1991 ጀምሮ ከሶማሊያ ነፃነቷን መልሳ ካወጀችበት ጊዜ አንስቶ፣ ከሶማሊያ ጋር ሲነፃፀር በተሻለ መረጋጋት እና ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ቢኖራትም፣ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ መደበኛ ዕውቅና ለማግኘት ጥረት እያደረገች ነው።

የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን መሐመድ አብዱላሂ እ.አ.አ በ2025 የዓለም መንግስታት ጉባኤ ላይ እንደተናገሩት፣ እውቅና ማግኘታቸው "ቅርብ ነው" ብለው ተስፋቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ዩናይትድ ስቴትስም ቀዳሚ ልትሆን እንደምትችል ገልጸው ነበር።

እ.አ.አ በ2025 ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው የአሜሪካ ጉብኝታቸው ከዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ባለስልጣናት እና የከፍተኛ የአፍሪካ ቀንድ ወታደራዊ መኮንንኖች ጋር ውይይቶች እንደሚያደጉ ይጠበቃል።

የሶማሊላንድ ስትራቴጂካዊ የቀይ ባህር አቅራቢያ የሚገኝ ቦታዋ፣ ወታደራዊ ትብብር ለማድረግ ያቀረበችው ጥያቄ እና ለአስፈላጊ ማዕድናት የሚሰጠው የፍቃድ እድል፣ በተለይም በትራምፕ አስተዳደር ላይ የሚያደርጉትን የሎቢ ጥረቶች አጠናክሮታል ተብሎ ይገመታል።
#የተባበሩት_አረብ_ኢሚሬትስ “የ #ኮሎምቢያ ቅጥረኛ ወታደሮችን” ሲያጓጉዝ የነበረ አውሮፕላን በሱዳን ጦር ተመቶ መከስከሱን አስተባበለች

የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ከሱዳን ጦር ኃይሎች የ የተነገረውንና “የኮሎምቢያ ቅጥረኛ ወታደሮችን” ሲያጓጉዝ የነበረ አውሮፕላን” በሱዳን ጦር ተመቶ መከስከሱን አስተባበለች ።

በዚህ ሳምንት የወጣው ዜና እንደሚገልጸው፥ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ አውሮፕላን ለተቀናቃኙ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል (RSF) የኮሎምቢያ ቅጥረኛ ወታደሮችን ሲያጓጉዝ በሱዳን ጦር መውደሙን የሚገልጽ ነበር።

ሱዳን ከሚያዚያ 2015 ጀምሮ በሀገሪቱ ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይል መካከል ከፍተኛ ጦርነት ውስጥ ትገኛለች። ጦሩ አቡ ዳቢ ፈጥኖ ደራሽ ኃይልን እየደገፈች ነው ሲል ለረጅም ጊዜ ሲከስ የቆየ ቢሆንም፣ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ግን ይህን ክስ ስትክድ ቆይታለች።

ረቡዕ እለት፣ የሱዳን የመንግስት ቴሌቪዥን፣ የሱዳን አየር ኃይል በጦርነት በምትታመሰው የዳርፉር ክልል ውስጥ በሚገኝ በRSF ቁጥጥር ስር ባለ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ያረፈውን የአረብ ኢሚሬትስ አውሮፕላን በመምታት 40 የሚሆኑ ኮሎምቢያዊ ቅጥረኛ ወታደሮች መገደላቸውን አስታውቋል።

ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አንድ የሱዳን ወታደራዊ ምንጭ እንደተናገሩት፣ አውሮፕላኑ “በዳርፉር ኒያላ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ተደበድቦ ሙሉ በሙሉ ወድሟል”።

ይሁንና፥ ከኤኤፍፒ ጋር የተነጋገሩ አንድ የኢሚሬትስ ባለስልጣን፣ እነዚህ “መሠረተ ቢስ ክሶች” “ፍጹም ውሸት” እና በማንኛውም ማስረጃ ያልተደገፉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የኮሎምቢያው ፕሬዚዳንት ጉስታቮ ፔትሮ በበኩላቸው፣ መንግስታቸው በጥቃቱ ስንት ኮሎምቢያውያን እንደሞቱ ለማወቅ እየሞከረ መሆኑን ባለፈው ሀሙስ ገልጸው፣ “የሟቾችን አስከሬን መመለስ ይችሉ እንደሆነ እናያለን” ሲሉ አክለዋል።
ዜና: በጎርፍ የተወሰደው የጊደብ ወንዝ ድልድይ ወደ አገልግሎት እንዲመለስ እየተሰራ ነው ተባለ

ከደብረማርቆስ ወደ ባህርዳር በሚወስደዉ መንገድ በጊደብ ወንዝ ላይ የተሰራዉ ድልድይ በጎርፍ መወሰዱን ተከትሎ በአስቸኳይ ወደ አገልግሎት እንዲመለስ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስታወቀ፡፡

ድልድዩ በጎርፍ የተወሰደዉ ቅዳሜ ነሐሴ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ሌሊት ጮቄ አካባቢ በጣለዉ ከባድ ዝናብ በተፈጠረ ጎርፍ ሲሆን ድልድዩ ጥዋት አካባቢ እንደተወሰደ ተጠቁሟል።

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደብረማርቆስ ጥገና ዲስትሪክት ቡድን መሪ አቶ መንግስቱ አስረስ መንገዱ ከፍተኛ የተሽከርካሪ ፍሠት ያለው መሆኑን አንስተው የመንገደኞች መስተጓጎል እንዳይፈጠር እየተሠራ ነው ብለዋል።

አክለውም ችግሩ እንደተከሰተ በፍጥነት ጊዜአዊ ተገጣጣሚ የብረት ድልድይ እንዲገነባ የመንገዶች አስተዳደር ደብረማርቆስ ዲስትሪክት መረጃ እንደተሰጠው ተናግረዋል።

በዚሁ መሰረትም ተገጣጣሚ የብረት ድልድይ ከአዲስ አበባ እየተጫነ መሆኑን ጠቅሰው በቅርብ ጊዜ ለአገልግሎት እንደሚመቻች አመልክተዋል።

ድልድዩ በደረሰበት አደጋ አሁን ላይ የትራንሰፖርት አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ መቋረጡን የዘገበው ኢቢሲ ነው፡፡

======================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
#ሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት በቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያዎች የታቀደውን የኢንተርኔት ዋጋ ጭማሪ በመቀልበስ ታቅዶ የነበረውን ህዝባዊ ተቃውሞ አስቆሙ

የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን መሐመድ አብዱላሂ (ዒሮ) በቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያዎች በቴሌሶም እና በሶምቴል የኢንተርኔት አገልግሎት ዋጋን በእጥፍ ለመጨመር የተላለፈውን ውሳኔ ሻሩ።

ይህ እርምጃ ለእሁድ ታቅዶ የነበረውን ህዝባዊ ተቃውሞ አስቀርቷል።

“እኔ የሶማሊላንድ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት እንደመሆኔ መጠን ሕዝቦቼን የማሳውቀው፣ መንግሥት እና በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ የቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያዎች የኢንተርኔት አገልግሎት እና የሞባይል ስልክ ጥሪዎች የዋጋ ጭማሪን በተመለከተ በቅርቡ የተላለፈውን ውሳኔ ለማገድ መስማማታቸውን ነው” ሲሉ ፕሬዝዳንት ዒሮ በፌስቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት መግለጫ አሳውቀዋል። “የአገልግሎቶቹ ዋጋ እስከሚቀጥለው ማስታወቂያ ድረስ ሳይለወጥ የሚቆይ ሲሆን፣ መንግሥትም ከኩባንያዎቹ ጋር በአስቸኳይ ውይይት ያደርጋል” ብለዋል ።

ሶምቴል ለዚህ ውሳኔ ምላሽ የሰጠ ሲሆን፣ በመግለጫው “እንደ አንድ የሕዝብ ኩባንያ፣ ውሳኔው እንዲታገድ መስማማታችንን እንገልጻለን” ብሏል።

የሶምቴል ውሳኔ በፕሬዝዳንት ዒሮ እና የሕዝቡን ተቃውሞ በማነሳሳት የተሳተፈውን የሕግ ባለሙያ ጉሌድ ዳፋዕን በሰፊው አድናቆት አስገኝቷል ሲል ሒራን ዘግቧል ።

ይህ ውሳኔ የተላለፈው ሶማሊያ የስታርሊንክን ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የሳተላይት ኢንተርኔት ማግኘት ከጀመሩ የአፍሪካ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ በይፋ ከተጨመረች ከሁለት ቀናት በኋላ ነው። በኤሎን መስክ ስፔስኤክስ (SpaceX) የተገነባው ስታርሊንክ፣ በሚያዚያ ወር የቁጥጥር ፈቃድ ከተሰጠ በኋላ ባለፈው ሳምንት ሰኞ ዕለት በአገር አቀፍ ደረጃ ሥራ ጀምሯል።
ዜና: ኢትዮጵያ በሃይል ማስተላለፊያ መስመሮች እጥረት ምክንያት ለአዳዲስ የ #ክሪፕቶ ማዕድን አውጪዎች ፍቃድ መስጠቷን አቆመች

ኢትዮጵያ በሃይል ማስተላለፊያ መስመሮች መሰረተ ልማት አቅም ውስንነት ምክንያት ለአዳዲስ የክሪፕቶ ማዕድን አውጪ ኩባንያዎች ፍቃድ መስጠቷን አቆመች።

በአሁኑ ሰዓት 25 የቢትኮይን አውጪ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በክሪፕቶ ማውጣት ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሲሆን በሀገሪቱ ያለውን ርካሽ ታሪፍ እና የተትረፈረፈ የኃይል ምንጭ ተከትሎ 20 የሚጠጉ ተጨማሪ ተቋማት ፈቃድ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለክሪፕቶ ማዕድን አውጪዎች የሚሸጠው ኃይል በውጭ ምንዛሬ የሚከፈል በመሆኑ ተጨማሪ ኃይልን ወደ ገንዘብ የሚቀይርበት መንገድ እንደሆነ አስታውቆ ነበር።

ይሁን እንጂ ባለሙያዎች ትክክለኛው የኃይል ፍጆታ ከተገለጸው በላይ ሊሆን እንደሚችል እና የሀገር ውስጥ የኃይል አቅርቦትን ሊጎዳ እንደሚችል ያስጠነቅቃሉ።

የክሪፕቶ ማዕድን አውጪዎች በ2017 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ከኤሌክትሪክ ኤክስፖርት ካገኘችው 338 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ውስጥ ሰፊውን ድርሻ እንደሚወስዱ ቢት ኮይን ድረ ገጽ ዘግቧል።

======================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
ዜና፡ የ #አፍሪካ ልማት ባንክ በ #ኢትዮጵያ ለሚገነባው የአፍሪካ ግዙፉ አውሮፕላን ማረፊያ 8 ቢሊዮን ዶላር ለማፈላለግ ስምምነት ፈረመ

የአፍሪካ ልማት ባንክ ግንባታው ሲጠናቀቅ የአፍሪካ ትልቁ አውሮፕላን ማረፊያ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀውን የ #ቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት ከሚያስፈለገው 10 ቢሊየን ዶላር፣ 8 ቢሊዮን ዶላር ለማፈላለግ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ተፈራረመ።

ስምምነቱን የአየር መንገዱ ቺፍ ኮሜርሻል ኦፊሰር ለማ ያደቻ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ ፕሬዝዳንት አኪንዉሚ አዴሲና (ዶ/ር) ዛሬ በአዲስ አበባ አከናውነዋል። በፊርማ መርሃ ግብሩ ላይ፤ የአየር መንገዱ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ እና የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ፣ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ እና የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ተገኝተዋል።

በስምምነቱ መሰረት ባንኩ 80 በመቶውን ከተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት የሚያፈላልግ ሲሆን 20 በመቶ የሚሆነውን ደግሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚሸፈን ይሆናል ተብሏል።

በሁለት ምዕራፍ የሚገነባ አየር ማረፊያው የመጀመሪያው ሲጠናቀቅ በዓመት 60 ሚሊዮን መንገደኞችን የሚያስተናግድ ሲሆን፤ በሙሉ አቅም ወደ ስራ ሲገባ ደግሞ ቁጥሩ ውደ 110 ሚሊዮን ከፍ ይላል።

ተጨማሪ ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8795
#አውስትራሊያ መስከረም ላይ ለ #ፍልስጤም ሀገርነት እውቅና ልትሰጥ ነው

አውስትራሊያ፤ #የዩናይትድ_ኪንግደም፣ የ #ፈረንሳይ እና #ካናዳን እርምጃ በመከተል፤ በመስከረም ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና የመስጠት እቅድ እንዳላት አስታወቀች።

የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዝ፤ ውሳኔው በመስከረም በሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተግባራዊ እንደሚሆን ገልጸዋል። አገሪቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችውም የፍልስጤም ባለስልጣን ቃል የተገባላቸውን ቁርጠኝነት ተከትሎ እንደሆነም ተናግረዋል።

"በመካከለኛው ምሥራቅ ያለውን የአመጽ ድግግሞሽ ለመስበር እንዲሁም በጋዛ ያለውን ግጭት፣ ስቃይ እና ረሃብ ለማስቆም የሁለት ግዛት መፍትሄ የሰው ልጅ ምርጥ ተስፋ ነው" ብለዋል።

በጋዛ የምታካሂደውን ጦርነት እንድስቆም ጫና እየበረታባት ያለችው እስራኤል፤ ለፍልስጤም አገረ መንግሥት እውቅና መስጠት "ሽብርተኝነትን የሚሸልም ነው" በማለት ትቃወማለች።

ከቅዳሜ ጀምሮ በጋዛ አምስት ሰዎች በረሃብ እና በተመጣጠነ ምግብ እጦት ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 217 እንደደረሰ በሐማስ የሚመራው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ከ2023 ጀምሮ እየተካሄደ ባለው የእስራኤል ወታደራዊ ዘመቻ የተገደሉ በጠቅላላው ሰዎች ብዛትም ከ61,000 በላይ መሆኑንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

https://www.bbc.com/amharic/articles/c9wyyd2wj9vo
ዜና: በትግራይ ክልል 440 ህገ-ወጥ የማዕድን ቁፋሮ ማሽኖች በቁጥጥር ስር ሲውሉ ከ 7 ቢሊዮን ብር በላይ ለኪሳራ መዳረጉ ተገለፀ

በትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ ዞን ከ440 በላይ ህገወጥ የማዕድን ቁፋሮ ማሽኖች በቁጥጥር ስር ውለው ወደ ማእከላዊ ቦታ እንዲዛወሩ መደረጉን በክልሉ ህገ-ወጥ ማዕድን ማውጣትን ለመከላከል የተቋቋመው ግብረ ሃይል አስታወቀ።

ግብረ ሃይሉ በመቀሌ ከተማ ከሚገኙ የዞን እና ወረዳ አመራሮች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት እንዲሁም ከፀጥታና ፍትህ አካላት ጋር ባደረገው ስብሰባ፤ ትግራይ ለብሄራዊ ባንክ ገቢ የምታደርገው ከ7 ቢሊየን ብር በላይ በህገ ወጥ የማዕድን ዝውውር ምክንያት ማጣቷ የተገለጸ ሲሆን በዚህ አመት ከወርቅ ገቢ የተገኘው ከተጠበቀው በታች 24 ሚሊየን ብር ብቻ መሆኑን የትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

የግብረ ኃይሉ ኃላፊ የሆኑት አቶ አማኑኤል አሰፋ በተለይ ከጦርነቱ በኋላ በህገ-ወጥ የማዕድን ቁፋሮ ምክንያት በሰው፣ በከብት እና በሥነ-ምህዳር ላይ የሚደርሰውን ብክለትን ጨምሮ በአካባቢ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ እንደሚገኝ አንስተዋል። አክለውም ከቁጥጥር ውጭ በሆነው የወርቅ ማውጣት ስራ ጥቅም ላይ የሚውሉ መርዛማ ኬሚካሎች አደገኛ ሁኔታ መፍጠራቸውን ተናግረዋል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ በበኩላቸው በተለይም በውጭ ሀገር ዜጎች እና ተባባሪዎቻቸው የሚፈጸመው ህገ-ወጥ የማዕድን ማውጣት ስራ እልባት ሊበጅለት ይገባል ብለዋል።

https://addisstandard.com/Amharic/?p=8805
#ኢትዮጵያ - ታዋቂዋ አሜሪካዊት ተዋናይት፣ የፊልም ባለሙያ እና ሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ አንጀሊና ጆሊ ትናንት #አዲስ_አበባ የሚገኘውን የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ጎበኘች

የጉብኝቷ ዋነኛ ትኩረት ሆስፒታሉ ሆስፒታሉ እየሰጠ በሚገኘው መድሃኒቱን የተላመደ ቲቢ (ኤም.ዲ.አር ቲቢ) ህክምና ዙሪያ እየተከናወኑ ያሉ እንቅስቃሴዎችን ፣ የሚታዩ ለውጦችን እንዲሁም ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ቦታዎች መለየት ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር።

እንደ ሆስፒታሉ ገለጻ፤ በጉብኝቷ ወቅት አንጀሊና የሆስፒታሉን የቲቢ እና MDR-TB ህክምና መስጫ ክፍሎች፣ የላብራቶሪ እንዲሁም ታካሚዎችን ተዘዋውራ አይታለች። “ከዓመታት በፊት ሆስፒታሉን መጎብኘቷን ያስታወሰች ሲሆን፣ ከዚያን ጊዜ ወዲህ በሆስፒታሉ የተደረጉትን “ብዙ ገጽታ ያላቸው ለውጦች” በማየቷ ደስታዋን ገልጻለች። በቂ ድጋፍ ከተደረገለት፣ ሆስፒታሉ አገልግሎቶቹን የበለጠ ለማሻሻል በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝም ገልጻለች” ሲልም ሆስፒታሉ ገልጿል።

ተጨማሪ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ https://www.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid02hdGoh8gNckNdMAJ2mhV7gouLNM4QNJDjhmZfSFwmQMR4TiGdzey5XsP89C55H5anl

__________________________
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
የአፍሪካ ልማት ባንክ ለአዲሱ የ #ኢትዮጵያ አውሮፕላን ማረፊያ 500 ሚሊዮን ዶላር ሊያቀርብ ነው

የአፍሪካ ልማት ባንክ በ2029 ሲጠናቀቅ የአፍሪካ ትልቁ አውሮፕላን ማረፊያ እንደሚሆን የሚጠበቀው አዲስ የኢትዮጵያ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ፋይናንስ ለማድረግ 500 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ።

እንደ ሮይተርስ ዘገባ፣ ባንኩ ለዚህ ትራንስፎርሜሽናል እና ክልላዊ ውህደት ትልቅ ፋይዳ ላለው ፕሮጀክት ፋይናንስ ለማድረግ “በባንኩ ቦርድ ከጸደቀ እስከ 500 ሚሊዮን ዶላር መድቧል” ብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምስራቅ 45 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ የሚገነባውን ባለአራት ማኮብኮቢያ አውሮፕላን ማረፊያ ዲዛይን ስምምነት ተፈራርሟል።

አየር መንገዱ ለ10 ቢሊዮን ዶላር ፕሮጀክቱ ከሚፈለገው ገንዘብ 20% የሚሆነውን እንደሚያቀርብ እና ቀሪው ደግሞ ከሌሎች አበዳሪዎች እንደሚገኝ አስታውቋል።

በሁለት ምዕራፍ የሚገነባ አየር ማረፊያው የመጀመሪያው ሲጠናቀቅ በዓመት 60 ሚሊዮን መንገደኞችን የሚያስተናግድ ሲሆን፤ በሙሉ አቅም ወደ ስራ ሲገባ ደግሞ ቁጥሩ ውደ 110 ሚሊዮን ከፍ እንደሚል ትላንት መዘገባችን ይታወሳል።

__________________________
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
ዜና: #ኢትዮጵያ#አሜሪካ ሕገ ወጥ የገንዘብ ማስተላለፊያ መንገዶችን ለመቆጣጠር መምከራቸው ተገለጸ

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን ህገወጥ ድንበር ተሻጋሪ የገንዘብ ማስተላለፊያ ግብይቶችን መከላከልና መቆጣጠር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መምከራቸው ተገልጿል፡፡

በዚህም በገንዘብ ማስተላለፊያ መንገዶች ላይ በሚደረገው ቁጥጥር ያላቸውን ትብብር ለማጠናከርና የገንዘብ ዝውውሩ በመደበኛ የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ መከናወኑን ማረጋገጥ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ተወያይተዋል ተብሏል።

በተጨማሪም በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ይበልጥ ማሻሻል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ባንኩ አስታውቋል፡፡

ውይይቱ የተካሄደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሐምሌ 26 ቀን 2017 ዓ.ም አራት ተቀማጭነታቸውን በአሜሪካ ያደረጉ የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሚሰበስቡት ገንዘብ አማካኝነት በወንጀል የተገኘ ንብረትን ህጋዊ የማስመሰል እና ሕገወጥ ተግባራትን በገንዘብ በመርዳት ወንጀል ላይ ተሳትፈዋል ሲል በይፋ ከከሰሰ በኋላ ነው።

እነዚህ ኩባንያዎች ሸገይ ገንዘብ አስተላላፊ፣ አዱሊስ ገንዘብ አስተላላፊ፣ ራማዳ ፔይ እና ታጅ ገንዘብ አስተላላፊ ሲሆኑ የሚገኙትም በቨርጂኒያ እና ሚኒሶታ ግዛቶች ነው። ከእነዚህ ኩባንያዎች መካከል ታጅ ገንዘብ አስተላላፊ በጎርጎሮሳውያኑ 2024 የ'ዩ.ኤስ. ባንክ ሴክሬሲ አክት' ን በመጣስ ጥፋተኛ እንደሆነ ማመኑን በዩናይትድ ስቴትስ የደቡብ ካሊፎርኒያ አቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት መግለጫ ያመላክታል።

https://www.facebook.com/share/1AD7YFyvgF/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v
#ግብፅ-#ዩጋንዳ: ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ ከፕሬዝዳንት ሲሲ ጋር በ #ናይል_ወንዝ ትብብር ላይ ለመወያየት ግብፅ ገቡ

የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ከግብፅ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ለማጠናከር እና በናይል ወንዝ ላይ ያለውን የክልላዊ ትብብር ለማሳደግ ያለመ የዲፕሎማሲ ተልዕኮ አካል በመሆን፣ በግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል-ሲሲ ግብዣ ሰኞ ዕለት ካይሮ ገብተዋል። ጉብኝታቸው የ3 ቀናት ቆይታን ያካትታል።

ይህ ጉብኝት ሙሴቬኒ የግብፅን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር በድር አብደላቲን በአንቴቤ ቤተ-መንግስት ተቀብለው ስለ ናይል ተፋሰስ ዘላቂነትና ልማት ውይይት ካደረጉ ከአንድ ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የተደረገ ነው።

በአንቴቤው ውይይት ላይ፣ ሙሴቬኒ እንደተናገሩት፣ ለወንዙ ትልቁ አደጋ የጂኦፖለቲካዊ ውዝግቦች ሳይሆኑ፣ በአካባቢ ላይ የሚደርሰው መራቆት እና በላይኛው ተፋሰስ ሀገራት ያለው የልማት ዝግመት ነው። እንደ UGDiplomat ዘገባ ከሆነ፣ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በማጣት ምክንያት የሚከሰተውን ደን መጨፍጨፍ እና “ኋላቀር የግብርና አሰራር” ለናይል ወንዝ ዘለቄታዊነት ዋና ዋና አደጋዎች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

“የናይል ወንዝ ባለድርሻ አካላት የሆኑ ሁሉም ሀገራት የወንዙን ህልውና ሳይጎዱ እንዴት በተሻለ መንገድ መጠቀም እንደሚቻል ላይ ከፍተኛ ደረጃ ውይይት ማድረግ አለባቸው” ሲሉም ሙሴቬኒ ተናግረዋል።
ተጨማሪ ለማንበብ
https://www.facebook.com/share/p/19pQC3ujk4/
__________________________
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm